TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠ/ሚር አብይ ነገ ጠዋት🛫እስራኤል ያመራሉ!

የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጋዜጠኞች በላከው መረጃ የኢትዮጵያው መሪ ከእስራኤሉ ጠ/ሚር ቤንጃሚን ኔታናያሁ እና ከፕሬዝደንቱ ሬኡቨን ሬቭሊን ጋር ሰኞ ይገናኛሉ።

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን በጸጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉ 14 ሺህ 500 ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገለጸ፡፡

የመምሪያው ኃላፊ አቶ መስፍን ደምሴ እንደገለጹት በ2010 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን አጎራባች አከባቢዎች ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር 34 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተማሪዎችን የሣይንስና ሂሣብ ትምህርቶች ውጤት ለማሻሻል በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ተገለጸ!

ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የትምህርት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሣተፉበት 29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ እንደቀጠለ ነው።

በጉባኤውም ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆኑ በተለይም የመማሪያ ግብአቶችን በማሟላትና የመምህራንን አቅም በሚገነቡ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ተብሏል።

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወደ ሀዋሳ መግቢያ ሀበሻ ባስ ተገልብጦ ሰው ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል። የአደጋው መንስኤ መኪና መንገድ ላይ ላም ገብቶ ነው።" #DOLO_LEMMA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሃይማኖታዊ አስተምህሮዎች ከወዴት አሉ? ግጭቶችን መከላከል ለምን ተሳናቸው? ሐዋሳ ላይ ከተሰበሰቡት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች አንዱ የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት መሀመድ ሙስጠፋ ለዚህ ምክንያት ነው የሚሉትን ይናገራሉ ።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
10ቱ የኤች አይ ቪ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ የሚታይባቸው የኢትዮጵይ ክፍሎች!

ኤች አይቪ ኤድስ ዳግም ተቀስቅሶ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ መሆንና ሽፋን ማግኘት ከጀመረ ውሎ አድሯል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተካሄደ አገራዊ የኤችአይቪ መከላከል ጉባኤ የቀረበ አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚያስረዳው ታድያ ስርጭቱ በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን አዲስ አበባም ደረጃውን ትከተላለች። ስርጭቱ ዝቅተኛ ሆኖ የጠመዘገበው በሱማሌ ክልል ሲሆን ይህም በመቶኛ 0.2 ነው።

ጥናቱ በተጨማሪ በየዓመቱ 15 ሺህ ሰዎች እንደ አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙና በኤድስ ምክንያ የሚሞቱ ናቸው። በኢትዮጵያም በተለይ ከ2010 ጀምሮ ስርጭቱ መቀነስን እያሳየ እንዳልሆነ ጥናቱ አካትቷል። ጥናቱ በኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት የተሠራውን ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ተኮር ጥናት ዋቢ አድርጎ እንደጠቀሰው፤ ኤችአይቪ በሴተኛ አዳሪዎች ያለው ስርጭት በጣም ከፍተኛ ሲሆን የሥርጭት መጠኑም 23% ነው።

ይህም ሆኖ በድምሩ በኤች አይቪ ምክያጥ የሚከሰት የሞት ቁጥር ቀንሷል። በተለይም እኤአ በ2004 የፀረ-ኤችአይቪ ሕክምና ከመጀመሩ በፊት ደርሶ ከነበረበት 83,000 እአአ በ2017 15,539 በመውረድ በ82 በመቶ መቀነሱ ይጠቀሳል። በጥቅሉም እ.ኤ.አ. ከ2010 እስከ 2017 በኤድስ ምክንያት የሚከሰት የሞት መጠንን በ57% መቀነስ መቻሉ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ በ2030 የተቀመጠውን ግብ መድረስ የሚያስችል ነው።

አሁንም ግን በአዋቂም ሆነ በወጣትነት ዕድሜ ክልል ባለው የማህበረሰብ ክፍል ኤችአይቪን ለመከላከልና አገልግሎቶችን ለመጠቀም የሚያስችል የግንዛቤና የባህሪ ለውጥ ምጣኔ በጣም ዝቅተኛ መሆኑ በጥናቱ ታይቷል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሐዋሳ ከተማ አዲስ ከንቲባ ልትሾም ነው!

የሲዳማ ክልልነት ጥያቄን ተከትሎ በተከሰተ የጸጥታ ችግር ምክንያት ከኃላፊነታቸው በተነሱት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ምትክ ሊሾም መሆኑ ተነገረ። የከተማው አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ነው። ጉባኤው ከሃላፊነታቸው እና ከደኢህዴን አባልነታቸው በታገዱት የቀድሞው የከተማው ምክትል ከንቲባ ምትክ አዲስ ከንቲባ እንደሚሾም ተገልጿል።

የሀዋሳ ከተማ ቀደም ሲል የከንቲባነት ሥልጣንና ኃላፊነት በነበራቸው ምክትል ከንቲባ ስትመራ መቆየቷ ይታወቃል። በተመሳሳይ ዛሬ ይጀመራል ተብሎ የነበረው የደቡብ ክልል ምክር ቤት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እያደረጉት ያለው የምክክር መድረክ ባለመጠናቀቁ ለነገ መዛወሩ ታውቋል።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዑጋንዳ ውስጥ አንዲት የ9 ዓመት ሕፃን በኢቦላ በሽታ መሞቷ ተገለጸ!

አንዲት በኢቦላ ቫይረስ የተያዘች የዘጠኝ ዓመት ኮንጎአዊት ሕፃን ዑጋንዳ ውስጥ መሞቷን የአገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ሕፃኗ ከእናቷ ጋር የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ድንበር አቋርጣ ወደ ዑጋንዳ ስትገባ ምፖንድዌ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የኢቦላ ምርመራ ተደርጎላት እንደነበር ታውቋል። ሆኖም ወዲያውኑ የትኩሳት ምልክት በማሳየቷ በምዕራባዊ የአገሪቱ ግዛት፣ ካሰስ ከተማ ለኢቦላ ሕመምተኞች ወደተዘጋጀ መጠለያ ብትገባም ህይወቷ ማለፉ ተረጋግጧል። የዑጋንዳ የጤና ባለሥልጣናት የሕፃኗን አስከሬን ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለመላክ ግንኙነቶች መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የሕፃኗ እናት በገለልተኛ ስፍራ እንድትቀመጥ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም፤ ኋላ ላይ ለበለጠ ክትትል ወደ አገሯ እንድትመለስ ተደርጋለች ሲል ዘኢስት አፍሪካን ዘግቧል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

አቶ #ጥራቱ_በየነ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል። #SMN #HAWASSA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

አቶ #ጥራቱ_በየነ የሐዋሳ ከተማ አሰተዳደርን በምክትል ከንቲባነት እንዲመሩ ዛሬ ተመረጡ። አቶ ጥራቱ የተመረጡት የከተማው አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔ ነው። አቶ ጥራቱ የተመረጡት ከኃላፊነታቸውና ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ደኢህዴን አባልነታቸው በታገዱት የቀድሞው የከተማው ምክትል ከንቲባ ምትክ ነው።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግለጫ እየተሰጠ ነው!

የፊታችን ጳጉሜ 1/2011 የፀሎትና ምህላ ቀን ሆኖ በመላ ሀገሪቱ እንዲከበር የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወሰነ። ጉባኤው የፀሎትና ምህላ ቀኑን እንዲሁም መጪውን አመት አስመልክቶ በፅ/ቤቱ መግለጫ እየሰጠ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው በአግባቡ ሊተገበር ይገባል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ተናገሩ። ለአዲሱ ፍኖተ ካርታ ስኬታማነት የትምህርት ባለሙያዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ትናንት የተጀመረው 29ኛው አገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ በአዲሱ የትምህርትና የስልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዓመታዊው የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በአዲስ አበባ ሊካሔድ ነው። በየዓመቱ የሚካሔደው እና ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ የሚደረገው ዓመታዊው የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ተባባሪ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ይካሔዳል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጳጉሜ 1/2011 በመላ ሀገሪቱ የፀሎትና ምህላ ቀን ሆኖ ይከበራል!

የፊታችን ጳጉሜ 1/2011 የፀሎትና ምህላ ቀን ሆኖ በመላ ሀገሪቱ እንዲከበር የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወሰነ። ጉባኤው የፀሎትና ምህላ ቀኑን እንዲሁም መጪውን አመት አስመልክቶ በፅ/ቤቱ መግለጫ እየሰጠ ነው። በመግለጫው ጳጉሜ 1 መላው ኢትዮጵያውያን በአንድ መንፈስ በመነሳት ለሀገርና ለወገን የሚያስቡበት እና ፀሎትና ምህላ የሚያደርጉበት ሆኖ እንዲውል ጉባኤው መወሰኑ በመግለጫው ተጠቅሷል። በሀገሪቱ ያለው ውስብስብ ችግር ተወግዶ አዲሱን አመት በሰላም፣ ፍቅርና አንድነት በአዲስ መንፈስ እንድንቀበል ያለው ጉባኤው በአዲሱ አመት ለሀገር የሚበጀውን እንድንሰራ፣ የቀደመውን ፍቅር የምንመልስበት እንዲሆን ሲል ጥሪውን አስተላልፏል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሶሪያ #PEACE😢ከአመታት በፊት ይህቺ ምድር ማንም እንዲህ ወደ ፍርስራሽነት ትቀየራለች ብሎ አልገመተም፤ግን ሆነ! ሶሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን አጣች፤ በሚሊዮኖች ተወልደው ካደጉበት ሀገር ተሰደዱ!! ጦርነቱ ዛሬም አላባራም ዛሬም ሰው ይሞታል!! #ያሳዝናል! #ልብ_ይሰብራል! ሶሪያውያን ይህ ከመሆኑ በፊት ከስሜታዊነት ወጥተው፤ በሰከነ መንገድ ተረጋግተው ተነጋግረው ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ባልመጣ ነበር። ማስተዋልን የመሰለ #ጥበብ ከየት ይመጣ ይሆን?

መገንባት እንደማፍረስ ቀላል አይደለም!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲሱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ!

በዛሬው ዕለት ምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ የፈፀሙት አቶ ጥራቱ ሐዋሳ #የቀደመ ስሟን በሚያስጠብቅ ሁኔታ ሁሉም ዜጎች በሰላም የሚኖሩባትና ሀብት የሚያፈሩባት እንዲሁም ምቹ የኢንቬስትመንት መዳረሻ ከተማ እንድትሆን የተጣለባቸውን ኃላፊነት በታማኝነት እና በትጋት ለመወጣት ቃል ገብተዋል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንታረቅ

እንታረቅ በሚል በተዘጋጀዉ መርኃግብር ላይ በርካታ ሰዎች ባለመግባታቸው ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው፡፡ ያነጋገርናቸው ቅሬታ አቅራቢዎች ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ከክልል ከተማ ከተጠቀሰው ጌዜ ቀድመን ብንመጣም መግባት አልቻልንም በማለት ቅሬታዎችን በጁፒተር ሆቴል በር ላይ ለነበሩ የሆቴሉ ሰራተኛኞችና ለጸጥታ አካላት ያቀረቡ ሲሆን የፕሮግራሙ አስተባባሪ በበኩላቸው "ቦታ ስለሞላ ነው የመረጥነው ሰው የለም ብለዋል በቀጣይ ሳምንት ተመሳሳይ ፕሮግራም እናዘጋጃለን ሰፊ አዳራሽ ባለማዘጋጀታችን ግን ይቅርታ እንጠይቃለን" የሚል ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቃውሞ አሰማች!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ነሐሴ 24/2011 ባወጣችው መግለጫ እሁድ ነሐሴ26/2011 በቀሲስ በላይ መኮንን በኦሮሚያ ባህል ማዕከል የተጠራውን እወጃ እና ጋዜጣዊ መግለጫ እውቅና እንደሌለው እና ሕገ ወጥ እንደሆነ አስታውቃለች። ቤተ ክርስቲያኗ አያይዛም መንግስት ይህን ሕገ ወጥ ተግባር እንዲያስቆም አሳስባለች።

Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update “የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ′ በፎቶግራፊ ሙያ ለዓለም ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩ የእውቁ ኬንያዊ ፎቶ ጋዜጠኛ መሐመድ አሚን ልጅ ሳሊም አሚን ገለፁ። ሳሊም አሚን በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገኝተው ከሚሲዮኑ ጋር በመተባበር “የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ′ በፎቶግራፊ ሙያ ለዓለም ማስተዋወቅ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከአምባሳደር #መለስ_ዓለም ጋር መክረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
«15 ሚሊዮን ብር #በማጭበርበር ከባንክ የወሰደ ሰው ታስሯል። በፌስቡክ ላይ ያለው ታሪክ ይኸ ሰው የታሰረው መንግሥትን ስለተቃወመ ነው የሚል ነው» የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ዑመር ተቃዋሚዎች ለምን ይታሰራሉ? ተብለው በOMN ሲጠየቁ።

«ለአካል ጉዳተኞች የሚገዙ #ዊልቸሮችን አጭበርብሮ የተሰባበሩ ያመጣና በኦዲት ከተረጋገጠ በኋላ የታሰረ ሰው አለ። እሱም በሶሻል ሚዲያ ላይ ፎቶው እየዞረ ይኸ ሰው የታሰረው በመንግሥት ላይ ቅሬታ ስላቀረበ ነው የሚባል ነገር አለ»

#ኦሮሚያ_ሚዲያ_ኔትዎርክ

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በዛሬው ዕለት ያደረጉት ንግግር...

📹#DW

@tsegabwolde @tikvahethiopia