TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከ208 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ህገወጥ መድኃኒት፣ አደንዛዥ ዕፆችና አልሚ ምግቦች መያዙን አስታወቀ። ባለስልጣኑ ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ጤና ተቆጣጣሪዎች ጋር በመተባበር በሱቆችና መድኃኒት ቤቶች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መያዙን አስታውቋል።

ድንገተኛ ፍተሻው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በሞያሌ ወረዳ እና በሱማሌ ክልል ደግሞ ሊበን ዞን ዳዋ ወረዳ የተደረገ ሲሆን፥ ከ181 ሺህ 60 ብር በላይ የሚገመት ህገወጥ መድኃኒት፣ አደንዛዥ ዕፆችና አልሚ ምግቦች አገልግሎት ላይ ሳይወሉ መያዝ ተችሏል ነው ያለው። የተያዙት ህገወጥ መድኃኒት፣ አደንዛዥ ዕፆችና አልሚ ምግቦች በስምንት ሱቆች እና በሶስት መድኃኒት ቤቶች ውስጥ የተገኙ ሲሆን፥ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገቡና የቅዝቃዜ ሰንሰለታቸውን ሳይጠብቁ በኮንትሮባንድ መልክ የገቡ ናቸው ተብሏል። ባለስልጣኑ ህገወጥ መድኃኒቶቹንና ምግቦቹን ለአገልግሎት እንዳይቀርቡ በማድረግ ሱቆችና መድኃኒት ቤቶቹ እንዲታሸጉ ማድረጉንም ነው ያስታወቀው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ድሬዳዋ

የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከህብረተሰቡ በደረሰ #ጥቆማ መሰረት ከፖሊስ አካላት ጋር በመተባበር በድሬዳዋ ከተማ አባይ በሚባል መድኃኒት ቤት ውስጥ እንዲሁም በአንድ ግለሰብ ሲዘዋወሩ የነበሩ መድሃኒቶችን ይዟል።

መድሃኒቶቹ 27 ሺህ 470 ብር የሚገመት ዋጋ ያላቸው ሲሆን፥ የመድኃኒት ቤቱ ባለቤት በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደበት ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ የቁጥጥሩ ባለቤት በመሆን ከማንኛውም ህገወጥ የምግብና የመድኃኒት ንግድና ዝውውር ራሱን በመጠበቅ የቁጥጥር ስራውን እዲያግዝም ጥሪውን አቅርቧል።

መሰል ህገወጥ የምግብና የመድኃኒት ንግድና ዝውውር ድርጊቶች ሲፈጸሙ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ የስልክ መስመር በ8482 ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፍትህ አካላትና የጤና ተቆጣጣሪዎች እንዲጠቁም ጠይቋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ወንጀል የተሳተፈ አካል እስከ 10 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ሊቀጣ መሆኑ ተገለፀ!

ከህገወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውር ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ ረቂቅ አዋጅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አስታውቋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ በህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና አያያዝ ወንጀል የተሳተፈ አካል እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

በአገሪቱ እየተስተዋለ የሚገኘውን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና አያያዝ በተመለከተ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ እየተዘጋጀ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ፀድቆ ስራ ላይ ሲውል በዋናነት ህጋዊ የጦር መሳሪያ አያያዝ ስርዓት በመፍጠር የአገርንና የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንደሚጠቅም የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

በወንጀሉ ዙሪያ ከዚህ በፊት በአገሪቱ የመቅጫ ህጎች የነበሩ ቢሆንም ህጎቹ በትክክል በጦር መሳሪያ አያያዝ፣ ፍቃድ፣ ቁጥጥርና አስተዳደር ዙሪያ በዝርዝር ያስቀመጡት ስርዓት እንዳልነበር ገልፀዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ከዚህ በፊት የነበሩት ህጎች በወንጀሉ ላይ የሚጥሉት የቅጣት መጠን ዝቅተኛ በመሆናቸው ዜጎች በወንጀል ድርጊቱ እንዳይሰማሩ የሚከለክሉ እንዳልነበሩም ተናግረዋል፡፡

አሁን ግን በባለድርሻ አካላት በውይይት እየዳበረ ያለው ረቂቅ አዋጅ በህገወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውርና አያያዝ ላይ የሚጥለው ቅጣት ከበድ ያለ በመሆኑ ጥፋተኞችን ብሎም ህብረተሰቡን የሚያስተምር እንደሚሆን አመልክተዋል አቶ ዝናቡ፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጋምቤላ ፈቃድ የሌላቸው 11 የውጭ ኮሌጆች ተገኙ!

ከየት እንደመጡ ያልታወቁ 11 ሕገወጥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋምቤላ ክልል ሲያስተምሩ እንደተደረሰባቸው፣ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው ከተለያዩ ግለሰቦች በደረሰው ጥቆማ መሠረት ወደ ክልሉ ተንቀሳቅሶ የለያቸው እነዚህ 11 ተቋማት በድኅረ ምረቃና በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እየተቀበሉ እንደሚያስተምሩ ለሪፖርተር የገለጹት፣ የኤጀንሲው የኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ገረሱ ናቸው፡፡

ከኤጀንሲው ፈቃድ ሳያገኙ ሊያስተምሩ የተገኙት 11 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በአገር ውስጥ የማይታወቁና እንግዳ መጠሪያ ያላቸውና ከውጭ የገቡ እንደሆኑ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

‹‹በተደጋጋሚ በደረሰን ጥቆማ መሠረት ለማጣራት ወደ ክልሉ ስናመራ የጠበቅነው አንድ ተቋም ብቻ ነበር፡፡ ስንደርስ ግን 11 ሆነው አገኘናቸው፡፡ በወቅቱ ምንም ማድረግ ስላልቻልን ለክልሉ መንግሥት ስለሁኔታው በማስረዳት የክልሉን ነዋሪዎች ከሕገወጦች እንዲጠብቅ ደብዳቤ ጻፍን፤›› የሚሉት አቶ ታረቀኝ፣ ለክልሉ ደብዳቤ ከተጻፈ ስድስት ወራት የተቆጠረ ቢሆንም ምንም ዓይነት ምላሽ ለኤጀንሲው አለመድረሱን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/eth-08-28-3
በቄለም ወለጋ ዞን የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች ለ4 ሺህ 360 መደበኛ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን የዞኑ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጣቸው!

ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሀገር ላይ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንደተሰጣቸው የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስርያቤቱ ዛሬ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት ከሀገራቱ ባለስልጣናት ጋር በተደረገ ግንኙነት መሰረት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡

እንደ ዶክተር ኤርጎጌ ገለፃ ከዚህ በፊት በሀገወጥ መንገድ ለሄዱት ዜጎች የተሰጠው ህጋዊ ፈቃድ ቢያስደስታቸውም ከዚህ በኋላ በሀገ ወጥ መንገድ ለሚሄዱ ዜጎች ምንም አይነት ምህረት እንደማይደረግና ሲያዙም ቀጥታ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቬራክሩዝ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት 8 ሴቶች እና 15 ወንዶች መሞቱ!

በሜክሲኮ በምሽት መዝናኛ ክለብ በተፈጸመ ጥቃት 23 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። በወደብ ከተማዋ ቬራክሩዝ በተፈጸመው ጥቃት 8 ሴቶች እና 15 ወንዶች መሞታቸው ነው የተነገረው። በወቅቱ በምሽት መዝናኛ ክለቡ ውስጥ እሳት መነሳቱንም ፖሊስ አስታውቋል።

እንደ ፖሊስ ገለጻ ከእሳቱ መነሳት ቀደም ብሎ መዝናኛ ክለቡ ላይ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶ ነበር። ከተኩሱ በኋላም በጠርሙስ የተዘጋጁ ተቀጣጣይ ቁሶችን ወደ ክለቡ በመወርወር እሳት እንዲነሳ መደረጉንም ገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመባት ከተማ ዋነኛ የእጽ አዘዋዋሪዎች መናኸሪያና በቡድን የሚንቀሳቀሱ ወንጀለኞች መገኛ መሆኗ ይነገራል። የአሁኑ ጥቃትም በእፅ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ሳይፈጸም አልቀረም ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ/fbc/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ስቱዲዮና መኖሪያ ቤት የሆነው “ቪላ አልፋ” እድሳት መጀመሩን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ደብቆ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በምዕራብ ሸዋ ዞን ጮቢ ወረዳ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ደብቆ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት የወንጀል መከላከል ኃላፊ ሳጅን ወርቅነህ ዲነግዴ እንደገለፁት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ዛሬ ጧት አራት ሰዓት አካባቢ ነው።

ግለሰቡ በወረዳው ቆርጬ ጨቢ ቀበሌ በሚገኝ በአንድ በእድሜ የገፉ አዛውንት መኖሪያ ቤት ውስጥ ሶስት ቦምቦች፣ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎችና 198 ጥይቶች ከስድስት የጥይት መያዣ ካዝናዎች ጋር ደብቆ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል። ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ግለሰቡ መያዙን የገለፁት  ሳጅን ወርቅነህ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ገለፀዋል። ህብረተሰቡ አጠራጣሪ የሆኑ ድርጊቶች ሲከሰቱ በአፋጣኝ ለፖሊስ በማሳወቅ ወንጀልን ለመከላከል እያሳየ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ሳጅን ወርቅነህ  አስገንዝበዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SayNoToRacism

ዉድ የቲኪቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ቤተሰቦች በዛሬው የቲኪቫህ ስፖርት አምዳችን አሳሳቢ እየሆነ በመጣው የዘረኝነት ጉዳይ ያዘጋጀንላችሁ ፅሁፍ አለ። በአንድ ወቅት ላይ የዚህ ድርጊት ሰላባ የነበረው የናፖሊ እና የሴኔጋል ብሐራዊ ቡድን የመሀል ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ካሰፈረው ማስታወሻ ላይ የተናገረውን ባማረ አቀራረብ አመሻሹ ላይ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ቲኪቫህ ኢትዮጵያ እና ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ዘረኝነትን ያወግዛል።

#SayNoToRacism #TikvahEthiopiaAgainstRacism
#TikvahEthiopiaSportAgainstRacism
#WeAreAgainstRacism

Join TIKVAH-ETH SPORT👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethsport
@kidusyoftahe
@yidaaa
ኢትዮጵያዊ ቦምብ የሚል ቃል ተጠቅሞ ቀልድ በመቀለዱ የ4 ወራት እስራት ቅጣት ተጣለበት!

ባለፈው ሚያዚያ በኬንያ አየር መንገድ የተሳፈረ አንድ ኢትዮጵያዊ ቦምብ የሚል ቃል ተጠቅሞ ቀልድ በመቀለዱ የ4 ወራት እስራት ወይም የ100 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ቅጣት እንደተጣለበት ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ፍርድ ቤት ቅጣቱን የጣለበት፣ የበረራ አስተናጋጇ የዕቃ ማስቀመጫዎችን ስትፈትሽ፣ “ምነው ፈራሽ? ቦምብ መሰለሽ?” ብሎ በመቀለዱ ነው፡፡ በቀልዱ ሳቢያ ባለፈው ሚያዚያ ወደ ጁሃንስበርግ ሊደረግ የነበረ በረራ እንዲሰረዝ እና የናይሮቢው ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያም ለ3 ሰዓታት እንዲዘጋ ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ከተሞች ተሸላሚ ሆኑ!

በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት በቆየው የሶስተኛው ዙር የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አሀድ የመጀመረያው ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ከተሞች ተሸላሚ ሆነዋል።

በሽልማት ፕሮግራሙም በተቋማዊ አፈፃፀም ውቅሮ ከተማ 93 ነጥብ በማምጣት በአንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ስትሆን፤ ጎንደር፣ ፍኖተሰላም እና ሞጣ የሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም አላማጣ እና አክሱም ከተሞች የሶስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።

እንዲሁም በመሰረተ ልማትና አገልግሎት አቅርቦት ዘርፍ እንዲሁ ውቅሮ ከ99 ነጥብ በላይ በማምጣት ቀዳሚ ስትሆን፤ አዲግራት እና አላማጣ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ደረጃን ማግኘት ችለዋል። በጀት አጠቃቀምና ኦዲት በተመለከተም ይርጋለም፣ ሀዋሳ እና አዳማ ከተሞች እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በማግኘት ተሸላሚ ሆነዋል።

በዚሁ ወቅት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እንደተናገሩት የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ከተሞች አሁንም ለላቀ ስራ ይበልጥ እንዲተጉ እና አነስተኛ አፈፃፀም ያሳዩ ከተሞች በአፋጣኝ ክፍተቶቻቸውን በመለየት እና ከሌሎች ከተሞች ልምድ በመውሰድ በያዝነው በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ሚኒስትሯ አክለውም በቀደሙት ጊዜያት በነበሩ ፕሮግራሞች በፕሮግሪሙ ታቅፈው የነበሩ 44 ነባር ከተምች የተመደበላቸውን በጀት ለታለመለት አላማ በማዋል የተቀመጠውን ስርዓት ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ በራሳቸው ገቢ መተዳደር መጀመር ቢኖርባቸውም ከተሞቹ ይህን አለማድረጋቸውን ጠቁመው በ2012 በጀት ዓመት ሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መርሃ-ግብር የሚጠናቀቅበት ዓመት በመሆኑ የተጀማመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ በፕላን የተመሩ ከተሞችን መፍጠር እና የህዝብን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በዘላቂነት ማረጋገጥ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በያዝነው በጀት ዓመትም በፕሮግራሙ የታቀፉ ሁሉም ከተሞች በሙሉ አቅማቸው ወደስራ እንዲገቡ ጥሪ አስተላልፈዋል። በመጨረሻም የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ከተሞች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ክብርት ሚኒስትሯ አበርክተዋል።

የከተሞቹን አፈፃፀም ነጥብ እና ሌሎች መረጃዎችን በዝርዝር በዚህ ድረገፅ www.mudc.gov.et/ መመልከት ይችላሉ!

Via Negede
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተሸላሚ ከተሞች!

በተቋማዊ አፈፃፀም፦

1ኛ ደረጃ - ውቅሮ ከተማ
2ኛ ደረጃ - ጎንደር፣ ፍኖተሰላም እና ሞጣ
3ኛ ደረጃ - አላማጣ እና አክሱም

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተሸላሚ ከተሞች!

በመሰረተ ልማትና አገልግሎት አቅርቦት ዘርፍ፦


1ኛ ደረጃ - ውቅሮ
2ኛ ደረጃ - አዲግራት
3ኛ ደረጃ - አላማጣ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተሸላሚ ከተሞች!

በበጀት አጠቃቀምና ኦዲት፦

1ኛ ደረጃ - ይርጋለም
2ኛ ደረጃ - ሀዋሳ
3ኛ ደረጃ - አዳማ

የከተሞቹን አፈፃፀም ነጥብ እና ሌሎች መረጃዎችን በዝርዝር በዚህ ድረገፅ www.mudc.gov.et/ መመልከት ይችላሉ።

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA ምድረ ቀደምት!

በአፋር አዲስ የቅድመ ሰው ዝርያ ተገኘ!

ከቅድመ ሰው ዝርያ ጋር በተያያዘ አዲስ ግኝት መገኘቱ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለልስጣን አስታወቀ። በአፋር ክልል ወራንሶ ሚሌ በተባለ የአረኪኦሎጂ ጥናት ቦታ ላለፉት ሶስት ዓመታት ጥልቅ ጥናት ሲያካሂድ የቆየው ቡድን ከቅድመ ሰው ዝርያ ጋር በተያያዘ አዲስ ግኝት ማግኘቱን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታቋል።

የጥናትና ምርምር ግኝቱም እ.ኤ.አ. ኦገስት 28/2019 በߵߵNatureߴߴ በተባለው አለም አቀፍ መፅሄት ታትሞ እንደሚወጣ የገለፀው ባለስልጣን መስሪያቤቱ፤ ግኝቱ በዘርፉ ጥናት በርካታ ማስረጃዎች በመገኘታቸው ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ߵߵNatureߴߴ የሰው ዘር መገኛߴߴ በሚል ለተሰጣት ስያሜ ተጨማሪ ምስክር ነው ብሏል።

ከዚሁ ግኝት ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከጥናት ቡዱኑ ጋር በመሆን ዛሬ (ነሐሴ 22 ቀን 2011 ዓ/ም) አምስት ኪሎ በሚገኘው የባለስልጣኑ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድሬዳዋ ከተማ በመብረቅ የሰው ህይወት አለፈ!

በድሬዳዋ ከተማ ትናንት የጣለው ከባድ ዝናብን ተከትሎ አንድ ሰው በመብረቅ ህይወቱ ሲያልፍ በሌሎች ሶስት ሰዎችና በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ባንተአለም ግርማ እንደገለፁት በከተማው ትናንት የጣለውን ሃይለኛ ዝናብ ተከትሎ በወረደው መብረቅ ገንደ ጋራ በተባለ ሰፈር አንድ ሰው ጭንቅላቱን ተመትቶ ወዲያውኑ ህይወቱን አልፏል። በተጨማሪም አንድ ባለሦስት ጎማ ታክሲ መንገድ ሲያቋርጥ በደራሽ ጎርፍ ተገልብጦ በሶስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል። እንደረዳት ኢንስፔክተሩ ገለፃ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በድልጮራ ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት የድሬዳዋ አስተዳደር አውቶሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ዘመድሁን እንደገለፁት ደግሞ ትናንት ማታ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። የኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ የእንጨትና የኮንክሪት ምሰሶዎች ማፈራረሱንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በተለይ በከተማው ከዚራና ነምበርዋን አካባቢው የሚገኙ ትልልቅ የዛፍ ግንዶች በንፋስ በመገንጠላቸው የኤሌክትሪክ መስመሮች ተበጣጥሰው አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ የኤክትሪክ ሰራተኞች ከትናንት ማታ ጀምሮ ባደረጉት ርብርብ አገልግሎቱእንዲጀምር መደረጉንም አቶ ወንድወሰን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ውጤት፦

"የጤና ሚኒስቴር የአገልግሎት ጥራትን ከማሻሻል አንጻር የተለያዩ ስራዎችን እየተገበረ ይገኛል ከነዚህም መካከል አንዱ የሆነው የጤና ባለሙያዎችን ከተመረቁ በኃላ ብቃታቸውን መዝኖ ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል ስርአት መዘርጋት ነው ይህንንም ለማከናወን እንዲያስችል ላለፉት አራት(4) አመታት የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ ከቆዩ በኃላ በዚህ አመት ከሀምሌ 1-9 2011 ዓ.ም ለ10,480 የጤና ሙያ ዘርፍ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና የተሰጠን ሲሆን #ወጤቱንም ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2011ዓ.ም ለጤና ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው ተቋማት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ ተማሪዎች ውጤታቸውን በዌብ ሳይት hple.moh.gov.et በመግባት registration number፣ ስም እና የአባት ስም በማስገባት መመልከት ይችላሉ፡፡"

የጤና ሚኒስቴር

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውጤታችሁን ነገ ማየት ትችላላችሁ!

የጤና ሙያ ዘርፍ ተመራቂዎች #የብቃት ምዘና የተሰጠን ሲሆን #ወጤቱንም ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2011ዓ.ም ለጤና ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው ተቋማት የጤና ሚኒስቴር የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡ ተማሪዎች ውጤታችሁን በዌብ ሳይት hple.moh.gov.et በመግባት registration number፣ ስም እና የአባት ስም በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

#Share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የASTU/AASTU የመመዝገቢያ መስፈርት!

ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2012 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ!

የምዝገባ ጊዜ፡- ከነሐሴ 23 - ጳጉሜ 03

የምዝገባ ቦታ፦

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ www.aastu.edu.et,  www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡-

በማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲዎቹ ዌብሳይት የሚገለጽ ይሆናል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-

በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

•ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣

•ከሚመዘገቡት አመልካቾች ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡-

www.aastu.edu.etwww.astu.edu.et
እንደአመቺነቱም በስልክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚገለፅ ይሆናል፡፡

•አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም የመሰናዶ (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡

•ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

•አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2011 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-28-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ድረገፅ በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦ https://www.astu.edu.et/announcements/2012