TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሲአን ትክክለኛው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የፌስቡክ ገፅ ይህ 5,740 like ያለው ነው። ከዚህ ቀደም ዋዜማ ሬድዮና ሌሎች ስለሀዋሳው የቀድሞ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ መረጃ አገኘን ብለው ያሰራጩት ከዚህ ትክክለኛ ገፅ የተወሰደ አይደለም። በሌላ አገላለፅ #በሀሰተኛ ገፅ ተታለው ነበር።

የሲአን ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ 5,740 like ያለው ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‘አፋር ኡጉጉሞ” ወደ አገሩ ገባ!

በኤርትራ በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀስ የነበረው ”አፋር ኡጉጉሞ” የተባለው ድርጅት አመራሮች ትናንት በሰመራ ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው። የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ (አብዴፓ)ሊቀመንበር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ በአቀባበል ሥነ ሥርዓት ላይ እንዳስታወቁት ድርጅቱ ከኤርትራ ወደ አገሩ የተመለሰው በመጋቢት 2011 በተደረገ ስምምነት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-27-2

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ አህመድ🛫ወደ ጃፓን አቅንተዋል!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ጃፓን አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በደቡብ ኮሪያ የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ነው ወደ ጃፓን ያቀኑት።

በጃፓን ቆይታቸውም በጃፓኗ ዮኮሃማ ከተማ በሚካሄደው 7ኛው የጃፓን-አፍሪካ የልማት ፎረም (የቲካድ ) የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል። ከጉባዔው ጎብ ለጎንም ከጃፓን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጃፓን-አፍሪካ የልማት ፎረም (የቲካድ ) ላይ እንዲሳተፉ እና ከጉባዔው ቀደም ብሎም በጃፓን ጉብኝት እንዲያደርጉ በጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጥቂ ቀርቦላቸው እንደበረ ይታወሳል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጉራጌ ልማት ማህበር ከህብረተሰቡ ተወላጆች ያሰባሰበውን 10 ሚሊየን ብር የሚገመት የደብተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከጉራጌ ልማት ማህበር እና ከህብረተሰቡ ተወላጆች ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ የጉራጌ ልማት ማህበር ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላደረገው የደብተር ድጋፍ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሶማሌ ክልል ለስድስት ቀናት በዘመቻ በተሰጠው የፖሊዮ ክትባት ከ647 ሺህ በላይ ህፃናት መከተባቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት መማክርት ጉባኤ በትምህርት ዘርፍ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተናገሩ።

https://telegra.ph/ET-08-27

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተውን የቺኩን ጉንያ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያግዝ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ከፌዴራል መንግስት ድጋፍ ሊደረግለት መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ገለጸ። ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ በኬሚካል የተነከረ የአጎበር አቅርቦት ድጋፍ ሊደረግለት መሆኑን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ፉአድ ከድር ተናግረዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ቺኩንጉንያ ቫይረስ ምንድነው? ቺኩንጉንያ ቫይረስ (ቺክቭ) በትንኞች አማካኝነት ወደ ሰዎች ይተላለፋል። ቺክቭ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳትና ድንገት የሚከሰት የመገጣጠሚያ ህምምን ያስከትላል። ቺክቭ አብዛኛው ጊዜ ሞትን አያስከትልም፣ ነገር ግን የሚወልዳቸው የጤና እክሎች ነገሮችን ከመስራት እስከማገድ የሚደርሱ ሆነው በተወሰኑ ሰዎች ላይ ደግሞ ለከባድ ተጨማሪ በሽታ ሊዳርጉ ይችላሉ። ቫይረሱን እና ኢንፈክሽኑ የምንከላከልባቸው መንገዶችን የተመለከተ እውቀት መጨበጥ ወሳኝ ነው። የሚወስዷቸው ጥንቃቄዎች ከሌሎች በትንኞች የሚመጡ በሽታዎችም ይከላከልልዎታል።

#DCSSH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የቺክቭ ምልክቶች ምንድናቸው? አንድ ሰው በተለከፈ ትንኝ ከተነከሰ በኋላ ከ 3 እስከ 7 ቀናቶች ውስጥ ምልክቶች ይታዩበታል። የቺክቭ ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው የሚለያዩ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦
 በድንገት የሚከሰት ከፍተኛ ትኩሳት (>102°F)
 ከባድ የሆነ የመገጣጠሚያ ህመም በተለይ በክንዶች ወይም እግሮች ላይ
 ራስ ምታት
 የጡንቻ ህመም
 የጀርባ ህመም
 ሽፍታ (~50% ተጠቂዎች ላይ የሚያጋጥም)

በብዛት በሚከተሉት ሰዎች ላይ ይስተዋላሉ፦
 ህጻናት (<1 ዓመት)
 አረጋውያን (>65 ዓመት)
 እንደ ስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ወዘተ በመሳሰሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች የተጠቁ ሰዎች።

*ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች በትንኝ እንዳይነከሱ ከሌሎች የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።*

ቺክቭ እንዴት ነው የሚታከመው? ቺክቭ ለማከም የሚውል ተለይቶ የታወቀ መድሀኒትም ይሁን ክትባት #የለም

#DCSSH

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የቺክቭ ምልክቶች ምንድናቸው? አንድ ሰው በተለከፈ ትንኝ ከተነከሰ በኋላ ከ 3 እስከ 7 ቀናቶች ውስጥ ምልክቶች ይታዩበታል። የቺክቭ ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው የሚለያዩ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦
 በድንገት የሚከሰት ከፍተኛ ትኩሳት (>102°F)
 ከባድ የሆነ የመገጣጠሚያ ህመም በተለይ በክንዶች ወይም እግሮች ላይ
 ራስ ምታት
 የጡንቻ ህመም
 የጀርባ ህመም
 ሽፍታ (~50% ተጠቂዎች ላይ የሚያጋጥም)

በብዛት በሚከተሉት ሰዎች ላይ ይስተዋላሉ፦
 ህጻናት (<1 ዓመት)
 አረጋውያን (>65 ዓመት)
 እንደ ስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ወዘተ በመሳሰሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች የተጠቁ ሰዎች።

*ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች በትንኝ እንዳይነከሱ ከሌሎች የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።*

ቺክቭ እንዴት ነው የሚታከመው? ቺክቭ ለማከም የሚውል ተለይቶ የታወቀ መድሀኒትም ይሁን ክትባት #የለም

#DCSSH

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በቺክቭ ተጠቂቻለሁ የሚል ጥርጣሬ ካደረብኝ ምን ማድረግ አለብኝ? ትኩሳት እና የመገጣጠሚያ ህመም ለመቀነስ መድሀኒቶችን መጠቀም ጥቅም ሊኖረው ይችላል። ሐኪም ያማክሩ።

ቺክቭ ይዞኝ ሉሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ካደረብዎ፦
 የታይብዎ ምልክቶችን መዝግበው በመያዝ ወደ ሐኪም ይሂዱ።
 ራስዎን ተጨማሪ በትንኝ ከመነከስ ይከላከሉ።
 በቺክቭ ከተያዙ በሽታው ወደ ሌሎች ሰዎች ላለማስተላለፍ እራስዎን ከትንኝ ንክሻ መከላከል ይኖርብዎታል።

ምን ማድረግ አለብኝ?

#ይልበሱ
ረዥም፣ ቀለል ያለ እና ቀላል ቀለም ያለው ልብስ ይልበሱ።

#ፈሳሽ_ማድረቅ
እቤት ውስጥም ከቤት ውጪም ያለ ማንኛውም ያቆረ ውሃ ያስወግዱ።

#ማታ እና #ጠዋት
ማታና ጠዋት ትንኞች በብዛት የሚንቀሳቅሱበት ጊዜ በመሆኑ በተቻለ መጠን ከቤት አይውጡ።

#DCSSH

#share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ይቅርታ ጠየቀ!

የአ.አ. ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ንፋስ ስልክ ላፍቶ በ2 አባላቱ ለተፈጠረው ድርጊት ኅብረተሰቡን ይቅርታ ጠየቀ!

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ ነሐሴ 20 ቀን 2011 ላይ ‘ሕጋዊ የኮሚሽን ሥራ እንሠራለን’በሚሉ እና ‘እኛም ሰፈራችን ስለሆነ እንሠራለን’ በሚሉ ግለሰቦች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማብረድ የፖሊስ አባላት የወሰዱት እርምጃ አነጋጋሪ ሆኗል።

በአካባቢው የነበሩት ፖሊሶች ፀብ ውስጥ የነበሩትን ግለሰቦች ‘ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዳችሁ ዳኝነት ታገኛላችሁ’ ቢሉም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አለመግባባት ተፈጥሮ የፖሊስ አባላቱ የተወሰኑ ሰዎችን መደብደባቸውን የአ.አ. ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽን እና የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለኢቲቪ አራት ማዕዘን ዝግጅት ክፍል አረጋግጠዋል።

ፖሊሶቹም ራሳቸው ደንብ ልብሳቸውን ለብሰው፣ ሥራ ላይ ተሰማርተው እያሉ፣ አንደኛው ላይ ከእነ ልብሱ ፖሊሱን በማነቁ፣ ሌላኛው ላይ ደግሞ መሣሪያ ጭምር ለመቀማት እና የመተናነቅ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል ብለዋል።

በዚህም የተነሣ ፖሊሶቹ ነገሩን ለማብረድ ጥይት ተተኩሰዋል፣ድብደባም ተፈጽሟል በማለት ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል።

የተፈጠረውን ድርጊት ተከትሎ የፖሊስ አባላቱ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስፈላጊውን ማጣራት እያደረገ መሆኑንም ገልፀዋል። ሆኖም ለድርጊቱ የአ.አ. ፖሊስ ኮሚሽን ኅብረተሰቡን ይቅርታ ይጠይቃል ብለዋል።

https://telegra.ph/ETH-08-27-3
ሰኔ 15 ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌን አጓጉዤያችኋለሁ ያሉ ምስክር ቃላቸውን ሰጡ!

የሰኔ 15ቱን የባህር ዳር ጥቃት #ተጠርጣሪዎች ጉዳይ የሚመለከተው ፍርድ ቤት ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት ብርጋዴየር ጄነራል አሳምነው ጽጌን ወደ ጎንደር መስመር አጓጉዤያቸዋለሁ ያሉ ሹፌርን የምስክርነት ቃል አደመጠ። በጥይት ቆስለው ሆስፒታል የሚገኙት ሹፌሩ ፍርድ ቤት የቀረቡት በተሽከርካሪ ወንበር ነው።

የሹፌሩን የምክርነት ቃል ዛሬ ረፋዱን በነበረው ችሎት ያደመጠው በእነ ብርጋዴየር ጄነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ የተጠረጠሩ 48 ሰዎችን ቅድመ ክስ እየተመለከተ የሚገኘው የባህር ዳር እና አካባቢው ፍርድ ቤት ነው። ፍርድ ቤቱ የአማራ ክልል አቃቤ ህግ አሉኝ ያላቸውን 17 ምስክሮችን ለማድመጥ ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም ዛሬ በችሎት የቀረቡት ሁለቱ ብቻ ናቸው። 

ሁለቱም ምስክሮች የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ሌሎች ባለስልጣናት በባህር ዳር በተገደሉበት ዕለት መኪና የማሽከርከር የስራ ስምሪት እንደተሰጣቸው ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል። በሰኔ 15 ብርጋዴየር ጄነራል አሳምነውን በመኪናቸው ማጓጓዛቸውን የተናገሩት አንደኛው ሹፌር ከዚያ አስቀድሞ ወታደሮችን ከቦታ ቦታ ሲያዘዋውሩ እንደነበር ተናግረዋል።

#DW

ይህን ይጫኑና ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-27-4
የኦነግ ወታደራዊ ዩኒፎም ተያዘ እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው!

በወልዲያ የፍተሻ ጣቢያ ላይ የተያዘው ወታደራዊ ዩኒፎርም መሰል አልባሳት የእኔ ነው ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ መነሻዉን መቐለ ያደረገ አይሱዙ ወልዲያ የፍተሻ ጣቢያ ላይ ሲደርስ በፍተሸ ጣቢያ ሰራተኞች ተይዞ ፍተሻ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ምክንያቱ ደግሞ የጫነዉ አልባሳትን ምንነት ለማረጋገጥ ነዉ ተብሏል፡፡

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሰለሞን ወርቁ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ መኪናዉን ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ቁጥጥርና ጥበቃ ሰራተኞች /ስካዉት/ የሚለብሱት ዩኒፎርም ነበር ብለዉናል፡፡ መኪናዉም 3 ሺህ የዩኒፎርም አልባሳትና 170 ጃኬቶችን ጭኖ ከመቀሌ አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ እንደነበረም ነዉ የተናገሩት፡፡

አልባሳቱ #የተጫነዉ በግል መኪና መሆኑና አልባሳቱ የኛ መሆኑን የሚያመለክት ደብዳቤ በአሽከርካሪዉ እጅ አለመገኘቱ ለጥርጣሬዉ መነሻ እንደሆነም አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተነጋግረን ማረጋገጫ ደብዳቤ እንድንጽፍ በጠየቁን መሰረት ደብዳቤ ጽፈናል፤በነገዉ እለትም መኪናዉ ወደ አዲስ አበባ ይንቃቀሳል ብለን እንጠብቃልን ነዉ ያሉት፡፡

ከዚህ ባሻገር ግን አልባሳቱ የኦነግ ነዉ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰዉ ወሬ #ከእዉነት_የራቀ_ነዉ፤ አልባሳቱ የኛ ነዉ፤ ለዱር እንስሳት ጥበቃ ለመተማሩ ሰራተኞች የተዘጋጀ ዩኒፎርም ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ በፌደራል ደረጃ በሚተዳደሩ 13 ብሄራዊ ፓርኮች 790 ስካዉቶች በስራ ላይ ተሰማርተዉ ይገኛሉ፡፡

Via #ETHIOFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በ2011 በጀት አመት ሊሰወር እና ሊጭበረበር የነበረ 50 ቢሊዮን ብር መገኘቱን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ከሂሳብ እና ከኦዲት ባለሙያዎች ጋር ውይይት በአዲስ አበባ እያደረገ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ሸዋ ዞን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በመፍሰስ ያስከተለው ጎርፍ 3ሺህ 500 ሄክታር የእርሻ ማሳ ላይ የተዘራ ሰብልን ከጥቅም ውጪ ማድረጉን የዞኑ ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጉታ ቡልቻ ለኢዜአ እንደገለጹት ጎርፉ ያደረሰው ጉዳት ኤጀርሳለፎ እና ኤጄሬ በተባሉ ወረዳዎች በሚገኙ 12 ቀበሌዎች ውስጥ ነው። በዚህም በ3ሺህ 500 ሄክታር ማሳ በመጥለቀለቁ ተዘርቶ የነበረ የስንዴ፣ የበቆሎ፣የማሽላና ሌላም ሰብል ከጥቅም ውጭ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር አራተኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ከነሐሴ 24 ጀምሮ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ። ምከር ቤቱ በቆይታዉ የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት የስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባኤው ምክር ቤቱ የክልሉን የጠቀላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስራ ቤትን ሪፖረትና እቅድን በማድመጥ ያጸድቃል ተብሏል።

በተያያዘ ዜና...

የምክር ቤቱ አባላት ከመደበኛ ጉባኤው አሰቀድመው በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሀዋሳ ከተማ ላይ እየመከሩ ነው። ምክክሩ በሀገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታና ክልላዊ ጉዳዮች ምን ደረጃ ላይ ናቸው የሚላውንና በክልሉ እየተነሱ ያሉት የአደረጃጀት ጥያቄዎች የሚመለከት ሁላት አንኳር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

እንደ ኤፍ ቢሲ ዘገባ መድረኩን የመሩት በሚንስትር መዓረግ የዲሞክራሲ ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ አቶ መለሰ አለሙ እንዳሉት የምክር ቤቱ አባላት በሀገራዊና ክልላዊ ነበራዊ ሁኔታ ላይ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ የመስፈጸም አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ለማስቻል የታሰበ ነው። በክልል ደረጃ በተነሳዉ የአደረጃጀት ጥያቄ በምሁራን የጠናው ጥናት ለምክር ቤቱ አባላት ቀርቦ ምክክር የሚደረግበት እደሆነም ተናግረዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሱዳናውያን ሴቶች አደባባይ ወጡ!

ሱዳናዊያን ሴቶች በሽግግር መንግስቱ ምስረታ የሴቶች ተሳትፎ #አልተረጋገጠም ሲሉ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡ ሱዳንን ለሦስት አስርት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ዑመር ሃሰን አል-በሽር በሕዝባዊ ተቃውሞ ባለፈው ሚያዝያ ላይ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላም ሱዳን ሰላም አልነበራትም፡፡

ከበርካታ ግጭቶች እና ተቃውሞዎች በኋላ ከሦስት ቀናት በፊት ለሚቀጥሉት 21 ወራት ሀገሪቱን የሚመሩ የሽግግር መንግስት አባላት ተሰይመዋል፡፡ የሽግግር መንግስቱ ከተቋቋመ እና ቃለ መሃላ ከፈፀመ በኋላ ትናንት ሰኞ በሱዳን ኦምዱርማን ሴቶች ‹‹በሽግግር መንግስቱ መስረታ በውሳኔ ሰጪነት ቦታ ላይ የሴቶች ተሳትፎ የለም›› በሚል ለተቃውሞ ጎዳና ወጥተዋል፡፡

በኡማ ፓርቲ መቀመጫ ኦምዱርማን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ሰልፈኞቹ ‹‹ትግላችን ለሴቶች እኩልነት፣ ፍትሃዊነት እና የሴቶችን ነፃነት እስኪረጋገጥ ድረስ ይቀጥላል›› ብለዋል፡፡ ሴቶች እንደማንኛውም የተፎካካሪ ፓርቲ ተደራጅተን ለመብታችን እንከራከራለን ወይም ደግሞ በሽግግር መንግስቱ አባላት ውስጥ ሴቶች በውክልና ሳይሆን 50 በመቶ የሚሆነውን ቦታ ሊሸፍኑ ይገባል ብለዋል፡፡ የውክልና መብታቸው እስኪረጋገጥ ድረስም ተቃውሞው እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፡- አፍሪካ ኒውስ/AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OLF

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በቀጣዩ ምርጫ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚወዳደር አስታውቋል። በምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሂደቱን ገና ያልጨረሰው ኦነግ ፤ በመላ ሃገሪቱ ምርጫ መወዳደር የሚያስችል ቁመና አለኝ ብሏል። ከምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሰርተፍኬት የማግኘት ሂደቱን ከጨረሰ በኋላ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጀምርም አስታውቋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-08-27-5

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሌሎች ድርጅቶች መካከል በትብብር የሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የታገደበት ዋና ዋና ምክንያቶች፦

1. በትብብር ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሥርዓት ባልተዘረጋበትና ተቋማት ተገምግመው ብቁ መሆናቸው ባልተረጋጠበት ሁኔታ እየተሰጠ ያለው ትምህርት ህጋዊና አግባብነት የሌለው እንዲሆን የሚያደርጉት ጉዳዮች ፡-

1.1. ዩኒቨርስቲዎች በትብብር የሚያስተምሩት ከኤጀንሲው እውቅና ከተሰጣቸው የግል ከፍተኛ ት/ተቋማትጋር ከሆነ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እውቅና ባገኙበት ግብዓት ላይ ተጨማሪ ተማሪ ማስተማር ህገወጥ ከመሆኑም በላይ በጥራት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር በመሆኑ፤

1.2. ዩኒቨርስቲዎች በትብብር የሚያስተምሩት ከኤጀንሲው እውቅና ካልተሰጣቸው ለሌላ አገልግሎት ከተመሰረቱ ተቋማት ጋር ከሆነ ትምህርቱ የሚሰጥበት ሁኔታ አነስተኛ የጥራት መለኪያ መስፈርቶችን ስለማሟላታው ባለመረጋገጡ የሚሰጠው ትምህርት ጥራት ያለውና አግባብ መሆኑ ስለማይታወቅ፤

1.3. ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት የሚሰጡት በመጀመሪያ ደረጃና በሁለተኛ ደረጃት ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ክፍሎችን በመከራየት ከሆነ ተማሪዎች ምንም አይነት የቤተ-መጸሀፍት፣ የዲሞኒስትሬሽን፣ የላቦራቶሪና የኮምፒዩተር ማእከልና ሌሎች ለትምህርቱ አጋዥ የሆኑ አገልግሎቶች በሌሉበት ሁኔታ የሚሰጥ በመሆኑ ለከፍተኛ የጥራት መጓደል የሚዳርግ በመሆኑ፤

****

2. የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከተቋማቸው (እውቅና ከተሰጣቸው ካምፓሶች) ብዙ ኪሎ-ሜትር በመራቅ እውቅና ባላገኙበት ካምፓስ (የማስተማሪያ ቦታ) ማስተማራቸው

2.1. ዩኒቨርስቲዎች መደበኛ ስራቸው ላይ እንዳያተኩሩ ችግር ከመፍጠሩም በላይ ከተሰጧቸው ዋና ዋና ተልእኮዎች መካከል ጥናትና ምርምርንና የማህበረሰብ አገልግሎትን በአጥጋቢ ሁኔታ እንዳያከናውኑ የሚያደርጋቸው በመሆኑ፣

2.2. መምህራን በተደጋጋሚ ከተቋማቸው ውጭ ስለሚንቀሳቀሱና ለረጅም ጊዜ ከተቋማቸው ርቀው ስለሚቆዩ መደበኛ ተማሪዎች በቂ ትምህርትና እገዛ እንዳያገኙ ስለሚያደርግ፤

2.3. የመንግስትን ሀብትና ንብረት ላልታለመለት አላማ እንዲያውሉ መደረጉ፤

****

3. አብዛኞቹ የትብብር ትምህርቶች የሚሰጡት ተባባሪ ተቋማት ከማስተማር የሚሰበሰበውን ፋይናንስ እንዲያስተዳድሩ በማድረግ በመሆኑ፣

3.1. ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ዩኒቨርስቲዎች ከመንግስት የፋይናንስ ስርዓት ውጭ የመንግስትን ሀብትና ንብረት አላግባብ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ አጋጣሚ ስለሚፈጥርና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስርዓትን በማዘጋጀት በሚነስትሮች ም/ቤት በማጸደቅ ተግባራዊ ያደረገውን አሠራር ስለሚጥስ፣

3.2. ተባባሪ ተቋማትን የሚመርጡበት የማወዳደሪያ መስፈርት ሂደትና የገቢ ክፍፍል ሁኔታ ግልጸኝነት የጎደለውና የመንግስትን መመሪያና ስርዓት ያልተከተለና ለኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር የተጋለጠ በመሆኑ፤
በአጠቃላይ በሀገራችን የትምህርት ጥራት ያለበት ሁኔታ ማንንም ቅን አሳቢ ዜጋ የሚያስጨንቅ በሆነበትና መንግሥትም ከመቹውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ በሚሰራበት ወቅት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሀገርን ጥቅም በዘላቂነት ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ ጥራትና አግባብነት ላይ በማተኮር በክፍለ አሀጉር፣ በአሀጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በሚያደርጋቸው ሥራ ላይ ከማተኮር ይልቅ እሴት በማይጨምርና በተቋማቸው ከሚሰጡት ትምህርት በባሰ መልኩ ብቃቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ ትምህርት መስጠቱ አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ ወደፊት ጥናት ላይ ተመስርቶ ሥርዓት እስኪበጅ ድረስ የትብብር ትምህርት የታገደ መሆኑን በድጋሚ እናስታውቃለን፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE ወደ አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ለመግባት የሚያስፈልጉ የመመዝገቢያ መስፈርቶች ይፋ ተደርጓል እየተባለ በአንዳንድ የማዕበራዊ ሚዲያዎች የሚወራው ውሸት ነው። ASTU/AASTU የመመዝገቢያ መስፈርት ገና ይፋ አልተደረገም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia