TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ወጣቶች አንድነታቸውን እና ጥንካሬያቸውን ለሀገር አንድነት፣ግንባታ እና ለሰው ልጆች መብት መከበር እንዲያውሉት የአዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ቧያለው ጥሪ አቀረቡ፡፡ የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል የማጠቃለያ ዝግጅት በአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አደራሽ ተከብሯል፡፡

በማጠቃላይ ዝግጅቱ የተገኙት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዩሐንስ ቧያለው በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው ‹‹ውበታችሁን፣ አንድነታችሁን እና ጥንካሬያችሁን ለሀገር አንድነት፣ ግንባታ እና ለሰው ልጆች መከበር ተጠቀሙበት›› ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ በበኩላቸው የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል በዓለም የማይዳሰስ የቅርስ መዝገብ ውስጥ እንዲሰፈር የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡ በበዓሉ ለታደሙት የኅበረተሰብ ክፍሎችም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው?

እኛ የአምቦ ወጣቶች ዛሬ!


Gammachuu haadholii keenya sanbataa

በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው እናቶቻችን ጎረቤታሞችና በአንድ ቀን በተመሳሳይ ሁኔታ ልጆቻቸውን በግፍ የተነጠቁ/የተገደሉባቸው እናቶች ናቸው። ምንም እንኳን ልጆቻቸውን በሞት ቢነጠቁም በልጆቻችው በአምቦ ወጣቶች እገዛ የቤት እድሳት ተደርጎላቸዋል። ወጣቶቹ ለዚህ ስራ ድጋፍ እገዛ ላደረጉላቸው ወንድሞቻቸው በአጠቃላይ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Galannii haadholii keenyaa isiin haa qaqqabuu

#አሸብር_መገርሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
285 ባለሀብቶች እንደተሰወሩ ተሰማ!

በጋምቤላ ክልል ለግብርና ኢንቨስትመንት መሬት የወሰዱ ባለሃብቶች ፈጥነው ወደ ሥራ እንዲገቡ የክልሉ መንግሥት ጥሪ አቀረበ። በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት መሬት የተረከቡ 285 ባለሃብቶች ከአካባቢው እንደተሰወሩ ተገልጿል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ሰሞኑን በአበቦ ወረዳ የባለሃብቶችን እርሻ በጎበኙበት ወቅት እንዳሳሰቡት ለኢንቨስትመንት የክልሉ መንግሥት ኢንቨስትመንት ለአገር ልማት ያለውን ድርሻ በመገንዘብ መሬት የተሰጣቸው ባለሀብቶች ሥራ ፈጥነው መጀመር ይጠበቅባቸዋል።

በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ከገቡት ከ700 በላይ ባለሃብቶች መካከል 285ቱ መሬት ተረክበው መሰወራቸውን ተናግረዋል። የኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለአገር ልማትም ሆነ ለዜጎች ሥራ ለመፍጠር ዓይነተኛ መሣሪያ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የክልሉ መንግሥት የባለሃብቶች ችግሮች ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል። ለዚህም አልሚ ባለሃብቶች በመደገፍ ረገድ የክልሉ መንግሥትና በየደረጃው ያለው አመራር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማስታወቂያ

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2012 ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል። በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦

1. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ 40 ብር በመክፈል የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ማቅረብ፤

2. በዲፕሎማችሁ ለምታመለክቱ150 ብር በመክፈል ከትምህርት ማስረጃ ጋር የCOC ደረጃ 3 ወይም 4 ማቅረብ

3. ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ 150 ብር በመክፈል ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ

4. ለPreparatory አመልካቾች ከ2004-2011ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ 40 ብር በመክፈል ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ

5. ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ 40 ብር በመክፈል ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ

6. ለያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት እና ለአለ ፈለግ ስእል ትምህርት ቤት በቀን መርሃ ግብር ማመልከት የሚችሉት በPreparatory ከ2004-2010 ዓ.ም. ተምረው የጨረሱና ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን አምጥተው ለነበሩ የወጪ መጋራት ክፍያ ያጠናቀቁበትን ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር ማያያዝ፡፡

የምዝገባ ቀን-ከነሐሴ 20 እስከ ጳጉሜ 1 2011 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ-በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
የክፍያ ቦታ-ከሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 7 ወይም 8

ማሳሰቢያ፡-

1. አመልካቾች በዩኒቨርስቲው ድረ-ገጽ (portal.aau.edu.et ) ላይ ማመልከትና የመመዝገቢያ ቁጥሩን በመያዝ የትምህርት ማስረጃ አንድ ኮፒ ከአንድ ጉርድ ፎቶግራፍ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲውን የመግቢያ ፈተና ጊዜን ፤ የትምህርት ክፍሎቹን ዝርዝር እና ተጨማሪ ማብራሪያ ከዩኒቨርስቲው ድረገጽ (www.aau.edu.et) እና (www.portal.aau.edu.et) ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

#አአዩ_ሬጅስትራር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
5ኛው አመት የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ከነገ ነሃሴ 20 እስከ መስከረም 30 በመላው ሀገሪቱ ይካሄዳል!!

ላለፉት አመታት በአብዛኛውን በከተሞች አካባቢ የሰራነውን ስራ #በማጠናከር ዘንድሮ ደግሞ ከከተማ ውጭ ወደሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረታችንን እናደርጋለን።

ምን አይነት መፅሃፍት ነው ከቤተሰባችን አባላት የምናሰባስበው?

•ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ መደበኛ የመማሪያ መፅሃፍትን/Text Book/ እንዲሁም አጋዥ መፅሃፍት ብቻ

•በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ትውልዱን ይጠቅማል፤ እውቀት ያስጨብጣል የምንላቸው መፅሃፍት።

•ትንሹ መስጠት የሚቻለው መፅሃፍ 1

•መፅሃፍቱ የሚገቡት ገጠራማ አካባቢ ለሚገኙ እና በአካል ሄደን ለምንለያቸው ቤተ መፅሃፍት

#እርሶ ምን ማድረግ ይችላሉ??

√ቢያንስ አንድ የመማሪያ መፅሃፍ ለሚወዷት ለኢትዮጵያ መለገስ ይችላሉ። እንዲሁም ከፍተኛ የመፅሃፍት ችግር ያሉባቸው ቦታዎችን በመለየት የማስተባበር ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።

•TIKVAH-ETH በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ለምትገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራት ይህን ሀገራዊ ስራ እንድታግዙ ጥሪውን ያቀርብላችኃል።

•የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ከተማራቹባቸው እና ስትጠቀሟቸው ከነበሩት መፅሃፍ መካከል ቢያንስ አንዱን ለመጪው ትውልድ በስጦታ አበርክቱ።

•በStopHateSpeech ጉዞ ተሳታፊ የነበራችሁ የቤተሰባችን አባላት ይህን ለሀገርና ለትውልድ የሚሰራን ስራ በሙሉ አቅማችሁ እንድታግዙ ጥሪ እናቀርባለን።

•በውጭ ሀገር የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቃሚ ናቸው የምትሏቸው መፅሃፍት በመላክ አልያም እዚህ ሀገር ባላችሁ ወዳጅና ዘመድ መፅሃፍት እንዲገዛ በማድረግ ይህን

#ኦሮሚያ
#አማራ
#ትግራይ
#ደቡብ
#ሱማሌ
#አፋር
#ሀረሪ
#ጋምቤላ
#ቤኒሻንጉል
#አ/አ ከተማ አስተዳደር
#ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

🏷በማኛውም አይነት ቋንቋ የተዘጋጀ የመማሪያ መፅሃፍ መለገስ ይቻላል!!
-------------------------------------------------------
በአሁን ሰዓት ልየታ ከተደረገባቸው አካባቢዎች መካከል፦

#ራያ_ቆቦ በራያ ቆቦና ዙሪያዋ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት መፅሃፍት ለመለገስ እና ይህን ስራ ለማስተባበር ከቤተሰባችን አባል #ሉላይ ጋር ይገናኙ፦ +251949256094

#ድሬዳዋ በድሬዳዋ ከተማ እና አካባቢው የምትገኙ ደግሞ ከቤተሰባችን አባል መሃሪ 0915034762/መሃሪ/ ጋር መገናኘት መፅሃፍ መለገስ ትችላላችሁ።

ሌሎች አካባቢዎች ላይ እኛም ለሀገራችን መስራት እንፈልጋለን የምትሉ እውቅና ያላችሁ ማህበራት ካላችሁ መልዕክት አስቀምጡልን @tsegabwolde 0919743630

5ኛው አመት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው የኮርያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋምን ጎብኝተው የኮርያን ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ሳይንስና ቴክኖሎጂ በተጫወተው ሚና ዙሪያ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል።

ምንም እንኳን ተቋሙ በአሁን ወቅት ያለው የሥራ ግንኙነት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርትና ከአዳማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር ቢሆንም ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ይህንኑ መሳይ ተቋም በኢትዮጵያ ለማቋቋም በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#uodate ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ሁለቱ ወገኖች ለኢትዮጵያ ሲደረጉ በነበሩና በአዳዲስ ድጋፎች ዙሪያ መክረዋል።

በአሁኑ ወቅት በኤግዚም ባንክ ድጋፍ ከ600 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚፈጁ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ 300 ሚሊዮን ዶላሩ በ2011-2012 በኮርያ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ፈንድ ማእቀፍ ስር የተፈረመ ነው።

ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው በደቡብ ኮርያ ይፋዊ ጉብኝታቸ በኮርያ ጦርነት ወቅት ለወደቁ መታሰቢያ በሆነው በሴውል ብሄራዊ #የመቃብር ቦታ ጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወረዳ አስተዳዳሪው ላውንቸር እና ሌሎች ከባድ የጦር መሣሪዎችን በማዘዋወር ተጠረጠሩ!

•የአፋር ክልል ፖሊስ ተጠርጣሪውን ይዞ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ደርሶታል።


በአፋር ክልል ዳሊሳጊ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት መሐመድ የጊሊስ ላውንቸር እና ከባድ መትረየስን ጨምሮ ሌሎች 11 ዓይነት ከባድ እና ቀላል መሣሪያዎችን ሲያዘዋውሩ ተገኝተዋል በሚል ክስ ተመሰረተባቸው።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በመሰረተው ክስ የወረዳ አስተዳዳሪው ከኹለተኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን በመንግሥት መኪና የጦር መሣሪያዎቹን ሲያዘዋውሩ ተገኝተዋል ሲል አብራርቷል። በአፋር ክልል ባቲ ተብሎ በሚታወቀው ኬላ ላይ በቁጥጥር ሥር የዋሉት እና መኪናውን ሲያሽከረክሩ የነበሩት ጀማል ሁሴን ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የዋስትና መብታቸውን ነፍጓቸዋል።

መሐመድ ጊሊስን ግን የክልሉ ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብ ቢታዘዝም ይዞ ለማቅረብ እንዳልቻለ ፖሊስ ለፍርድ ቤት ገለጿል። የክልሉ መንግሥትም የተያዙት ጦር መሣሪዎች የክልሉ ንብረት ከሆኑ እንዲያሳውቅ እንዲሁም የሚዘዋወሩትም ለሥራ ዓላማ ከሆነ እንዲገለጽ ከፍርድ ቤቱ ጥያቄ ቀርቧል።

እስካሁን በቁጥጥር ሥር ያልዋሉትን አንደኛ ተከሻሽን የፌደራል ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብ ችሎቱ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን በተመሳሳይም የክልሉ ፖሊስም ተከሻሹን እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቶች እስከ ጥቅምት መጀመሪያ በእረፍት ምክንያት በሥራ ላይ ያለመሆናቸውን ተከትሎም ለኅዳር አንድ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን በተመሳሳይ በዕለቱ ፍርድ ቤቱ ክስ እንደሚሰማ ይጠበቃል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-26

Via አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጎርፍ አደጋ ከ60 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል!

በሱዳን ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ በሃገሪቱ ከሃምሌ ወር ጀምሮ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በ15 አካባቢዎች ከ2መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል፡፡

እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ከ 37 ሺህ በላይ ቤቶች በጎርፉ ሳብያ ፈርሰዋል ወይም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በሱዳን የዝናባማ ወቅት እስከ የፊታችን ጥቅምት ወር ድረስ የሚቆይ በመሆኑ ጎርፍ ከዚህ በላይ አደጋ እንዳያደርስ ተሰግቷል፡፡

Via #ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመማሪያ መፃህፍትን ለግሱ!

#አዲስ_አበባ
👉ዮናስ ገ/መስቀል
0970514616
👉መባ
0924140293

#ሰበታ
👉ያሬድ ለማ
0932540523
👉ያብስራ ካሳ
0921421493

#መቐለ
👉ኤርሚያስ ደጀኔ
0912178520
👉ፊራኦል መስፍን
0923602445

#ራያ_ቆቦ
👉ሉላይ
+251949256094

#ድሬዳዋ
👉መሃሪ
0915034762

#አዳማ
👉ሰላም
0949377735

5ኛው አመት የTIKVAH-ETHIOPIA የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ግብፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ይዛ የመጣችውን አዲስ ሃሳብ እንደማትቀበል አስታወቀች፡፡ ግበፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦችን ይዛ ብቅ ማለቷን ተከትሎ፣ የኢትዮጲያ መንግስት ቀደም ሲል ከተቀመጠዉ መርህና አሰራር ውጪ በግብፅ የሚነሱ ሃሳቦች ተቀባይነት የላቸውም ብሏል፡፡

ግብፅ ከ ሰሞኑ የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት በሰባት አመታት ውስጥ ይሁንልኝ ብላለች፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ኢትዮጲያ ያላት አቋም በ2012 የዉሃ ሙሌቱ ይጠናቀቃል የሚል ነዉ፡፡ ከምንከተለዉ መመሪያና የተፋሰስ ሃገራቱ ካስቀመጧቸው የመደራደሪያ ነጥቦች ውጪ በግብጽ የሚነዳዉ ሃሳብ ተቀባይነት እንደሌለዉም አስታውቀዋል፡፡

ሱዳንን ጨምሮ ሶስቱ ሃገራት በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚያካሂዱትን የሶስትዮሽ ድርድር በሱዳን የፓለቲካ ቀውስ ምክንያት መስተጓጎሉን ጠቅሰዉ፣በቀጣይም ድርድሩ የሶስቱንም ሃገራት የጋራ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ውጪ ከሱዳንም ሆነ ከግብፅ የሚነሱ ምክንያታዊ ያልሆኑ አሉታዊ መግለጫዎች በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት እንደማይኖራቸዉ አቶ ነብያት ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቀጣዮቹ 5 አመታት የሚያገለግል ስትራቴጅካዊ ረቂቅ እቅድ ማዘጋጀቱን ገልጿል። የከፍተኛ ትምህርት አማካሪ ምክር ቤት ሁለተኛው ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴሩም በጉባኤው ላይ ለቀጣዮቹ 5 አመታት የሚያገለግለውን እና ያዘጋጀውን ስትራቴጅካዊ ረቂቅ እቅድ አስተዋውቋል።

በቀረበው ረቂቅ እቅድ ላይም በጉባኤው ባለድርሻ አካላት እየመከሩበት ይገኛል። እቅዱ የከፍተኛ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ያሉባቸውን ክፍተቶች ለማስተካከል የሚያግዝ ነው ተብሏል። ከዚህ ባለፈም አዳዲስ አሰራሮችን ለመዘርጋት እንደሚያግዝም ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።

ረቂቅ እቅዱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪዎች ጋር በቅንጅት መስራት ላይ ያሉባቸውን ችግሮች በምን መልኩ መፍታት ይገባል የሚለውን ተመልክቷልም ነው የተባለው፡፡ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ዙሪያ የሚታየውን የጥራትና ፍትሃዊነት ጥያቄዎችን ለማሻሻል እንደሚረዳም ታምኖበታል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ በከፍተኛ ዲፕሎማቶቻቸው የሚመራ የጋራ ኮሚቴ ለመመስረት ተስማሙ፡፡ ሁለቱ አገራት ከዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሙን ጄኢን ጋር ዛሬ በሶል በተገናኙበት ወቅት፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ሃይ” ባይ የሚሻው የዋጋ ንረት!

አሁን ያለው የገበያና ግብይት ሁኔታ ማነጋገር ከጀመረ ሰንብቷል። በተለይም በከተሞች ያለው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ የሸማቹን አናት እያዞረ፤ አቅሙን እያሽመደመደ፣ ኑሮውን አደጋ ላይ እየጣለና ህልውናውን እየተፈታተነው ይገኛል።

የሰሞኑንም ሆነ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲከሰቱ የነበሩትን ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪዎችንና ንረትን ቀረብ ብሎ ለተመለከተ በአንድ የገበያ ስርአት ውስጥ አበይት የሆኑ ባህርያትን – መንግስት፣ ህዝብና ነጋዴው – እየተናበቡ ሳይሆን እየተገፋፉ፣ እየተቀራረቡ ሳይሆን እየተራራቁ መሆናቸውን፤ ይህም የገበያ ስርአት አልበኝነትን ሳይፈጥር እንዳልቀረ መረዳቱ የግድ ነው። ለዚህ ደግሞ የግብይት ስርአቱ ሙሉ ለሙሉ በአንድ ወገን ተፅእኖ ስር መውደቁን ያሳያል።

የዚህ ስርአት አልበኝነት መንሰራፋት ለህገ ወጦች በተለይም ለደላላው ክፍል ሰፊ የመፈንጫ ሜዳን ያመቻቸ፣ ለሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ መልካም አጋጣሚን የፈጠረ ሲሆን የእነዚህ ድምር ውጤትም ሸማቹን እያማረረው ይገኛል። በዚህ ላይ የገንዘብ ግሽበት፣ የገበያ አሻጥር፣ ድህነት ወዘተ ሲጨመርበት ደግሞ ጉዳዩ ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል።

የመጫወቻ ካርዱን “ነፃ ገበያ” ካደረገው የአገራችን የንግድና ግብይት ስርአት የታሪፍ ህዳግም ሆነ የምርቶችና የአገልግሎቶች የመናሻ ዋጋ የሌለው መሆኑ የመግዛት- መሸጡን ሂደት ቅጣንባሩን አጥፍቶታል። ይህም ለህገ- ወጥ ደላላውና በገንዘብና ንግዱ ዘርፍ የበላይነትን ለያዙ ጥቂት ወገኖች ምቹ የመፈንጫ ሜዳን ፈጥሮላቸዋል። ለሸማቹ ደግሞ በተቃራኒው።

#አዲስ_ዘመን

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-26
አሳዛኝ ዜና!

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ 12 ሰዎች ተገደሉ!

በሰሜናዊ ኬንያ ማርሳቤት ግዛት 12 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ታወቀ። ፈረንሳይ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው በአካባው በተቃጡ ኹለት ጥቃቶች 12 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከሟቾችም ውስጥ ሦስቱ ሕፃናት እንደሆኑ ገልጿል። ጥቃቱን በሚመለከት የኬንያ ፖሊስ ጥቃት አድራሾች የኢትዮጵያ የቦረና ጎሳዎች ናቸው ሲል አስታውቋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከግድያውም ባለፈ 5መቶ ቀንድ ከብቶች እንዲሁም 1 ሽሕ ፍየሎችም መወሰዳቸውን ጨምሮ ገልጿል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @gikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ ተጥሎ የነበረው የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ እገዳ ተነስቷል!

ባለፈው ወር በሀዋሳ ከተማ ተፈጥሮ ከነበረው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ በኮማንድ ፖስቱ ተጥሎ የነበረው የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ እገዳ ከዛሬ ጀምሮ ተነስቷል። ነገር ግን ሞተር ማሽከርከር የሚቻለው ከጥዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:00 ብቻ መሆኑ ነው የተገለፀው። ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ ከፀጥታ አካላት ውጪ የትኛውም አካል ሞተር ሳይክል ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም ተብሏል።

Via #SRTA/የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሲምካርድ ከአገር ውጪ በዝቅተኛ ክፍያ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ። ድርጅቱ በሮሚንግ አገልግሎት ላይ የክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን ገልጿል። የሮሞንግ አግልግሎት ኢትዮጵያዊያን ወይም የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ለስራ፣ ለትምህርት እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች ከሀገር ሲወጡ ሲም ካርድ መቀየር ሳያስፈልጋቸው በሄዱበት ሀገር በዓለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱ ከዚህ በፊትም የነበረ ቢሆንም ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም ደንበኞች ይህ አገልግሎት ውድ ነው በሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱበት ነበር። ኢትዮ ቴሌኮም ይሄነን ቅሬታ ለመፍታት ከተለያዩ ሀገራት ኦፕሬተሮች ጋር በመነጋገር የክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሰላም፣ልማትና ዴሞክራሲ የሰፈነባትን ሃገር ለመገንባት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል"—ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

ሰላም የሰፈነባት ፣ ህዝቦቿ እንደታሪካቸው በመከባበር የሚኖሩባትን ሀገር ለመገንባት ሁላችንም የድርሻችንን ማበርከት ይጠበቅብናል ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።

ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ ይህን የተናገሩት “ህገ-መንግስትና ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓትን ማዳን ለዴሞክራሲያዊ ሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመቀሌ ከተማ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ ሲከፍቱ ነው።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት አንዣብቦ በታየው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት የዜጎች መብቶች በአደባባይ ሲጣሱ የታየበት ፣ ህዝቦች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት የማይችሉበት፣ ሃብት ለማፍራት የተቸገሩበት ፣ ለጥቃት የተጋለጡበትና የህግ የበላይነት አደጋ ላይ የወደቀበት መሆኑንም ተናግረዋል።

“ይህ አስከፊና አደገኛ ሁኔታ ለዜጎች ህይወት መጥፋት ፣ ጉስቁልናና የወደፊት ተስፋ መታጣት ምክንያት ሆኗል” ያሉት ዶክተር ደብረፅዮን በዚህ ከቀጠለ በአገሪቱ አንድነትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ላይ የከፋ አደጋ እንዳይከሰት ስጋት መፍጠሩንም አስረድተዋል።

“እየታየ ያለውን ከፍተኛ ስጋትም ሁላችንም ተባብረን በመታገል ህዝቦቻችን የሚፈልጉትን ሰላም ፣ ልማትና ዴሞክራሲ ለማስፈን ችግር የሚፈጥሩ አካላትን በብቃት መመከት አለብን” ብለዋል።

“አሁን በአገሪቱ በስፋት እየተከሰቱ ያሉትን ቸግሮች ህገ-መንግስቱን ካለማክበርና የህግ የበላይነትን ካለማረጋገጥ የሚመነጩ ናቸው” ብለዋል።


https://telegra.ph/ETH-08-26-2
የኢፌዴሪ ቆንስላ ፅ/ቤት!

"የዘንድሮውን የሀጅ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርአት ለመፈፀም ከአገራችን የመጡ ታዋቂ እንግዶችን ለማስተዋወቅ እና ለማመስገን በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ለመታደም የተገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ነሀሴ 12 ቀን 2011 በመካ ከተማ ከለሊቱ ስድስት ሰአት ገደማ በፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው..." ታውቋል። ደብዳቤው የተፃፈው ጅዳ በሚገኘው የቆንፅላ ፅ/ቤት ነው።

Via Elias Mesert
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሱዳን ህዝብና መንግስት ያጋጠማቸው ችግር በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ሚና መጫወቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የመንግስት ምስረታው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው ብሏል። የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ኃይሉ በኢትዮጵያ አደራዳሪነት ከቀናት በፊት የሽግግር መንግስት ለመመስረት መስማማታቸው ይታወሳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia