TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመቐለ ከተማ ሴቶች የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በሰማዕታት ሐውልት ግቢ ችግኝ ተከሉ። ሴቶቹ ችግኞቹን የተከሉት በዓሉን ከማድመቅ በተጨማሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራምን ለማሳካት እንደሆነም ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአንድ ቦታ፣ በአንድ ጊዜ አራት የመኪና አደጋ ደረሰ!

በባሕር ዳር ዙሪያ በተከሰተ የመኪና አደጋ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የመኪና አደጋ ተከስቷል።

አደጋው የተከሰተው ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር እየሄደ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ሸዋ ሮቢት ቀበሌ ላይ ዛሬ 8፡20 አካባቢ በመጀመሪያ ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው።

አውቶብሱ ከጎንደር አቅጣጫ እየመጣ ከነበረ ሲኖ ትራክ መኪና ጋርም ተጋጭቷል። አደጋው በዚህ አላበቃም፤ ከባሕር ዳር አቅጣጫ በፍጥነት እየተሽከረከረ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ፣ ተጋጭቶ ከቆመው ሲኖ ትራክ ጋር መጋጨቱም አራተኛ አደጋ ፈጥሯል።

በዚህም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ዘጋቢያችን ተመልክቷል፤ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የሰው ህይዎት እንዳላለፈም ነው ዘጋቢያችን መረጃ ያደረሰን።ተጎጅዎችም ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው። የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ከስፍራው ተገኝቶ ጉዳዩን እያጣራ ይገኛል። ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን ጥረት ብናደርግም አሁን መረጃ መስጠት የሚችሉበት ደረጃ ላይ አለመሆናቸውን አሳውቀውናል።

Via #አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ

"ሱሉልታን ከአ/አ የሚያገናኘው መንግድ በጎርፍ በመሙላቱ መኪናዋች ቆመዋል።" #TIKVAH_ETHIOPIA #AHMUU

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ በአዋሽ ወንዝ መሙላት ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። የአዋሽ ወንዝ መሙላት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ በርካታ ዜጎችን ጉዳት የደረሰ ሲሆን፥ የተዘሩ የተለያዩ ሰብሎችንም ከጥቅም ውጪ ማድረጉ ይታወቃል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#P1

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2012 የትምህርት ዘመን በሚያስጀምራቸዉ የመንግስት የአዳሪ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ላይ መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የቅበላ መስፈርት!
#P2

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2012 የትምህርት ዘመን በሚያስጀምራቸዉ የመንግስት የአዳሪ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ላይ መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የቅበላ መስፈርት!
#ጅግጅጋ

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አራተኛው አስቸኳይ ጉባዔ የቢሮ ኃላፊዎችን ሹመትና ረቂቅ ዓዋጅ አፀደቀ። ምክር ቤቱ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ የቀረቡለትን ኃላፊዎችን ሹመት ያፀደቀው አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች እንደገና ለማደራጀት ሥልጣንና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ ዓዋጅ ካፀደቀ በኋላ ነው።

ተሿሚዎቹ  ባላቸው የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድና የፖለቲካ ብቃት መሠረት በማድረግ መመረጣቸው ተገልጿል። ምክር ቤቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ሁለት የምክር ቤቱ አባላትን #ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ወስኗል። እንዲሁም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ ዓዋጅ ለሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

በምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ አግኝተው የተሾሙት፦

•አቶ አብዲቃድር ሐሺ – የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ሱቤር ሁሴን – የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ጠይብ አህመድኑር – የእንስሳት ልማት ቢሮ ኃላፊ
•አቶ አብዲሰላም ዩሱፍ – የኢንቨስትመንትና ዲያስፖራ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ሩብሌ አዋሌ– የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ፣

ባሉበት እንዲቀጥሉ የተደረጉት፦

•ዶክተር ዩሱፍ መሐመድ የጤና ቢሮ ኃላፊ
•ዶክተር አብዲቃድር ኢማን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ
•ወይዘሮ ዘይነብ ሐጂ አደን የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ሙበሽር ዱበድ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ኤልያስ አቢብ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ሐሰን መሐመድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አገር አቀፍ የፍትህ ቀን የፊታችን ጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ይከበራል፡፡ ቀኑ የሚከበረው “እኔ ለሕግ ተገዥ ነኝ” በሚል መሪ ቃል እንደሆነ ለመስማት ተችሏል። #ETHIOPIA
አሜሪካ የመካከለኛ ርቀት ሚሳኤል ማስወንጨፏ ተነገረ!

አሜሪካ የመካከለኛ ርቀት ተወንጫፊ ክሩዝ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን በወታደራዊ መስሪያ ቤቷ ፔንታገን በኩል አስታውቃለች። ከሩሲያ ጋር አድርጋው የነበረውን የኒየክሌር ተሸካሚ መሳሪያዎች እቀባ ስምምነት አልተገብርም ካለች ከሳምንታት በኋላ ሚሳኤል መሞከሯ እያነጋገረ ነው።

ፔንታገን እንዳስታወቀው ባለፈው ዕሁድ በካሊፎርኒያ ዳርቻ የተሳካ የሚሳኤል ሙከራ አድርጓል። ሞስኮ በበኩሏ ዋሽንግተን ወታደራዊ ውጥረቱን እያባባሰችው ነው በሚል ድርጊቱን ኮንናለች።

አሜሪካ ከመካከለኛ ርቀት ተወንጫፊ የኒዩክሌር ባለቤት ኃይሎች ስምምነት በሩሲያ ተጥሷል በሚል በፈረንጆቹ 2019 ነሐሴ 2 ቀን ከስምምነቱ መውጣቷ ይታወሳል። ሩሲያ ከአሜሪካ የቀረበባትን የስምምነት መጣስ ውንጀላ አጣጥላለች።

ተንታኞች የስምምነቱ ገቢራዊ አለመሆን አዲስ ወታደራዊ ፉክክርን ሊያመጣ ይችላል በሚል ስጋታቸውን ገልፀዋል። ከቀዝቃዛው ጦርነት ማግስት ተፈርሞ የነበረው ስምምነቱ ከ500 እስከ 5 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፉ ሚሳኤሎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ እገዳ የጣለ ነበር ብሏል የቢቢሲ ዘገባ።

Via #BBC/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሱሉልታ

"ሱሉልታ መንገድ ውሀ ሞልቶ የገኛል በዚህ የተነሳ ለሰአታት ቆመናል።" #Sington #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዳሽን ባንክ ጅማ ቅርንጫ ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱ ተከሳሾች ላይ ክስ ተመሰረተ። ተከሳሾች 1ኛአህመድ አብዶ፣ 2ኛ ጌቱ ወልደስላሴ፣ 3ኛ ዚያድ ሀሰን፣ 4ኛ የሱፍ ከድር፣ 5ኛ አንዋር ማሙድ፣ 6ኛ ገነት ሲሳይ፣ 7ኛ ሰይድ ሲራጅ፣ 8ኛ እንድሪስ ዓሊ እና 9ኛ ኦርጋኒክ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆኑ በፈፀሙት ከባድ የሙስና ወንጀልና በሙስና ወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20-4
በማይጨውና አዲሹ ከተሞች ጅብ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ!

በትግራይ ደቡባዊ ዞን በማይጨውና ሀዲሹ ከተሞች ጅቦች አምስት ሰዎችን በማጥቃት ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታወቀ። ጅቦቹ  ጉዳት ካደረሱባቸው ሰዎች መካከል አምስቱ በማይጨው ቀሪዎቹ ደግሞ በአላጄ ሀዲሹ የሚኖሩ ናቸው። በሰዎቹ ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድ ቢሆንም እስካሁን ግን ህይወቱ ያለፈ እንደሌለ የዞኑ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ኮማንደር ሐለፎም ሀዱሽ ገልጸዋል።

በማይጨው ከተማ በጅብ ተነክሰው የተጉዱት ሰዎች ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ወደ ጸበል ለመሄድ በመጓዝ ላይ እንዳሉ ሲሆን በለምለም ካርል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው። በወቅቱ በሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰው ጅብ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ትብብር መገደሉን ኮማንደሩ አመልክተዋል። በሀዲሹ ከተማ የተጎዱት ደግሞ ባለፈው እሁድ ምሽት አንዲት አዋቂ ሴት እና አንድ ህጻን ልጅ በከተማ በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ ሲሆን በከተማ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል። ህብረተሰቡ ሌሊት ላይ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ኮማንደሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE የዩኒቨርሲቲ መግቢያ #የመቁረጫ ነጥብ #ይፋ ተደርጓል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰረጫ ያለው መረጃ ሀሰት ነው። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
IS ፊቱን ወደኢትዮጵያ እያዞረ ነው!

በሱማሊያ የሚንቀሳቀሱ የእስላሚክ ስቴት (#አይኤስ) ታጣቂዎች ፊታቸውን ወደ ኢትዮጵያ እያዞሩ ነው - ሲል ዘግቧል እንግሊዝኛው ቪኦኤ፡፡ አይኤስ የጂሃድ መልዕክቶችን በአማርኛ ቋንቋ የማሰራጨት ዕቅድም አለው፡፡ ጂሃዲስቶቹ የሀገሪቱን ብሄር ግጭቶችና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በመጠቀም፣ ዐላማቸውን ወደ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ለማስረጽ ጥረት እደረጉ ነው- ብሏል የአፍሪካ ቀንድ ጸጥታ ተንታኙ ማት ብራይደን፡፡ ቡድኑ ከ2 ዐመት በፊት ባሰራጨው የፕሮፓጋንዳ ቪዲዮ መልዕት አንድ አማርኛ ተናጋሪ ጂሃዲስት አቅርቦ ነበር፡፡ ቡድኑ አሁን 8 ኢትዮጵያዊያን ጂሃዲስቶች እንዳሉት ይታመናል፡፡ ቡድኑ ከአልሸባብ ተደጋጋሚ ጥቃት ይደርስበታል፡፡

Via #VOA/#wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አይኤስ/IS/ ፊቱን ወደኢትዮጵያ እያዞረ ነው!

ተከታዩን የVOA ዘገባ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20-5
"እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ!

ሶማልያ ያለው “እስላማዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገልጿል። ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ምልመላ የማካሄድ ዓላማ እንዳለው ያመለክታል ተብሏል።

ይህ ማስታወቅያ ባለፈው ወር በሦስት ደቂቃ ቪድዮ መልክ የተለቀቀው በፅንፈኛው ቡድን ደጋፊ ድረ-ገፆች ላይ ሲሆን ኦፊሴላዊው እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ሚድያ ደግፎታል። ቪድዮው የአማርኛ ቃላትን ተጠቅሟል፣ ተጨማሪ ጽሑፎችን በአማርኛ እንደሚያወጣም ተናግሯል ተብሏል።

ማት በረየደን የተባሉ ኬንያ ባለው የሳሃን ጥናትና ምርምር ተቋም የሚሰሩ ተንታኝ እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን #ያለመረጋጋት ሁኔታን ተጠቅሞ ሙስሊም ማኅበረሰብን የመስበክ ዓላማ አለው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

አያይዘውም ተንታኙ #ጽንፈኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድል እንዳለው ይታየዋል የሚል አመለካከት እንዳላቸው ጠቁመዋል። እስካሁን ባለው ጊዜ በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ብዙም ባይሳካለትም አፍሪካ ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘትና እንቅስቃሴውን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ይላሉ ብራይደን።

ምንጭ፦ ቪኦኤ አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update “ሆራ ፊንፊኔ” የኢሬቻ በዓልን በአዲስ አበባ ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረትና የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ አስታወቁ። የኦሮሞ ህዝብ የምስጋና ቀን የሆነው ኢሬቻ በዓል በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል። የመጀመሪያው የክረምት መውጣትን ተከትሎ በውሃማ አካባቢዎች የሚከበር ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በበልግ ወቅት በተራራማ አካባቢዎች ይከበራል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን የትብብር መስኮች የማስፋት ፍላጎት እንዳላት ፕሬዝዳንት #ሳህለወርቅ_ዘውዴ ገለጹ። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ኢትዮጵያና ኳታር በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ጠንካራ የሚባል ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በተለያዩ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን #የመግባቢያ ሰነዶች መፈራረማቸውም ይታወቃል። ኢትዮጵያም ከኳታር ጋር ያላትን የግንኙነት መስኮች የማስፋት ፍላጎት አሳይታለች።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የአቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት #ስንዘክር ስራዎቻቸውን ከዳር ለማድረስ ቃላችንን በማደስ ሊሆን ይገባል" - የትግራይ ክልላዊ መንግስት
.
.
“የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመትን ስንዘክር የጀመሯዋቸውን ታላላቅ ስራዎች ከዳር ለማድረስ ቃላችንን በማደስ ሊሆን ይገባል” ሲል የትግራይ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።

የዝክረ መለስ ሰባተኛው ዓመት ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው አቶ መለስ ዜናዊ ከኢትዮጵያ አልፎው ለአፍሪካ ልማትና ብልጽግና መረጋገጥ ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ፈጽመዋል።

የክልሉ መንግስት “ የአቶ መለስ ዜናዊ ራዕይና ክብሮች የህዳሴያችን፣ የፅናታችንና የማይቀረው ድላችን ዋስትናና ነው ‘’ በሚል መሪ ሀሳብ በወጣው በዚሁ መግለጫው አቶ መለስ ኢትዮጰያን በአለም የተመሰከረለት የምጣኔ ሀብት እድገት እንዲመጣ የጎላ ሚና መጫወታቸውን አስታውቋል።

በፖለቲካው ዘርፍም ከኢትዮጵያና ከአፍሪካ አልፎ በዓለም መድረኮች የጎላ ተቀባይነት እንደነበራቸውም ተመልክቷል።

አቶ መለስ ዜናዊ ይህንኑ ብቃት እንዲላበሱ ያደረጋቸው ጥልቅ ህዝባዊ ፍቅርና መሪ ድርጅታቸው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ መሆኑ ተገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Eth-08-20-6
ፎቶ📸በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ ዛሬ ለወጣቶች የመልካም እሴቶችና የምክንያታዊነት ማጎልበቻ ሥልጠና ሲሰጥ ውሏል። #ETHIOPIA

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአፋር ክልል ከሚገኘው የማዕድን ሀብት ህብረተሰቡና ክልሉን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ገለጸ። በክልሉ ህገ-ወጥ የማዕድን ግብይትን መቆጣጠር ላይ ያተኮረና የወረዳና ክልል ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ትላንት በሰመራ ከተማ ተካሄዷል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20-7

@tsegabwolde @tikvahethiopia