TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA💪ክብር ይገባችኃል!

ስንተባባር በአንድነት ስንቆም ምንም ነገር አያቅተንም!! 6710 የልብ ህሙማን ህፃናትን አለንላችሁ እንበላቸው!!

#TIKVAH_ETHIOPIA_FAMILY

Screenshot ወደዚህ ግሩፕ👇

https://t.iss.one/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ

#አንድነት #ተስፋ #መተሳሰብ #ፍቅር #ቲክቫህ
ከትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ምስጋና ቀረበ!

በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በሚመራው "በእኛ ለእኛ" መርሃ ግብር ላይ ባለፉት ቀናት የደብተር ማምረት ስራ ላይ እንድትሳተፉ ባቀረብነው ጥሪ መሰረት የቲክቫህ ቤተሰቦች ከእኛ ለእኛ አባላት ጋር በመሆን 100,000 ደብተሮችን ለማምረት ችለዋል፡፡ በዚህም በስራው ላይ ለተሳተፉ አባላት በሙሉ ትምህርት ሚኒስቴር በቲክቫህ በኩል ምስጋናዬ ይድረስልኝ ሲል መልክቱን አስተላልፏል፡፡

እስካሁን በተካሄደው ዘመቻ በተለያዮ የእድሜ ክልል እና የትምህርት ደረጃ ላይ ያሉ በጎ ፍቃደኛ ኢትዮዽያውያን እየተሳተፋ ይገኛሉ :: ይህ በእንዲህ እያለ በበጎ ፍቃደኞች ትብብር ላለፋት 5 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የደብተር ማምረት ስራ ሂደትም በሚቀጥለው ሳምንት ማለትም ከሰኞ ከነሐሴ 13 -እስከ አርብ ነሐሴ 18 ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለፅን በስራው ላይ በፍቃደኝነት መሳተፍ የምትፈልጉ በጎ ፍቃደኞች በዚህ ስልክ 📞 +251 91 148 5705 በመደወል ተመዝግባችሁ መሳተፍ እንደምትችሉ በአክብሮት እንጠይቃለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምርምር ተቋም ሊሆን የሚችል ዩኒቨርሲቲ የለም!

በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወቅታዊ አቅምና ሁኔታ የምርምር ተቋም ሊሆን የሚችል ዩኒቨርሲቲ አለመኖሩን የሳይንስና ከፍተና ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

በሸራተን ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የለውጥ ስራዎችን ማስጀመሪያ መድረክ ላይ የመነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሁን ባለው ሁኔታ በኢትዮጵያ የምርምር ተቋም ሊሆን የሚችል ዩኒቨርሲቲ የለም ብለዋል፡፡

በአለም አቀፍ መስፈርት መሰረት 50 በመቶ የስታፍ አባላት ፕሮፌሰሮች ሊሆኑ ይገባል ያሉት ዶ/ር ሳሙኤል በኢትዮጵያ ደግሞ ይህንን ያሟላ ዩኒቨርሲቲ ባለመኖሩ ዩኒቨርሲቲዎችን በተልእኮ በመመደብ ሂደቱ የምርምር ተቋም ሊሆን የሚችል ዩኒቨርሲቲ እንደሌለ ጠቅሰዋል፡፡ በመሆኑም የዩኒቨርሲዎችን አቅም መገንባት በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት እንደሚሆን ዶ/ር ሳሙኤል ገልፀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሳዑዲ አረቢያው አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ጋር በስልክ ተወያዩ።

በውይይታቸውም የሳዑዲ አረቢያው አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ኢትዮጵያ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደሰላም እንዲመጡ የነበራትን ሚና አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት እያከናወነወች ያለውን ተግባር ሳኡዲ አረቢያ እንደምትደግፍም መናገራቸውን የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል።

Via #FBC
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ኢትዮጵያ ?

•እስከ መጋቢት 2011 ዓ.ም. ድረስ ያለው የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭና የአገር ውስጥ ብድሮች ዕዳ 1.5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል

•የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮ ቴሌኮም የውጭ ብድር ዕዳ 111.9 ቢሊዮን ብር ነው።

•የሌሎቹ የልማት ድርጅቶች የውጭና የአገር ውስጥ አጠቃላይ የብድር ዕዳ 594 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

•ማዕከላዊ መንግሥትና የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልመለሱት ዕዳ 412.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

•መንግሥት ከንግድ ባንክ የወሰደውን ብድር መመለስ ባለመቻሉ በየዓመቱ እስከ 25 ቢሊዮን ብር ወለድ እየከፈለ ነው።

Via #REPORTER
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ያስገነባቸው አራት ትምህርት ቤቶች በመስከረም ስራ ይጀምራሉ!

የአይነስውራን ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን ጨምሮ በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ከሚገነቡት 21 ትምህርት ቤቶች ውስጥ አራቱ በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ ግንባታቸው ተጠናቆ ለመጪው ዓመት ተማሪዎችን የሚቀበሉ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፈንታ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተገነቡትና ሊበን ጭቋላ፣ ጉጂ፣ ጃኮና ሎዛ ማርያምየተባሉት አራት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ከ80 እስከ 87 ከመቶ የደረሰ ሲሆን በዚህ ክረምትም ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባሉ፡፡

አራቱ ትምህርት ቤቶች በመጪው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙሉቀን ለተማሪዎቻቸውም የደንብ ልብስና ቦርሳ የሚበረክትላቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

Via #EPA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመጀመሪያ ዓመት ኮርሶች👆በ2012 የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፍረሽማን መርሃ-ግብር ውስጥ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ሴሚስተር የሚሰጡት ኮርሶች!

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ50 በመቶ በላይ ወጣቶች የጫት ሱስ ተጠቂ ሆነዋል ተባለ!

የሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ባሳፍነው ሳምንት ይፋ ባደረገው ጥናት በኢትዮጵያ ካሉ አዋቂዎች እና ወጣቶች መካከል 51 በመቶ የሚሆኑት ጫት ቃሚዎች መሆናቸውን እና ከዚህም ውስጥ የወንድ ጫት ቃሚዎች ቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ጥናቱ አመላክቷል።

ከከተሞች ይልቅ #በገጠራማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጫት መቃም እንደበለጠ የገለጸው ጥናቱ፤ በተለይም በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሶማሌ እና በአማራ ክልሎች ከሌላው የአገሪቱ አካባቢዎች በበለጠ በገጠራማ ክፍሎቻቸው የጫት ቃሚዎች ቁጥር እንደሚበዛም አመላክቷል። ጥናቱ በማከልም ከተለዩት የጫት ቃሚዎች በአማካኝ በ17 ዓመት ዕድሜያቸው ጫት መቃም እንደሚጀምሩ ገልጿል።

በጫት ምርት፣ ንግድ እንዲሁም ማኅበራዊ ውጤቶች ላይ በርካታ ምርምሮችን እንዲሁም መጽሐፍትን ያዘጋጁት ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳ፤ ጥናቱ በተለይም የጫት ቃሚዎች ቁጥር በገጠራማ አካባቢዎች ቁጥሩ ከፍ ያለ ነው የሚለውን እንደማይስማሙበት ገልጸው በተለያዩ ዓመታት በሠሯቸው ጥናቶች ከተሜው የበለጠ ጫትን እንደሚቅም ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

#አዲስማለዳ

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-19
ቅሬታዎች ወደTIKVAH-ETH መምጣታቸው ቀጥሏል!

ከዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ አሁንም ቅሬታዎች እየቀረቡ ናቸው። ኤጀንሲው ላቀረብንለት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ብለዋል ውጤታችን ትክክል አይደለም ያሉ ተማሪዎች።

#ከአፕቲትዩድ ውጪ ያሉት ትምህርቶች ቢፈተሹ ጥሩ ናቸው ያሉት ቅሬታ አቅራቢ ወላጆችና መምህራን ሲሆኑ ከተስተካከለው ትምህርት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ችግር ባይኖር እንኳን የሚቀርበውን ጥያቄው ተቀብሎ መልስ መስጠት ይኖርበታል ብለዋል።

🏷TIKVAH-ETH ኤጀንሲው እየቀረበለት ለሚገኘው ቅሬታ ምን አይነት ምላሽ ለመስጠት ጥረት እያደረገ ነው?? እስካሁንስ ቀርበዋል በተባሉት የ9,000 ተማሪዎች ቅሬታ ላይ ምን ችግር ተገኘ?? በተጨማሪ የታገደባቸው ተማሪዎች እጣ ፋንታ ምን ይሆናል?? የሚለውን የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግሮ ምላሽ ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ህዝብን ለግጭት የሚያሰልፉ አመራሮችን መለየትና በግልጽ መታገል ያስፈልጋል።" (የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልሎች የትብብር ሰነድ ሲፈራረሙ ከተናገሩት የተወሰደ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
e903df39-1035-44e8-b13d-4397366f8960_32k.mp3.crdownload
5.1 MB
ፌክ ኒውስ - የፈጠራ ወሬ፡- ምንጩ፣ መገለጫው፣ መዘዙ፣ ማርከሻው...
ፌክ ኒውስ - የፈጠራ ወሬ፡- ምንጩ፣ መገለጫው፣ መዘዙ፣ ማርከሻው...

የፈጠራ ወሬ ወይም FAKE NEWS አንባቢን ወይም አድማጭን ለማታለል ወይም ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ ሆን ተብሎ የሚሠራጭ አሳሳችና የሃሰት ዜና ነው።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በተለይ አሁን አሁን ብዙ አድማጭና አንባቢ ከሚታወቁ የዜና ማሠራጫ ጣቢያዎች ይልቅ ከተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች ዜና በሚፈልግበት፣ በሚቃርምበትና ሃሣቡንም በሚያንሸራሽርበት ዘመን አደጋው ከፍተኛ ሆኗል።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በማኅበረሰብ ውስጥ መተማመንን ያሳጣል፤ መንግሥትና ሕዝብን፣ ሕዝብን ከሕዝብ ያጋጫል። በFAKE NEWS ወይም በፈጠራ ወሬ ሥርጭት ላይ ጥናት ያደረጉ ማርከሻውንም የሚመክሩ ባለሙያ አቶ ዳኛቸው ተሾመ በዚህ ጉዳይ ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

አቶ ዳኛቸው ተሾመ ሎስ አንጀለስ - ካሊፎርኒያ የሚኖሩ ላለፉት ሰላሣ ዓመታት በትምህርት፣ በምርምርና በሥራም ከኮምፕዩተር ሳይንስ ጋር ያሉ ሰው ናቸው። በዳታ ቤዝ ዲዛይንና አርክቴክቸር ላይ ሠርተዋል። የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ምርምርና ፅሁፍም የሠሩት ድምፅን በመፈተሽና ለይቶ በማወቅ ክህሎት ላይ መሆኑን ይናገራሉ። ከዚያ በተለይ ግን አቶ ዳኛቸው እራሴን ማሳወቅ የምፈልገው “ሕይወቱን ለሰው ልጅ መብት መከበር እንደሰጠ ሰው ነው” ይላሉ።

የጄነራል አሳምነው ፅጌና የአማራ ክልል መገናኛ ብዙኃን ኃላፊ የመጨረሻ የስልክ ምልልስ የድምፅ ቅጂም ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ዲጂታል አሻራ መርማሪ ቡድን አስመርምረው ያገኙትን ውጤትም ያካፍላሉ።

ይቀጥላል👇
ይህ የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ - የድርጅቱ ስም ነው - /ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች/ ሙያዊ አስተያየት ነው። ሪፖርተሩና ሟቹ /አሁን “ተናጋሪው” የሚባሉት/ የተቀረፁት በአንድ ጊዜ /በተመሣሣይ ጊዜ ወይም አንድ ላይ/ ነው፤ ወይም /የሁለቱም ድምፅ/ እንደገና ተቀርፆም ከሆነ የተቀረፀው በአንድ ጊዜ /ወይም አንድ ላይ/ ሊሆን ይችላል።

ያልተቋረጠ /ወይም የተያያዘና ተከታታይ/ ኢ.ኤን.ኤፍ. - የእንግሊዝኛ አባባል ምኅፃር ነው - የኤሌክትሪክ ትስስር /ኔትወርክ/ ሞገድ አለ። የድምፁ ሂደት የተሰባበረ አይደለም፤ ይህ ማለት ለእኛ በተላከልን የተቀረፀ ድምፅ ላይ ሪፖርተሩና ተናጋሪው የተቀረፁት በአንድ ጊዜ /በተመሣሣይ ጊዜ ወይም በአንድ ላይ/ መሆኑን ያረጋግጣል። በሌላ በኩል ደግሞ የኤሌክትሪክ ትስስር ሞገዱ /ኢ.ኤን.ኤፍ/ እንዳይቆራረጥ ለማድረግ ሪፖርተሩ መጠይቆቹን ተገቢ ጊዜያቸውን እየጠበቀ የተናጋሪውን ቀድሞ የተቀረፀ ድምፅ እያጫወተ ቀርፆ ሊሆንም ይችላል። የሪፖርተሩ ድምፅ ከተናጋሪው ድምፅ ጋር እየተቆራረጠ አልተቀጣጠለም።

ይቀጥላል👇
ይህ የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ - የድርጅቱ ስም ነው - /ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች/ ሙያዊ አስተያየት ነው። ምንጩ ላይ ለማስተካከል ወይም ለመቀማመር ተብሎ በእጅ የተከናወነ ሥራ የለም። አንዱን ድምፅ በሌላኛው ላይ ማስኬድን፣ ወጥነት የሌላቸው የድምፅ ውጣ ውረድ ዓይነቶችን፣ ቆርጦ መቀጠልን ወይም መሰል ለማጭበርበር ተብሎ የተፈፀመ የአርትኦት ሥራ የለበትም።

ይቀጥላል👇
በመጨረሻም ሪፖርተሩ ያወጣው የተቀረፀ ድምፅና የቀረቡት ሁለት ናሙናዎች ተመሣሣይ /ወይም አንድ/ መሆናቸውን የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ - የድርጅቱ ስም ነው - /ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች/ ሙያዊ አስተያየት ያረጋግጣል። የተቀረፀውን ድምፅ አሻራ የያዘውን ድምፅ በጊዜ ውስጥ የሚያሳየውን ሞገድ ሂደት የሚያመላክቱ ምሥሎች /ስፔክቶግራምስ/ በተለይ የተከበቡትን ሞገዶች ይመልከቱ። ከተናጋሪው ድምፅ ጋር የተቀላቀሉ ሌሎች የጀርባ የድምፅ ሞገዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አነስተኛ ለውጦችን ቢያሳዩም ዋናዎቹ ነጥቦች፣ እንዲሁም ቁልፍ በሆኑት ሞገዶች መካከል ያሉት ክፍተቶች ግን አሉ።

Via VOAአማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሱዳን

የሱዳን ተቃዋሚ ሃይሎች አምስት ሲቪል የሉአላዊ ምክር ቤት አባላትን መምረጣቸው ተገለፀ። በሱዳን ተቃዋሚዎች ጥምረት የመረጧቸው የኡአላዊ ምክር ቤቱ አባላቱ በዛሬው እለት ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተነግሯል። ከወታዳራዊ ሽግግር ምክር ቤት፤ መሪውን አብደል ፈታህ አልቡራን፣ ምክትላቸውን ሞሃመድ ሃማዳን ዳጋሎ እና የወታዳራዊ ሽግግር ምክር ቤት ቃል አቀባይ ሌተናል ጀኔራል ያሰር አል አታን ይጨምራል ነው የተባለው፡፡

Via #CGTN/#FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKENEWS

የፈጠራ ወሬ ወይም FAKE NEWS አንባቢን ወይም አድማጭን ለማታለል ወይም ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ ሆን ተብሎ የሚሠራጭ አሳሳችና የሃሰት ዜና ነው።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በተለይ አሁን አሁን ብዙ አድማጭና አንባቢ ከሚታወቁ የዜና ማሠራጫ ጣቢያዎች ይልቅ ከተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች ዜና በሚፈልግበት፣ በሚቃርምበትና ሃሣቡንም በሚያንሸራሽርበት ዘመን አደጋው ከፍተኛ ሆኗል።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በማኅበረሰብ ውስጥ መተማመንን ያሳጣል፤ መንግሥትና ሕዝብን፣ ሕዝብን ከሕዝብ ያጋጫል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በእነ ብርጋዴየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ክስ መመስረቻ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ!

ከሰኔ 15ቱ የባሕር ዳር ጥቃት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ያሉትን የእነ ብርጋዴየር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ እየተመለከተ ያለው የባህርዳር እና አካባቢው ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ለመመስረት ወይም ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠት የሚያስችል ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ከሁለት ቀናት በኋላ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል።

ከባሕሩ ዳሩ ጥቃት ጋር በተያያዘ በሶስት የተለያዩ መዝገቦች የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ብዛት 61 ናቸው። በተጠርጣሪዎቹ ላይ ሲቀርብ የቆየውን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮዎችን ሲፈቅድ የቆየው የባሕር ዳር ወረዳ ፍርድ ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት ባስቻለው ችሎት የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ፍርድ ቤቱ “በተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ለክስ በቂ ነው” በማለት ነበር ከዚህ በኋላ የምርመራ ጊዜ እንደማይፈቅድ በማስታወቅ መዝገቡን የዘጋው።

ጉዳዩን የያዘው መርማሪ ቡድን ግን “ምርመራዬን አላጠናቀቅሁም” በማለት ለባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤት ብሏል። የተጠርጣሪ ጠበቆች “የጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ የማይባልበት አሰራር ስለሌለው ፍርድ ቤቱ የመርማሪ ቡድኑን ጥያቄ ውድቅ ሊያደርገው ይገባል” ሲል ተቃውመዋል። ዛሬ ጉዳዩን ሲያከራክር ያረፈደው የባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሁለቱንም ወገኖች ክርክር መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለነሐሴ 16 ቀን 2011ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የዕለቱን የችሎት ውሎ ቋጭቷል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia