TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ📸"በያገባኛል ይመለከተኛል"የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ፣ ኢ/ር እንዳወቅ አብቴ ፣ ከተለያዩ ቤተ-እምነት የመጡ የሃይማኖት አባቶች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም በርካታ የከተማው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ70_እንደርታ #ፋሲል_ከነማ

የመቐለ 70 እንደርታ ቡድን በካኖ ስፖርትስ አካዳሚ በፓብሎ ቦያስ ደሳምፓካ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዱን ትላንት አድርጓል ። የቡድኑ ተጨዋቾች #በጥሩ_ጤንነት መሆናቸውን ተሰምቷል።

በሌላ ዜና...

የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ እግር ኳስ ውድድር ፋሲል ከነማን ከታንዛንያው አዛም ክለብ ጋር ያገናኛል፡፡ ጨዋታው ነገ እሁድ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ይደረጋል፡፡ የፋሲል ከነማ ምክትል አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ እንደተናገሩት አፄዎቹ ለማሸነፍ የሚያስችል መልካም የስነ ልቦና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ እንደ ምክትል አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ ገለጻ ተጫዋቾቹ ለማሸነፍ የሚያስችል ልምምድ በባሕር ዳር ከተማ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አፄዎቹ የመጨረሻውን ልምምድ ትናንት አድርገው ዛሬ ዕረፍት ላይ ናቸው፡፡ ጉዳት የደረሰበት ምንም ተጫዋች እንደሌለ እና የተሻለ የስነ ልቦና መነቃቃት እንደሚታይባቸውም ነው የተናገሩት፡፡

Via #AMMA & #ethiokickOff

የስፖርት ጉዳዮችን ብቻ ትከታተሉ ዘንድ👇
@tikvahethsport

⛹‍♀🏋‍♀🏂🏄‍♂🚴‍♀🥊🥋🏇🤼‍♂https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
#NewsAlert

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ንግሥት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አሥፈፃሚነት ራሷን #አገለለች። በደብረብርሀን እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ የ2012 እቅድ አፈፃፀም ድምፅ ሊሰጥ ሲቃረብ ደራርቱ" በቃኝ ከፍተኛ #መገለል እየደረሠብኝ ነው። ወደዚህ ጉባኤ እንኳን ስመጣ በግል እንጅ እንደሌላው ምንም መጥሪያ አልደረሠኝም ብላለች። ሁላችሁንም እወዳችኋላሁ ያለችው ደራርቱ ሥፖርቱ እንዲያድግና የሀይሌ ራእይ እንዲቀጥል ነው ፍላጎቴ አሁን ግን ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አሥፈፃሚነት ይበቃኛል በማለት ተናግራለች።

ዶ/ር አሸብር በበኩላቸው ያለደራርቱ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ማሠብ ከባድ ነው ጉዳዩን ቁጭ ብለን እንፈታዋለን ብለዋል። ደራርቱ የተከፋችበት ጉባኤ መሆኑ አሳዝኖናል ደራርቱ ትመለሳለች፤ ትመለሳለች፤ ትመለሳለች ሲሉም ተናግረዋል። ቀጣዩ የ2012 ጠቅላላ ጉባኤ ትግራይ የ2013 ደግሞ አማራ ክልል እንዲያዘጋጁ ተወሥኗል። ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክሥ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት ሥትሆን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚ አባል ነች።

Via ግርማቸው እንየው/ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
69 ሚሊዮን ኮንዶም እንዳይሰራጭ ታግዷል!

"በጥራት ጉድለት ከሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ 69 ሚሊዮን ኮንዶም ወደ ገበያ እንዳይሠራጭ ታግዷል" አቶ ኃይሉ ታደግ፣ የፕሮሞቲንግ ዘኳሊቲ ኦፍ ሜዲሲን ፕሮግራም ኃላፊ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ አዲስ እንቁጣጣሽ ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ
የተለጠፈው ባነር ተነስቷል!

የጆርካ ኢቨንት ባለድርሻ አቶ አጋ አባተ ለTIKVAH-ETH፦

"ለሚሊኒየም አዳራሽ/አዲስ ፓርክ #ሊደርስ የሚገባው መረጃ ባለመድረሱ በmiscommunication ምክንያት ነው የተለጠፈው። ባነሩ ተነስቷል! በአሁን ሰዓት ሚሊኒየም አዳራሽ ማንም ሰው መጥቶ መመዝገብ ይችላል። ባዛሩ ነሃሴ 15 በድምቀት ይከፈታል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia

መቀሌ 70 አንደርታ ከኢኳቶሪያል ጊኒዉ ከካኖ ስፖርት አካዳሚ ጋር የሚደረግዉ ጨዋታ 11፡ 00 ሰአት ይጀመራል ቢባልም ለጊዜው ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ጨዋታዉ ወደ ምሽቱ 1 ሰአት ተላልፏል።

Via #EthioKickOff

የስፖርት ጉዳዮችን ብቻ ትከታተሉ ዘንድ👇
@tikvahethsport

⛹‍♀🏋‍♀🏂🏄‍♂🚴‍♀🥊🥋🏇🤼‍♂https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብን

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና ሌሎች ሶስት ሰዎች ላይ የተጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ ቀሪ የምርመራ ስራዎችን አጠናቆ የተጠርጣሪዎቹን የወንጀል ተሳትፎ ለይቶ እንዲያቀርብ ለጳጉሜ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓም በተከሰተው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የግድያ ወንጀል ላይ ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ትናንት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉበትን ወንጀል ለማጣራትና ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ሲጠይቅ፤ ተጠርጣሪዎቹ ”በቁጥጥር ስር የዋልነው በፖለቲካ አቋማችን ነው” በማለት ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ABN-08-10

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Cano Sport Vs Mekelle 70 Enderta

የስፖርት ጉዳዮችን ብቻ ትከታተሉ ዘንድ👇
@tikvahethsport

⛹‍♀🏋‍♀🏂🏄‍♂🚴‍♀🥊🥋🏇🤼‍♂https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
ማስታወሻ🗓

የ12ኛ ክፍል ውጤት /ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤት/ ነገ እሁድ ነሐሴ 5፣2011 ይፋ ይደረጋል።

🏷ተፈታኞች ውጤታችሁን የፊታችን እሁድ ከ8፡00 ጀምሮ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት Admission በሚለው ሳጥን ውስጥ የመፈተኛ ቁጥራችሁን (Registration Number) በማስገባትና go የሚለውን አንዴ click በማድረግ መመልከት ትችላላችሁ!

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia
4 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው!

አራት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ገለጸ። ኮርፖሬሽኑ በፓርኮች ግንባታና ምርት ዙሪያ ከምሁራን፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የሙያ ማህበራት ጋር ተወያይቷል። ውይይቱ በኢትዮጵያ በመስኩ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ፣ እየተገኙ ያሉ ውጤቶችና ችግሮች ላይ ያተኮረ ነው።

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሺፈራው ሰለሞን እንደተናገሩት፤ አሁን ካሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ አራት ፓርኮችን ለመገንት የሚያስችል ጥናት እየተከናወነ ነው። አሶሳ፣ አረርቲ፣ አይሻና ሰመራ ከተሞች ላይ ለመገንባት እንደታቀደ ጠቁመው፤ በተለይ #ሰመራ ላይ #የኢትዮጵያና #ኤርትራ ግንኙነት መሻሻልን ተከትሎ የወደብ አማራጭ በመኖሩ የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

አሶሳ ላይ ደግሞ የቀርከሃ ምርት በስፋት በመኖሩ ለቢሮ፣ ለቤት እቃዎችና መርከብ ግንባታ የሚሆን ግብዓት ለማምረት የሚያስችል የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት እየተጠና መሆኑን ጠቁመዋል። በቀርከሃ ምርት ለመሰማራት ቻይናዊያን ባለሃብቶች ከፍ ያለ ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጸዋል። ”የጥናት ሂደቱ እንደተጠናቀቀ በውጤቱ መሰረት ወደ ግንባታ ይገባል” ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካሽሚር ነገር...

ፓኪስታን ህንድን የሚያወግዝ የውሳኔ ሀሳብ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ልታቀርብ መሆኑን አስታወቀች። የውሳኔ ሀሳቡ ህንድ የካሽሚር ግዛት የነበረውን የልዩ አስተዳደር መብት መግፈፏን የሚቃወም ነው።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በዩኒቨርስቲ የሚታዩ በዘርኝነት የሚከሰቱ መጠፋፋቶች ኋላ ቀር አስተሳሰብ በመሆናቸው ይህ ትውልድ መፍቀድ የለበትም" አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ታዳሚውን ያስለቀሰው የብሩክ የሺጥላ ንግግር...

NB: ቪድዮው 17 mb ስለሆነ በWiFi ብታወርዱት ይመረጣል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደራርቱ ውሳኔዋን አጥፋለች!

ደራርቱ ቱሉ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት ራሷን ለማግለል ያሳለፈችውን ውሳኔ አጠፈች። በደብረ ብርሀን ከተማ በሚደረው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከሥራ አስፈፃሚነት ለመልቀቅ መወሰኗን የተናገረችው ደራርቱ በጠቅላላ ጉባኤው በርካታ ሰዎች ውሳኔዋን እንድታጥፍ ግፊት ማሳደራቸውን የስፖርት ጋዜጠኛ ኦምና ታደለ ለጀርመን ራድዮ ተናግሯል። ኦምና እንደሚለው ደራርቱ ግፊት ያሳደሩ ሰዎችን #ማሳዘን አልፈለገችም።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት የምትመራው ደራርቱ በውሳኔ አሰጣጥ ረገድ የምትመለከታቸውን ሕጸጾች ከዚህ በኋላ የማይታረሙ ከሆነ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ራሷን እንደምታገል አስጠንቅቃለች።

በሁለት የኦሎምፒክ ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ የነበረችው ደራርቱ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ከሚመሩት የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚ አባልነት መልቀቋን ያሳወቀችው በዛሬው ዕለት ነበር። «ከዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ እና እርሳቸው ከሚመሩት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በተፈጠረ መቃቃር ምክንያት» ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ደራርቱ ራሷን ለማግለል አስገድዷት ነበር።

ዶክተር አሸብር ሥመ-ጥሩዋን የሩጫ ንግሥት ወደ ሥራ አስፈፃሚነቷ ለመመለስ ቃል ገብተው ነበር። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በአማራ ክልል ደብረ ብርሀን ከተማ ጠቅላላ ጉባኤ እያካሔደ ነው።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ለ1 ሺህ 440ኛው ዓመተ ሒጅራ የኢድ-አል አድሐ (ዓረፋ) በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፦

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ መልዕክት👇
🏷https://telegra.ph/EID-08-10
Audio
የሀዋሳው ውይይት ከወታደራዊ ዕዝ ጋር!
ሰላም ማረጋገጥ ከተቻለ ወታደራዊ ዕዙ ግዳጁን በሁለት ወር ውስጥ አጠናቅቆ ይወጣል፤ የማይረጋጋ ከሆነ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ሊታወጅ ይችላል!

በሃዋሳ ከተማ አሳቻ ሰዓትና ቦታ በመጠበቅ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችና የሰዎች ማንንት ላይ ያተኮሩ ትንኮሳዎች ነዋሪው ተርጋግቶ እንዳይኖርና ስጋት ውስጥ እንዲገባ አድርጓል ሲሉ የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
 
ክልሉን እያስተዳደረ ካለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አስፈፃሚ ዕዝ ጋር የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተወካዮች በየተወያዩበት ወቅት ወታደራዊው ዕዝ እንዲያበቃና የመከላከያ ሠራዊትም ከከተማው #እንዲወጣ የጠየቁ ነበሩ።

በሌላ በኩል ደግሞ “የለም ሠራዊቱ መቆየት አለበት፤ ሰላም ያገኘነው ወታደራዊ ዕዙ፣ የመከላከያ ሠራዊትና ፌዴራል ፖሊስ ከተማዪን ከተቆጣጠሩ ወዲህ ነው” ያሉም ነበሩ። ሰላም ማረጋገጥ ከተቻለ ወታደራዊ ዕዙ ግዳጁን በሁለት ወር ውስጥ አጠናቅቆ እንደሚወጣ፤ የማይረጋጋ ከሆነ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ሊታወጅ እንድሚችል ዕዙ አስታውቋል።

Via #VOAamharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግራይ በኤሊኖ ምክንያት ድርቅ ሊከሰት ይችላል!

በትግራይ ክልል ኤሊኖ ባስከተለው የዝናብ እጥረት ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ድርቅ ለመከላከል አርሶ አደሮች የመሬት እርጥበትን ይዞ ለማቆየት ከወዲሁ መትጋት እንዳለባቸው የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ አሳሰበ፡፡

በቢሮው የቅድመ ማስጠንቀቂያና አስቸኳይ የአደጋ ዝግጁነት ዳይሬክተር አቶ ገብረእግዚአብሄር አረጋዊ እንዳሉት በተያዘው የመኸር ወቅት በኤሊኖ የአየር መዛባት ምክንያት በክልሉ የድርቅ አደጋ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ተደቅኗል።

በዚሁ ምክንያት በትግራይ ምስራቃዊ፣ ደቡባዊ ምስራቅና ደቡባዊ ዞኖች የዝናብ መቆራረጥና የእርጥበት እጥረት መስተዋሉን ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TG-08-10
ታዳሚውን ያስለቀሰው የብሩክ የሺጥላ ንግግር...

"ከዛሬ ጀምሮ ይህቺ ምደገፍባት ነገር አታስፈልገኝም ለምን መሰላችሁ ሲደክመኝ ሚደግፈኝ #ኢትዮጵያዊ_ወንድም አለኝ፤ ሲርበኝ አይዞህ ብሎ የሚያበላኝ እህትና ወንድም አለኝ፤ እኔ ማውቃት ኢትዮጵያ ይህቺን ነው፤ እኔ #የኖርኩባት ኢትዮጵያ ይህቺ ነች፤ ልጄም ይህንን እውነት እንዲኖረው እፈልጋለሁ፤ #ልጆቻችንም ይሄንን እውነት የሆነ ኢትዮጵያ ኖረው እንዲያልፉ ሁሉንም ነገር #እናመቻችላቸው፤ ችግርን ከመፍጠር ይልቅ ብዙ ችግሮች አሉብን ስለ ችግሮቻችን ካወራን ችግሮቻችን አያልቁም። መሪዎቻችን ደግሞ ገና #በተመቻቸ ሁኔታ ላይ አይደሉም፤ እነሱ ላይ ብዙ ችግር አንፍጠርባቸው፤ እኛ የምንችለውን ችግር እንፍታ እነሱም ደግሞ መፍታት የሚችሉትን ያህል ችግር ይፍቱልን። የሚቀጥለው መሪ የተሻለ ወንበር እንዲያገኝ፤ የተመቻቸ ወንበር እንዲያገኝ፤ እኛንም ከዚህ በተሻለ በደንብ መምራት እንዲችል ሁሉን ነገር እኛ እናመቻችለት።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢድ ሙባረክ!

እንኳን #ለ1440ኛው ዓመተ-ሒጂራ የኢድ-አል-አድሃ (#ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፤የፍቅር፤ #የመተሳሰብ ይሁንልን!!

#TIKVAH_ETH🕋#EidAlAdha🕋#EidMubarak

@tsegabwolde @tikvahethiopia #EidMubarak