TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰኔ 15ቱ ጥቃት ሰለባ ቤተሰቦች አቤቱታ አሰሙ!

የጀርመን ራድዮ ካነጋገራቸው ሁለት እናቶች አንደኛዋ የባለቤታቸው የጡረታ መብት መከበሩን እንዲሁም የስድስት ወር ደሞዝ ማግኘታቸውን ቢገልፁም ከ4, ሺህ ብር በላይ የወር የቤት ክራይ እየከፈሉ ሦስት ሕጻናትን በማሳደግ ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ። ድርስ ነፍሰጡር መሆናቸውን የተናገሩት ሌላኛው በበኩላቸው የጡረታ መብታቸውን ተሯሩጠው ማስፈፀም እንዳልቻሉ፤ የስድስት ወር ደመወዝም እንዳላገኙ ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/SENE15-08-09
የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን ከእስር እየተፈቱ ነው!

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ውስጥ ታስረው ከሚገኙት ኢትዮጵያውያውያን መካከል የተወሰኑት ፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባደረገው ጥረት ከእስር እየተለቀቁ መሆኑ በቦታው የሚገኙ ነጋዴዎች ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ገለፀዋል። ነገር ግን የተወረሰባቸው ንብረት መጠን ብዙ በመሆኑ ከፍተኛ እገዛ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ኢምባሲ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን እና ይህንኑ ጥረቱንም እንደሚቀጥል አስታውቋል። በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን 150 ናቸውም ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Libya📸Before and After...
#ሊቢያ

የዓረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ተጠየቀ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተፋላሚ ሃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ፡፡ ተፋላሚዎቹ የኢድ አል አድሃ(ዓረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ነው በመንግስታቱ ድርጀት ጥሪ የቀረበው፡፡

እስከ ዛሬ ምሸት ድረስም ሁለቱ ተፋላሚዎች ጥሪውን ስለመቀበል አመቀበላቸው ለመንግስታቱ ድርጅት የሊቢያ መልዕክተኛ የጽሁፍ ማረጋገጫ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከአውሮፓውኑ ሚያዚያ ወር ጀምሮ በጄኔራል ከሊፋ ሃፍጣር የሚመራው ሃይል የሊቢያን መዲና ትሪፖሊን ለመቆጣጠር በሚያደርገው ዘመቻ በተመድ እውቅና ከተሰጠው የፋይዝ አል ሳራጅ አስተዳደር ጋር ግጭት ውስጥ ገብቷል።

በዚህ ግጭት ሳቢያም ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ህይወት ሲያልፍ 5 ሺህ 700 ያህሉ ለአካል ጉዳት ዳርጓል፡፡ ከዚህም ሌላ 120 ሺህ ያህል ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ማፈናቀሉን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመላክታል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲኤ ን/fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ያገባኛል #ይመለከተኛል የመዝሙር ኮንሰርት

እስካሁን ትኬት ካልገዙ ነገ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ መግቢያ በሮች ላይ ያገኛሉ፦

ዋጋ መደበኛ 100 ብር
VIP 1000 ብር


"ልጆቻቻችን ከጎዳና ህይወት ለማውጣት በኢትዮጵያ ወንጌላውያን መሪዎች ህብረት የተዘጋጀ!"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መካ #HajjPilgrimage ከሁለት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሙስሊሞች መካ ላይ ተሰብስበዋል፡፡ #VOA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቤንች_ሸኮ

በቤንቺ ሸኮ ዞን ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር በመሳተፍ የተለያዩ #ወንጀሎችን ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ። ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በቤንች ሸኮ ዞን ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር በመሳተፍ በሰው ግድያ፣ የአካል ጉዳት በማድረስ፣ ንብረት በማውደምና ዘረፋ በመፈጸም ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ እየተደረጉ ነው።

የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥና የኮማንድ ፖስት አባል ዋና ኢንስፔክተር ምናሉ ታደሰ እንደገለፁት ከ100 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ተጣርቶ በእስራት እንዲቀጡ እየተደረገ ነው። በጦር መሳሪያ ታግዘው ከባድ ወንጀል የፈጸሙና በአስገድዶ መድፈር መሳተፋቸው በማስረጃ የተረጋገጠባቸው አራት ግለሰቦች ከ8 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ መደረጉን ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጀምሯል!

TIKVAH-ETH ስፖርት ከቅዱስ እና ጎይቶም ጋር!

ይህ የTIKVAH-ETH የስፖርት ገፅ ነው ይቀላቀሉ👇

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
ለመሆኑ ስፖርት ሲባል እግር ኳስ ብቻ ነው?

TIKVAH-ETH የስፖርት ገፅ ይዞ ብቅ ያለው የተደገመውን ለመድገም የተሰማውን ድጋሚ እያሰማ ለማሰልቸት አይደለም። የስፖርት ገፁ የመጣው በአጠቃላይ በሀገሪቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ትኩረቱን አድርጎ ለመስራት ነው። ያልተዳሰሱትን በስፋት ለመዳሰስ፤ የልተነገረላቸውን ለመናገረ፤ እየጠፋ የመጣውን ባህላዊ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለመዳሰስ፤ ካራቴውን፣ ቴኳንዶውን፣ የሳይክል ውድድሩን የመኪና ውድድሩን፣ ቅርጫት ኳሱን፣ መረብ ኳሱን ... ለመዳሰስ ነው የመጣው።

በቅርቡ እጅግ ያማረ እና የወጣ አቀራረብ ይዞ ወደናተ ይደርሳል። ለጥቂት ጊዜ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የእግር ኳስ ውድድሮች እየዳሰስን አብረን እንቆያለን።

ይህ የTIKVAH-ETH የስፖርት ገፅ ነው ይቀላቀሉ👇

⛹‍♀🏋‍♀🏂🏄‍♂🚴‍♀🥊🥋🏇🤼‍♂https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethsport
በኢሕአዴግ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ፦

ኢሕአዴግ "ዝርዝርና ብስል" ግምገማ አድርጊያለሁ ብሏል። አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት ሥራ አስፈጻሚው በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል አንድነትን የሚጎዱ ነገሮች እንዲታረሙ፣ ፓርቲዎቹም እርስ በርስ #ከመወነጃጀል እንዲቆጠቡ ድምዳሜ ላይ ተደርሷል።

"የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በሙሉ ልብ ሁሉም ወስደው በተመሳሳይ ሁኔታ ያለመፈጸም" ችግር በኢሕዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል መኖሩን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንደደረሰበት አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል። በጋራ የተወሰኑ ጉዳዮች እኩል ተግባራዊ አይሆኑም ብለዋል።

የሕግ የበላይነትን ማስከበር ፣ ለውጡን ተቋማዊ ማድረግ፣ "የለውጡን ምንነት ማስረዳት"፣ በ2012 "ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትኃዊ ምርጫ" ለማካሔድ መዘጋጀት፣ ደኢሕዴን ላሰራው "ሳይንሳዊ ጥናት" ድጋፍ ማድረግ ከኢሕአዴግ ውሳኔዎች መካከል ይገኙበታል።

Via #EshetBekele
@tsegabwode @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

”ማንም ሰው ሌላውን ሰው በዘሩ እና በቆዳው ቀለም፤ ውይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ አልተወለደም፤ ሰዎች መጥላትን ተምረውት ነው። የሰው ልጅ #ጥላቻን ከተማረ፤ ፍቅርንም መማር ይችላል፤ እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው።” ኔልሰን ማንዴላ

#share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር ታከለ ኡማ ለቡ አከባቢ ሰሞኑን በፈረሰው አሊፍ መስጅድ በመገኘት ከሀይማኖት አባቶች ጋር ተነጋግረዋል፡፡
-

ኢ/ር ታከለ ኡማ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ያለ ከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጪ የፈረሰውን የአሊፍ መስጅድ ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ጥቂቶች የከተማ አስተዳደሩን በተንኮል ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ሊያጋጩ እና በሴራ ሊበትኑ ቢያስቡም እኛ ግን ችግሮችን በተሻለ መንገድ እናልፋቸዋለን ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የማምለኪያ ቦታዎችን በተመለከተ ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ከሁሉም የእምነት ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነም ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

መስጅዱን በማፍረስ የተሳተፋ አካላትን ተጠያቂ ከማድረግ ጎን ለጎንም መስጅዱን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት በን/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ አንድ 4 ሺህ ካ.ሜ ተለዋጭ ቦታም ለአዲስአበባ መጅሊስ ተላልፏል፡፡

ከተጀመረው የለውጥ ጉዞ የሚያስተጋጉሉንን ለመግታት አሁንም የጋራ ጥረታችን ሊቀጥል እንደሚገባም ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
4 ሺህ ካ.ሜ ተለዋጭ ቦታ ተላለፈ!

መስጅዱን በማፍረስ የተሳተፋ አካላትን ተጠያቂ ከማድረግ ጎን ለጎንም መስጅዱን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት በን/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ አንድ 4 ሺህ ካ.ሜ ተለዋጭ ቦታም ለአዲስአበባ መጅሊስ ተላልፏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations #ASTU የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ወደበኃላ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርቃት ጋር የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን አቀርባለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 100 ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ። ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተከናወነ ስነ ስርዓት የተመረቁት 100 ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ 92 ፖስት ስታፍ እና ስምንት የሁለተኛ ድግሪያቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥም 21 ተመራቂዎች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል። እነዚህ ተመራቂዎችም ከጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ መሆናቸው ነው የተመለከተው።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድም ለተመራቂዎች ዲፕሎማ ከሰጡ በኋላ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። ተመራቂዎች በስነ ምግባር፣ በወታደራዊ ጥበብ፣ በሙያዊ ብቃት እና በላቀ ዝግጅት የሰራዊት አባላትን ለመምራት እና ለድል ለማብቃት የሚያስችላቸውን እውቀት እና ከህሎት ለማግኘት ለአንድ ዓመት ትምህርታቸውን መከታተላቸውን አንስተዋል።

በመሆኑም በትምህርት የገበዩትን እውቀት ከዚህ በፊት ካገኙት ልምድ፣ በንባብ ከሚያገኙት እና በተፈጥሮ ከያዙት እውቀት ጋር በማዋሃድ በትጋት ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ነው ያሳሰቡት።

ወታደራዊ ተቋማት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ መሪዎች፣ በስነ ምግባር አርኣያዎች፣ ሀገርን እና ወገንን በመጠበቅ አኩሪዎች፣ ህግና ስርዓትን በማክበር እና በማስከበር ተምሳሌት እንዲሆኑም ያስፈልጋል ብለዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸አቶ ለማ መገርሳ/የመከላከያ ሚኒስትር/፣ ዶ/ር አብይ አህመድ/የኢፌዴሪ ጠ/ሚ/፣ጀነራል አደም መሃመድ/የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅማ_ዩኒቨርሲቲ

ዛሬ የጅማ ዪኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ለአርንጓዴ አሻራ ከ5 መኪና በላይ ወደ ግልገል ጊቤ በመሄድ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

ASTU 1859 ተማሪዎችን አስመረቀ!

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ/ASTU/ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 353 ሴት ተማሪዎችን ጨምሮ 1859 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም በዩኒቨርስቲ የሚታዩ #በዘርኝነት የሚከሰቱ #መጠፋፋቶች ኋላ ቀር አስተሳሰብ በመሆናቸው ይህ ትውልድ መፍቀድ የለበትም ብለዋል፡፡ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማርያም በበኩላቸው ተማሪዎች በተማሩበት መስክ ጠንካራ ሰራተኛ በመሆን የአገልጋይነት ስሜት በመላበስ የተጣለባቸውን አደራ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ከ25 አመታ በፊት የተቋቋመው ዩኒቨርስቲው በልዩ የመግቢያ ፈተና በዓመት 5ሺህ የሚሆኑ ለፈተና ቢቀርቡም 1500 ብቻ ናቸው ዕድሉን የሚያገኙት ተብሏል፡፡ ዩኒቨርስቲው የምርምር እና የጥናት የልህቀት ስራዎችን የሚያካሂድበት 8 የልህቀት ማዕክል አሉት፡፡

በዩኒቨስቲው የሚገኘው ላብቶሪ ለዩኒቨርስቲ ለተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር አገልግሎቱን እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡ ሙህራን በዘርፉ ላይ ምርምር እና ጥናት ሊያካሂዱበት የሚችል በአይነቱ ለየት ያለ የምርምር ማዕከል በዩኒቨርስቲው ውስጥ እየተገነባ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ፦

በሀገር ደረጃ የሚስተዋለው የብሄር ፅንፈኝነት ለሀገራዊ አንድት ተግዳሮት በመሆኑ መታገል እንደሚገባ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

የብሄር ፅንፈኝነት ለሀገራዊ አንድነት እና ለፌደራላዊትና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ተግዳሮት እንደሆነ በውይይቱ በማንሳት መታገል እንደሚገባ ኮሚቴው ተመልክቷል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ኢትዮጵያዊ ማንነትን አስታርቆና አቻችሎ ማስኬድ እንደሚገባ መነሳቱንና በማህበራዊ ሚዲያው ከሚንፀባረቁትና አመራሩም ከሚገዛቸው ፅንፈኝነት በመውጣት መታገል እንደሚገባ ዝርዝር ግምገማ ማካሄዱን የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባልና በኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/EPRDF-08-10
ምርጫው በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ ኢህአዴግ ወሰነ!

ምርጫ 2012 በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንደወሰነ ተገልጿል። ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከነሀሴ 2 እስከ 3/2011 ስብሰባውን አካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia