This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
20,042 ተማሪዎች ፈተናውን ወድቀዋል!
ከአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች መካከል 4 ተማሪዎች ብቻ የዘንድሮውን ከፍተኛ ማርክ (96%) አምጥተዋል፡፡ በተቃራኒው 20,042 ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል አላለፉም፡፡
Via #shegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ጅማ
የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ በጅማ ከተማ ለሚገኙ ከ400 በላይ ነዋሪዎች ድጋፍ ተደረገ። ዛሬ ድጋፉ የተሰጠው በጅማ ዩኒቨርሲቲ እንስሳትና ህክምና ኮሌጅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በተዘጋጀው ስነስርአት ላይ ነው፡፡
ፎቶ፦ #Amole

የሃጂና ዑምራ ስነ ስርዓት መካሄድ ጀመረ!
ከ2 ሚሊየን በላይ ህዝበ መስሊም የሚሳተፍበት የሃጂና ዑምራ ስነ ስርዓት በሳዑዲ ዓረቢያ መካሄድ ጀመረ፡፡ በሳዑዲ ዓረቢያ በየአመቱ የሚካሄደው የሃጂና ዑምራ ስነ ስርዓት በአለም ቀዳሚው እና በርካታ ህዝብ የሚሰበሰብበት ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓት ነው፡፡ ስነ ስርዓቱ በእስልምና ሀይማኖት አምስቱ ማዕዘናት ከሚባሉት አንዱ ሲሆን፥ ህዝበ ሙስሊሙ በህይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ወደ ቦታው ማቅናት ይጠበቅበታል፡፡
በቅዱስቲቱ የመካ ከተማ እና በዙሪያዋ በሚገኙ አካባቢዎች ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓት ይፈፀማል፡፡ የሃገሪቱ የፀጥታ ሀይል ቃል አቀባይ ሁሉም የጦር አባላት የስነ ስርዓቱን ፀጥታ ለማስከበር በአካባቢው እንደተሰማሩ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ዓመት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን #ህዝበ_ሙስሊም በቅድስቲቱ ከተማ እንደሚሰባሰብም ነው የሚጠበቀው፡፡እንዲሁም ለ1 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚሆኑ የሃጂና ዑምራ ተጓዦች ያለምንም የሰው ጣልቃ ገብነት በኢንተርኔት ቪዛ እንደተሰጣቸው የሳዑዲ ዓረቢያ የሃጂ ሚኒስትር ሃቲም ቢን ሃሰን ቃዲ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡- ኤ ኤፍ ፒ

ግልፅ እንዲሆን!
"ከአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች መካከል 4 ተማሪዎች ብቻ የዘንድሮውን ከፍተኛ ማርክ (96%) አምጥተዋል፡፡"
የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ውጤትን በተለመለከት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊን በስልክ አነጋግሬያቸው ነበር ተከታዩን ብለዋል፦
"ቁጥሩ ካሉት ተማሪዎች ውድድር አንፃር ነው፤ የ8ኛ ክፍል ውጤት እርስ በእርስ ከተማሪዎች ጋር እኛ የምንከተለውን ፕሪንሲፕል በተማሪዎች መካከል ባለው በሚመዘገበው ውጤት አንፃር በሚደረግ ፉክክር እንጂ የተቀመጡ ከስታንዳርድ ጋር የሚደረግ ውድድር አይደለም። ስለዚህ ከተመዘገበው ውጤት አንፃር ሲታይ ካሉት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው። ከተቀመጠው ስታንዳርድ ሳይሆን ካሉት ከተፈተኑት ተማሪዎች አንፃር ሲታይ የ4ቱ ተማሪዎች ከፍ ያለ ነው።"

#እንኳን_አደረሳችሁ
"የአረፋ በዓልን አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ማክበር ይገባል" - ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ 1 ሺህ 440ኛውን የአረፋ በዓል አስመልክተው ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዚሁ መልዕክታቸው በዓሉን የተቸገሩትን በማሰብና በማካፈል ማሳለፍ እንሚገባ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አንገብጋቢው ጉዳይ አንድነትና ሠላምን ማስጠበቅ መሆኑን የጠቀሱት ሃጅ ኡመር “በሀገርም ሆነ በውጭ ያለን ሁሉ አንድነታችንንና ሠላማችንን ልንጠብቅ ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ

የፖሊስ መኪና ተገልብጦ ጉዳት ደረሰ!
በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቃጫ ቢራ ወረዳ መሳፊ ቀበሌ አካባቢ ንብረትነቱ የቃጫ ቢራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የሆነ ፓትሮል ተሽከርካሪ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ አሽከርካሪውን ጨምሮ በሁለት የፖሊስ አባላት ላይ ከባድና ቀላለ የአካል ጉዳቶች ደረሰዋል፡፡ በአሁኑ ሰኣትም በሺንሺቾ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
Via #Y /ከሺንሺቾ የTIKVAH ETH ቤተሰብ አባል/

#አሳዛኝ_ዜና
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የአፈር መደርመስ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የመረጃ ኢንተለጀንስ ቡድን መሪ ሳጅን ጌታሁን ተስፋዬ እንደተናገሩት፥ አደጋው የተከሰተው በወረዳው ጋንታ ካንቻሜ ቀበሌ ልዩ ስሙ “መርከብ ጣቢያ” በሚባል ስፍራ ነው። አደጋው በአንድ ብሎኬት ማምረቻ ድርጅት ውስጥ መድረሱንም ተናግረዋል።
የአደጋው መንስኤ የብሎኬት ማምረቻ ሰራተኞች አፈር በመቆፈር ላይ እያሉ በዙሪያው ከፍተኛ መጠን ያለው አፈር መደርመሱ መሆኑንም አስታውቀዋል ፡፡ሳጅን ጌታሁን እንዳሉት በአደጋው በአፈር ቁፋሮ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ወድያውኑ ሕይወታቸው አልፏል። ከሟቾች መካከል ሁለቱ ወንድማማቾች መሆናቸውም ነው የተገለጸው። በቁፋሮ የወጣው የሟቾች አስክሬን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ምርመራ ተደርጎለት ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱ ተዘግቧል።
Via ኢዜአ

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እሁድ የሚከበረውን 1440ኛው የኢድ አል አድሃ (#አረፋ) በዓልን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሰይድ መሐመድ ኡመር 1440ኛው ሂጂራ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሲከበር የተቸገሩትን በመርዳት እና ለሀገር ሰላም ፀሎት በማድረግ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ሙስሊሙ ማኅብረተሰብ አቅም የሌላቸው እና የተቸገሩ የኃይማኖቱ ተከታዮች በአሉን ተደስተው እንዲያከብሩ የማድረግ ኃማኖታዊና ማኅበራዊ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ነው ፕሬዝዳንቱ ያስገነዘቡት፡፡
የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች በሀገሪቱም ሆነ በአማራ ክልል በተከሰተው አለመረጋጋት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና ወደ ቀድሞው ህይወታቸው እንዲመለሱ በመርዳት በዓሉን እንዲያከብሩም ሺህ ሰኢድ መሃመድ ኡመር ጠይቀዋል፡፡
ምእመኑ በዓሉን ከሌሎች የኃይማኖት ተከታይ ወገኖቻቸው ጋር በማክበር ለዘመናት የዘለቀውን የአብሮነትና የመተሳሰብ እሴት ማጎልበት ላይ እንዲያተኩሩም ነው ያሳሰቡት፡፡ በዓሉ በባሕር ዳር አለም አቀፍ ስታዬም የሚከበር ይሆናል፡፡ የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችም በሥፍራው ተገኝተው መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል፡፡
Via #AMMA

መንገዱ ድጋሚ ተዘጋ!
#ከሀረር ወደአዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ድጋሚ #መዘጋቱን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
በስልክ ያነጋገሩት የቤተሰባችን አባል ይህን ብሏል፦
"ከሀረር ወደ አዲስ አበባ እየሄድን ነበር አዋሽ ላይ/ወደ ጅቡቲና አዲስ አበባ #መገንጠያ ላይ መንገድ ተዘግቶ ቆመናል። አስፓልቱ ላይም ጎማ እየተቃጠለ አይተናል። #አንዳንድ መኪኖች #ወደሀረር እየተመለሱ ነው።"

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን!
1440ኛው የአረፋ በዓልና የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን የእግር ኳስ ውድድር ምንም አይነት የጸጥታ ችግር እንዳይገጥማቸው በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ 1440ኛው የኢድ አል አድሃ( አረፋ) በዓል ፊታችን ዕሁድ ይከበራል፡፡
በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ደግሞ እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ ሀይማኖታዊ ክንዋኔዎች እንደሚካሄዱበት ይጠበቃል፡፡ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ ደግሞ በስታዲዬሙ ፋሲል ከነማ ከታንዛንያው አዛም ጋር ይጫወታሉ፡፡ በመሆኑም በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የሚደረገውን የእግር ኳስ ጨዋታ ለመከታተል ደጋፊዎች ወደ ሜዳ መሄድ ያለባቸው ከ4፡00 ጀምሮ እንደሆነ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እሁድ ነሀሴ 5/2011 ዓ.ም በእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች የሚከበረውን 1440ኛ የአረፋ በዓልና በዚያው ቀን በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የሚካሄደውን የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን የእግር ኳስ ውድድር በሰላም ለማጠናቀቅ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

#ያገባኛል #ይመለከተኛል የመዝሙር ኮንሰርት የመጨረሻ ልምምድ
እኛ ተዘጋጅተናል! እርስዎስ?
ትኬት ካልገዙ አሁኑኑ በአቅራቢያዎ ካለ የብርሀን ባንክ በመግዛት የታሪክ ተካፋይ ይሁኑ!
ዋጋ መደበኛ 100 ብር
VIP 1000 ብር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እኛ ተዘጋጅተናል! እርስዎስ?
ትኬት ካልገዙ አሁኑኑ በአቅራቢያዎ ካለ የብርሀን ባንክ በመግዛት የታሪክ ተካፋይ ይሁኑ!
ዋጋ መደበኛ 100 ብር
VIP 1000 ብር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሃብት የሚያባክኑ የመንግሥት ሹማምንትንና ከፍተኛ ባለሙያዎችን በሕግ ለመጠየቅ መርማሪ ቡድን አቋቁሜያለሁ- ብሏል የፌደራሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፡፡ የሹማምንቱን ማንነትም በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።
Via #shegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #shegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ አምስት ሰዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ!
ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባና በባህርዳር ከተሞች ከመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ሰዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባና በባህርዳር ከተሞች ከመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ፣ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ሰዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ባቀረው የጊዜ ቀጠሮ ላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
በዚሁ መዝገብ ፍርድ ቤት የቀረቡት 1ኛ በሪሁን አዳነ፣ 2ኛ መርከቡ ኃይሌ ፣ 3ኛ ስንታየሁ ቸኮል፣ 4ኛ ጌዲዮን ወንድወሰን፣ 5ኛ ማስተዋል አረጋ እና 6ኛ ኃየሎም ብርሃኔ ናቸው።
ተጠርጣሪዎቹ የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸውን ጠቅሰው የዋስትና መብታቸው እንዲከበርና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ ፍርድ ቤቱም መዝገቡን #መርምሮ 4ኛ ተጠርጣሪ ጌዲዮን ወንድወሰን በአራት ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ውሳኔ ሰጥቷል። በቀሪዎቹ አምስት ተጠርጣሪዎች ላይ ደግሞ ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ እንዲቀጥል ከሐምሌ 24 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ የሚታሰብ ተጨማሪ 28 ቀን ፈቅዶለታል።
Via #ኢዜአ

ፍንዳታውን የፈፀመችው አይነ-ስውር ሴት ናት!
#የሶማልያ መንግሥት በተናገረው መሰረት በቅርቡ የሞቃዲሾ ከንቲባን ህይወት ያጠፋውን ፍንዳታ የፈፀመችው በሌላ ሴት የተመራች አይነ-ስውር ሴት ነች። የሶማልያ መንግሥት ዛሬ ያወጣው መግለጫ፣ ሁለቱ ሴቶች ተገቢ የማጣርያ ሂዳት ሳይደረግባቸው በከተማይቱ የመንግሥት መሥርያ ቤት ተቀጥረው ይሰሩ እንደነበር ገልጿል።
ሁለቱም ሴቶች በሀገሪቱ በአሸባሪዎች ቁጥጥር ሥር ባሉት ቦታዎች ለመዘዋወር በአንድ ወር ውስጥ በተከታታይ ዕረፍት ወስደው እንደነበር መግለጫው ጠቁሟል። አል ሸባብ እአአ ባለፈው ሃምሌ 24 ቀን ለተፈፀመው ፍንዳታ ኃላፊነት መውሰዱ ይታወሳል።
የሞቃዲሾ ከንቲባ አብዲራሕማን ኡመር ኦስማንን ያካተቱ ሌሎች የአስተዳደራቸው ባለሥልጣኖች ያሉባቸው ስምንት ሰዎች በፍንዳታው ተገድለዋል። ከንቲባው በፍንዳታው ቆስለው ኳታር ሲታከሙ ከቆዩ በኋላ ባለፈው ሳምንት ሃሙስ ማረፋቸው ይታወቃል። በአሜሪካ ድምፅ ያለው የሶማልኛ አገልግሎት በዘገበው መሰረት ሁለቱ ሴቶች፣ በከተማይቱ አስተዳደር ለመቀጠር ሲሉ የሃሰት ስም ነበር የተጠቀሙት።
Via #VOA

መንገዱ ተከፍቷል!
ከሀረር ወደአዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ #መዘጋቱን ገልጬላችሁ ነበር አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት መንገዱ ተከፍቶ #ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል።

”በአሁን ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በሰላም የመኖር ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል ተናገሩ።
ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ይህን ያሉት ዛሬ የሰላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን አስመልክቶ በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ነው።
ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው በዘርና በጎሳ ተከፋፍሎ ወደ ግጭት የመግባት አባዜ ከየትኛውም የሃይማኖት አስተምህሮ ጋር አይስማማም።
ከውጭ አገር ጦር መሳሪያ አስገብቶ በወገን ላይ ጉዳት ማድረስ፣ ማፈናቀልና መግደል 97 በመቶ ያህል የሃይማኖት ተከታዮች አላት በምትባል አገር የማይጠበቅ አሳዛኝ ድርጊት መሆኑንም አመልክተዋል።
የሃይማኖት አባቶች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በእኩይ ተግባር ከመሰማራት ተቆጥበው ለተከታዮቻቸው ዓረዓያ መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
Via #ENA

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
"ወረፋ በመብዛቱ ምክንያት ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ በወቅቱ ባለመፈፀማቸው ደንበኞች ላይ ምንም አይነት ቅጣት አይጣልባቸውም" - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
.
.
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያ ለመክፈል ወረፋ በመብዛቱ ምክንያት ደንበኞች ላይ ምንም ዓይነት ቅጣት እንደማይጣልባቸው አስታወቀ።
አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ደንበኞች የአገልግሎት ክፍያ መፈጸሚያ 33 የክፍያ ማዕካላት እንዳለው ገልጾ ደንበኞች ወረፋ በማይበዛባቸው አካባቢዎች በመሄድ የፍጆታ ሂሳባቸውን መክፈል ይችላሉ ብሏል።
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳገኘነው መረጃ ከቀጣይ ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ አሁን የተፈጠረውን መጨናነቅና መጉላላት ለመቅረፍ ደንበኞችን ቀድሞ እንደነበረው በአራት ምድብ በመክፈል ማለትም ግሩፕ 1- ከ26 እስከ 30፣ ግሩፕ 2- ከ1 እስከ 8፣ ግሩፕ 3- ከ7 እስከ 15 እና ግሩፕ 4- ከ12 እስከ 17 ባሉት ቀናት አገልግሎቱን የሚሰጥ ይሆናል፡፡
አገልግሎቱ አክሎም ፍቃደኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት ደንበኛ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ደብተር በመክፍት በአቅርቢያው በሚገኝ የተቋሙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል የተዘጋጀውን የስምምነት ቅፅ በመሙላት ወርሃዊ ክፍያውን በባንኩ በኩል መፈፀም እንደሚችል ገልጿል፡፡
ለቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞችም የወረፋ መብዛትና መጨናነቅን ምክንያት በማድረግ ካርድ እንሙላላችሁ እያሉ የሚያጭበረብሩ ግለሰቦች ስላሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባችኋል ሲል ተቋሙ አስጠንቅቋል።
Via #EPA

ከአህመዲን ጀበል
በትናንትናው እለት የፈረሰውን የአሊፍ መስጊድን ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ ነገ ጠዋት በአካል በቦታው ተገኝተው በነበረበት ሁኔታ እንዲገነባ ያስደርጋሉ።
በከተማ አስተዳደሩ ያለከንቲባው ጽ/ቤት አውቅና መስጊዱ በመፍረሱና የመስጊድ ችግሮችን አጥንቶ መፍትሄ እንዲያቀርብ የተቋቋመው ኮሚቴ ሳያውቅ መስጂዶቹን አፍርሰዋል የተባሉና በትናንትናው እለት መስጊዱን የማፍረሱን ሂደት የመሩ አቶ ፀጋዬ ደምሴ የወረዳው የደንብ ማስከበር ኃለፊ እና አማን ገ/ሚከኤል የወረዳው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዛሬ በተደረገ ግምገማ ከስራ ተባረው በቁጥጥር ስር ዉለዋል። አቶ ታከለ ዑማም ነገ ጠዋት በ3:30 በስፍራው በመገኘት ህብረተሰቡን ይቅርታ በመጠየቅ መስጊዱ በነበረበት መልኩ እንዲገነባ ያስደርጋሉ።
የአከባቢው ሙሰሊሞች፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ አመራር አባላትም በስፍራው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል። የአከባበው ሙስሊምም በስፍራው በመገኘት መስጊዱን እንዲገነባ ጥሪ በቀርቧል። በዚህ አጋጣሚ አቶ ታከለ ኡማ ጋር በመሆን በኢስላማዊ አደብ በትብብርና በወንድማማችነት መንፈስ መስጊዱን እንዲገነባ እኔ አህመዲን ጀበል ጥሪ አደርጋለሁ።
ከአቶ ታከለ ኡማ ጋር በስልክ ባደረግነው ንግግር እንደገለፁት በየቀኑ በአዲስ አበባ ከተማ 118 ወረዳዎች ዉስጥ የሚደረገውን እያንዳንዱን ነገር በቀጥታ እንደማያዙና ከዚህ የተነሳ መስጂዱ እንደሚፈርስ ምንም መረጃ እንደሌላቸው እንዲሁም ህገወጥም ቢሆን እንኳ የከንቲባ ፅ/ቤቱ ሳያውቅ የትኛውም የሃይማኖት ተቋም እንዳይፈርስ ከተሰጠው አቅጣጫ ዉጭ በመንቀሳቀስ መስጂዱን ባፈረሱት አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱንና ከአሁን በዃላም ሆነ ብለው ህዝብና መንግስትን የሚያጋጩት ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

መስጅድ እንዲፈርስ ያደረጉት በቁጥጥር ስር ዋሉ!
የከተማውን አስተዳደር ከሕዝበ ሙስሊሙ ጋር ለማጣላት እና በጋራ ኮሚቴው የተሰራውን ሥራ ለማጠልሸት የሚሞክሩ፣ የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም መልካም ስም ለማጉደፍ የሚኳትኑ እንዳሉ ልንገነዘብ ይገባል።
የእኩይ ተግባር ሥራ አንዱ መስጅድ በማፍስ እና የተጀመረውን መግባባት ለመናድ መሞከር ቢሆንም ግን እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል። ነገ ጠዋት የመጀመሪያ ሥራችን የተሻለ ቦታ በመስጠት ለሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ያለንን የማይነቃነቅ ድጋፋችንን እናሳያለን።
ለማንኛውም ለተፈጠረው ስህተት እና ዕኩይ ድርጊት በራሴ እና በከተማችን አስተዳደር ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ። በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉት እና ድርጊቱን ያስፈፀሙት በሕግ እንዲጠየቁ እና ተልዕኮአቸውን ለማጣራት ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏል።
ኢ/ር ታከለ ኡማ

#ድሬዳዋ
"አንድ ዕድል ለሰላም" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የዛፍ ጥላ ሥር ውይይት ነገ በድሬዳዋ አስተዳደር እንደሚካሄድ የአስተዳደሩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። በውይይቱ የሚስዝ ወርልድ 2019 አሸናፊ ፣የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊቢራና ሌሎችም ተዋቂ ሰዎች እንደሚሳተፉም ተመልክቷል። ፕሮግራሙን አስመልክተው የድሬዳዋ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ዛሬ እንደተገለጹት ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ባህሎችን በመጠቀም ሽምግልና በአካባቢና በሀገር ሰላም ዘላቂነትን ላይ ያለውን ሚና በትውልድ ውስጥ ማስረጽ ነው፡፡ የዛፍ ጥላ ስር ውይይትን በመጀመርና ተቋማዊ አደረጃጀትን በማኖር ከባቢያዊ ግጭቶች በመከላከል ሀገር አቀፍ ሰላም እንዲረጋገጥ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡