#update ሰሜን ኮሪያ የጦር መሣሪያ መርሃ ግብሯን ለመደጎም “2 ቢሊዮን ዶላር በሳይበር ጥቃት መስረቋን” ሾልኮ የወጣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት ይፋ አደርጓል። ፒዮንግያንግ ገንዘቡን ለመሰብሰብ ባንኮችን እና በኢንተርኔት ሲስተም የሚደረጉ የገንዘብ ልውውጦችን ዒላማ ማድረጓን ነው ምሥጢራዊ ሪፖርቱ የጠቆመው።
የተመድ የዘርፉ ጠበብቶች የ'ሳይበር ማይኒንግ' ድርጊቶችን ማለትም እጅግ የረቀቁ ኮምፒዩተሮችን በመጠቀም የሚደረጉ የውጭ ገንዘብ የመመንተፍ ድርጊቶች ላይ ምርመራ እያካሄዱ ይገኛሉ። ሪፖርቱ ለተባበሩት መንግስታት ደርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ምርመራ ለሚያደርገው ኮሚቴ የተዘጋጀ ነው።
ሪፖርቱ ከሳይበር ጥቃቱ ባሻገርም ከዚህ በፊት ሰሜን ኮሪያ ተጥሎባት የነበረውን ከመርከብ መርከብ የእቃዎች ሽግግር መፈፀሟን የሚገልፁ መረጃዎችም ተካተዋል። ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር የጀመረችው ድፕሎማሲ ጥረት አልሳካ ሲላት የተለያዩ ርቀት ያላቸው ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ተከትሎ ዳግም ቀጠናው ወደ ውጥረት መመለሱን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡
Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ጥንቃቄ #12ኛክፍል
በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ #ስም ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገፅ በመኖራቸው ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ትክክለኛውን የኤጀንሲውን ገፅ ብቻ ብትከተሉ መልካም ነው። ትላንት እንደተሰማው የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት አርብ ወይም ከዛ በፊት ይፋ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

በአሜሪካ ቁጣን የቀሰቀሰው ፎቶ!
በአሜሪካ ሁለት ነጭ ፓሊሶች በፈረስ ላይ ሆነው አንድን ጥቁር ግለሰብ አስረው ሲሄዱ የሚያሳየው ፎቶ ብዙዎቸን አስቆጥቷል፡፡ ሁለቱ ነጭ ፓሊሶች በፈረስ ላይ በመሆን አንድን ጥቁር ግለሰብ በገመድ አስረው ሲሄዱ የሚያሳየው ፎቶ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ከተለቀቀ በኋላ በመላ አሜሪካ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡
አጋጣሚው በአሜሪካ የነጭ እና ጥቁር ክፍፍል በነበረበት ወቅት የነበረውን ዘረኝነት፣ ግጭት እና የባሪያ ንግድ የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡ በቴካሳስ ግዛት የምትገኘው ጋልቬስቶን ከተማ የፓሊስ ሃላፊ ቬርኖን ሃሌ ስልተፈጠረው ነገር ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን መግለጫቸው ግን ደካማ ነው በማለት ተቃውሞ ቀርቦባቸዋል፡፡
Via #ኤፍቢሲ

አብዲ ኢሌን ለማስለቀቅ አሲረዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማና ሌሎች ከተሞች ላይ በተፈጸመ ግድያ፣ አካል ማጉደል፣ ማፈናቀል፣ አብያተ ክርስቲያናትና የንግድ ተቋማትን በማቃጠል ምክንያት ክስ የተመሠረተባቸውን የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ለማስለቀቅ ሴራ አቀነባብረው የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሪፖርተር ዘገበ።
.
.
ቃሊቲ ማረሚያ ቤት መግቢያ አካባቢ መኪና አዘጋጅተው ነበር የተባሉት ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች የተከሳሹን መምጣት በመጠባበቅ ላይ እያሉ፣ ያቆሙትን መኪና ከማረሚያ ቤቱ አካባቢ እንዲያነሱ በትራፊክ ፖሊስ ሲጠየቁ ‹‹አናነሳም›› የሚል ምላሽ መስጠታቸውንም የሪፖርየር ምንጮች አስረድተዋል፡፡
.
.
በዚህ ጊዜ የቆመው መኪና እንዲፈተሽ ሲጠየቁ በፈጠሩት አታካራ ሳቢያ ተኩስ መለዋወጣቸውንና ከየትኛው ወገን እንደሆነ ግልጽ ባይሆንም፣ አንድ ሰው መመታቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከግለሰቦቹ መካከል የተወሰኑት ሲያመልጡ አንዲት ሴትን ጨምሮ አብዛኞቹ በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ መሆናቸውንም የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AB-08-07

#የኢፌዴሪ_ትምህርት_ሚኒስቴር
"የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው"- የትምህርት ሚኒስቴር
.
.
የግል ባለሀብት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና ህብረተሰቡን በማሳተፍ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ትምህርት ቤቶች እንዲሰሩና መሳሪያዎች እንዲሟሉ እየተደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል፡፡
መምህራንንና ተማሪዎችን ማብቃት፣ ለትምህርት ቤቶች ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ካሪኩለሞችን በተማሪው ልክ የመቅረጽ ስራዎችን በመስራት የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆች እየተተገበሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
የመምህራንን አቅም በተለያዩ መርሃ ግብሮች የማሳደግ ስራ፣ በተለይም የክረምት መርሃ ግብርና አጫጭር ኮርሶችን በመስጠት የመምህራንን አቅም የማሳደግ ስራ እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ይህም የተማሪና መምህራንን ግንኙነት መልካም በማድረግ መምህሩ የተዘጋጀውን መጽሃፍ በተገቢው ሁኔታ አውቆ በማሳወቅ ለተማሪው እውቀት ለማስጨበጥ ይረዳል ነው የተባለው፡፡
የመምህራን ማህበር አደረጃጀት፣ የተማሪ ወላጅ ህብረት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲቋቋም በማድረግ ለትምህርት ጥራት መምጣት ትኩረት መሰጠቱም ተገልጿል፡፡
የትምህርት ቤቶች መስፋፋትና ለትምህርት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች መሟላት ለትምህርት ጥራት የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ያሉት ወ/ሮ ሀረጓ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች እየተሰሩ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
https://telegra.ph/FT-08-07
Via #ኢቲቪ

"መረጃው ሀሰት ነው" የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር
የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንትን #ለማስመለጥ የሞከሩ ሰዎች ተያዙ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሃሰት መሆኑን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ።
በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገረመው አያሌው እንዳሉት ዘገባው ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል። አቶ ገረመው የተፈጠረውን ነገር እንዲህ ሲሉ አስረድተዋል፦
"ባሳለፍነው ሰኞ እለት የአዲስ አበባ ፖሊስ በአካባቢው በወንጀል የሚፈልገውን አንድ ተጠርጣሪ ለመያዝ ባደረገው ጥረት በስፍራው ተጠርጣሪው እጅ ላለመስጠት ሽጉጥ ወደ ፖሊሶቹ በመተኮሱ ምክንያት የተፈጠረ ግርግር ነበር እንጂ ከቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዘዳንት መሃመድ ኡመር ጉዳይ ጋር አይገናኝም" ብለዋል።
ምንጭ፦ #ኢትዮኤፍኤም

የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ጋር ለሚያገናኘውና በአዲስ መልክ ለሚሰራው የመንገድ ትራንስፖርት ኮሪደር ፕሮጀክት የሚውል የ98 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ በትላንትናው ዕለት ማፅደቁን አስታውቋል። #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአማራ ክልል የሚገኙ 39 የግል ኮሌጆች ችግር እንዳለባቸው ተነገረ፤ ቢሮው ለጊዜው ለአዳዲስ ኮሌጆች ፈቃድ እንደማይሰጥም አስታውቋል!
በአማራ ክልል ዕውቅና ከተሰጣቸው 93 የግል ኮሌጆች መካከል 39 ችግር ያለባቸው መሆኑን የክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡ ኮሌጆቹ የሚሰጡት ትምህርት የሥራ #ገበያ_ፍላጎት፣ ያላቸውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እና ሌሎች መመዘኛ መስፈርቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነበር ዕውቅና የተሰጣቸው፡፡ ይሁን እንጂ ከተፈቀደላቸው አሠራር ውጭ በርቀት የሚያሰለጥኑ፣ ከተፈቀደላቸው የስልጠና የሙያ ዘርፎች ውጭ ስልጠና የሚሰጡ፤ ከተፈቀደው የመግቢያ ነጥብ በታች ተማሪዎችን እየተቀበሉ የሚያሰለጥኑ እና ከተፈቀደው የሰልጣኝ ቁጥር በላይ ከፍተኛ ሰው የሚያሰለጥኑ ኮሌጆች መኖራቸውን የቢሮው ኃላፊ አቶ የሻምበል ከበደ አስታውቀዋል፡፡ በገበያ የማይፈለጉ ሙያዎች ማሰልጠን እና የስልጠና ዕውቅና ሳይኖራቸው አሰልጥነው የምሥክር ወረቀት መስጫ ጊዜያቸው ሲደርስ ወደ ቢሮው የሚሄዱ ኮሌጆች እንዳሉም ተመላክቷል፡፡
Via #AMMA

#ሜቴክ
የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በመንግሥት ውሳኔና ኮርፖሬሽኑ በፈጸመው የተሳሳተ አካሄድ 70 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ሲገልፅ፤ 57 ቢሊዮን ብሩን መንግሥት እንዲሰርዝለትና ወደ ካፒታል እንዲቀይርለት ጥያቄ ማቅረቡን አመለከተ። በያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ከዲዛይንና ማስተባበረ ውጭ እንዳልተሳተፈም ገልጿል።
Via #EPA

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ከሰዓት ይለቀቃል!
የ12ኛ ክፍል #መልቀቂያ ወይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ከሰዓት በኋላ ይፋ እንደሚሆን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚያብሄር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ፈተናዎቹ ዓለም አቀፍ ተወዳሪነታቸው በተመሰከረላቸው ዘመናዊ አዳዲስ የማረሚያ ማሽኖችን በመጠቀም በጥራት የታረሙ መሆናቸውም ተነግሯል። ይሁንና በማህበራዊ ብዙሃን መገናኛዎች የ12ኛ ከፍል ውጤት ተለቋል ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ሃሰት ነው ብለዋል። የእርማቱ ስራ የተጠነቀቀቀ በመሆኑ ኤጀንሲው ዛሬ ወይም ነገ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ በመግባት ተማሪዎች ውጤቶቻቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።
Via #ኢትዮኤፍኤም

#አዲስ_አበባ
22 አካባቢ ዛሬ የሁለት ሰው ህይወት አለፈ!
የአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛው #ኤልያስ_መሰረት በስፍራው ተገኝቼ አየሁት እንዳለው ፖሊስ ሁለት የሰው ህይወት ያለፈባቸው ስፍራዎችን ከቦ መረጃ ሲወስድ ነበር። ፖሊሶች "እያጣራን ስለሆነ መረጃ አሁን የለንም" ብለዋል።
በአካባቢው የነበሩ እማኞች ግን አንድ ግለሰብ "ሞባይል ሊሰርቀኝ ነበር" በማለት የሌላ ሰው ጭንቅላት ላይ ተኩሶ ገድሏል። ከዛም ተኳሹ በሰዎች ተይዞ አካባቢው ወዳለ ፖሊስ ጣብያ ቢወሰድም የገዳዩን ሽጉጥ ይዞ የነበረው ፖሊስ "ባርቆበት" በአካባቢው የሱቅ ባለቤት የነበረን ግለሰብ መትቶ እሱም ህይወቱ አልፏል ብለዋል።

#PMO
ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ ብሄራዊ የኢንቨስትመንት እና የስራ እድል ፈጠራ መሪ ኮሚቴን ስራ አስጀመሩ። የብሄራዊ ኮሚቴው መቋቋም ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ነሃሴ 5 ይወጣል!
በሰኔ 6፣7፣10 እና 11/2011 ዓ.ም የተሰጠው የዩንቨርስቲ መግቢያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ነሐሴ 5/2011 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይፋ እንደሚደረግ ኤጀንሲያችን ያሳውቃል፡፡ ይህንን ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 322,717 ተማሪዎች መካከል 319,264 የሚሆኑት ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን እነዚህ ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት Admission በሚለው ሳጥን ውስጥ የመፈተኛ ቁጥራቸውን (Registration Number) በማስገባትና go የሚለውን አንዴ click በማድረግ መመልከት የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው ያስገነዝባል፡፡

ይህ ስህተት ታርሟል!
ኤጀንሲው በፌስቡክ ገፁ የ12ኛ ክፍል ፈተና የተሰጠው ሰኔ 3-5 ብሎ ያወጣው መረጃ #ስህተት ነው ታርሟል። ፈተናው የተሰጠው ከሰኔ 6 ጀምሮ ነው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ውጤት ነሃሴ 5 ይፋ አንደሚሆን ተገለፀ!
ኤጀንሲው ይህንን ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 322,717 ተማሪዎች መካከል 319, 264 የሚሆኑት ፈተናውን መውሰዳቸው ተነግሯል፡፡ ውጤቱን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት መመልከት እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡
Via FBC/ፋና ብሮድካስቲንግ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤጀንሲው ይህንን ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 322,717 ተማሪዎች መካከል 319, 264 የሚሆኑት ፈተናውን መውሰዳቸው ተነግሯል፡፡ ውጤቱን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት መመልከት እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡
Via FBC/ፋና ብሮድካስቲንግ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ
የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሚዲያ ላይ ቀርበው በሚያደርጓቸው ንግግሮች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል። ከዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤት መልቀቅ ጋር በተያያዘ ትላንት፣ ዛሬና አሁን የሰማናቸው መረጃዎች የሚጣጣሙ አይደሉም።
√ አቶ አርዓያ ገብረ ከአርብ በፊት ለማድረስ እየተሰራ እንደሆነ ትላንት በልዩ መረጃ የራድዮ ዝግጅት ላይ ተናግረዋል!
√ ዛሬ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አቶ አርዓያን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ ደግሞ ዛሬ ከሰዓት ወይም ነገ ከሰዓት የሚል ነበር!
√ አሁን ኤጀንሲው በህጋዊና ትክክለኛ ገፁ ፈተናው ውጤት ነሃሴ 5 ነው የሚወጣው ብሏል።/በሚዲያ ዛሬ የተባለው ነገር ስህተት ነው ወይም ልክ ነው በዚህ ምክንያት ነው ነሃሴ 5 የተባለው የሚልም ነገር አልሰማንም በደፈናው ነሃሴ 5/
🏷በሚዲያዎች ወጥተን የምንናገራቸው ነገሮች ብዙ ሚሊዮኖች ጋር ነው የሚደርሱትና ጥንቃቄ ያሻቸዋል። መናበብም ቢኖር መልካም ነው እንላለን!!
እኛ እንደTIKVAH-ETH ይቅርታ እንጠይቃለን!

ይህ ሀሰተኛ ገፅ ነው!
nea.gov.et በሚል በፌስቡክ #ከ95_ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት ገፅ ሀሰተኛ ነው። የሚተላለፉት መረጃዎችም ከእውነት የራቁ ናቸው።
#ሼር #share

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤት የፊታችን እሁድ ይፋ ይደረጋል!
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤት የፊታችን #እሁድ ነሐሴ 5፣ 2011 ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ገ/እግዚያብሔር እንደገለፁት የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እርማት በመጠናቀቁ የፊታችን እሁድ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ኤጀንሲው ይፋ ያደርጋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናውን 319,264 ተማሪዎች ከሰኔ 6 እስከ 11፣2011 ድረስ መውሰዳቸውን ኃላፊው አስታውሰዋል፡፡
ተፈታኞች ውጤታቸውን ከፊታችን እሁድ ከ8፡00 ጀምሮ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት Admission በሚለው ሳጥን ውስጥ የመፈተኛ ቁጥራቸውን (Registration Number) በማስገባትና go የሚለውን አንዴ click በማድረግ መመልከት እንደሚችሉ ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡
#ሼር #share
Via #etv

በ95 ኤጀንሲዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ!
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ኤጀንሲዎች ላይ እርምጃ ወሰደ። ቢሮው ከተፈቀደው ውጭ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ከ95 በላይ ኤጀንሲዎች ላይ ፍቃድ የመንጠቅ እርምጃ ወስዷል። ከእነዚህ ውስጥ 25ቱ ህጋዊ እርምጃ በተጨማሪነት የተወሰደባቸው ናቸው ተብሏል።
ኤጀንሲዎቹ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ የዓረብ ሃገራት ስራ እናስቀጥራችኋለን በማለት ገንዘብ ሲቀበሉ የነበሩ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ስራ ፈላጊዎችን ለአላስፈላጊ ወጪ ሲዳርጉ እንደነበርም ቢሮው አስታውቋል። ቢሮው በወሰደው እርምጃም 130 ሺህ ብር አካባቢ የሚሆንና ከስራ ፈላጊዎች የተጭበረበረ ገንዘብ ማስመለስ መቻሉን አስረድቷል።
አሁን ላይም ከ350 በላይ ህጋዊ የሀገር ውስጥ ኤጀንሲዎች ስራ ላይ ናቸው ያለው ቢሮው፥ እነዚህን ኤጀንሲዎች በመደገፍም ህገ ወጥነት የመከላከል ስራ እሰራለሁ ብሏል። በቀጣይም በህገ ወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሱ ኤጀንሲዎች ላይ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ገልጿል።
Via FBC

#update ባለፉት ሶስት ቀናት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በቀን 28/11/2011 በሁለት መኪና ተጭኖ ወደ ድሬዳዋ ሊገባ የነበረ ግምቱ 1,785,140 ብር የሚያወጣ የምግብ ዘይት ሶማሌ ክልል ሽንሌ ወረዳ በፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር ውሎ ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ ተደርጓል።
በተመሳሳይ ቀን ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ይሄድ የነበረ የመንገደኞች ባቡር ሞተሩ ባለበት ክፍል ውስጥ በጥርጣሬ በተደረገ ፍተሻ 4955 የሞባይል ፍላሾች፣ 1195 የሞባይል ከቨር እንዲሁም 14 ዎኪቶኪ የሬድዬ መገናኛ በአጠቃላይ ግምታቸው 1.2 ሚሊዬን ብር በላይ የሚያወጡ ዕቃዎች በጉምሩክ ፈታሾችና የፌደራል ፓሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡
በቀን 29/11/2011 ዓ.ም በቱሪስት ስም ገብቶ ታርጋ የቀየረ RAV 4 መኪና በአዳማ ከተማ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ከአዲሰ አበባ ወደ ጅማ ከተማ ሲገባ የነበረ ግምታዊ ዋጋ 480,000 ብር የሆነ ዘይትም እንደተያዘ ተነግሯል፡፡ በቀን 30/11/ 2011 ዓ.ም በሞያሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ግምታዊ ዋጋው 11.42 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ 2855 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ የተያዘ ሲሆን በወንጀሉ የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር

#CAF
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) የባሕር ዳር እና የመቐለ ዓለም ዓቀፍ ስታዲዮሞችን ለጨዋታ ፈቀደ። ሜዳዎቹ የሚጠበቀውን መስፈርት እንዲያማሉ እንደሚሠራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) የባሕር ዳር እና የመቐለ ስታዲዮሞች ለተወሰነ ጊዜ ጨዋታ እንዲያስተናግዱ መፍቀዱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።