TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ📸ለኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የግመሎች ስጦታ ተበረከተላቸው። ለኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ከሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሐመድ ኡመር የግመሎች ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡አቶ ሙስጠፋ 7 ግመሎችን ከግልገሎቻቸው ጋር ነው ለአቶ ሽመልስ በስጦታ ያበረከቱት፡፡

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የተሰጠ ማሳሰቢያ!

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 650/2001 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የህግ ጥሰት የሚፈጸሙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የጀመረውን የክትትል እና ቁጥጥር ስራዎችን ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እየገለጸ ተማሪዎች፤ ወላጆች፣ ቀጣሪና የሙያ ፍቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች እና መላው ህብረተሰብ ለሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት የበኩላቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪውን ያስተላልፋል።

1ኛ- ከእውቅና ፈቃድ ጋር በተያያዘ ሊደረጉ የሚገባቸው ቅድመ-ጥንቃቄዎች፡-

 ማንኛውም አገር በቀልም ሆነ ድንበር ተሻጋሪ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በቅድመ-ምረቃ እና በድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብሮች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የሚችለው የእውቅና ፈቃድ ባገኘባቸው የትምህርት መስኮችና ካምፓሶች ብቻ ነው፤ ለአንዱ ካምፓስ የተሰጠ የእውቅና ፈቃድ ለሌላው ካምፓስ አያገለግልም፤ ለርቀት ትምህርት ተማሪ መመዝገብ እና ትምህርት መስጠት የሚቻለው የእውቅና ፈቃድ ባገኙባቸው ማዕከላት ብቻ ይሆናል። የእያንዳንዱ የትምህርት መስክ የእውቅና ፈቃድ ሳይታደስ አዲስ ተማሪ መመዝገብ የተከለከለ ነው።

 ተቋማት ከኤጀንሲው ያገኙትን ህጋዊ የእውቅና ፈቃድ ኮፒውን ለተማሪዎች እና ለአካባቢው ህብረተሰብ በሚታይ ቦታ የመለጠፍና ሲጠየቁ የማሳየት ኃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል።

2ኛ- በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት መመዝገብ የሚችሉ አመልካቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው የቅበላ መስፈርቶች ፡-

1. የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ከሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ለትምህርት ዘመኑ የሚያሳውቀውን የመቁረጫ ነጥብ ሟሟላት አለባቸው፣

*

2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች ከሰለጠኑበት የሙያ መስክ ጋር ተዛማጅ በሆነ የስልጠና መስክ በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በደረጃ 4፣ (ወይም በቀድሞ 10+3 ወይም 12+2) ያጠናቀቁ ሆነው፣-

•የደረጃ አራት የብቃት ማረጋገጫ (COC level 4) ተፈትነው ያለፉ፣

•በሙያው ቢያንስ አንድ አመት የስራ ልምድ ያላቸው እና

•በየተቋማቱ የሚዘጋጁትን የመግቢያ መስፈርቶችና ፈተናዎች ያለፉ ሆነው እነዚህን መረጃዎች በምዝገባው እለት ሙሉ ለሙሉ አሟልተው ማቅረብ የሚችሉ ብቻ መሆን አለባቸው።

*

3. እውቅና ካለው ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመጀመሪያ ዲግሪና በላይ የተመረቁ እና ተዛማጅ ባላቸው የትምህርት መስኮች፤

4. በውጭ ሀገር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና የትምህርት ማስረጃቸው በኤጀንሲው የአቻ ግምት የተሰጣቸው መሆን አለባቸው።

በተጨማሪም፡-

===>>ከህሙማን ጋር ግንኙነት ባለው የጤና የትምህርት ዘርፍ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በማታ፣ በቅዳሜና እሁድ ማስተማር የተከለከለ ነው፡፡

===>>ማንኛውም የመንግስት የከፍተኛ ትምርህርት ተቋም ከሀገር ውስጥ የግል ከፍተኛ ትምርህርት ተቋም ጋር የትብብር ስልጠና መስጠት የተከለከለ ነው፡፡

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ህጋዊ መመሪያዎችን ጥሶ የተገኘ ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስነ-ስርዓት መመሪያ መሰረት በፍትሐብሄር ተጠያቂ እንደሚሆን እየገለጽን ከህግ ውጪ ገብተው የሚማሩ ተማሪዎችም ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱ የራሳቸውና የተቋሙ ብቻ ስለሚሆን አስፈላጊውን ቅድመ-ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

ለተጨማሪ መረጃ የኤጀንሲውን ድህረ-ገጽ www.herqa.edu.et ይጎብኙ ወይም በስልክ ቁጥር 0111236130/0111232230 ይጠቀሙ።

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
CSA ግቢ ውስጥ ተኩስ ነበር!

የማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዛሬ ተኩስ ነበር ተብሏል። ጋዜጠኛ አሮን ማሾ ትዊተሩ ላይ እንዳሰፈረው ተኩሱ የነበረው ለህዝብና ቤት ቆጠራ የሚያገለግሉ ታብሌት ኮምፒውተሮችን ይጠብቁ በነበሩ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት መሀከል ነበር ብሏል። ስለ ጉዳዩ ያውቁ እንደሆን የተጠየቁ ሁለት የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች "ልክ ነው፣ ግን መናገር አንችልም። ፖሊሶች መጥተው ምርመራ አርገው ሄደዋል" ብለው።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/#AP/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

#የባሕር_ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የእነ ብርጋዴየር ጀነራል #ተፈራ_ማሞን ጉዳይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተመልክቷል፡፡ መርማሪ ፖሊስ #ተጨማሪ_መረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚል 14 ቀናት ጠይቆ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን #ውድቅ አድርጎታል፡፡ እስከ ነሀሴ 13/2011 ዓ.ም ድረስ ክስ እንዲሰመርትም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

የባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት 13 ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው መርማሪ ፖሊስ በእነ ብርጋዴል ጀነራል ተፈራ ማሞ የምርመራ መዝግብ ያቀረበውን የ14 ቀናት ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

ሰኔ 15 ቀን 2011 በባህር ዳር ከተማ በክልሉ የስራ ሃላፊዎች እና በፌደራል መከላከያ ሰራዊት የስራ ሃላፊዎች ላይ ከተፈጸመው ግድያ ጋር በተያያዘ መርማሪ ፖሊስ በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ላይ የ28 የቃል ምስክሮችን፣ የቴክኒክ እና የሰነድ ማስረጃዎችን አሰባስቦ ለፍድር ቤቱ አቅርቧል።

እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ ሌሎች የቃል ምስክሮችን፣ የቴክኒክና የሰነድ ማስረጃዎችን እንዲሁም የፎረንሲክ እና የኢትዮ ቴሌኮም የስልክ መረጃዎን ለማሰባሰብ የ14 ቀናት የተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ከላይ የተጠቀሱት 28 የቃል ምስክሮች የቴክኒክና የሰነድ መስረጃዎች በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረቡ እንጂ በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የምርመራ መዝገብ ላይ ያለመቅረባቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል።

የተጠየቀው የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርማራ ጊዜም ምንም መረጃ ባለተያዘበት ሁኔታ ደንበኞቻችን የሚጉላላ ነው ብለዋል። በዚህም መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው የተጨማሪ ምርመራ ጊዜ እንዲዘጋ ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ማርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ ምርማራ ጊዜ አሳማኝ አለመሆኑን በመግለጽ የምርመራ መዝገቡ እንዲዘጋ ውሳኔ አሳልፏል። ተጠርጣሪዎቹ የተጠረጠሩበት ጉዳይ በወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 109 መሰረት በግድያ ወንጀል በመሆኑ እስከ ነሃሴ 13 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትእዛዝ ስጥቷል

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CSA

በአዲስ አበባ ከተማ በማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በጥበቃ ስራ ላይ የተሰማራ የፌድራል ፖሊስ አባል ተኩስ ከፍቶ ሁለት ባልደረቦቹን ገድሏል። ድርጊቱ የተፈጸመው ዛሬ ቀትር ላይ ሲሆን፣ ገዳዩ በቁጥጥር ስር ውሏል።

Via #ethiopialiveupdate
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2 ወር ደሞዝ አልተከፈላቸውም...

የአፍሪሄልዝ ቴሌቪዥን ሰራተኞች የ2 ወር ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ተናገሩ። አፍሪሄልዝ ቴሌቪዥን ትኩረቱን በጤና ነክ ጉዳዮች ላይ በማድረግ ነበር በቅርቡ ወደ ተመልካቾች መድረስ የጀመረው።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት የዚህ ቴሌቪዥን ጣቢያው ሰራተኞች ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንደተናገሩት ድርጅቱ በወቅቱ የሰሩበትን ደመወዝ እየከፈላቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል። ሰራተኞቹ እንዳሉትም በድርጅቱ ከተቀጠሩበት ወቅት አንስቶ ደመወዛቸው በወቅቱ ተከፍሏቸው አያውቅም።

እንደ ሰራተኞቹ ገለጻ ከሆነ ለመጨረሻ ጊዜ ደመወዝ ከተከፈላቸውም 2 ወር አልፏቸዋል፣ ለድርጅቱ የበላይ ሃላፊዎች ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው ሲጠይቁ በቂና ተገቢ መልስ ካለመሰጠቱም በላይ ጥያቄውን የሚያነሱ ሰራተኞች ከስራ ይሰናበታሉ፣ካለፍላጎታቸው የዓመት እረፍት እንዲወጡ ይደረጋሉ።

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሜሎን ሰራተኞቹ ያነሱት ቅሬታ ትክክል አለመሆኑንና ድርጅታቸው ለሰራተኞቹ የሰሩበትን ደመወዝ በወቅቱ እየከፈለ መሆኑን ተናግረዋል። በድርጅቱ ሰራተኞች ላይ የተፈጸመ የህግ ስህተት የለም የሰሩበት ክፍያም ተፈጽሟል ዝቅተኛ የስራ አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞችን ብቻ ከስራ አሰናብተናል ሲሉ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

Via #EthioFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢ/ር እንዳወቅ አብቴ እና አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ ጋር በመሆን በቦሌ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት በመገኘት እየተካሄደ ያለውን የእድሳት እና ጥገና መርሃ-ግብር ተመልክተዋል፡፡

በ1967 ዓ.ም የተመሠረተው የቦሌ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት ላለፉት በርካታ ዓመታት ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ ለተማሪዎች የተግባር ተኮር እና የማታ መርሃ ግብር ትምህርት ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ደረጃውን የጠበቀ ጥገና ሳይደረግለት ቆይቷል፡፡

የተማሪዎች የመመገቢያ አደራሾቹ ያሬጁ በመሆናቸው ለተማሪዎቹ በሚያመች መልኩ በሁሉም የትምህርት ደረጃ ላሉ ተማሪዎች አዳዲስ የመመገቢያ አዳራሾች ግንባታ የግል ባለሃብቶችን በማስተባበር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

2700 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ያለው የቦሌ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት በጊቢው ውስጥ ያለውን የአረንጓዴ እና የመጫወቻ ቦታዎች ግንባታም ለተማሪዎች በሚያመች መልኩ እንደሚሰራ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የዳግማዊ ሚኒሊክ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tiivahethiopia
10 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ከሐምሌ 24 እስከ 26/2011 ባሉት ሶስት ቀናት በቶጎ ዉጫሌ፣ አወበሬና ጭናቅሰን አስር ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የመከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራልና የክልል ፖሊስ እንዲሁም የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች በቅንጅት መስራት በመቻላቸው እንደሆነ መረጃው አክሏል።

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ህግን ለማስከበር ከማስተማር ስራ ጎን ለጎን ተጠያቂነት እንዲሰፍን የጀመሯቸዉን ስራዎች አጠናክረው ለማስቀጠል በመስራት ላይ እንደሚገኙም መረጃው ያመለክታል።

Via ገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወጣት ታምራት...

ኢ/ር #ታከለ_ኡማ እና ኢ/ር #እንዳወቅ_አብቴ ከሶስት አመት በፊት ሜክሲኮ አከባቢ በተፈጠረ ከባድ የእሳት አደጋ ከተዘጋ ቤት ውስጥ ተራ በተራ እየተመላለሰ 12 ሰዎችን ከእሳት የታደገውን ወጣት ታምራት ጎሹ በስራ ቦታው ተገኝተው በመጎብኘት ላደረገው #ሰብዓዊነት ምስጋና ችረውታል።

ወጣቱ በዚህ ምግባሩ ሙሉ በሙሉ ሰውነቱ በእሳት ተቃጥሎ ሁለት አመት አልጋ ላይ ያሳለፈ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም የ8 ወር ነብሰጡር ከሆነችው ባለቤቱ ጋር በሚሰሩበት ምግብ ቤት ውስጥ እየኖሩ እንደሚገኙ ኢ/ር ታከለ በጉብኝታቸው ተመልክተዋል። ኢ/ር ታከለ ኡማ ወጣት ታምራት ጎሹ ላሳየው ሰብዓዊነት ያላቸውን አድናቆት ገልፀው ቀሪ ህይወቱን የሚመራበት የመኖሪያ ቤት እንደሚያገኝ ቃል ገብተዋል።

Via MayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አገልጋይ ዩናታን አክሊሉ፦

"…እሳቱም፣ ዱቄቱም፤ ቂጣውም፣ ሃሳቡም፣ ምጣዱም፣ ምድሪቱም ለሁላችንም የምትበቃ ሆና ሳለ፤ እንዳትበቃ የምንጣላ፤ እንዳትበጀን የምንባጅ፣ ለምን እንደምንሆን ግራ ያጋባኛል" - አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/YAK-08-05
የኮማንድ ፖስቱ ማስጠንቀቂያ!

<<በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት እውቅና ሳይሰጣቸው ተሰቅለው የሚገኙ አርማዎችና ሰንደቅ ዓላማዎች በአስቸኳይ እንዲነሱ>> ሲል የደቡብ ክልል ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት #አስጠነቀቀ

ኮማንድ ፖስቱ ዛሬ በክልሉ መንግስት ራዲዮ ጣቢያ አማካኘነት ባስሳተላለፈው ማሳሰቢያ፤ ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ አንዳንድ ዞኖች እና ወረዳዎች በህግ የማይታወቁ አርማዎችን፣ ሰንደቅ ዓላማዎችን፣ ባነሮችን እና የአድራሻ ማስታወቂያዎችን (ታፒላዎችን) የሰቀሉ አካላት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሁለት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ እንዲያነሱ ሲል አሳስቧል።

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የክልሉን #ህጋዊ ሰንደቅ ዓላማ በማውረድና የመንግስት ተቋማት የአድራሻ ማስታወቂያዎችን በመንቀል በምትኩ እውቅና የሌላቸውን የመትከል ሙከራዎች መከናወናቸውን ኮማንድ ፖስቱ በመግለጫው አስታውቋል።

በመሆኑም «ህገ ወጥ»ያላቸውን አርማዎችን፣ ሰንደቅ ዓላማዎችን እና የአድራሻ ማስታወቂያዎችን በተሰጠው የሁለት ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ በማንሳት ህጋዊ» የሆኑትን በአስቸኳይ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ሲል ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።

በተጨማሪም መግለጫው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በክልሉ ሁሉም ዞኖች ፣ ወረዳዎች ፣ በከተሞች አና በቀበሌዎች የመስተዳድር ክልል ውስጥ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ተቋማት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች #ትክክለኛ የአድራሻ ማስታወቂያዎችን (ታፒላዎችን) እና ህጋዊ የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ብቻ እንዲጠቀሙ አመልክቷል።

እንዲሁም በተለያዩ የህትመት ውጤቶች የተዘጋጁና በህግ የማይታወቁ አርማዎችንና ሰንደቅ ዓላማዎችን መልበስ ፣ ይዞ መዘዋወር ፣ መሰቀልም ሆነ መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው ሲል አስታውቋል። በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ መመሪያውን ተፈፃሚ በማያደርጉ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና ድርጅቶች ላይ በየደረጃው በተዋቀሩ የኮማንድ ፖስት አማካኝነት #ህጋዊ_እርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

በደቡብ ክልል የሀዋሳ እና የወላይታ ሶዶ ከተሞችን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በክልል መደራጀትን ለመጠየቅ በተዘጋጁ ሰልፎች ላይ ወደፊቱ ለሚመሰርቷቸው ክልሎች በሰንደቅ ዓላማነት ሊያገለግሉ ይችላሉ በሚል የዘጋጁቸውን አርማዎችን ሲያውለበልቡ እንደነበር አይዘነጋም። በተለይም በሲዳማ ዞን ከባለፈው ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓም ወዲህ በዞኑ የሚገኙ አንዳንድ የወረዳዎች መስተዳድር ፅህፈት ቤቶች የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚሉ የአድራሻ ማስታወቂያዎችን በጎዳናዎች በመትከል በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴ አውታሮች እያሰራጩ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BBC ከTIKVAH-ETH ጋር ያደረገው ቆይታ!

የጥላቻ ንግግር ለምን ወጣቶቹን አሳሰባቸው?

በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን በአንድ መድረክ ላይ አሰባስቦ የጥላቻ ንግግርን ለመግታት እንዲሁም በጎ ተግባራት ላይ ለመሳተፍ እየሰሩ ያሉት እነዚህ ወጣቶች እየተሳካላቸው ነው። ከዚህም በላይ ለመጓዝ ጥረት እያደረጉ ነው። እነማን ናቸው?

ይህን👇ማስፈንጠሪያ በመጫን ያንብቡ!

https://bbc.in/2Kp1NMs
#NewsAlert

በሊብያ ሙርዙቅ በደረሰው #የአየር_ጥቃት 42 ሰዎች ተገደሉ። የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንደገለፁት በደቡባዊ ምስራቅ ሊቢያ የሚገኘው በጄነራል ከሃሊፋ ሃፍታር በሚመራ ሃይል በደረሰው የአየር ጥቃት የ42 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጥቃቱ የደረሰባቸው ሰዎች በሙርዙክ ከተማ የሰርግ ስነ-ስርዓት እየታደሙ ባሉበት ወቅት ነው። በምስራቃዊ ሊብያ ያለው የጄነራል ሃፍተር ሃይል እንደገለጸው እሁድ ማታ የደረሰው የአየር ጥቃት ሲቪል ሰዎችን አላማ ያደረገ አልነበረም፡፡

አገሪቷ እአአ ከ 2011 ከሙሃመድ ጋዳፊ ውድቀት በኋላ በጦርነት ላይ መሆኗም ተገልጿል። የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመለክተው ካለፈው ሚያዚያ ወር ወዲህ በሀገሪቱ በነበረው ግጭት የ1ሺህ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፡፡

ጥቃት የደረሰበት አካባቢ ከፍተኛ የነዳጅ ምርት ያላትና በፈረንጆቹ 2019 የመጀመሪያ ዓመት የተወሰነ አካባቢ በታጣቂ ቡድኑ ቁጥጥር ሥር የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን ለቀው መውጣታቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Via #bbc/ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMO

የሴት ሚኒስትሮች የአመራርነት ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ። ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው። በስልጠናው ላይ ሁሉም ሴት ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል።

ስልጠናው ሴቶች በአመራርነት ወቅት የቤት ውስጥ ስራቸውን እና ማህበራዊ ህይዎታቸውን እንዴት አጣጥመው መሄድ እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነው ተብሏል። በስልጠናው ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን እና የቀድሞዋን የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍን ጨምሮ የአፍሪካ ሃገራት የስራ ሃላፊዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል።

ከዚህ ባለፈም በዘርፉ ልምድ ያላቸውና ከተለያዩ ሃገራት የመጡ የስራ ሃላፊዎች ስልጠና ሰጥተዋል። በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይም ሚኒስትሮቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ችግኝ ተክለዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሃ በተለይ በጤናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ ላበረከቱት አስተዋፆ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ እውቅናና ሽልማት ተበረከተላቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የ25 ዓመቱ ወጣት የፖለቲካ ድርጅት አመራር...

#ወጣት_ቢሊሱማ_ብርሃኑ_አራርሳ
ወጣቱ የፖለቲካ ድርጅት አመራር...

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሽግግር እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንድነት ተዋህደው በቅርብ ከመረጡት የጋራ አመራሮች ውስጥ አንዱ ወጣት ቢሊሱማ ብርሃኑ አራርሶ ነው። ከVOA ጋር ባደረገው ውይይት፤ ወጣቶች #ከስሜታዊነት ይልቅ በምክኒያት ቢያምኑ ጠቃሚ ነው ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ እና ሱዳን የደህንነት ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማሙ። ስምምነቱን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጀኔራል ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል ከሱዳኑ ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አቡበክር ዳምብ ላም ጋር ተፈራርመውታል። በስምምነቱ መሰረትም ሽብርተኝነት፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ፣ የገንዘብና የሰዎች ዝውውር እንዲሁም በሃገራቱ የድንበር ወሰን አካባቢዎች የሚፈጸሙ የተደራጁ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ውይይቶችን በማድረግ መረጃ የሚለዋወጡ ይሆናል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia