TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ውብ ሀገሬ!

ውብ ሀገሬ፤ ውብ ሀገሬ፣ውብ ሀገሬ
ባንቺ እኮ ነው፤ መከበሬ፤ መከበሬ
.
.
እናት አባት ቢሞት በሀገር #ይለቀሳል
እህት ወንድም ቢሞት በሀገር ይለቀሳል
#ሀገር የሞተ እንደሁ ወዴት ይደረሳል?

▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️

#ኢትዮጵያን መውደድ ማለት፦ ህዝቦቿን፣ የህዝቦቿን ባህል፣ ቋንቋ፣ እምነት እና ስርዓት #መውደድ እና #ማክበር ማለት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

3ኛው ዙር የማስ ስፖርት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በማስ ስፖርት መርሃ ግብሩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች ፣ ሚኒስትሮች ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ፣ የተለያዩ የስፖርት ማህበራት ፣ አርቲስቶች እና ከ50ሺ በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ፦

L & T construction - Power Transmission & Distribution

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

የኦሮሞና የሱማሌ ህዝቦች የወንድማማችነት የምክክር መድረክ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተጀምሯል፡፡ በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሐመድ ኡመር፣ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች እና የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሁለቱ ክልል ህዝቦች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
145 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል...

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንና በአማራ ክልል አዊ አስተዳደር ዞን የተከሰተውን ኹከት ለመቆጣጠር የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት 145 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። 785 ቀስት፣ 4 ክላሽ፣ 9,392 ጥይትና 10 ሺ ሐሰተኛ ብር ተይዟል ተብሏል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🏷«ለተማሪዎች ምዝገባ ክፍያ መጠየቃችን #ቅሬታ ፈጥሮብናል» ልጆቻቸውን በመንግሥት ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ ወላጆች

🏷«ክፍያ በሚጠይቁ ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል» አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
__________________________________

በአንዳንድ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች መመዝገቢያ እየተባለ የሚጠየቀው ክፍያ ቅር እንዳሰኛቸው ወላጆች ገለጹ። የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ የከተማ አስተዳደሩ ለመንግሥት ትምህርት ቤቶች እና ለተማሪዎች ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ ልዩ ድጋፍ እያደረገ ባለበት ወቅት ለምዝገባ በሚል ገንዘብ የሚሰበስቡ ትምህርት ቤቶች #ሕገወጥ መሆናቸውን አስታውቋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በአሁኑ ሰዓት "ምቹ ጊዜ ለአትዬጵያ" በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ ወንጌላዊያን አማኞች ቤተ ክርስተሰያናት የተውጣጡ 2012 አዳጊ ወጣቶች (ታዳጊዎች) በአድዋ ፓርክ 2012 ችገኞችን እየተከሉ ነው። ታዳጊዎቹም "እድሜያችን የምትዘሩብንን ለማብቀል ምቹ ጊዜ ነው ስለዚህ የምትዘሩብንን አስተውሉ!" የሚሉ በርከት ያሉ መልዕክቶችን ይዘውና እያሰሙ ከመገናኛ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ድረስ የእግር ጉዞ አድርገዋል።" #ኤርሚያስ/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደብረ_ማርቆስ_ዩንቨርስቲ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ከዳያስፖራው ጋር በመተባበር የአዳሪ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ እንዳስታወቁት፣ ዩኒቨርሲቲው የአዳሪ ትምህርት ቤቱን ለማስገንባት መሬት ተረክቧል፤ የሕንፃው ዲዛይን ሥራ እያሰራ ይገኛል፡፡ በቅርብ የዲዛይን ሥራው ተጠናቆ በ2012 ዓ.ም የግንባታ ሥራው ይጀመራል። ዩኒቨርሲቲው ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ለሚያሰራው የአዳሪ ትምህርት ቤት የሥርዓተ ትምህርት ጥናት አስጠንቶ መጨረሱን የገለጹት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ከዚህም በተጨማሪ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ዳያስፖራው ድጋፍ ለማድረግ ፍቃደኛ በመሆኑ ትምህርት ቤቱ ጠንካራና የተሻለ ሀገራዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

#የኦሮሞና #የሶማሌ ክልል ህዝቦች ሰላምና አብሮነት ከኢትዮጵያ አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሚናው የጎላ በመሆኑ ትስስሩን ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ የሁለቱ ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች ተናገሩ። የሁለቱ ክልል ህዝቦች ግንኙነትን መልሶ ለማጎልበት ያለመ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እየተካሄደ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

"ዛሬ በመስቀል አደባባይ በደማቅ ሁኔታ በተካሄደዉ 3ኛው ዙር የማስ ስፖርት መርሃ ግብር ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የማርሻለ አርት ክለብ አሠልጣኞች ተማሪዎቻቸዉን በማስተባበር በርካታ ደርዘን ደብተሮችን እና የተለያዩ የትምህርት መሳሪያዎችን አቅማቸዉ ለማይችሉ ተማሪዎች በስጦታ አስረክበዋል።" #አዩብ_ላዉጋለት/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

"#የሁላችንም የሆነች #ኢትዮጵያን ለመፍጠር ቀን ከሌት እንሰራለን" የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

"ወንድማማችነትን በማጠናከር የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ለኢትዮጵያ ዋልታና ማገር ለመሆን እንሰራለን" የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፌ_መሀመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

ኤልፓሶ ውስጥ 20 ሰዎች ሲገደሉ 26 ሰዎች ቆሰሉ!

በቴክሳሷ ከተማ ኤልፓሶ በጅምላ ተኩስ 20 ሰዎች ሲገደሉ 26 መቁሰላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ የከተማዋ ገዢ ግሪግ አቦት ሁኔታውን “በቴክሳስ ታሪክ አጅግ የተጎዳንበት ቀን” ብለውታል፡፡

ጥቃቱ የተፈፀመው ሲኤሎ ቪስታ ሞል አቅራቢያ የሚገኝ የገበያ ማእከል እቃ ማከማቻ ቦታ ላይ ሲሆን ከአሜሪካ ሜክሲኮ ድንበር ጥቂት ማይሎች ብቻ እንደሚርቅም ታውቋል፡፡ በግድያው የተጠረጠረው የ21 አመት ወጣት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ነዋሪነቱም በዳላስ አቅራቢያ የምትገኘው የአለን ከተማ ነዋሪ እንደሆነ ተገልጿል፣ አለን ከኤል ፓሶ 1ሺህ 46 ኪሎሜትር እርቀት ላይ እንድምትገኝም ዘገባው አመላክቷል፡፡

የአሜሪካን ሚዲያዎች ተጠርጣሪውን ፓትሪክ ክሩሰስ ተብሎ እንደሚጠራ ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድርጊቱን “የፈሪና የጨካኞች ተግባር” ሲሉ አውግዘውታል፡፡ “የዛሬውን የጥላቻ ድርጊት ከሃገሬ ዜጎች ጎን ሆኜ አወግዛለሁ፣ ንፁሃን ዜጎችን መግደል በምንም መልኩ በምክንያትም ሆነ በይቅርታ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም” ብለዋል በቲውተር ባስተላለፉት መልእክት፡፡

ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች እስካሁን በስም ያልታወቁ ሲሆን በአንፃሩ የሚክሲኮው ፕሬዝዳንት ማኑኤል ሎፔዝ ኦፕራዶር ከሟቾች ሶስቱ ሜክሲኳውያን መሆናቸውን ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ የአሁኑ ጥቃት በካሊፎርንያ የምግብ ፌስቲቫል ላይ በታዳጊ ታጣቂ የተፈፀመውንና ለሶስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ጥቃት ሳምንት ሳይሞላው የተፈፀመ እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡ የቴክሳሱ ጥቃት በዘመናዊዋ አሜሪካ ለስምንተኛ ጊዜ የተፈፀመ የጅምላ ተኩስ እንደሆነ ዘገባው ገልጿል፡፡

Via #BBC/#ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምክትል ከንቲባው ምስጋና~ለአዲስ አበቤዎች!

ክብረትና ጤና ይስጥልኝ፦

ዛሬ #በመስቀል_አደባባይ በነበረን ቆይታ እጅግ ደስ ብሎኛል። የሃሴቴ ምንጭ ለጋራ የጤና ጥበቃ እና የመንፈስ መታደስ የታደምነው አዲስአበቤዎች ቁጥራችን ብዙ ስለነበረ ብቻ አይደለም። በጋራ መቆማችን፣ የነበረን ፍቅርን እና ጨዋታ ነው ይበልጥ ያስደሰተኝ።

ሶስት ወራትን ያስቆጠረው የጋራ ስፖርት እንቅስቃሴያችን ካለምነው በላይ ህያው የሆነ ትሩፋት እያጎናፀፈን፣ ለቀጣዩ ወር ይዞት ለሚመጣው ድንቃድንቅ እያጓጓን መጥቷል።

ወንድም እህቶቼ፣ እርስ በእርስ ለመደጋገፍ እና ለጤናችን #መትጋታችንን እንቀጥል። ለሰርከስ፣ ለጂምናስቲክስ፣ ለማርሻል አርት ትርኢት አቅራቢዎች፣ ለጋራ ስፖርት አሰልጣኞች እነሆ የተለየ ምስጋና። #እንደሁሌውም ለምታኮሩኝ አስደናቂዎቹ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጤና እና ክብረት ይስጥልኝ።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CBE

ባንኩ ያጋጠመውን የ‹‹ሲስተም›› ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገጠመው ‹‹የሲስተም›› ችግር በሁለት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሊፈታ እንደሚችልም አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላለፉት ሁለት ቀናት የ‹‹ሲስተም›› ብልሽት አጋጥሞታል፡፡ በዚህም የተነሳ ደንበኞች ለእንግልት መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀገር በየወቅቱ እየተፈጠረ ባለው የ‹‹ኔት ወርክ›› እና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ባንኩ ለችግር እየተጋለጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ የአብሥራ ከበደ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ ይህም ደንበኞቹን ለእንግልት እየዳረገበት እንደሆነም ነው አቶ የአብሥራ ያስታወቁት፡፡

ለሁለት ቀናት በባንኩ ደንበኞች ላይ የተፈጠረው መጉላላት ምክንያቱ የ‹‹ሲስተም›› ብልሽ እንደሆነ የገለጹት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ችግሩ ከተከሠተበት ጊዜ ጀምሮ በፍጥነት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

ባንኩ በመላው ሀገሪቱ ከ 1ሺህ 450 በላይ ቅርንጫፎች አሉት ተብሏል፡፡ ደንበኞች በበዙ ቁጥር ችግሩ ስለሚኖር ይህንን የሚፈታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወደ ሥራ ለማስገባት በእቅድ እየተሠራ እንደሆነ ነው ባንኩ ለአብመድ ያስታወቀው፡፡ ችግሩ ዛሬ ወይም ነገ ሙሉ በሙሉ ሊፈታ እንደሚችልም አቶ የአብሥራ አስታውቀዋል፤ ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ደንበኞች ችግሩ እስኪፈታ #በትዕግሥት እንዲጠብቁም ባንኩ ጠይቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጠባቂዎቻቸው ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ ችግኝ ተክለዋል።

Via #fbc/#PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፡የግል ድርጅቶች፤ኤምባሲዎች እና በሚዲያ ተቋማት መካከል ሲደረግ የነበረውን ዓመታዊ የእግር ኳስ ውደድር በአሸናፊነት አጠናቀቀ፡፡ ኮሌጁ የ2011 ዓ/ም የዋንጫ ተሸለሚ ለመሆን የበቃው ባለፈው እሑድ በቢሾቱ ከተማ የተስፋ ድርጅትን 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፎ ነው።

Via Neway
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሕገ ወጥ መንገድ በቡድን ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮሚሽኑ ገለፀ፡፡ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በቡድን በሕገ ወጥ መንገድ የነበሩ ተጠርጣሪዎች፣ መሳሪያና ገንዘብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በዞኑ ጎዛምን ወረዳ ጭምት በተባለ ቀበሌ ሐምሌ 26/2011ዓ.ም ነው በሕገ ወጥ መንገድ በቡድን መሳሪያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 ሰዎችን እና ለጊዜው መጠኑ በግልፅ ያልታወቀ ‹‹ ከፍተኛ ገንዘብ›› በቁጥጥር ስር ማዋሉን በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽን እና ሚዲያ ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ አህመድ ለአብመድ የገለፁት።

ተጠርጣሪዎቹ 4 የጦር መሳሪያ ( ሁለት ክላሸንኮቭ፣ አንድ አብራራው እና አንድ መትረየስ) እና ቁጥሩ ለጊዜው በውል ያልታወቀ በርካታ ገንዘብ ይዘው መገኘታቸውንም ረዳት ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

በሕገ ወጥ መሳሪያው ምን ሊያደርጉበት ነበር? ስለሚለው ጉዳይ አሁንም ተጨማሪ ምርመራዎች እየተደረጉ መሆኑንም ረዳት ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። የኅብረተሰቡን ተደጋጋሚ የሰላም ይከበርልን ጥያቄ ለመመለስ በየደረጃው ያለ የክልሉ የፀጥታ ኃይል የክልሉን ሠላም እና ደኅንነት ለማስከበር በሰፊው እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አስታውቀዋል። ኅብረተሰቡም ትብብሩን እንዲያጠናክር ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ ጠይቀዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሱዳን

የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤትና የተቃውሞ መሪዎች አምባሳደር መሐመድ ድሪርን ጨምሮ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪዎች በተገኙበት የሽግግር መንግሥት የሚመሰረቱበትን ስምምነት ተፈራርመዋል። በነሐሴ 13 የሽግግር መንግሥቱ አባላት ይታወቃሉ።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ ዘንድሮ አሸንዳና ሻደይ በዓላትን በድምቀት ለማክበር መሰናዶዋን እያጠናቀቀች መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ፅ/ቤት አስታውቋል። ከሀገራችን በርካታ የባህል መገለጫ እሴቶች መካከል ተጠቃሽ የሆኑትን እነዚህን በዓላት በሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና አዲስ አበባ በልዩልዩ ዝግጅቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በድምቀትና በልዩ ድባብ ለማክበር የሚያስችል መርሃግብር ወጥቷል። በየዓመቱ በተለይም በትግራይና አማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን ልዩ ልዩ ባህላዊ ትውፊቶች የሚያጎሉት የሻደይና አሽንዳ በዓላት በዲስ አበባ ደረጃ በተናጠልና በጋራ ይከበራሉ። የሻድይ በዓል ነሃሴ 19 የእሸንዳ በዓል ደግሞ ነሃሴ 26 በመዲናዋ በልዩ ድምቀት ለማክበር መታቀዱን ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በተጨማሪም በዓላቱ የበለጠ ወንድማማችነትንና አብሮነትን በሚያጎለብቱ ዝግጅቶች በጋራ በአንድ ቀን በበለጠ ድምቀት ነሀሴ30 ይከበራሉ። አስተዳደሩ ከሻደይና አሸንዳ በተጨማሪ ሌሎች ታላላቅ የባህል እሴት ያላቸውን በዓላትም የሀገራችን ህዝብ እብሮነትና ትስስርን የበለጠ በሚያጠናክር መንገድ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና በተመሳሳይ ድምቀት ለማክበር አቅዷል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህብራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በ16 መስኮች የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቅ ፖሊሰዎችን ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።

የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ፥ ፖሊሲዎቹ ከ70 በላይ በሚሆኑ ምሁራን መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ምሁራኑ መንግስት እየተመራባቸው ያሉ ፖሊሲዎችን በዝርዝር እና በጥልቀት በመገምገም፤ የመጀመሪያ ደረጃ ሪቅቅ ፖሊሲ አዘጋጅተው አቅርበዋል።

በግብርና፣ ኢንደስትሪ፣ቱሪዝም፣ ትምህርት፣ የውጭ ጉዳይ፣ ንግድ እና ሌሎች መሰኮች ላይ በተዘጋጀው ሪቂቅ ፖሊሲ ላይም የፓርቲው አመራሮች ከምሁራኑ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ረቂቅ ፖሊሲው በፓርቲው አመራሮች እና በአዘጋጅ ምሁራን በዝርዝር ከተመከረበት በኋላ፤ በፓርቲው የተለያዩ መዋቅሮች ደረጃ ውይይት እንደሚካሄድበትም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ከፓርቲው አባላት ጋር ከሚደረግ ውይይ በኋላ ረቂቅ ፖሊስው ስልጣን ባለው የፓርቲው አካል ፀደቆ የኢዜማ የፖሊሲ ሰነድ እንደሚሆንም ተነግሯል።

የኢዜማ መሪ ፕሮፌስር ብርሃኑ የፖለሲ ዝግጅቱ የፓርቲው የምርጫ ዝግጅት አካል ይሆን ወይ ተብለው ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፥ ምርጫው በየትኛውም ጊዜ ይካሄድ ፓርቲው ፖሊሲዎችን የማዘገጃት ግዴታውን እየተወጣ ነው ብለዋል።

ሰለቀጠዩ ምርጫም በሰነዘሩት ሃሳብም የምርጫው ማከናወኛ ወቅት ከጊዜ ይልቅ በሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ቢወሰን የተሻለ ነው ብለዋል።

በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት መስፈኑ፣ ፓርቲዎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በነፃነት ለመንቀሳቀስ የሚችሉበት አውድ መኖር እና ምርጫ ቦርድ ትክክልኛ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ማረጋገጫ መስጠቱ፤ የምርጫውን መከወኛ ጊዜን የመወሰን አቅም እንዳለቻውም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia