TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር!

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት #ሳህለወርቅ_ዘውዴ በአሁን ሰዓት የቀይ መስቀልን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።

Via Mandefro Negash/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀረር

የምሥራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የጸጥታ ምክር ቤት የምክክርና የሰላም መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የአጎራባች ክልልች ተወካዮችና የጸጥታ አካላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቤኒሻንጉል_ጉምዝ

ለኢንቨስትመንት መሬት ከወሰዱና ከአላለሙ ባለሃብቶች በመንጠቅ ለአልሚ ባለሀብቶችና ለወጣቶች እንደሚሰጥ የቤኒሻንጉል ክልል ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ በጀመረው የ5ኛ 5 ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 9ኛ ጉባኤም የአስፈጻሚ አካላት ሪፖርት ሲገመግም እንደገለጸው፣ በተለይ የግብርናውንና የማዕድን ዘርፍ ስራዎችን ለመስራት መሬት ወስደው ያላለሙት ይነጠቃሉ፤ ለወጣቶችና ለአልሚ ባለሃብቶችም ይሰጣል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ታደሰ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ክልሉ የበርካታ ጸጋዎች ባለቤት እንደሆነ ጠቅሰው፤ በተለያዩ ዘርፎች ማልማት የሚፈልጉ ባለሃብቶች መሬት ተረክበው መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡

Via አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
/በአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/

#ScamPageAlert

ፌስቡክ ላይ "Adey Foreign Employment Agency" በሚል ስም ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎችን እየጠቀሰ ስራ እናስቀጥራለን፣ ቪዛ እናስገኛኛኘን እንዲሁም የመኖርያ ፈቃድ እናሰጣለን የሚል ገፅ አለ። ገፁ በሀሰት መረጃ ሰዎችን እያጭበረበረ እንደሆነ እንዲሁም የሚጠቅሳቸው የውጭ ኩባንያዎች እንዲህ የሚባል ድርጅት እንደማያውቁ ተደርሶበታል።

ጠንቀቅ እንበል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከADEY የተሰጠ ምላሽ፦

🏷እኛ #Adey_Foreign_Employment_Agency የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚያውቀውን #ህጋዊ ኤጀንሲ ነን፤ ማንኛውም ህጋዊነታችንን ማረጋገጥ የሚፈልግ ሰው የምንሰራበት ቦታ ድረስ መጥቶ ማረጋገጥ ይችላል፤ የተባለው ነገር ስህተት ነው ሊታረም ይገባል ሲሉ ለTIKVAH-ETH ተናግረዋል።

ይህንንም መረጃ አያይዘው ልከዋል፦

PHON:-+251-11-551-70-80 or +251-11-551-83-79
email:[email protected]
website:- www.mols.gov.et
Facebook:-Ministry of Labor and Social Affairs
Located in kirkos sub-city Wereda 8, Kazanchis

🏷ከአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በኩል የሚሰጥ ምላሽ ካለ ተከታትለን እናቀርባለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በ2011 የበጀት አመት አጠናቅቃቸዋለሁ ያላቸውን 11 ፕሮጀክቶች በጨረታ ሒደት መጓተትና በወሰን ማስከበር ችግሮች የተነሳ መጨረስ አለመቻሉን ተናገረ፡፡ በበጀት አመቱ 4 ቢሊዮን ብር ለወሰን ማስከበር ስራ ወጪ ማድረጉንም ተናግሯል፡፡

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ከተማዋ ሌሊት መተኛት የለባትም”-ዶ/ር #ሰለሞን_ኪዳኔ

#አዲስ_አበባ

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የተደረገው የትራንስፖርት ስርዓቱን ለማሳለጥ የወጣው መመሪያ ሌሊት ጭምር የስራ እድል እንዲፈጠር የሚያስችል በመሆኑ ‹‹ከተማዋ ሌሊት መተኛት የለባትም፡፡” ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪና የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ገለጹ፡፡

ኃላፊው ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በአዲስ አበባ ከተማ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ሊኖር የሚገባው ቀን ብቻ አይደለም፡፡ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ 24 ሰዓት ሊኖር ይገባል፤ አንዱ ሲተኛ ሌለው ወደ ስራ የሚገባበት ከተማ ልትሆን ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

‹‹አሁን ባለው ሁኔታ ከተማዋ ሌሊት የምትተኛ ነች›› ያሉት ዶክተር ሰለሞን ነገር ግን ከተማዋ ልትተኛ አይገባም፤ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በሰዓት የሚገድበው መመሪያም ከተማዋ እንዳትተኛና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር እንደሚያስችል አንስተዋል፡፡

Via አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakePage የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከህጋዊው የፌስቡክ ገፅ ውጪ የቴሌግራም ገፅ የለውም። የተለያዩ አካላት ሀሰተኛ ገፆችን በመክፈት ተማሪዎችንና የተማሪ ወላጆችን ሀሰተኛ መረጃ በማቀበል እያወዛገቡ ይገኛሉ። ስለሆነም ጥንቃቄ እድታደርጉ እንላለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጆችን ጨምሮ በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች እጃቸው አለበት የተባሉ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪዎቹ በእስር እና በምርመራ ወቅት «ዛቻና ማስፈራሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እየተፈጸሙብን ይገኛል» ሲሉም ለፍርድ ቤት አቤት ብለዋል።
.
.
የመርማሪ ፖሊስ ግለሰቦቹን በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ከሀምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በተከሰቱ ሁከቶች ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት ጠርጥሪያቸዋለሁ ሲል ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል።
.
.
ተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ ለመመስረትም የምስል ፣ የድምፅ እና የሰነድ ማሰረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ለችሎቱ ያስረዳው መርማሪ ፖሊስ «ቀሪ የምርመራ ሰራዎችን ለማካሄድ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠኝ» ሲልም ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Hawassa-08-01
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤት ገና ይፋ አልተደረገም!

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤት ገና ይፋ አለማድረጉን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። በአሁኑ ወቅት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ተለቋል በማለት እየተሰራጨ ያለው ወሬ የተሳሳተ መረጃ መሆኑን የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ረዲ ሺፋ ለኢቲቪ ገልፀዋል።

የ12ኛም ሆነ የ10ኛ ክፍል የፈተና ውጤት በሚለቀቅበት ወቅት ኤጀንሲው በፌስ ቡክ ገፁ እና በድረገፁ www.neaea.gov.et ይፋ የሚያደርግ መሆኑን አቶ ረዲ አመልክተዋል። የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ቀድመው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስለሚገቡና የተፈታኞቹ ቁጥር ከአስረኛ ክፍል ተፈታኞች ቁጥር አንፃር አነስተኛ በመሆኑ ውጤታቸውን ቀድሞ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በመሆኑም የብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የኤጀንሲውን ማህበራዊ ገጾች በማስመሰል ከሚለቀቁ የተለያዩ የተዛቡ መረጃዎች እንዳይወናበዱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በቢሯቸው በተፈጸመ #ጥቃት ቆስለው በወታደራዊ አውሮፕላን ለሕክምና ወደ ኳታር የተወሰዱት የሞቃዲሾ ከንቲባ አብዲራሕማን ኦማር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
.
.
የሞቃዲሾ ከንቲባ አብዲራሕማን ኦማር በቢሯቸው በተፈጸመ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት መቁሰላቸው ይታወሴ። በወቅቱ ጥቃቱ ሲፈጸም በከንቲባው ቢሮ በጸጥታ ጉዳይ ላይ ውይይት እየተደረገ አይዘነጋም።

Via #Eshete_Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለኬንያ ፓርላማ የተላከ ላፕቶፖ የያዘ ኮንቴይነር ባዶ ሆኖ ተገኘ!

#ቻይና ለኬንያ ፓርላማ ድጋፍ ያደረገቻቸው ላፕቶፕ የያዘው ኮንቴይነር ሲከፈት ባዶ ሆኖ ተገኝቷል። ኮንቴነሮቹ እንዴት ባዶ ሆነው ከቻይና ወደ ኬንያ ሊጫኑ እንደቻሉ ባለስልጣናትን ግራ አጋብቷል። የኬንያ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር ጆርጅ ኪኖቲ፣ “ኮንቴይነር ከቻይና ባዶውን ተጭኖ መላኩ ሊገባኝ አልቻለም” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አክለውም፣ ይህ አይነቱ ክስተት በኬንያ ሲፈጸም ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፤ ቢቢሲ/#ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በ2010 ዓ.ም በ55 መስሪያ ቤቶች ኦዲት ተደረጎ የተገኘ 257 ሚሊየን ብር በላይ የኦዲት ግኝት እንዳልሰበሰበ ተገለጸ፡፡ ሶስተኛ ቀኑን በያዘው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ የዛሬ ውሎ የክልሉን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አፈጻጸም ተመልክቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገንዘቡ ገቢ አልተደረገም...

ለተፈናቃዮች ማቋቋሚያ ቃል የገቡ አካላት በቃላቸው መሠረት ገንዘቡን ገቢ እንዲያደርጉ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጠየቀ፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም ቃል የተገባው ገንዘብ በተባለው መሠረት ገቢ አልተደረገም፡፡

በአማራ ክልል የሚገኙ ከ107 ሺህ በላይ ተፈናቀዮችን በመንግሥት አቅም ብቻ ማቋቋም እና በዘላቂነት ወደ ቀደመ ሕይወታቸው መመለስ አልተቻለም፡፡ በመሆኑም ኮሚቴ ተዋቅሮ መጋቢት 2011 ዓ.ም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል መዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡ መርሀ ግብሩ በአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር (አልማ) ከተዘጋጀ በኋላም ከአዲስ አበባ ውጭም በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሏል፡፡

በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ባለሀብቶች እና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች 720 ሚሊዮን ብር ለመርዳት ቃል ገብተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቃል ከተገባው ውስጥ በአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የባንክ ሒሳብ ቁጥር ገቢ የተደረገው 384 ሚሊዮን 151 ሺህ 812 ብር ብቻ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር እታገኘሁ አደመ ተናረዋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢቦላ

ሩዋንዳ ድንበሯን ዘጋች!

ሩዋንዳ በኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ገለጸ። ሩዋንዳ እርምጃውን የወሰደችው በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በምትገኘው የጎማ ከተማ ሦስተኛ የቫይረሱ ምልክት በመታየቱ ነው። ኪጋሊ የወሰደችው እርምጃ የዓለም የጤና ድርጅት ወደ ኮንጎ የሚደረግ ጉዞ ላይ ገደብ እንዳይጣል እና ከሀገሪቱ ጋር ያለው ድንበር እንዳይዘጋ ካቀረበው ጥሪ ጋር የሚጻረር ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ መገለጫ ሰጥተዋል!

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ከጥያቄዎቹም ከምርጫ ጋር የተያያዘው አንዱ ነበር።

በዚህም በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ይራዘም የሚሉ እና ወቅቱን ጠብቆ ይካሄድ የሚሉ የራሳቸው ምክንያት ያላቸው አካላት እንዳሉ አንስተዋል።

ነገር ግን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባው ምርጫ ከማካሄድ ጋር በተያያዘ በዝርዝር እንደተወያየበትና ምርጫው አይደረግም የሚል አቋም እንደሌለው አስታውቀዋል።

ኢህአዴግ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ለዚህም በቂ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም አያይዘው ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ ኢህአዴግ ምርጫው ይካሄድ የሚለው ላይ ብቻውን ውሳኔ ማሳለፍ አይችልም ያሉ ሲሆን፥ ሁሉን የፖለቲካ ፓርቲዎች በማሳተፍና በህዝቡ ይሁንታ የምርጫው ሁኔታ ላይ ከስምምነት በመድረስ እንደሚከናወንም አብራርተዋል።

ከዚህ ጋር አያይዘውም አዲስ የምርጫ ህግ እየተዘጋጀ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ህጉ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሚመለከታቸውን አካላት ባሳተፈ መልኩ መዘጋጀቱን አንስተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/PMO-08-01

Via #fbc
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በጋዜጣዊ መግለጫው ካነሷቸው ነጥቦች መሀል፦

/ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/

- ስለ ጄነራል ሰአረ መኮንን ገዳይ: ወታደሩ (ጠባቂው) አሁን በህክምና ላይ ይገኛል፣ አንገቱ ላይ ቆስሏል። ከሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ተይዘዋል። ጥቃቱ የተፈፀመ ቅፅበት "(ጥቃቱ ሲፈፀም) ደውለህ ትነግረኛለህ" ብሎ ነገሮት በሁዋላ ደውሎ የነገረው ተይዟል።

- የሰኔ 15ቱን ሁኔታ አቅልሎ ማየት ልክ አይደለም። እንቅስቃሴ ሲደረግ የነበረው ተጨማሪ ጀነራሎችን ጭምር ለመግደል እንደነበር መረጃ ደርሶናል።

- እኔ በፊት የተለየ የህዝብ ተቀባይነት የነበረኝ፣ አሁን ደሞ የተለየ ተቀባይነት የሌለኝ ነበርኩ ብዬ አላስብም። ተቀባይነቱ ቀነሰ የሚሉ ምን መረጃ ኖሯቸው እንደሆነ አላውቅም።

- የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ገንዘብ አሰባሰብ እኔን ከመደገፍ እና ካለመደገፍ ጋር መያያዝ የለበትም። ሆኖም ከነበረ መሆን አልነበረበትም።

- በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙርያ: አሁን ጭለማ ቤት ታስሮ ያለ የለም፣ ሰው አይገረፍም፣ ጥፍር አይነቀልም።

-ምርጫ: በኢህአዴግ ዘንድ ምርጫው አይደረግ የሚል አንድምታ የለም። ምርጫው ይካሄዳል ብለን እየተዘጋጀን ነው።

- ኢንተርኔት መዘጋት: መዘጋቱ ያስፈለገው የሰዎችን ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ ነው። ኢንተርኔት ውሀ ወይም አየር አይደለም። ለመዝጋት ምክንያት የሆኑንን ምክንያቶች ካልፈታን ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው ሊዘጋ ይችላል።

- አሜሪካ ኤምባሲ ለፕሬዝደንት ፅህፈት ቤትነት ተገንብቶ የነበረው ህንፃ ለሰላም እና እርቅ ኮሚሽን ቢሮ ሆኗል። መከላከያ ትልቅ እና ውብ ህንፃ እየገነባ ነው፣ በቅርቡ ይጠናቀቃል። INSAም የራሱን ህንፃ ቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ እየሰራ ነው። ሁሉንም በመጪው አመት ለመጨረስ ታስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዶክተር_አብይ_አህመድ

የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ፦

#PMO የሲዳማ ዞን የክልልነት #ጥያቄን በተመለከተ፤ ክልል የመሆን ጥያቄው ለረጅም ዓመታት የነበረ መሆኑን እና ከለውጡ በኋላ ጎልቶ መውጣቱን አንስተዋል። የክልልነት ጥያቄው ከፖለቲካ በተጨማሪ #የሀብት_ክፍፍል እና ህጋዊ ሂደቶች ያስፈልጉታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ የክልልነት ጥያቄውን መሰረት በማድረግ ህዝበ ውሳኔው ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚከናወንም አስገንዝበዋል። #fbc

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ የቤት ልማት መርሃግብር ሊጀምር ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የቤት ልማት መርሃግብር ወደ ስራ ሊገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለጸ፡፡ አስተዳደሩ ለቤት ልማት መርሃግብሩ 1500 ሄክታር መሬት ማዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ገልጸዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የግሉን ዘርፍ ለማሳተፍም ዝግጅቶች መጠናቀቁም ተገልጿል፡፡

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የ2012 በጀትን 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር አድርጎ አጽድቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢህአዴግ ውህደት የማይቀር ነው!

የኢህአዴግ ውሕደት የማይቀር መሆኑን የግንባሩ ሊቀመንበር ተናገሩ፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) ከጋዜጠኞች ጋር ዛሬ በነበራቸው ቆይታ የተለያዩ ሐሳቦችን አንስተዋል፡፡

በቅርቡ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ስለተስተዋለው የመግለጫ መልልስ ሐሳብ የሰጡት የግንባሩ ሊቀ መንበር ‹‹የኢህአዴግ ድርጅቶች የየራሳቸው ፍላጎት አላቸው፤ ያለሌሎች ድርጅቶች ድጋፍ ግን ፍላጎታቸውን ማሳካት አይችሉም›› ብለዋል፡፡

ህወኃት እና አዴፓ በቅርቡ በመግለጫ ምልልስ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የተንጸባረቀን ልዩነት በተመለከተም ‹‹ሁለቱ እህት ድርጅቶች በልዩነታቸው ዙሪያ በኢህዴግ ጉባኤ መድረክ ላይ እንዲነጋገሩ ይደረጋል፤ በእህት ድርጅች መካከል ልዩነት ቢታይም በኢህአዴግ ውሕደት ሐሳቡ ላይ ግን ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፤ ውሕደቱም አይቀሬ ነው›› ብለዋል፡፡

‹‹ኢህአዴግ እንደፓርቲ በውስጡ ብዙ የሐሳብ ልዩነቶች አሉበት፤ ይህንን ለመፍታትም ነው በየጊዜው ሰዎች እየተቀያዬሩ ያሉት፤ የውስጥን ችግር ለመፍታት እየሠራን ነው›› ብለዋል ሊቀመንበሩ፡፡ መገናኛ ብዙኃኑም የትኛው ተቋም ጥሩ ይሠራል የትኛው ተቋም ጥሩ አይሠራም እያሉ የተቋማትን ስኬትና ውድቀት ማጋለጥ ይኖርባዋል ነው ያሉት፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia