TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አንዋር_መስጂድ

"በትላንትናው እለት በአንዋር መስጂድ ሀጂ ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍትሂ ባሉበት የአንዋር መስጂድ ኢማም ሸህ ጠሀ ባሉበት የችግኝ የከላ ተፈፅሙዋል!" ሱሌማን/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASTU የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች እና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። #አዳማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮኮሳ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። #ኦሮሚያ #ኢትዮጵያ
#ደሴ "ወገኔ በጎ አድራጎት" አባላት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፍኖተ_ሰላም የምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሠላም ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና የፀጥታ ኃይል አባላት በጋራ በመሆን ችግኝ እየተከሉ ነው። በፍኖተ ሠላም ከተማ ዛሬ ብቻ 45 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉ ይጠበቃል፡፡
#ቢሾፍቱ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሣ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን አስጀምረዋል፡፡ በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም በርካታ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎችም ይህን መርሃ ግብር በማስኬድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁለት መቶ ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር የመትከል ፕሮግራም በመላው ሀገሪቱ እየተካሄደ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ በትግራይ ክልል እንደርታ ወረዳ እንዳባሸለማ በሚባል ስፍራ የትግራይ ክልል ምክትል ርእስ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የችግኝ ተከላ እየተከናወነ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ የጋምቤላ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ ቀን ዛሬ የችግኝ ተከላ አካሄዱ። በችግኝ ተከላው መርሐ ግብር ላይ በውጭ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆችም ተሳትፈዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ #ከፍተኛ_ጥንቃቄ_ይደረግ

ፌስታሉን ካልሰበሰብነዉና ካላነሳነዉ ሌላ ዘመቻ ያስፈልገናል 200 ሚሊዮን ፌስታል ለመልቀም ~ የሚተክል ያስተዉል፤ ጉዳዩ ጥንቃቄ ያሻዋል!!

#ሼር #share

Via #ዝንቅ_መዝናኛ
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ -- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን #አብራሪዎችና #ቴክኒሻኖች ለአረንጓዴ አሻራ ወደ አድዋ ፓርክ እየተጓዙ ይገኛሉ!

ፎቶ: Sh/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የአረንጓዴ_አሻራ_በደቡብ_ክልል

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ የሚገኙት #የደኢህዴን ከፍተኛ አመራር አባላት በዛሬው እለት የአረንጓዴ አሻራ አካል በመሆን በሃዋሳ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡
#ሀዋሳ

"ሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ PVHAM ካምፓኒ ተክለን ወደ ስራችን ተመልሰናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በመገኘት የችግኝ ተከላ ስራ አስጀመሩ፡፡ ፕሬዚዳንቷ የችግኝ ተከላውን ያስጀመሩት በወረዳዋ በምትገኘው ምንዝሮ ቀበሌ በመገኘት ነው። በችግኝ ተከላው ፕሮግራም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በስፍራው በመገኘት አብረው እየተሳተፉ ነው፡፡
#አረንጓዴአሻራ

የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በከተማዋ ሁሉም ክፍሎች በድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ለረዥም ጊዜያት በከተማዋ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ በቆየው በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ችግኝ ተክለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአረንጓዴ አሻራ ቀን በወላይታ ሶዶ ችግኝ ተክለዋል። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና አምባሳደር ተሾመ ቶጋን ጨምሮ፥ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞኑ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በሶዶ ከተማ ስምንት ችግኝ መትከያ ቦታዎች የተለዩ ሲሆን፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንደኛው በመገኘት ችግኝ ተክለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶዶ ስታዲየም በመገኘት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለሚመለከተው_አካል

ጥቂት በማይባሉ አካባቢዎች ነዋሪዎች ችግኝ ለመትከል እና አሻራቸውን ለማኖር ከፍተኛ ተነሳሽነትን ቢያሳዩም "ችግኝ የለም፣ ችግኝ አልቋል" የሚሉ ምላሾች እየተሰጡ ነው። በሀገር አቀፍ ደረጃ ይህን መርሃ ግብር የሚያስተባብረው አካል ጉዩን ይመልከተው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ የሀበሻ ስቲል ፒሌሲ የችግኝ ተከላ ተካሂዷል። "Guyya Ashaaraa Magarisumma"
#አዳማ የአዋሽ ባንክ አዳማ ሪጅን ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሰራተኞች በባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በቡሬ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።