TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መቐለ

ሁለተኛ ዙር አለም አቀፍ የትግራይ ተወላጅ ምሁራን ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ ተጀመረ። “ቀጣይነት ያለው #እውቀት መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚና ማህበረሰብ መገንባት”በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ኮንፍረንሱ በአምስት ቀናት ቆይታው አምና ተመርጠው ጥናት በተካሄደባቸው ዘርፎች ዙሪያ ውይይት ያደርጋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 1 ሺህ 63 ተማሪዎች ትላንት አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 206ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ተገኝተው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ሐራቤ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት አሰመርቋል። በምርቃ ስነስርዓት ወቅትየኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ገላና ወልደሚካኤል በክብር እንግድነት ተገኝተው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ቤቴል ሚዲካል ኮሌጅ በጤና ዘርፍ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን 107 ተማሪዎች አስመረቀ። ቤቴል ሚዲካል ኮሌጅ በክሊኒካል ነርስ 20፣ በጤና መኮንነት 21 እንዲሁም በህክምና ዶክተርነት 66 በአጠቃላይ 107 ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።

@tsegabwolde @tikvahethipia
#fanaTv ቀን በነበረው የቀጥታ ስርጭት በፋና ቴሌቪዥን መከታተል ያልቻላችሁ #በድጋሜ ከጥቂት ደቂቃ በኃላ ይተላለፋል መከታተል ትችላላችሁ! እንኳን አደረሰን በድጋሚ!!

#ሁለተኛው_ዓመት የTIKVAH-ETH ምስረታ በዓል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ችግኝን እንዴት መትከል እና መንከባከብ አለብን?

#ሼር #share

ነገ ሐምሌ 22 /2011 በሐገር ዓቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ውስጥ እንገኛለን፡፡ ሆኖም ከመትከል ባለፈ ዘመቻው ውጤት ያመጣ ዘንድ ችግኞቹን በአግባቡ መትከል እና መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡

ለዚህ ይረዳ ዘንድ ተከታዮቹን ተግባራት በቅደም ተከተል ማከናወን አለብን፡-

• በመጀመሪያ ችግኞቹን የምንተክልበት ጉድጓድ ውስጥ እንደ ድንጋይ እንጨት፣ ቅጠል እና ውሃ ያሉ ባዕድ ነገሮች ካሉ ማውጣት አለብን፤

• ከጉድጓዱ ተቆፍሮ የወጣውን አፈር ከችግኙ ስሮች ይጣጣም ዘንድ እስከ ጉድጓዱ አጋማሽ ድረስ መልሶ መሙላት ይገባል፤

• በመቀጠልም ችግኙ ላይ ያለውን ፕላስቴክ አፈሩ ሳይፈስብን በጥንቃቄ በመላጥ ችግኙን እስከ ግንዱ መጀመሪያ ድረስ በጉድጓዱ ማኖር፤

• ችግኞቹ ተጣመው እንዳይቆሙ በመጠንቀቅ ተቆፍሮ የወጣውን አፈር በፕላስቲክ ተሸፍኖ በነበረው አካል ዙሪያው ጠቅጥቆ መሙላት

• ከተተከለ በኋላ ውሃ በመጠኑ ማጠጣት (በተለይም አፈሩ ደረቅ ከሆነ)

• ችግኝ ተሸፍኖባቸው የቆዩትን ፕላስቲኮች በመሰብሰብ በተገቢ ሁኔታ ማስወገድ

በችግኝ ተከላ ወቅት የሚስተዋሉና መቅረፍ የሚገባን ተደጋጋሚ ስህተቶች፦

• ችግኝን ከነፕላስቲኩ መትከል

• የችግኙ ስር አንዲታይ አድርጎ መትከል

• የችግኙን ግንድና ቅጠል ጭምር በጉርጓዱ መቅበር

• አፈሩን በትክክል አለመሙላት እና አለመጠቅጠቅ

• ችግኙን ሳይተክሉ በጉድጓድ ውስጥ አስቀምጦ ብቻ መሄድ

• አጣሞ መትከል

• ከአንድ በላይ ችግኝ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ መትከል

• የችግኙን ስር አጣሞ መትከል

• በውሃ በተሞላ ጉድጓድ ውስጥ መትከል
ችግኞችንስ ዕንዴት እንከባከብ?
እንደየ ዝርያ፣ የተተከሉበት አካባቢ እና ወቅት ቢለያይም ችግኞች እስከ ሶስት ዓመታት ድረስ ልዩ እንክብካቤን ይሻሉ፡፡

በዚህም መሰረት፦

• ከተተከሉበት ዕለት አንስቶ ችግኞቹን ከሰውና እንስሳት ንክኪ መጠበቅ (ከተቻለ ማጠር)፣ በዙሪያቸው ያለውን አረም፣ ደረቅ ሳር ወዘተ…ማንሳትና ከእሳት መጠበቅ እንዲሁም ከተባይና ነፍሳት ጥቃት በመታደግ ጥበቃ ማድረግ፤

• ብርሃን፣ ውሃና ንጥረ ነገሮችን ስለሚሻሟቸውና ለተባይ መራቢያ ስለሚሆኑ በዙሪያቸው ያለውን አረም ችግኞቹ ከተተከሉ ከሁለተኛው ሳምንት ጀምሮ በተከታታይ ማንሳት፤

• የሞቱ ችግኞች ካሉ ለይቶ መተካት፤

• ከክረምቱ ማብቂያ አንስቶ መኮትኮት፤

• የተተከሉበት አፈር ለምነት የጎደለው ሊሆን ስለሚችል ጉዝጓዝ፣ ቀልዝ፣ ፍግ ወይም ማዳበሪያ ከበጋው ወቅት ጅማሮ አንስቶ ማድረግ

• በበጋው ወቅት ሲገባ ወይም የተተከሉት እርጥበት አጠር ቦታ ሲሆን ውሃ ማጠጣት፤

• ቅርንጫፎችን መመልመልና ማሳሳት

(ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት)

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ #የኢንተርኔት_አገልግሎት_መስራት_ጀምሯል

ከሳምንት በላይ ለሚሆን ጊዜ በሀዋሳ ከተማና ዙሪያዋ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ መስራት ጀምሯል።
#አርብ_ምንጭ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተሳተፉ ነው። በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ200 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዝግጅቱ ተጠናቆ ዜጎች በየአቅራቢያቸው የዛፍ ችግኞችን በመትከል ላይ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተሳትፈዋል፡፡ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ በመላ አገሪቱ እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ #የኢንተርኔት_አገልግሎት_መስራት_ጀምሯል

ከሳምንት በላይ ለሚሆን ጊዜ በሀዋሳ ከተማና ዙሪያዋ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ መስራት ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አርብ_ምንጭ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተሳተፉ ነው። በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ200 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዝግጅቱ ተጠናቆ ዜጎች በየአቅራቢያቸው የዛፍ ችግኞችን በመትከል ላይ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተሳትፈዋል፡፡ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ በመላ አገሪቱ እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አርባ_ምንጭ

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አርባምንጭ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። #PMO #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አርባ_ምንጭ

ዛሬ ሐምሌ 22፣ 2011 ዓ.ም 200 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ኃገር አቀፍ ፕሮግራም ተጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም በአርባ ምንጭ ተገኝተው ችግኞችን ተክለዋል። ይህ አረንጓዴ አሻራን እንተው የሚል ዓላማን ያነገበው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ማህበራዊ ምርታማነትን ለመጨመር፤ ተጋላጭነት ለመቋቋም ያለመ ነው።

Via #bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ "መልካም ወጣት" ለችግኝ ተከላ ወደ ታቦር ተራራ እየተጓዙ ናቸው።
Channel photo updated
#መቐለ

"ዘመቻ መለስ ለአረንጓዴ ልማት" በሚል መሪ ቃል ከ80 ሚልዮን ችግኝ በላይ በዚህ የክረምት ወቅት ለመትከል የታቀደ ሲሆን እስከ ትናንት ድረስ 30ሚልየን ችግኞች ተተክለዋል። በዛሬው እለት በትግራይ #መቐለ ከተማ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ አመራሮች፣ የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ አባላት ፣የክሉሉ የፀጥታ ሀይል አባላት፣ ከተለያዩ የክልል ቢሮዎች የተውጣጡ የመንግስት ሰራተኞች እና ነዋሪዎች በተገኙበት ችግኝ ተከላ ተካሂዷል። ዛሬ ሀምሌ 22 /2011 በክልል ደረጃ 9 ሚልየን ችግኞች እንደሚተከሉ ታውቋል።

Via Tigray Express
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ - ዘፀአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተ ክርስቲያን

ፎቶ፦ ኤልያስ ዱካሞ/TIKVAH-ETH/
የራይድ አሽከርካሪዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር #Ride