TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60.9K photos
1.54K videos
215 files
4.23K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀገረሰላም

በሲዳማ ዞን ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ የሁላ ሀገረሰላም ወረዳ ነዋሪዎች በአዲስአበባና ሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች 200 ሺህ ብር ግምት ያላቸው የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡ የአካባቢው ተወላጆች በወረዳው አስተዳደር ቅጥር ግቢ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖችን በመጎብኘት 20 ኩንታል ዱቄትና አልባሳት አበርክተዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አዮ ጓጉሳ ወረዳ በሚገኘው አዮ ወንዝ ላይ ሲገነባ የነበረው ድልድይ ተጠናቆ ተመረቀ፡፡ በምረቃ ሥነ ሥረዓቱ የአማራ ክልል መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈንታ አዋየው እና ሌሎች የብሔረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA

ኦሮሞ ስተዲስ አሶስዬሽን(ኦሳ) [የኦሮሞ ጥናት ማህበር] 33ኛው ጉባኤ ዛሬ ለ3ኛ ቀን በአዲስ አበባ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።

Photo: OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA #ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የኦሮሞ ጥናት ማህበር ጉባኤ ላይ (ኦሳ) ዛሬ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ማህበሩ ማዕከሉን አዲስ አበባ ላይ እንዲያደርግና ከዚህ በኋላ ዝግጅቱን ለማካሄድ ወደ ባዕድ ሃገር መመልከት የለበትም ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ #BBC👇
https://telegra.ph/OSA-07-28
#2ተኛ_አመት 🎂 በአሁን ሰዓት በአበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት እየተከናወነ በሚገኘው ዝግጅት ላይ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ፣ ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ፣ ዶክተር ኤልያስ ገብሩ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ደግሞ ወ/ሮ ፂዮን ቤተሰቡን ተቀላቅለው ቀኑን እያከበሩ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዘፈቀደ የሚተገበረው የታክሲ ታሪፍ፦

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት መጨናነቅና እጥረት መኖሩ ታክሲዎች በዘፈቀደ እንዲያስከፍሉ ምክንያት ከሆነ ሰንብቷል፡፡ በአብዛኛዎቹ የትራንስፖርት ቦታዎች ላይ የሚታዩ የተለያዩ ችግሮችን ተቋቁመው አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጋፉ ሰዎችም ለስርቆት ሲዳረጉ ማየቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

በአገሪቱ የሚታዩ ክፍተቶችን በመጠቀም ዋጋ መጨመርና ኅብረተሰቡን ማማረር የተለመደ ከሆነባቸው ዘርፎች አንዱ ትራንስፖርት ነው፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ከሜክሲኮ ዓለም ባንክ ለመሄድ ተሠልፈው ያገኘናቸው አቶ ኬራሚድ ሙራድ፣ በተለያዩ ቦታዎች መሄድ የሚፈልጉ ተሳፋሪዎችን እንግልት በመመልከት፣ መንግሥት ካወጣው ታሪፍ በላይ በመጠየቅ ተሳፋሪውን አማራጭ የሚያሰጡ፣ በኑሮ ውድነት ላይ ሰውን የሚያማርሩ የታክሲ ትራንስፖርት ሰጪዎች መበራከታቸውን ይገልጻሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ #ሪፖርተር_ጋዜጣ👇
https://telegra.ph/AA-07-28-3
ችግኝ የሚተከልባቸው ቦታዎች👆

የተከበራችሁ የአ/አ ከተማ ነዋሪዎች ከላይ በተገለፁት ቦታዎች ነገ ሃምሌ 22 አረንጓዴ አሻራችሁን እንድታሳርፉ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ጥሪውን አቅርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EthioTelecom በሃገርአቀፍ ደረጃ ችግኞች ለመትከል ዝግጅቱንአጠናቋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ለመትከል ከታቀደው 3 ሚሊዮንችግኞች 1 ሚሊዮኑ በኢትዮ ቴሌኮም የሚተከሉበመሆኑ ለመትከያ የሚሆን የጉድጓድ ቁፋሮ እና የችግኝ አቅርቦት ስራዎችን አጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀረሪ

በሀረሪ ክልል ለሚካሄደው አረንጓዴ የአሻራ ቀን ለሚተከሉ ችግኞች አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሐብት ቢሮ አስተውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ከአጋሮ

"የአጋሮ ከተማ public service ሰራተኞች ለነገው የአረንጓዴ አሻራ ቀን በሚገባ የተዘጋጀን ሲሆን ነገ ማለዳ 2:30 አጋሮ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘ ቢሮ መነሻ በማድረግ የከተማው የሙስሊም መቃብር አካባቢ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ ቦታ ላይ ቢያንስ 40 ችግኝ ለመትከል ሀምሌ 22ትን ብቻ እየጠበቅን ነው።" #FAZ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አረንጓዴ አሻራችንን በትላንትናው ዕለት አሳርፈናል ብለዋል። #ASTU


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ‹የአረንጓዴ አሻራ› ችግኝ ተከላ ቅድመ-ዝግጅት በስኬት መጠናቀቁ ተሰምቷል። በነገው ዕለት 50ሺህ የሚጠጋ ችግኞችን ለማስተከል እንደታቀደ ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅማ_ዞን_ቤተሰቦች

"በጅማ ዞን ኦሞ ናዳ ወረዳ ለነገው ኣርንጓዴ አሻራ ለማሳረፍ ለነገው ችግኝ ተከላ ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል። ጉድጓዶች ተዘጋጅተዋል።" #AJ

@tsegabwolde @tikvahethipa
በሕግ ሥልጣን ያልተሰጠው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ሕገወጥ መሆኑ ተጠቅሶ፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ነፃ ለማውጣት (Habeaus Corpus) ለፍርድ ቤት የቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል፡፡ በሽብር ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩት የአብን የሕዝብ ግንኙነትና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በአራት ተጠርጣሪዎች ላይ የተጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ 28 ቀናት ተፈቀደ፡፡

ተጨማሪ የሪፖርተርን ዘገባ ያንብቡ👇
### https://telegra.ph/A-07-28
#ከፍቼ_ቤተሰቦች

"ፍቼ ሰላሌ~ፍቼ ከተማ አስተዳደር ለነገው የአረንጓዴ አሻራ ቀን ተገቢውን ዝግጅት ጨርሷል። 400,000 ችግኞችን ለመትከልም ታቅዷል።" #አድማሱ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ከወሊሶ_ቤተሰቦች

"በወሊሶ ከተማ በነገው ዕለት የሀምሌ 22/2011 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራን የማስቀመጥ ቀንን በማስመልከት በከተማዋ በተመረጡ ቦታዎች #ከ50 ሺህ በላይ ችግኞች እንደሚተከሉና ህብረተሰቡም #በንቃት እንዲሳተፍ የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ጥሪውን እያስተላለፈ ይገኛል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጎንደር

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት ጎንደር ከተማ ገቡ፡፡ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ #ተመስገን_ጥሩነህ ጋር በአፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባብል ተደርጎላቸዋል፡፡ በቆይታቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የችግኝ ተከላና የሚሳተፉ ሲሆን የፋሲለደስ ግንብንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia