TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

ደኢህዴን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሲዳማ እና የሀድያ ዞን ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነት አገደ። የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ ነው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎቹ ከስራ መታገዳቸውን ያስታወቀው።

ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማና እና በሲዳማ ዞን የገጠር አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት የራሳቸው ሚና ነበራቸው በሚል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ዞን አመራሮች ከስራ መታገዳቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።

የሃድያ ዞንም ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች በመስተዋላቸው የማገድ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ደኢህዴን አስታውቋል።
ደኢህዴን በተጨማሪም በከፋ እና በወላይታ ዞኖች ተመሳሳይ ድርጊቶችም እየተስተዋሉ መሆኑን በመጥቀስ፥ የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ናቸው ሲል አሳስቧል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
'አረንጓዴ አሻራ እናሳርፍ በአንድ ጀምበር 200 ሚሊየን ችግኝ እንትከል!' በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ የዋዜማ መርሃ-ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንገግር ያደረጉት ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ ለሚቀጥለው ትውልድ የተሻለ ከተማን ለማስተላለፍ ሁሉም በሚኖርበት አከባቢ በነቂስ ወጥቶ ችግኝ እንዲተክል ጥሪ አስተላልፈዋል።

በዛሬው እለት በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ ከአራቱም የከተማዋ ቴአትር ቤቶች የተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች፣ የታክሲ ባለቤቶች፣ የከተማው ወጣቶች እና ሌሎችም ተሳታፊ ሆነዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነአቶ በረከት ስምዖን የክስ መዝገብ ሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት የክስ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ በቀጠሮው መሠረትም ዛሬ ጉዳዩን ተመልክቷል፡፡

የፍርድ ቤቱ የሥራ ቋንቋ አማርኛ ሆኖ እያለ አብዛኛው የዐቃቤ ህግ የክስ ማስረጃ የቀረበው በእንግሊዝኛ ቋንቋ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ መረጃውን መመርምር አልቻለም ተብሏል፡፡ ስለሆነም ዐቃቤ ህግ መረጃው በአማርኛ አስተርጉሞ ለመስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲያቀርብለት ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

Via #AMMA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
የአማራ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ለመጪዉ ዓመት ለክልሉ የ47.4 ቢሊዮን ብር በጀት አፀደቀ። አራተኛ ቀኑን የያዘዉ የምክር ቤቱ 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ጠዋት ያፀደቀዉ በጀት ከቀዳሚዉ በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ3.8 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አለዉ።

በሌላ በኩል...

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጀት #እንዲጸድቅ ያቀረበውን 971 ሚሊዮይ 632 ሺህ 330 ብር ምክር ቤቱ አጽድቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው!

"በመቐለ ያሉ ሁሉም #የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንኮች ሆነ ኤቲኤሞች እየሰሩ ኣይደለም" ይህ መልዕክት ከመቐለ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰቦች የተላከ ነው። በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ ቤተሰቦቻችን እንደሰማነው "ሲስተም የለም" በሚል የባንክ አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ ነግረውናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹የክልልነት ጥያቄው ወደ ግጭት እንዲያመራ የሚፈልጉ ኃይሎች አሉ››- ፕሮፌሰር #ሕዝቅኤል_ገቢሳ
.
.
ለእኔ ኢህአዴግ ኢህአዴግ ነው። አስተሳሰቡም፣አሰራሩም፣ አደረጃጀቱም አሁንም ቢሆን ከበፊቱ ተለውጦ አላየሁትም።

እኔ ህገ መንግስቱ መሻሻል የለበትም የሚል አቋም የለኝም። ህገ መንግስቱ እራሱ መሻሻል እንደሚገባው መብት ይሰጣል።

ክልሎች ፕሬዚዳንት አላቸው፣ ህገ መንግስት አላቸው፣ ባንዲራ አላቸው፣ ፓርላማ አላቸው፣ ቢሮክራሲ አላቸው፣ ብሄራዊ መዝሙር አላቸው።ስለዚህ ክልሎች ሀገር ለመሆን የቀራቸው ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘት ብቻ ነው።

መብትን ቀምቶ የተደራጀን ነገር አፍርሶ 70 ዓመት ወደኋላ መውሰድ አይቻልም ነው ያልኩት። እኔ የገለጽኩት ትክክለኛ ሀሳብ ይሄ ሆኖ ሳለ ሰዎች ሀሳቤን ካለመረዳት ሳይሆን ሆነ ብለው በመጠምዘዝ ሌላ አቅጣጫ አስይዘውታል።

እኔ የኩሽን ህዝብ አላቋቁምም። ኢትዮጵያ ውስጥ 75 በመቶ የሚደርሱት ህዝቦች የኩሽ ውልደት ያላቸው ናቸው። እነዚህ የባህልና የቋንቋ ግንኙነት ስላላቸው ህብረት ቢኖራቸውና ቢጠናከሩ ሀገሪቱም ልትጠናከር ትችላላች የሚል አስተሳሰብ አሁንም አለኝ።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጅማ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ...

"የንግድ ባንክ ሲስተም ችግር #መቐለ ብቻ ሳይሆን #ጅማ ከተማም #ተመሳሳይ ነበር። ግን አሁን 7:30 ሲስተም መስራት ጀምሯል።" /Yr ከጅማ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወ/ሮ #ሙፈሪያት_ከሚል

"በሰላም ሚኒስትር እና የደህዴን ሊቀመንበሯ ሙፈርያት ካሚል ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ" ተብሎ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ እውነትነት የራቀ መሆኑ የሰላም ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ሄርሜላ ሰለሞን ለአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናገሩ። ዳይሬክተሯ ወሬውን ለማጣራት ወ/ሮ ሙፈርያት ጋር ከደወሉ በሁዋላ ይህንን ብለዋል፦

"ሚኒስትሯ ቀኑን ሙሉ ሀዋሳ ስብሰባ ላይ ነው የዋሉት። እንኳን ሙከራ ሊደረግ ለመሞከር እድል የሚኖርበት ሁኔታ አልነበረም። ለማንኛውም የተባለው ሙሉ ለሙሉ #ውሸት ነው ብለው ሚኒስትሯ እራሳቸው አሁን በስልክ ነግረውኛል። ምንም የተለየ ነገር አልተፈጠረም።"

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የክልሉ ባለስልጣን መረጃው ፌክ ኒውስ ነው ሲሉ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethuopia
የቱኒዝያ ፕሬዘዳንት አረፉ!

የቱኒዝያ ፕሬዘዳንት ቤጂ ካይድ ኤስቢሲ በ92 ኣመታቸው ማረፋቸውን የሀገሪቱ የፕሬዘዳንት ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠው ወደ ስልጣን የመጡት ኤስቢሲ በገጠማቸው የጤና እክል ሳቢያ ሆስፒታል ከገቡ አንድ ወር አስቆጥረዋል፡፡

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2014 ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዚዳንቱ ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ቆይተው የነበሩትንና በአረብ አብዮት እኤአ በ2011 ከስልጣን የተወገዱትን ዘይን ኤል አቢንዲን ቤን አሊን በመተካት ነው።

Via አልጄዚራ/ENA/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴአሻራ
#ሐምሌ22እንገናኝ

ሐምሌ 22 ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የከተማ አስተዳደሩ ባደረጋቸው ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ የከንቲባ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክረቴሪያት ወ/ት ፌቨን ተሾመ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ወ/ት ፌቨን በመግለጫቸው ፦

✿ የቦታ ልየታን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ፤

✿ በከተማዋ ባሉ 116 ወረዳዎች ወጣቶችን በማሳተፍ 2.8 ሚሊየን ጉድጓድ ቁፋሮ መደረጉን ፤

✿ በዕለቱ 400 በላይ የመትከያ ሳይቶች መዘጋጀታቸውን ፤

✿ በከተማዋ ያሉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የሚሳተፍበት ቦታ ተዘጋጅቷል ፤

✿ በዕለቱ 100ሺ የሚሆኑ ወጣቶች ዝግጅቱን ለማስተባበር መዘጋጀታቸውን ፤

✿ በዕለቱ የሚሰሩ ስራዎችን የሚመራ ግብረ ሃይል መቋቋሙን በመግለጫቸው ጠቅሰዋል፡፡

ስለዚህ በአራዳ ክ/ከተማ ፣ ልደታ ክ/ከተማ ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተማ የመትከያ ሰፋፊ ቦታ የሌላቸው ወረዳዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ በወረዳቸው በመገኘት ችግኞችን በመውሰድ በጊቢያቸው እና በ20/50 ራድየስ መትከል ይችላሉ፡፡

በማስፋፍያ አከባቢ የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በየአከባቢዎቻቸው በተዘጋጁ የመትከያ ጣቢያዎች በመገኘት መትከል ይችላሉ፡፡

በዕለቱ የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች በሙሉ የችግኝ ተከላ ላይ ስለሚሳተፉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ለአገልግሎት ዝግ ይሆናሉ፡፡

የከተማው ነዋሪ ለከተማው ያለውን ፍቅር እና በጎ አመለካከት ችግኝ በመትከል በተግባር እንዲገልፅ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአ/አ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሒሩት ወ/ማሪያም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ችግኝ ተከሉ። ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ እንዳተገኘው መረጃ ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም ከዩኒቨርሲቲው የቦርድ አመራሮች ጋር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ጊቢ ችግኝ ተክለዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአውሮፓ የሙቀት መጠን በድጋሜ ከፍተኛ ሪከርድ ሊያስመዘገብ እንደሚችል ተጠቆመ። በአብዛኛው የምዕራብ አውሮፓ ሃገራት በአንድ ወር ውስጥ ክብረ ወሰን ይሰብራል በተባለለት የሙቀት ወጀብ እንደሚመቱ ቢቢሲ ዘገቧል፡፡

ፖሪስ ውስጥ ያለው የትንበያ ተቋም በሰሜናዊ ፈረንሳይ 41 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚለካ ሙቀት ሊኖር እንደሚችል መተንበዩን ዘገባው አመልክቷል፡፡

እንግሊዝ ደግሞ 39 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት የሚለካ ሙቀትን የምታስተናግድ ሲሆን የባቡር እንቅስቃሴዎችም ሙቀቱን ለመቋቋም በሚያስችል ፍጥነት በዝግታ እንዲጓዙ ታዘዋል ነው የተባለው።

በቤልጂየም፣ ጀርመንና ደች የሚስተዋለው የሙቀት መጠን ለሁለተኛ ጊዜ በሁለት ቀናት ውስጥ ክበረ ወሰን ይሰብራል መባሉንም ዘገባው አስፍሯል፡፡

የእንግሊዝ ብሄራዊ የአየር ንብረት አገልግሎት እንዳስታወቀው የአየር ንብረት ለውጡና የሙቀት ሁኔታው በመላው አውሮፓ ከባድነቱ እየጨመረ መጥቷል ሲልም ጠቁሟል፡፡

ትላንት ቤልጅየም፣ ጀርመንና ኔዘርላንድስ በቅደም ተከተል 39.9 ፣ 40.5 እና 39.3 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሆነ ከፍተኛ ሙቀት ማስመዝገባቸውን ነው ቢቢሲ የዘገበው።
የተለያዩ ቅሪተ አካላት እና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች የፕላኔቷን የአየር ንብረት ፈተና ውስጥ ከቶታል ሲሉ የዘርፉ ምሁራን አመልክተዋል፡፡

Via #bbc/#ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ? #BBC የአማርኛው አገልግሎት በዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዞ ወጥቷል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ESGED-07-25
#update በመካከለኛው የሜድትራኒያን ባሕር ጀልባ ሰጥሞ 150 ስደተኞች መጥፋታቸውን የተ.መ.ድ የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ። ሌሎች 145 ስደተኞች በባሕር በር ጠባቂዎች ወደ ሊቢያ የባሕር ዳርቻ ተመልሰዋል። #ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን ጨምሮ አፍሪካውያን ስደተኞች አውሮፓ ለመሻገር የሚመርጡት የጉዞ መስመር ነው።

ምንጭ፦ እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቦይንግ

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ማምረት #ሊያቆም እንደሚችል ገለጸ፡፡ ቦይንግ ከዚህ ቀደም ያመረታቸው አውሮፕላኖች ወደ በረራ ካልተመለሱ የ737 ማክስ ምርቱን ሊያቋርጥ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

ኩባንያው ይህን ያለው በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኪሳራ በሩብ ዓመት ብቻ በማስመዝቡ ነው፡፡ አሁንም በዓለማቀፍ ደረጃ የበረራ ባለስልጣናት ፈቃድ ካልሰጡና አውሮፕላኖቹ ወደ ሥራ ካልተመለሱ ምርቱን ሊቀንስ በሂደትም ማምረቱን ሊያቆም እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

የቦይንግ ኃላፊ ዴኒስ ሙይልበርግ ግን በመጭው ጥቅምት አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ እንደሚመለሱ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ‹‹ጥረታችንን ቀጥለናል፤ 737 አውሮፕላኖቻችን ችግሮቻቸው ተቀርፈው ወደ በረራ እንደሚመለሱ ተስፋ እናደርጋለን›› ብለዋል፡፡

‹‹ነገር ግን ወደ በረራ የመመለሻ ጊዜው ከተገመተው በላይ ጊዜ ከወሰደ ምርትን ከመቀነስ አልፎ የማክስ አውሮፕላኖችን ምርት ወደ ማቆም እንገባለን›› ብለዋል ኃላፊው፡፡

ባለፈው መጋቢት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ተከስክሶ 157 ሰዎች መሞታቸውና አደጋው በጥቅምት ወር መጨረሻ አካባቢ ሌላ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን በኢንዶኔዥያ ተከስክሶ 189 ከሞቱበት አደጋ ጋር መመሳሰሉ ምርቱ ችግር እንዳለበት ፍንጭ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎም አብዛኞቹ የዓለም ሀገራት ሞዴሉን ከበረራ አግደውታል፤ ይህም ኩባንያውን ለኪሳራ ዳርጎታል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ/AMMA/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወ/ሮ ሙፈሪያት #የግድያ ሙከራ አልተደረገባቸውም!

በደኢሕዴን ሊቀመንበር ሙፈሪያት ከሚል ላይ ግድያ ሙከራ እንደተደረገ በማኅበራዊ ሜዲያ የሚሰራጨው ዜና ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሐምሌ 22 የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ሆነው እንደሚውሉ ተገለፀ፦

ሐምሌ 22 ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የቦታ ልየታን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ባደረጋቸው ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ የከንቲባ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክረቴሪያት ወ/ት ፌቨን ተሾመ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ወ/ት ፌቨን በመግለጫቸው በከተማዋ ባሉ 116 ወረዳዎች ከ400 በላይ የመትከያ ሳይቶች መዘጋጀታቸውንና ወጣቶችን በማሳተፍ የ2.8 ሚሊዮን ጉድጓድ ቁፋሮ መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡ የዕለቱን የችግኝ ተከላ ስራ የሚመራ ግብረ ሃይል መቋቋሙንና 100ሺ የሚሆኑ ወጣቶች ሁነቱን ለማስተባበር መዘጋጀታቸውንም ገልፀዋል፡፡

በዕለቱ የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች በሙሉ በችግኝ ተከላው ላይ ስለሚሳተፉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ሆነው ይውላሉም ብለዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ለከተማው ያለውን ፍቅር እና በጎ አመለካከት ችግኝ በመትከል በተግባር እንዲገልፅ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ፡- የከንቲባ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዝግ_ነው #ሀምሌ22

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ ሀምሌ 22 በሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ስለሚሳተፉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ሆነው ይውላሉ።

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ግብፅ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር #ገዱ_አንዳርጋቸው ወደ ግብፅ አቅንተው ከፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ ተገናኝተዋል። ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ፕሬዝዳንቱን ሲያገኙ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እና የጠቅላይ ምኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ ግርማ ብሩ አብረዋቸው ነበሩ።

Via #Eshet_Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሞተር እገዳ~በሀዋሳ ከተማ!

በሐዋሳ ከተማና በዙሪያዋ አጋጥሞ ከነበረው ሁከት ጋር በተያያዘ ለጸጥታ ሲባል በከተማዋ ውስጥ ሞተር ሳይክሎች እንዳይቀሳቀሱ እገዳ መጣሉን ቢቢሲ ያናገራቸው የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች አረጋግጡ።

እርማጃው የተወሰደው ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው ብለው የሚያምኑት የከተማዋ ነዋሪዎች እገዳ መጣሉ በክልሉ መገናኛ ብዙሃን በኩል እንደተገለጸ ጠቅሰዋል። አሽከርካሪዎች ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በዚህም ምክንያት በሐዋሳ ከተማ በብዛት ይተዩ የነበሩት ሞተር ሳይክሎች #ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ እንደሌሉ የገለጹት አንድ ነዋሪ ትራፊክ ፖሊሶችም መንገድ ላይ ያገኟቸውን ሲያስቆሙ መመልከታቸውንና መኪኖችና ባጃጆች ግን በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ እንደሚታዩ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች መድረክ ረግጠው ወጡ!

በኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህገ-ረቂቅ ውይይት ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች መድረክ ረግጠው ወጡ፡፡ በህገ-ረቂቁ እንዲካተቱ ያቀረብናቸው ማሻሻያዎች አልተካተቱም ፤ ሃሳቦቻችንና አስተያየቶቻችን ያልተካተቱበትን ሰነድ ለመቀበል እንቸገራለን በማለት ነው የተወሰኑ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች መድረኩን እረግጠው የወጡት፡፡ እንዲካተቱ ያቀረብናቸው ማሻሻያዎች ሳይካተቱ ህገ-ረቂቁ እንዳይጸድቅ ሲሉ ቋሚ ኮሚቴውን አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የመንግስት ሰራተኞች ለምርጫ በእጩነት ከተመዘገቡበት ጊዜ ጀምሮ የምርጫ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከስራ ገበታቸው በጊዜያዊነት እንደሚለቁና ደመወዝና ጥቅማ-ጥቅማቸውም እንደማይከር በሚዘረዝረው ረቂቅ-ህግ አንቀጽ 33 ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በደመወዙ ኑሮውን መደጎም ያልቻለን የመንግስት ሰራተኛ ለምርጫ በዕጩነት ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ደመወዙና ጥቅማ-ጥቅሙ አይከበርም ማለት ወደ ምርጫ አትግቡ ከማለት ለይተን አናየውም ብለዋል የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ፡፡

የመንግስት ሰራተኞች በስራ ሃላፊነት ያገኙትን ስልጣን ፣ የመንግስትንና የህዝብን ሃብትና ንብረት ለምርጫው አገልግሎት እንዳያውሉት ለማስቻል እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል፡፡ በግንቦት ወር 2011 ዓ.ም 107 የነበሩ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ቁጥር አሁን ላይ 137 እንደደረሰ ወይዘሪት ብርቱካን ገልጸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia