ደኢህዴን❓
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ከነገ ጀምሮ ከንቅናቄው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ምክክር ሊያካሂድ እንደሆነ ተሰማ። የጀርመን ራድዮ ታማኝ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል እንዳለው ነገ በሚጀምረው በስብሰባ ንቅናቄው በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ ያካሄደው ልዩ ስብሰባ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ ምክክር ያደርጋል። ውይይቱ በተለይም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የራስ ገዝ ወይም በክልል የመደራጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ በተካሄደው ጥናት እና አፈጻጸም ዙሪያ ያተኩራል ተብሏል። ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ይኽው የምክክር መድረክ በሃዋሳ እና በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ምንጮቹ አመልክተዋል። በስብሰባው ላይ የዞኖች እና የወረዳዎች አመራሮች የካቢኔ አባላት በከፍተኛ እና በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ የንቅናቄው ካድሬዎች እንደሚሳተፉ ራድዮ ጣቢያው ጨምሮ ግ0ልጿል።
ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#SMN የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ አመራሮች በሀዋሳ ከተማ ከተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። አመራሮቹ ስላሉበት ሁኔታ ከቤተሰቦቻቸው መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርጊያለሁ። ከታሳሪ ቤተሰቦች አንድ ሰው በስልክ አነጋግሬ ያገኘሁትን መረጃ ወደበኃላ ወደናተ የማደርስ ይሆነል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት፦
* አፈፃፀሙ 43 በመቶ ብቻ ነው፤
* ግንባታውን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 30 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፤
* የፕሮጀክቱ እቃዎች በጸሐይና ዝናብ ከጥቅም ውጪ እየሆኑ ነው፤
የተራራው ግማሽ ጎን ተሰንጥቋል። በተሰነጠቀው ተራራ ስር ሰፊ ደልዳላ ሜዳ ተሰርቷል። በተሰራው ሜዳ ላይ እዚህም እዚያም ጅምር የፋብሪካ መትከያ ህንፃዎች፣ መጋዘኖች፣ ቢሮዎች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ ጅምር የኤሌክትሪክ ማመንጫ ፋብሪካዎችና ሌሎች ህንፃዎች ጉች ጉች ብለው የአካባቢውን ተፈጥሮ በዙሪያቸው እየተመለከቱ ቆዝመዋል። ወደ ቤቶቹ ውስጥ ሲገባ በእርጥበት ወይበዋል። ፍየሎች ከዝናብ ስለሚጠለሉበት ከእነርሱ ጠረን ጋር ተዳምሮ ሰፋፊዎቹ ህንፃዎች ውስጣቸው በመጥፎ ጠረን ታውዷል። በአጠቃላይ የዋሻ ዘመንን ኑሮ ያስታውሳል።
ከአንደኛው ጫፍ ወደ ሌላው ጫፍ ለመድረስ የሚያታክተው ሰፊ ግቢ በአረምና በሳር ተወርሯል። ግቢው ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁርጥራጭ ፣ ትላልቅና ወፋፍራም ብረቶች፣ በትናንሽና ትላልቅ ማሽኖች፣ ኮንቴይነሮች፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ተዘርዝረው በማያልቁ ቁሶች ተሞልቷል። ዝናብ፣ ቁሩና ጸሐይ የተፈራረቀባቸው ቁሶች በዝገት መልካቸው ጠፍቷል። ይህ የሀገር ሀብት ብክነትና ብልሽት ሲታይ ህሊናን በኀዘን ይሸነቁጣል።
የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ በዓመት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል አውጥቶ በመጠቀም 90 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ፣ በዓመት 300ሺ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ፣ 60ሺ ቶን ሜታኖል፣ 5ሺ ቶን አሞኒያ፣ 4ሺ500 ቶን ሰልፈር እንዲሁም ኦክስጂን፣ ካርቦንዳዮክሳይድ፣ ናይትሮጂንና አርገን የሚባሉ ጋዞችን እንዲያመርት የታለመለት ግዙፍ ፕሮጀክት ነበር።
Via ኢፕድ

#update ኢራን ያገተችውን የብሪታኒያ መርከብ ከእገታ ነጻ እንደምትለቅ ፍንጭ ሰጠች። ፕሬዚዳንት ሀሰን ሮሃኒ “ብሪታኒያ በሃምሌ ወር መጀመሪያ ያገተችውን መርከባችንን ከለቀቀች ኢራንም ተመሳሳይ መልስ ትሰጣለች” ብለዋል። “ግሬስ-1” የተሰኘው ግዙፍ መርከብ የአውሮፓን ማዕቀብ በመጣስ ነዳጅ ጭኖ ወደ ሶሪያ ሲጓዝ በሃምሌ ወር መጀመሪያ የጂብራልተር የባህር ዳርቻ ላይ በብሪታኒያ መታገቱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ የብሪታኒያን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልብ ስቴና ኢምፔሮ የተሰኘ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በሆርሙዝ ሰርጥ ሲያልፍ በኢራን ታግቷል። ኢራን መርከቡን ያገትኩት የአሳ ማጥመጃ መርከብን ስለገጨ እና ዓለም አቀፋዊ ህግን ስለጣሰ ነው ብላለች። ብሪታኒያና ኢራን በመርከብ እገታ እርስ በእርስ ወደ ውጥረት መግባታቸውን አልጄዚራ ዘግቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
animation.gif
455 KB
40/60 የጋራ መኖሪየ ቤት...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፣ ዕግድ የተጣለባቸውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለይቶ እንዲያሳውቅ በፍርድ ቤት ታዘዘ፡፡
ትዕዛዙን የሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ነው፡፡ ኢንተርፕራይዙ ባለሦስት፣ ባለሁለትና ባለአንድ መኝታ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በየትኞቹ ሳይትና ብሎክ እንደሚገኙና የተሰጣቸውን የቤት ቁጥር ጭምር ለይቶ እንዲያሳውቅ ተነግሮታል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ትዕዛዙን ፈጽሞ የሚቀርበው ሐሙስ ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡
የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕግድ የተጣለባቸው በምዝገባ ወቅት መቶ በመቶ ክፍያ የፈጸሙ በርካታ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ የዕድሉ ባለቤቶች እንደሚሆኑ ተነግሯቸው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ውል ከፈጸሙ በኋላ፣ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. የከተማ አስተዳደሩ ከ18 ሺሕ በላይ የሚሆኑ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን፣ ከ40 በመቶ በላይ የቆጠቡ ሁሉ በዕጣው በማካተቱና በማውጣቱ ምክንያት ክስ በመመሥረቱ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ፍርድ ቤቱ መጀመርያ ክስ ባቀረቡት 98 ሰዎች አቤቱታ መሠረት ሁሉንም ዕጣ የወጣባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችና በቀጣይ የሚወጡትም ጭምር ዕግድ የጣለ ቢሆንም፣ ቆይቶ ክስ ባቀረቡት ልክ ብቻ በማገድ የሌሎችን ቤቶች ዕግድ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ መቶ በመቶ መክፈላቸውን በመግለጽ ለፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 700 መድረሱ እየተነገረ ነው፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር

በእነ አብዲ መሀመድ ዑመር የክስ መዝገብ 12 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡ በእነ አብዲ መሀመድ ዑመር የክስ መዝገብ የቀረቡ ተከሳሾች ‹‹ወንጀሉን አልፈፀምንም፤ ጥፋተኛም አይደለንም›› አሉ፡፡ በእነ አብዲ መሀመድ ዑመር የክስ መዝገብ ላይ 14 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን መቃወሚያ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ ብይን ሰጥቷል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/A-07-24
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/A-07-24
የጥናት ውጤቱ ይፋ ተደረገ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ በደቡብ ክልል የሚነሱ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምላሽ ለመስጠት ያስጠናው ጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ ሆነ።
ላለፉት ሰባት ወራት በምሁራን የተካሄደው የደቡብ ክልል አዲስ አከላለልን የተመለከተው ጥናት ውጤትን በተመለከተ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/A-07-24-2

#update በጀርመን ኤርትራዊ ወጣት ላይ በደረሰበት ጥቃት በርካቶች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን ገለፁ። ከቆዳው ቀለም ጋር ተያይዞ በጥይት በተመታው ኤርትራዊ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጀርመን ዋችተርስባች ከተማ ለተቃውሞ መውጣቸው ተገለፀ፡፡
የጀርመን የአገር ውስጥ ሚድያ እንደገለፀው የ26 አመቱ ኤርትራዊ ወጣት በጥቃቱ ከፍተኛ ጉዳት ቢያጋጥመውም አሁን ላይ እየተሻለው መሆኑ ተገልፅዋል፡፡
የፍራንክፈርት ግዛት አቃቤ ህግ ቃል አቀባይ አሌክሳንደር ባድል እንዳሉት የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከውጪ ሃገር ዜጎች ጥላቻ የመነጨ ሊሆን ይችላል ያሉትን ጥቃት እየመረመሩ ይገኛሉ፡፡
ቃል አቀባዩ ጨምረውም ጥቃት አድራሹ በዘፈቀደ እንደተኮሰ ገልጸው እራሱን ማጥፋቱን አመልክተዋል፡፡ ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪ ወንጀለኛው አጎራባች ከተማ መኪና ውስጥ ህይወት አልባ ሆኖ መገኘቱን ገልፆ በሆስፒታል መሞቱ ተረጋግጧል ብሏል፡፡
የተጠርጣሪው ቤትና መኪና ሲፈተሸም ሁለት በከፊል አውቶማቲክ የሆኑ ህጋዊ ሽጉጦች መገኘታቸውንና ተጠርጣሪው የዘረኝነት ጥቃት የመፈፀም ዝንባሌ እንዳለው ተረጋግጧል መባሉን ዶቼ ዌሌ ፖሊስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
መርማሪዎች በበኩላቸው የ55 አመቱ ጥቃት አድራሽ ቀኝ አክራሪ ናሽናሊስት መሆኑን እስካሁን አላረጋገጥንም ብለው ምርመራው መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡-አልጀዚራ/#ENA/

#update የቤኒሻልጉል ጉሙዝ ክልል እና የሱዳኑ ብሉናይል አስተዳደር ለሁለቱ ሕዝቦች ሠላም እና የልማት ተጠቃሚነት የጀመሯቸውን ሥራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሱዳን ሪፐብሊክ የብሉናይል አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት ምክክር በአሶሳ ከተማ ትናንት ተጀምሯል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደቡብ❓
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚታዩ የክልል እንሁን ጥያቄዎችን በጥናት ለመፍታት የክልሉ ገዥ ፓርቲ ደኢህዴን ሲያስጠና ቆየው ጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ ሆነ።
የጥናት ቡድኑ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት 20 አባላት ያሉት የጥናት ቡድን ተዋቅሮ ላለፉት ሰባት ወራት ሰፊ ጥናት ሲያካሂድ ቆየቷል። በዚህም መሰረት ሶስት አማራጮችን አስቀምጧል ብለዋል ምክትል ሰብሳቢዋ።
በጥናቱ የተለየው የመጀመሪያው አማራጭ አብዛኛው የክልሉ ህዝብ አሁን ያለው የክልሉ አደረጃጀት ቢቀጥል የህዝቦችን አብሮነትና ያጠናክራል፤ ጠነካራ የደቡብ ህዝቦች ክልልንና የኢትዮጵያን አንድነት ያጠናክራል የሚል ነው።
በጥናቱ የተለየው መጀመሪያ አማራጭ አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሮ ተቀባይነት የሚያጣ ከሆነ በጥናቱ በሁለተኝነት የተለየው አማራጭ ደግሞ ክልሉን በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በመክፈል ከዚህ በፊት ይነሱ የነበሩ የፍተሃዊነት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ነው።
በጥናቱ በሶስተኝነት የተቀመጠው ሃሳብ ደግሞ ሁለቱ አማራጮች ተግባራዊ የማይሆኑ ከሆነና ሁኔታው ከክልል አልፎ በአገሪቱ ሰላምና አንድነት ላይ ጫና የሚፈጥር ከሆነ ጉዳዩ ለጊዜው ቢቆይና በእርጋታ ቢታይ የሚል ነው። እንደጥናት ቡድኑ ምክትል ሰብሳቢ ከ17 ሺህ በላይ ሰዎች በላይ ለጥናቱ በመረጃ ሰጪነት ተሳትፈዋል።
ምንጭ፦ ኢፕድ

የመኖሪያ ቤት ችግር ይፈታ ይሆን❓
በመጪው አዲስ ዓመት በተለይ #ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለመንግሥት ሰራተኞች በርካታ ቁጥር ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ተናገሩ። ግንባታው የሚካሄደው እንደከዚህ ቀደሙ በመንግሥት ሳይሆን በግል ተቋማት ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው መንግሥት የመቆጣጠርና የማስተባበር ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ተናግረዋል።
Via #BBC

#SMN
ከቀናት በፊት ከሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በሀዋሳ ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጆችን ጨምሮ የተቋሙ የቦርድ አባላት መታሰራቸው ይታወቃል። ለመሆኑ ታሳሪዎቹ በምን አይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?? ብዬ ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች መካከል አንድ ሰው አናግሪያለሁ...የታሰሩት በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንደሆነ የገለፁልኝ እኚህ ሰው ተከታዩን ብለዋል፦
"አሁንም ቢሆን #እየተሳቀቅን ነው ሄደን የምንጠይቃቸው፤ በር ላይ ያሉት የፀጥታ ኃይሎች ያሸማቅቁናል፣ ይሰድቡናል። በር ላይ ያሉት ሰዎች ለቤተሰቦች ተገቢውን ክብር እየሰጡ አይደለም፤ በስንት ልመና ነው ምግብ እንኳን የምናስገባላቸው። ከትላንት በስቲያ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ፣ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስና የክልሉ ፖሊስ አነጋግረዋቸው ነበር ምርመራ እያደረግን ነው በ14 ቀን ውስጥ ዝርዝር ጉዳዩን እና በምን ምክንያት እንደታሰሩ እናሳውቃችኃለን ብለዋቸው የነበረ ሲሆን ቀኑ መብዛቱን ቅሬታ ያሰሙት የSMN አመራሮቹ ከ14 ቀን በፊት ዝርዝሩ እንዲነገራቸው ጠይቀው ተፈቅዶላቸዋል። ለምን እንደታሰሩ ምን እየተፈፀመ እንዳለ አያውቁም፤ ፖሊስም ካሰራቸው በኃላ ነው መረጃ እያፈላለገ የሚገኘው ይህ ፍፁም ተገቢ አይደለም። ምን አይነት ስራ እየተሰራ እንዳለ አናውቅም፤ ቤተሰብ ብዙ ጊዜ እንዲያገኛቸው አይፈቀድም ነገር ግን ባገኘናቸው ሰዓት የሚነግሩን አያያዛቸው ጥሩ እንዳልሆነ ነው።"
🏷በታሳሪዎቹ ላይ ድብደባ እና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው የሚል ወሬ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ አይቼ ነበር ምን ያህል እውነት ነው ብዬ ለጠየኳቸው ጥያቄ የሰጡኝ ምላሽ፦ "እኔ ይህን እርግጠኛ #አይደለሁም፤ እርግጠኛ የምሆንበትን ነገር ብቻ ደውዬ አሳውቅሃለሁ"
@tikvahethiopia @tsegabwolde

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ...
የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ታሪኩ ለማ ባለፉት ቀናት የሚገኙበት የጤና ሁኔታ ጥሩ እንዳልሆነ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የምክትል ስራ አስኪያጁ የቅርብ ሰው ግልፀዋል። "በተደጋጋሚ ወደተሻለ የህክምና ተቋም እንዲወስድ ጠይቀናል የክልሉ ፕሬዝዳንት አማካሪም ጋር ጉዳዩ ደርሷል እስካሁን በቂ ምላሽ አላገኘንም በዚህም ሳቢያ ተጨንቀናል፤ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይፈልግልን" ብለዋል።

#አብን
አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ታፍሰው #ታሰሩብን" ሲል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ አቤቱታ አሰማ። ሃያ ስምንት እንደሚሆኑ አብን ያሳወቃቸው አባላትና ደጋፊዎቹ የታሠሩት የመሪዎቻቸውን ጉዳይ ለመከታተል አዲስ አበባ፤ አራዳ ምድብ ችሎት ተገኝተው በነበረ ጊዜ መሆኑንም አብን ገልጿል። “የታሠሩብን ‘አማራነት እና እውነት አይታሰርም’ የሚል ሸሚዝ የለበሱ ናቸው” ሲሉ የንቅናቄው የፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በለጠ ካሣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። የተያዙት ሰዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የሦስት ሺህ ብር ዋስ እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውንም አቶ በለጠ አመልክተዋል።
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ

በመጪው ሀምሌ 22 ቀን ለሚካሄደው በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገር አቀፍ ዘመቻ ላይ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ 30 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ “በሀገሪቱም ሆነ በክልል የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ እየጎለበተ መሄዱን” ጠቅሶ በተቃራኒው ግን “የለውጥ ተፃራሪዎችና የለውጡን ሂደት በአግባቡ ያልተረዱ” ያላቸው “ሁከትና ብጥብጥ በክልሉ አስነስተዋል” ሲል ከስሷል። ለህገ መንግሥታዊው በክልል የመደራጀት መብት ጥያቄ የሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ምላሽ ባለመስጠታቸው በእንጥልጥል እንዲቆይ መደረጉን ሲአን አመልክቶ መልሱ መሰጠት በነበረበት ጊዜ ያለመሰጠቱንም “የፖለቲካ ሴራ” ብሎታል።
Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም ሲኖር ሐገር አለ!
ሰላም ሲኖር ልማት አለ!
ሰላም ሲኖር እድገት አለ!
ሰላም ሲኖር ቤተሰብ አለ!
ሰላም ሲኖር መቻቻል አለ!
መቻቻል ሲኖር መተሳሰብ አለ!
መተሳሳብ ሲኖር መፈቃቀር አለ!
የሰላም ዋናው ምንጭ ከግለሰቦች ነው የሚጀምረው እና ወንድም እህቶቼ ከምንም ነገር በፊት ለሰላም ቅድሚያ እንስጥ እላለሁ።
Via #Afandi_Sufiyan
ሰላም እደሩ!

#update የአማራ ክልል የ2012 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 47 ነጥብ 4 ቢሊዮን እንዲሆን ታቅዷል፡፡ የዕቅዱን ዝርዝር ሀሳቦች በተመለከተ ለምክር ቤት አባላቱ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው፡፡ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን መሐሪ (ዶክተር) የበጀት ዓመቱን በጀት ለክልሉ ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ የበጀት ዕቅዱ የተጀመሩ እና በአዲስ የሚጀመሩ የማስፈጸሚያፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም፣ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ያልተሳኩ ዕቅዶችንም ለማሳካት፣ ለድህነት ተኮር ዘርፎች ትኩረት ለመስጠት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራው እና ሌሎችም ዐበይት ተግባራት ማስፈጸሚያነት እንዲሆን ታስቦበት እንደተዘጋጀ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert
የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የምርመራ ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል:
.ተጠርጥረው ከተያዙ 218 የልዩ ሀይል አባላት 113ቱ ተለቀዋል
በአማራ ክልል በሰኔ 15/2011 ዓ.ም ተሞክሮ የከሸፈውና የክልሉን ከፍተኛ አመራሮች ለህልፈት የዳረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የምርመራ ውጤት በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን እያካሄደ ባለው 5ኛ ዙር፤ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ከምክር ቤቱ አባላትም በሰኔ 15 በተፈጸመው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እና ሌሎች የክልሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል።
Via #EPA

#ሰበር_ዜና
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሲዳማ እና የሀድያ ዞን ከፍተኛ ባለስልጣናትን ከኃላፊነት #ማገዱን አስታወቀ።
#ደኢህዴን ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ዞን አመራሮች የታገዱት ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማና እና በሲዳማ ዞን የገጠር አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት የራሳቸው ሚና ነበራቸው በሚል ነው። የሃድያ ዞን አመራሮች በዞኑ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ላይ ከሚጥሉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ የማገድ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል።
ድርጅቱ ከስልጣን አግጃቸዋለሁ ያላቸውን የሲዳማና የሀድያ ዞን ባለስልጣናት ''የፊት አመራሮች '' ከማለት ውጪ ቁጥራቸውንም ሆነ ማንነታቸውን አልጠቀሰም። በደቡብ ክልል በከፋ እና በወላይታ ዞኖች የተስተዋሉት ተመሳሳይ ድርጊቶችም የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ናቸው ሲል ድርጅቱ በመግለጫው ጠቁሟል።
ምንጭ: የጀርመን ራድዮ