TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሐዋሳ አካባቢ ያለው እንቅስቃሴ ወደ #ሠላማዊ ሁኔታ እየተመለሠ መሆኑ ተገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/HW-07-21
‹‹ግድያውን ብርጋዴር ጄኔራል #አሳምነው ጽጌ ብቻውን መርቶታል ማለት ከባድ ነው›› አምሳል ጌትነት ከበደ (ኢንጂነር)፣ የቀድሞ ፖለቲከኛ
.
.
አቶ አምሳል፡- "አምባቸው እንዲህ በአጭር ጊዜና ባልተጠበቀ ሁኔታ ይገደላል ወይም ይሞታል ብዬ አልገመትኩም፡፡ ይሁንና የብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ሁኔታ ግን አይጥመኝም ነበር፡፡ አምባቸውን፣ እዘዝን ወይም ምግባሩን ይገድላቸዋል የሚል ጥርጣሬ አልነበረኝም፡፡"

ሪፖርተር ጋዜጣ ከኢንጂነር አምሳል ጌትነት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ👇
https://telegra.ph/BGAT-07-21
"የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ጉዳይ ነው" የኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን

https://telegra.ph/D-07-21
#ባህር_ዳር

የአማራ ክልልና የሱማሌ ክልሎች ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ በባህርዳር ከተማ የክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ በምክክር መድረኩ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር፣ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚደንት ላቀ አያሌው የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የሕዝብ ለሕዝብ ውይይቱ ለሶማሌ ክልል የልዑክ አባላት #ሥጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የአማራ ክልል ለሶማሌ ክልል ሁሉም የልዑክ አባላት አገልግል እና የዘጌ ቡና በስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጦፋ ሙሐመድ ዑመር የተመራው የሶማሌ ክልል ልዑክ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትሥሥር የሚያጎለብት ውይይት ተካሂዷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አሳዛኝ

የ30 ዓመት ጓደኛሞች መሀል የገባ ቀላል ፀብ ነፍስ ነጠቀ። #ETHIOPIA #ETHIOFM107.8

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ_70_እንድርታ

ዛሬ በወጣው የ2019/20 የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ድልድል የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው መቐለ 70 እንደርታ በቅድመ ማጣርያው ከ ኢኳቶርያል ጊኒው ካኖ ስፖርት አካዳሚ ጋር ተደልድሏል።

Via #SoccerEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፋሲል_ከነማ

በ2019/20 ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣርያ ድልድል ዛሬ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው ፋሲል ከነማ ከ ታንዛኒያው አዛም ጋር ተደልድሏል።

Via #SoccerEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ

የትግራይ ክልልን #ለማልማት በመቐለ ከተማ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ። በገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ 400 ሚሊየን ብር ለማግኘት ታቅዶ ከእቅድ በላይ 519 ሚሊየን ብር ተገኝቷል ተብሏል። 'የክልሉ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባዘጋጀው መድረክ ላይ የክልሉ ባለሃብቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። በዛሬው መድረክ ላይ ከእቅድ በላይ የተገኘ ሲሆን፥ ገቢው ክልሉን ለማልማት በተደረገው ጥሪ መሰረት የተገኘ ነው ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ካይሮ ሰላም ነው

የብሪታኒያ አየር መንግድ (ብሪቲሽ ኤርዌይስ) ''ለደህንነት ሲባል'' ወደ ካይሮ ግብጽ የሚደርገውን በረራ ለአንድ ሳምንት ያክል አግጄያለሁ ሲል አስታወቀ። ተጓዦች ለንደን ሂትሮ አየር ማረፊያ ከደረሱ በኋላ የብሪታኒያ አየር መንገድ ወደ ካይሮ የሚያደርገው በረራ መሰረዙ እና ለአንድ ሳምንት ያክል ተለዋጭ በረራ እንደሌለ ተነግሯቸዋል። አየር መንገዱ በረራውን ለአንድ ሳምንት ለመሰረዝ ያደረሰው የደኅንነት ስጋቱ ምንነት በዝርዝር አልገለጸም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ድሬዳዋ

የተለያዩ ምሁራንና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም የምስራቅ ተጎራባች ክልሎች የሚሳተፉበት “የአዲስ ወግ” የውይይት መድረክ ነገ በድሬዳዋ እንደሚካሄድ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፌደራል_ፖሊስ

ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦችን በህገ ወጥ መልኩ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፋይናንስ ወንጀል ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው ለኤፍ ቢ ሲ እንደተናገሩት፥ ገንዘቦቹ በተለያየ ጊዜና በተለያየ ቦታ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ በጉምሩክ ኮሚሽንና በፌደራል ፖሊስ የተያዙ ናቸው። ከዚህ ውስጥ 2 ሚሊየን 486 ሺህ 500 የአሜሪካ ዶላር፣ 55 ሺህ 664 ፓውንድ፣ 25 ሺህ 670 የካናዳ ዶላር፣ 8 ሺህ 800 የአውስትራሊያ ዶላር፣ 19 ሺህ 700 ድርሃም፣ 18 ሺህ 390 ሪያል እና 24 የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦች መያዛቸውንም ተናግረዋል። ግለሰቦቹ ጉዳያቸው በምርመራ አልቆ በፍርድ ቤቱ መያዙንም ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሲዳማ ዞን ሶስት አካባቢዎች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 34 መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ተቃዋሚው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ፓርቲ ገለጹ። አንድ የዓይን እማኝ በሁላ ወረዳ ሀገረ ሰላም ከተማ 14 ሰዎች ሲገደሉ መመልከታቸውን ተናግረዋል። ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሁላ ነዋሪ ለጀርመን ራስዮ እንደተናገሩት ከትላንት በስቲያ አርብ ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ወደ ፌደራል ፖሊሶች የሄዱ የከተማይቱ ነዋሪዎች ተኩስ ተከፍቶባቸዋል። በጥይት የተመቱት አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን የተናገሩት የዓይን እማኙ ወዲያውኑ ወደ ሁላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢወሰዱም አስራ አራቱ ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መሥራችነት የተጀመረው የባሕር ዳር የሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከል ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ የሳይንስ ማዕከሉ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን የሳይንስ ትምህርቶችን ያስተምራል፡፡ ተማሪዎቹ በ8ኛ ክፍል ውጤታቸው ተመርጠው ነው ማዕከሉን የሚቀላቀሉት፡፡ ማዕከሉ የመጀመሪያዎቹን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ዛሬ ሐምሌ 14 2011ዓ.ም አስመርቋል፡፡ ማዕከሉ በቴክኖሎጂ የላቁ ተማሪዎችን ለማፍራት ዓላማ አድርጎ ነበር የተቋቋው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations #መቐለ የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ በመቐለ ካምፓሱ ያስተማራቸውን ከ600 በላይ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በሰማዕታት አዳራሽ አስመርቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሲዳማ ዞን ከተሞች እንዴት ዋሉ? የዛሬ ዉሎ ምን ይመስል ነበር?

ከ20 ደቂቃ በኃላ እመለሳለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ ሰላም ቀድሞ ወደነበረበት እየተመለሰ ይገኛል። በከተማይቱ የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም እየተጀመረ ነው። ካለፉት ቀናት በእጅጉ የተሻለ መረጋጋት እና ሰላም በከተማዋ መስፈኑን በስልክ ያነጋገርናቸው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።

#ወንዶገነት

በወንዶ ገነት ከተማ አርብ ዕለት ተከስቶ በነበረው ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሚታወስ ሲሆን ትናንት ቅዳሜም በወንዶ ገነት ውጥረት ነግሶ ነው የዋለው። ይሁን እንጂ ዛሬ እሑድ በከተማው መረጋጋት እንደሚታይ አንድ የአይን እማኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል “የትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል። ሱቆችም ከሞላ ጎደል ተከፍተዋል። የጸጥታ ኃይል አስከባሪዎች በስፋት በከተማዋ ሲንቀሳቀሱ ነው የዋሉት።
/BBC/

#ይጋለም

ከተማዋ ወደ ቀድሞ እንቀስቃሴ አልተመለሰችም፤ ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ #መረጋጋት አለ። ዛሬ ላይም ቢሆን በይርጋለም ከተማ የደህንነት ስጋት መኖሩን ለBBC የተናገሩ የከተማዋ ነዋሪ፤ በዚሁ ምክንያት በርካታ የንግድ ተቋሟት በራቸውን ዝግ አድርገው እንደዋሉ ገልፀዋል።

#ሀገረሰላም

በስልክ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ዛሬ ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ ሰላም እና መረጋጋት እንደታየ ገልፀዋል፤ ስጋቶች ግን አሁንም አሉ ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊት በከተማው ይገኛል በየቦታውም ቅኝት ሲያሰርግ ውሏል ሲሉ የዛሬውን ሁኔታ አስረድተዋል።

#አለታወንዶ

የዛሬው ዉሎ ከትላንትና እና ከትላንት በስቲያ ከነበረው እጅጉ የተሻለ እና መረጋጋት የታየበት እንደነበር ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በሲዳማ ዞን የኢንተርኔት አገልግሎት አልተጀመረም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ለetv የተናገሩት፦

“በሲዳማ ዞን ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ መደፍረስ የጸጥታ ኃይሉ ከሕዝቡ ጋር በመሆን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር አውሎታል። ይርጋለም፣ አለታ ወንዶ፣ ሃገረ ሰላም እና ወንዶ ገነት ችግሮች ተከስተው ነበር፤ በተጠቀሱት አከባቢዎች ንብረት የመዝረፍ እና የማውደም ተግባራት ተስተውሏል፤ በተፈጠረው ሁከት በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት አጣርተን ስንጨር ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን!"

#ቢቢሲ_አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲዳማ_ዞን

በሲዳማ ዞን ስለጠፋው ክቡር የሰው ህይወት የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ነዋሪዎችን ዋቢ አድርገው ከሚገልፁት ቁጥር ውጪ በመንግስት በኩል ይፋ የተደረገ መረጃ የለም። እኛም በተለያየ መልኩ ስለጠፋው የሰው ህይወት የተረጋገጠ መረጃ ለማግኘት እየጣርን ነው። የወደመ የተቋማት እና የግለሰቦች ንብረትን በተመለከተም አስተማማኝ መረጃ ወድናተ ለማድረስ ጥረት እያደረግን ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዱከም_መልካ

በኦሮሚያ ክልል በመጪው ኃምሌ 22 ቀን 2011 ዓም ለሚካሄደው የ“አረንጓዴ አሻራ ቀን” ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቱ የቪዥን ብራይት በጎ አድራጎት ማህበር  በመተባበር በዱከም ከተማ አካባቢ ያለውን አነስተኛ የደን ሽፋን ለመመለስ ‘ዱከም መልካ’ በሚባል ስፍራ ዛሬ ተገኝተው  ከማህበሩ አባላት ጋር ችግኝ ተክለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምርጫ “ይራዘም አይራዘም” አስገራሚ ውዝግብ!

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AD-07-21