TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለሶስት ሰዎች የክብር ዶክትሬት ሰጠ!

ዶክተር ሰገነት ቀለሙ፣ ፕሮፌሰር ሃንስ ማትሰን እና ማርክ ጌልፋንድ ናቸው በባህርዳር የኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት የክብር ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል፡፡

ዶክተር ሰገነት ቀለሙ በልዩ መሪነትና ተመራማሪነት ዘርፍ የተመረጡ ሲሆን ናይሮቢ የሚገኘው ዓለማቀፉ የነፍሳት ግብረ አካል እና ሥነ-ምኅዳር የመጀመሪያዋ ሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ከ25 ዓመታት በላይ በሰሜን አሜሪካና በላቲን አሜሪካ በርካታ ምርምሮችን ሠርተዋል፡፡ በዓለማቀፍ ደረጃ ዕፅዋትን በሚያጠፉ በሽታዎች ላይ ሳይንሳዊ ምርምር በማድረግ ቀዳሚ ሴት ተመራማሪ በመሆናቸውም በርካታ ሽልማቶችን አሸንፈዋል፡፡

#ስዊድናዊው ፕሮፌሰር #ሃንስ_ማትሰን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲና በምሥራቅ አፍሪካ የመሬት አስተዳደር ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

አሜሪካዊው ማርክ ጌልፋንድ በበኩላቸው በኢትዮጵያና በሌሎች ታዳጊ ሀገራት የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የምሕንድስና እና የሒሳብ ትምህርቶች ልዩ ትኩረት እንዲሰጣቸው ድጋፍ ያደረጉ ምሁር ናቸው፡፡ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባና በሌሎችም 12 ዩኒቨርሲቲዎችና አካባቢዎች የስቲም ማዕከላት እንዲከፈቱ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እያካሄደ ባለው የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ስርዓት ለሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጦፋ ሙሐመድ ዑመር የክብር ሜዳልያ ሸልሟል፡፡ የክብር ሜዳልያውን የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌውና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ አበርክተውላቸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሃዱ ጋዜጠኞች ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ ተቋረጠ!

በኦሮሚያ ክልል የፊንፊኔ ልዩ ዞን የበረህ ወረዳ አቃቢ ህግ ከ67 ቀናት በፊት ነበር በአሃዱ ሬድዮ ጋዘጠኞች ላይ ከወራት በፊት በተሰራ ዘገባ ምክንያት ክስ የመሰረተው። ጋዜጠኛ ታምራት አበራ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ ሊዲያ አበበና ሱራፌል ዘላለም ክሱ የተመሰረተባቸው ጋዜኞችም ናቸው።

የወረዳው ፍርድ ቤትም በጋዜጠኞቹ ላይ 1ኛ ስም በማጥፋት፣ 2ኛ ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት እንዲሁም የብሮድካስት ህግን መተላለፍ በሚል ነበር ሶስት ክሶችን የመሰረተው። የበረህ ወረዳ ፍርድ ቤትም በጋዜጠኞቹ ላይ የቀረበውን ክስ ካዳመጠ በኋላ ጋዜጠኞቹን እንዲከላከሉ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ይሁንና ጋዜጠኞቹ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት ዛሬ የመከላከያ ምስክሮችንና ሰነዶችን ይዘው ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም በጋዜጠኞቹ ላይ የተመሰረተው ክስ በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ትዕዛዝ እንዲቋረጥ መወሰኑን የአሃዱ ሬድዮ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በውስኔው ደስ መሰኘታቸውን የገለጹት ጋዜጠኛ ጥበቡ ክሱ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትንና የጋዜጠኝነት ሙያን የሚጋፋ ነው ብለዋል። ጥፋት እንኳን ቢኖር ጉዳዩ መታየት ያለበት በብሮድካስት ባለስልጣን በኩል ነበርም ብለዋል ጋዜጠኛ ጥበቡ።

ጋዜጠኛ ጥበቡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር የተመሰረተባችሁን ክስ አስመለክቶ ምን ድጋፍ አደረጉላችሁ ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄም ማህበሩ ምንም አይነት ድጋፍ አላደረገም ጉዳዩንም አላወገዘም ሲሉ ተናግረዋል።

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

በምእራብ አርሲ ሄቨን ወረዳ 177 ችግኞችን #የነቀለው ግለሰብ በስድስት አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡ በምእራብ አርሲ የሙኔሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ሃምሌ 12፣ 2011 በዋለው ችሎት ሄቨን አርሲ ወረዳ ደጋጋ ቀበሌ 177 ችግኞችን በመንቀል የተጠረጠውን ግለሰብ ፋይል ተመልክቷል፡፡ ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ የወረዳው ነዋሪ የሆነው ትቤሶ ያለቱ ሃምሌ 9፣ 2011 ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ በሙኒሳ ዲስትሪክት የመንግስት ደን ውስጥ በዚህ ክረምት ከተተከሉችግኞች መካከል 177 ችግኞችን በመቀል በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ብሎታል፡፡ በዚህም በተከሳሹ ላይ የስድስት ዓመት ጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ችግኞቹ 3 ሺህ 640 ብር ግምት እንዳላቸውም ነው የተገለጸው

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኒውካስትል ዩኒቨርሲቲ ለዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የክብር ዶክትሬት አበረከተ!

የእንግሊዙ ኒውካስትል ዩኒቨርሲቲ የዓለም የጤና ድርጅት ጄነራል ዳይሬክተር ለሆኑት ለዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የክብር ዶክትሬት አበረከተ፡፡ ኒውካስትል ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የተከታሉበት ዩኒቨርሶቲ መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ ኒውካስትል ዩኒቨርሲቲ እኤአ በ1834 የተቋቋመና በጤና የትምህርት መስክ ስመ ጥር ከሚባሉ ዩኒቨሪስቲዎች መካከል የሚመደብ ነው፡፡

https://twitter.com/DrTedros/status/1152247956533370882?s=09
#Congratulations የሚዛን ቴፒ የዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውንና ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ዶክተር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናገሩ ተብሎ የተለቀቀዉ መረጃ ፈጠራ/ሀሰት ነዉ። ከላይ ያለዉ ምስል ከሳምንት በፊት ከታተመዉ ጋዜጣ የተወሰደ ነዉ፣ የወጣዉን ዕትም እና ተመሳሳይ የቅፅ ቁጥር በመጠቀም የተቀናበረ (photoshop) ነዉ። ሪፖርተር ጋዜጣ የተመሠረተበት ዓመት ጳጉሜ 6 ቀን 1987 ዓ.ም ሲሆን በግራ በኩል በምታዩት የሀሰት ምስል 21987 ተመሰረተ ተብሎ ተለጥፎል።

Via Dawit Endeshaw/ሪፖርተር/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚኒባስ አሽከርካሪውን ከነረዳቱ የገደሉት ተከሳሾ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጡ፦

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ስሙ #ቤተል ሆስፒታል አካባቢ ከባድ የሰው መግደል ወንጀል የፈፀሙት ተከሳሾች ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጡ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CH-07-20
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ከድንበር ተሻጋሪ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በትብብር ማስተማር እንደማይቻል የመጨረሻ ያለውን ማሳሰቢያ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሰጥቷል፡፡ ኤጀንሲው በ2000ዓ.ም እና በ2007ዓ.ም በትብብር ማስተማር እንደማይቻል ደብዳቤ ለዩኒቨርሲቲዎች መጻፉን አስታውሶ ‹‹አሁንም የተሰጠውን መመሪያ በመተላለፍ በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያ የሚያስነግሩ መኖራቸውን ለማረጋገጥ ችለናል›› በማለት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስቧል፡፡ ከድርጊታቸው በማይቆጠቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ይመልከቱ👇
https://telegra.ph/MSHEE-07-20
#Congratulations

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 425 ተማሪዎች ማስመረቁ ይታወቃል። ዩኒቨርስቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 2 ሺህ 418 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። የዛሬው ምረቃ ለዩኒቨርስቲው 27ተኛ ጊዜ ነው። ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ሰአት ከ33 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH🎂 ሀምሌ 21 #እንገናኝ!!

#8_ቀን_ቀረው!! TIKVAH-ETHIOPIA የተመሰረተበት ሁለተኛው አመት ክብረ በኣል የፊታችን ሀምሌ 21 በአበበች ጎበና ህፃናት እንክብካቤና የልማት ድርጅት ይከበራል!! #አዲስ_አበባ

ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኃል!!

ለተጨማሪ መረጃ፦ +251913134524
ሁላችሁም ሀምሌ 21 በክብር ተጋብዛችኃል!

/የTIKVAH-ETH ሁለተኛው አመት ምስረታ ክብረ በኣል~በአበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት/

ፒያሳ ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ(1) ወደ ዮሐንስ(2) ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን የሚወስደውን መንገድ ይዘው ቤተ ክርስቲያኑ ጋር እንደደረሱ ከመጡበት አቅጣጫ በስተግራ ታጥፈው ትንሽ እንደተጓዙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎጃም በረንዳ ቅርንጫፍን(3) ያገኛሉ ከዛም ከባንኩ በስተቀኝ በኩል ወደላይ የምትወስድ መንገድ ያገኛሉ ከዛም በየቦታው የምንሰቅላቸውን ባነሮች እየተመለከቱ ከቦታው ይደርሳሉ፡፡ አልያም የአከባቢውን ሰዎች ብጠይቋቸው ይጠቁሟችኀል፡፡

ለበለጠ መረጃ በእጆት ላይ ባለው ስልክ Google map መሰረት ወደ Abebech Gobena Children's Care and Development Association (AGOHELMA) ምራኝ ብትሉት ይመራዎትና ከቦታው ያደርሶታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopi
Abebech Gobena Children's Care and Development Association (AGOHELMA)
Dej. Nesibu St, Addis Ababa
011 155 3622
https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285
TIKVAH-ETHIOPIA pinned «Abebech Gobena Children's Care and Development Association (AGOHELMA) Dej. Nesibu St, Addis Ababa 011 155 3622 https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285»
#ወንዶ_ገነት

ትናንት በወንዶ ገነት ከተማ በተነሳ ተቃውሞ ላይ በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የሦስት ወጣቶች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/WG-07-20
‹‹ባለፈ ታሪክ መነታረክን ትተን በጋራ የምንጋፈጠውን ነገር እንዴት እንሻገር ብለን ማሰብ አለብን፤ የነገን ጥያቄ እና የወደፊቱን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ደግሞ ትምህርት ጥሩ ስንቅ ነው›› የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ
#update የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ሰሚት አካባቢ ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ በዕጣ ለሠራዊት አባላትና ለተቋሙ ሲቪል ሠራተኞች አስረከበ። በዕጣው በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦች ያለ ዕጣ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል። በዕጣው ከተሳተፉት መካከል 20 ከመቶ የቆጠቡ የሠራዊቱ አባላት፣ የመስሪያ ቤቱ ሲቪል ሰራተኞች እንዲሁም ጡረታ የወጡና በዝውውር በሌላ ተቋም የሚሰሩ ይገኙባቸዋል። የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ርክክብ ሴቶችን ልዩ ተጠቃሚ ያደረገ፣ የሠራዊቱን የአገልግሎት ዘመን መሰረት ያደረገና የጠቅላይ ኢታማዦር አለቆችንም ያካተተ ነው ተብሏል። 112ቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች 27 ባለ አራት፣ 34 ባለ ሶስት፣ 19 ባለ ሁለት መኝታ ክፍልና 18 ባለ አንድ መኝታ ናቸው።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FDRE_DEFENCE_FORCE በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦች ያለ ዕጣ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ #የገዳ ስርዓትን ለአለም ማህበረስብ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ እውቅና ሰጠ። ለፕሮፌሰር አስመሮም እውቅና የተሰጣቸው ዩኒቨርስቲው ለዘጠነኛ ጊዜ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 200 ተማሪዎችን ዛሬ በስመረቀበት ወቅት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

"የሕዝብ ለሕዝብ #ትስስሩ የተዘራውን #የውሸት ትርክት ማርከሻ መድኃኒት ነው!" አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ዑመር

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BC-07-20
#የትግራይ_ህዝብ_ፍቅር_ነው!

"ወደ ትግራይ እንዳትሄድ ብለው አስጠንቅቀውኝ ነበር! የመጣነው ከአዳማ፣ ኦሮሚያ ነው። ልጆቻችን ለማስመረቅ ወደ መቐለ እንሄዳለን ብለን ስንናገር #ይቅርባችሁ ተብለናል። እንሄዳለን ብለን ስንወስንም በሉ አፋን ኦሮሞ እንዳትናገሩ ብለው መክረው ስለ ላኩን አሁን ግን የቴሌቪኑ የስርጭት ቋንቋ አማርኛ ቢሆንም ደስታዬ እና መልእክቴን በአፋን ኦሮሞ ነው ማስተላልፈው!" ብለው በኣፋን ኦሮሞ ደስታቸውን መልዕክታቸውን ተናገሩ። (ከትግራይ ህዝብ ጋር 'በ በሬ ወለደ ውሸታቸው ሊለያዩን የሚያስቡ ሰዎች ጤነኛ ናቸውን?) በማለት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በአፋን ኦሮሞ ሐሳባቸውን ገለፁ።

የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛም ጎበዝ ነበር እንደ እሳቸው በአፋን ኦሮሞ ጥያቄውን አስከተለ (አንድ ቋንቋ የሚናገር አንድ ሰው ነው:ሁለት የሚናገር ሁለት ሰው ነው ይባል የለ?) ጋዜጠኛው ብዙ ሰው ነበረ፡፡ እንግዳውም ቀጥለው... በአማርኛ ቋንቋ የትግራይ ህዝብ በሄዱበት መስጊድ፣ ምግብ ቤትና መኝታ ቤት በታላቅ ክብር እንዳስተናገዷቸው ገልፀው አመሰገኑ፡፡"

ፍቅር፤ ሰላም፤ አንድነት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia