TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደኢህዴን #SEPDM መደበኛ ጉባኤዉን ሲያካሂድ የቆየቅ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ በሲዳማ ክልልነት ጉዳዩ ላይ የደረሰበትን ውጤት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ። ይሁን እንጂ ከመግለጫው አስቀድሞ የንቅናቄው ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲዳማ ክልል ሆኖ እንዲመሰረት የሚያስችለውን ውሳኔ አሳልፏል የሚሉ መረጃዎች በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ ። ያም ሆኖ ግን እሰከአሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ከክልሉ ገዢ ፓርቲም ሆነ ከመንግስት በኩል የተሰጠ ይፋዊ ማረጋገጫ የለም። ጉዳዩን ለማጣራት የጀርመን ራድዮ ወደ በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ጹህፈት ቤት ሃላፊዎች ስልክ ደውሎ ያገኘው ምላሽ ተከታዩ ነው፦ «ንቅናቄው የራሱን መግለጫ እስኪያወጣ #ጠብቁ»

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ #ኢቦላ መከሰቱ ተረጋገጠ፡፡ ቫይረሱ በአካባቢው ሊከሰት የቻለው አንድ ታማሚን ጨምሮ 18 ተሳፋሪዎችን ያሳፈረ ተሸክርካሪ በትናንትናው እለት ጠዋት ላይ ከቡተምቦ ተነስቶ ኖርድ ኪቩ ግዛት ውስጥ የመትገኘው ጎማ ከተማ መግባቱን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል። በዚህም ግለሰቡ ላይ በአፋጣኝ በተደረገ ምርመራ የኢቦላ ቫይረስ እንዳለበት የተረጋገጠ ሲሆን፥ ከታማሚው ጋር የተሳፈሩ መንገደኞች እና አሽከርካሪው ክትባት እንዲሰጣቸው መደረጉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ጎማ ከተማ በሀገሪቱ በዓመቱ በሁለተኛ ደረጃ ቫይረሱ ስርጭት ከተመዘገበበት አካባበቢ በስተደቡብ አቅጣጫ የምትገኝ ሰፊ ከተማ መሆኗም ነው የተነገረው። በጎማ ከተማ ቫይረሱ መከሰቱ በሩዋንዳ አወሳኝ አካባቢ እንደመሆኑ እና አካባቢው ህዝብ በሰፊው በሰፈረበት በመሆኑ በፍጥነት ይዘመታል ተብሎ ስጋት መፍጠሩም ተነግሯል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የ100 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በኩል የከሊፋ ፈንድ የቦርድ ሰብሳቢ ሁሴን ጃዚም አል ኖዌስ ተፈራርመውታል። ድጋፉ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የሚውል ነው ተብሏል። ከዚህ ባለፈም ለቴክኖሎጅ እና የፈጠራ ስራዎችን ለመደገፍ ይውላል መባሉንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስኬት ማለት? ~ [ ወድቃለች ከሚሏት ኢትዮጵያ ]

"ስኬት ማለት አሜሪካ መሄድ ቆንጆ ልብስ መልበስ ወይ መኪና መንዳት አይደለም! ወድቃለች ከሚሏት ኢትዮጵያ ወጥተው አድጋለች ከሚሏት አሜሪካ የወደቀ ኑሮ የሚመሩ ብዙ አሉ። ስኬት ማለት ባንተ ኑሮ ውስጥ ሌሎች ኑሮኣቸውን ማምጣት መቻል ማለት ነው።ባንተ ሳቅ ውስጥ የሚስቁ ሰዎችን መፍጠር ባንተ ደስታ ውስጥ የሚደሰቱ ሰዎችን መፍጠር ነው። ስኬትህ የሚናገረው የምትኖርበትን ቦታ ሳይሆን የምትኖርበትን አላማ ነው።" አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ

Via #Getu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሊቢያ የሚገኙ የስደተኛ ማጎሪያ ጣቢያዎች እንዲዘጉ ጠየቀ፡፡ እስር ቤቶቹ ስደተኞችን ለመያዝ የሚያስችል መስፈርትን የሚያሟሉ አለመሆናቸዉንም በምክንያትነት አስቀምጧል፡፡ በሀገሪቱ መንግሥት የሚተዳደሩ እስር ቤቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን በተጎሳቆለ መንገድ እንደያዟቸውም አስታዉቋል፡፡ ከ2 ሳምንታት ቀደም ብሎ በማጎሪያ ጣቢያዎች ላይ በደረሰ ጥቃት 50 ስደተኞች ሲገደሉ 130 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸዉ መነገሩ ይታወሳል፡፡

Via #ETHIOFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወታደራዊ ልምምዳቸው ጀመሩ...

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሚያደርጉትን አመታዊ #ወታደራዊ ልምምድ ጀመሩ። ልምምዱ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ የደረሰችው ስምምነት ሲሆን፥ በዛሬው እለትም የአሜሪካ መከላከያ አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ጋር በጥምረት ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል።

ወታደራዊ ልምምዱ በሶማሊያ በተሰማራው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) አባላትን አቅም ማሳደግ ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ ወደ 1 ሺህ 100 የሚጠጉ ወታደራዊና የመንግስት ሃላፊዎች ይሳተፉበታል።

ልምምዱ የመከላከያ አባላትን ዝግጁነትና አቅም በማሳደግ ሰላምን ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉና በቀጠናው ሰላምን ለማስፈን እንደሚያግዝም ታምኖበታል። ከዚህ ባለፈም ሽብርተኝነትና የእርስ በርስ ግጭቶችን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚያስችልም ተገልጿል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሀዋሳ

የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ 'ይሁንታ ተሰጠ' በሚል በሐዋሳ በርካቶች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ምንም እንኳን ከየትኛውም የመንግሥት አካል የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ ባይኖርም፤ ክልሉን የሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ሲዳማ በክልል እንዲዋቀር 'ያለውን ድጋፍ ገልጿል' በሚል በርካቶች በተለያየ መንገድ ደስታቸውን እየገለጹ ነው።

ተጨማሪውን የቢቢሲ ዘገባ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/SRS-07-15
ቪድዮ #BBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የኢትዮጵያን የምርት ጥራት ደረጃ ያላሟሉ አምስት የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች ይፋ ሆኑ። የንግድ ቁጥጥርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን እንዳለው በተለያዩ የቤት ክዳን ቆርቆሮ መሸጫ ሱቆች ባደረኩት ማጣራት፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁና የደረጃ ማህተም የሌላቸው የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች በገበያ ላይ መኖራቸውን ደርሼበታለው ብሏል፡፡ የባለስልጣኑ አቤቱታ ምርመራ ክስ አቀራረብ ዳሬክቶሬት እንዳስታወቀው፣ ባለስልጣኑ ባደረገው ድንገተኛ ማጣሪያ በአዲስ አበባ መርካቶ በሚገኙ የተለያዩ የቤት ክዳን ቆርቆሮ መሸጫ ሱቆች ባደረገው የገበያ ዳሰሳ መሰረት👉ቢዊሳን bwg 35፤ ጂንዳል ሜድ ኢን ኢንዲያ፤ ቡሁሃን bwg 34 ስማርት በኮከብ የተከበበና፤ ጂንዳል ትሬድ ማርክ ጤና bwg 34፣ ጥላ ምልክት ያላቸውን ምርቶች በኢትዮጲያ ደረጃዎች ማህተም የሌላቸውና የጥራት ደረጃቸውን ያላሟሉ ሆነው አግኝቻቸዋለው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

Via #ኢትዮFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ ተጠናቀቀ
==================================
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት 10 ቀናት ከሰኔ 28 እስከ ሐምሌ 07/2011 ዓ/ም በአገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታዎች እንዲሁም አዳዲስ ክልል ሆኖ የመደራጀት ጥያቄዎች ላይ ሲያካሄድ የነበረውን ስብስባው በስኬት አጠናቋል፡፡

ማእከላዊ ኮሚቴው አገራችን አሁን ያለችበትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የተጀመረው አገራዊ ለውጥ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መክሮ አቋም ወስዷል፡፡ ክልላዊ አደራጃጀቱን በተመለከተ ዝርዝር ሳይንሳዊ ጥናት ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ጊዜ ወስዶ በሳል ውይይት ተካሂዶበታል፤ የቀጣይ አቅጣጫም ተቀምጧል ፡፡ በማያያዝ የክልሉን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ጥልቅ ውይይት ተካሂዶ ጠንካራ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ስለሆነም የደኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን አጠናክሮ የማስቀጠል፣ የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችንና ውጤታቸው ተጠናክረው እንዲሁም የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጽናትና በመርህ ላይ ቆሞ በመታገል ለላቀ ስኬት እንዲበቃ ማእከላዊ ኮሚቴው በሙሉ መግባባብት ላይ በመድረስ ለቀጣይ ተልእኮም በቁርጠኝነት መዘጋጀቱን አረጋግጧል፡፡

ዝርዝር መግለጫው እንደደረሰ ይቀርባል፡፡

Via #ደኢህዴን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የጋምቤላ ክልል አራት የክልሉን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሃላፊነት አነሳ። የጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ኡዶል አጉዋ ለጀርመን ራድዮ እንደገለፁት በክልሉ በተለያዩ ጊዜዎች ከሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊ፣ የክልሉ የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ፣ የጋምቤላ ከተማ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ከሀላፊነታቸዉ ተነስተዋል፡፡ እንደ አቶ ኡዶል ገለፃ ውሳኔው የተላለፈው የክልሉ መሪ ድርጅት፣የሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ጉዳዩን ከገመገመና አቅጣጫ ከሰጠ በሁላ ነዉ። በተነሱት ሃላፊዎች ሌሎች መመደባቸውንና ለጋምቤላ ከተማ ክንቲባነትም እስከ ቀጣዩ ምርጫ የሚያገለግሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሁለት ከንቲባዎች ተመድበዋል ብለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ #ተጠናቋል። ዝርዝር #መግለጫ ይሰጣል ተብሏል። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ሲያካሂድ የነበረውን የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ውይይት በዛሬው እለት አጠናቋል። ውይይቱን አስመልክቶም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

Via ADP
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ/ የማእከላዊ ኮሚቴ አቶ ዩሐንስ ቧያለው የፓርቲው ም/ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል በተመሳሳይ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አገኘው ተሻገርን ለአዴፓ ስራ አስፈፃሚነት እና ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚነት እንዲያድጉ ተደርጓል። ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደርነት ደግሞ አቶ ተመስገን ጥሩነህን በእጩነት እንዲቀርቡ ወስኗል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የአቶ ተመስገን ጥሩነህ አጭር ፕሮፋይል!!

የትውልድ ቦታ፡- ጎጃም፣ ብቸና ደብረወርቅ ልዩ ስሙ ወይራ
የትምህርት ዝግጁነት፡- የመጀመሪያ ዲግሪ በኮምፒውተር ሳይንስ እና የሁለተኛ ዲግሪ በተቋም የለውጥ አመራር
የትዳር ሁኔታ፡- ያገባ

የሰሩባቸው ቦታዎች፡ -

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ሲያገለግል እስከ ሻለቅነት መዕረግ ድረስ የደረሱ
• የሃገር መከላከያ ሰራዊት መረጃ ዋና መምሪያ
• ኤሌክትሮኒክስ መምሪያ
• ቴክኒካል መረጃ መምሪያ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መስራች አመራር የነበሩ
• ከመምሪያ ኃላፊነት እስከ ዋና ዳይሬክተርነት የመሩ
በአማራ ክልል በተለያዩ የኃለፊነት ደረጃ ያገለገሉ
• የርዕሰ-መስተዳድሩ የፀጥታ እና ቴክኖሎጂ አማካሪ
• የአማራ ገጠለር መንገዶች ባለስልጣን ም/ስራ አስኪያጅ
• የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ
• የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ
• የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
. የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር
• የኢትዮቴሌኮም ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ
በመጨረሻም በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ሁነው ሰርተዋል።

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

በዓምላክ ተሰማ የአፍሪካ ዋንጫ #የፍፃሜ ጨዋታን እንዲመራ ተመረጠ። በአፍሪካ ዋንጫ ወሳኝ ጨዋታዎችን እየዳኘ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው በዓምላክ ተሰማ የፍፃሜው ጨዋታ እንዲመራ በካፍ የዳኞች ኮሚቴ ተመርጧል። በግብፅ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ውድድር ሁለት የምድብ፣ አንድ የሩብ ፍፃሜ እና ትላንት ወደ ፍፃሜ ለማለፍ ወሳኝ የነበረው የሴኔጋል እና ቱኒዚያን የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታን የመራ ሲሆን የፊታችን ዓርብ በካይሮ ስታዲየም በአልጄርያ እና ሴኔጋል መካከል የሚደረገውን የፍፃሜ ጨዋታም የሚመራ ይሆናል።

Via ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ራሱን በማክሰም ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን ተቀላቅሏል። ከተመሠረተ 11 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) በዛሬው ዕለት ባከሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ራሱን በማክሰም ኢዜማን መቀላቀሉን የኢራፓ ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ ተናግረዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት የ3ኛ ተከሳሽ ኢሳያስ ዳኘው እና የ4ኛ ተከሳሽ አብዱል ሀፊዝ አህመድ የክስ ዝርዝር በዛሬው እለት በችሎት ተነበበ፡፡

ተጨማሪውን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/FD-07-15
#udate ህንድ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስፔስ ልታደርግ የነበረውን ጉዞ ከአንድ ሰዓት በታች ጊዜ ሲቀረው በቴክኒክ ችግሮች አማካኝነት ሰርዛለች፡፡ ሳተላይቱ በምስራቃዊ ህንድ ስሪሃሪኮታ ስፔስ ሰኞ 2፡51 ለመንቀሳቀስ ፕሮግራም እንደነበረ ቢቢሲ በዘገባው ገልጿል፡፡ የተሰረዘው የስፔስ ጉዞ መቼ እንደሚደረግ በቀጣይ የሚገለፅ መሆኑም ተገልጿል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግስት በአዴፓ እና በህወሐት መካከል ሰሞኑን የታየው አለመግባባት #በሰከነ መንገድ ሊፈታ ይገባል ሲሉ የጨፌ ኦሮሚያ አባላት ገለጹ። ችግሩ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው የዓላማ አንድነት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አፅህሮተ-ስያሜውን ያካተተው ዓርማ ከላይ የምትመለከቱ ነው፡፡ #ADP #አዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) የሥራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴው በክልሉ ወቅታዊ እና በለውጥ ስራዎች ላይ ሲመክር ሰንብቶ ዛሬ ሐምሌ 08/2011 ዓ.ም መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ADP-07-15