#ሲኣን "የለውጥ ሀይሉ ከትክክለኛ #ለውጥ ፈላጊዎች ጋር ሊናበብ ይገባል" - አቶ ዱካሌ ላሚሶ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ሊቀመንበር
ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/SID-07-11-2
ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/SID-07-11-2
#ዜና_ዕረፍት:የቀድሞው የዓረና ፓርቲ ሊቀመንበር እና ያሁኑ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ብርሃኑ በርኸ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
Via አብርሃ ደስታ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via አብርሃ ደስታ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን የኦሮሞ ነፃንት ግንባር ደጋፊዎች በመባል ስዎች በጅምላ እየታሰሩ ነዉ ታባለ። የታሰሩት እና ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት መነፍጋቸውን የታሳሪ ወላጆች እና የምስራቅ ኦሮምያ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ፅህፈት ቤት አስታውቀዋል። የዞኑ ባለሥልጣናት በበኩላቸው በቁጥጥር ሥር የዋሉት ስዎች በወንጀል ተጠርጥረው ነው ብሏል።
Via #VOA
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #VOA
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን አብን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል። አብን ስለሁኔታውም እንዲህ ብሏል፦ "ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው ዕለት ማለትም ሐምሌ 4/2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ አባላቶችን ለመጠየቅ በሄዱበት ወቅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊውን አቶ ክርስቲያን ታደለን በቦታው የነበሩ ደህንነቶች ነጥለው እንፈልግኃለን በማለት አስረውታል።"
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ: "መልካም ወጣት ለኢትዮጵያ #አንድነት 2011" የተሰኘ በአገልጋይ #ዮናታን_አክሊሉ የሚዘጋጅ የወጣቶች መርሃ ግብር #በትላንትናው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በተገኙበት መከፈቱ ተሰምቷል። በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የገቢዎች ሚንስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተው ነበር።
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሶማሊያ ጦር ከሁለት ዓመታት በፊት በሞቅዲሹ በሚገኝ ሆቴል ላይ ጥቃት በመፈጸም የተከሰሱ ሦስት ሰዎች በሞት መቀጣታቸውን አስታወቀ።
ሦስቱ ሰዎች በትላንትናው ዕለት በሞቃዲሾ በሚገኝ የፖሊስ ማሰልጠኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ በጥይት #ተደብድበው መገደላቸውን የሶማሊያ ጦር ባሰራጨው መግለጫ ጠቁሟል።
በጎርጎሮሳዊው ጥቅምት 2017 ዓ.ም. ናሳ ሐብሎድ በተባለው ሆቴል ላይ በተፈጸመው እና ሦስቱ ሰዎች ተሳትፈውበታል በተባለው ጥቃት 18 ሰዎች ሲገደሉ 47 ሰዎች ቆስለዋል። ተከሳሾቹ የአል-ሸባብ ታጣቂ ቡድን አባላት ሲሆኑ በጥቃቱ ወቅት በቁጥጥር ሥር የዋሉ ነበሩ።
Via #DW
ፎቶ:ፋይል
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሦስቱ ሰዎች በትላንትናው ዕለት በሞቃዲሾ በሚገኝ የፖሊስ ማሰልጠኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ በጥይት #ተደብድበው መገደላቸውን የሶማሊያ ጦር ባሰራጨው መግለጫ ጠቁሟል።
በጎርጎሮሳዊው ጥቅምት 2017 ዓ.ም. ናሳ ሐብሎድ በተባለው ሆቴል ላይ በተፈጸመው እና ሦስቱ ሰዎች ተሳትፈውበታል በተባለው ጥቃት 18 ሰዎች ሲገደሉ 47 ሰዎች ቆስለዋል። ተከሳሾቹ የአል-ሸባብ ታጣቂ ቡድን አባላት ሲሆኑ በጥቃቱ ወቅት በቁጥጥር ሥር የዋሉ ነበሩ።
Via #DW
ፎቶ:ፋይል
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Meda
በፌደራሊዝም ስርዓትና በኢፌዴሪ ህገ መንግስት ዙሪያ የሚያተኩር የምሁራን የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል። መቐለ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን ተሳትፈዋል።
የውይይት መድረኩ ነፃ ሃሳብ የሚንፀባረቅበትና በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት የሚደረግበት መሆኑን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም መሰል መድረኮችን ማዘጋጀቱን የገለጹት ፕሮፌሰር ክንደያ፥ በዚህም ሀገሪቱ የምትከተለውን የፌደራል ስርዓትን የሚያጠናክሩ ሃሳቦች መገኘታቸውን አስታውሰዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፖለቲካ ምሁርና ተንታኝ ፕሮፌሰር ህዝቄል ገቢሳ የፌዴራል ስርዓት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ጥያቄ የመለሰ ስርዓት መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ ስርዓት በተፃራሪ መሄድ ሀገሪቱን ወደ አልተፈለገ ሁከትና ብጥብጥ ሊያመራት ይችላል የሚል ሀሳብ አስቀምጠዋል።
ህግ መንግስቱ እንዲሻሻል ጥያቄ የሚያቀርቡ አካላት መኖራቸውን ያስታወሱት ፕሮፌሰር ህዝቄል፥ የሚነሱ ጥያቄችን ህገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ መመለስ እንደሚቻል አብራርተዋል።
Via #FBC

#NewsAlert የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2012 አገር አቀፍ ምርጫ በህገ-መንግስቱ መሰረት በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲካሄድ የተጣለበትን ሃላፊነት እንደሚወጣ አፈ-ጉባኤው ገለጹ። ምክር ቤቱ የ2011 በጀት ዓመት የስራ ዘመኑን ቢያጠናቅቅም የምርጫ አዋጁን በልዩ ስብሰባ ሊያጸድቀው እንደሚችልም ነው የተናገሩት።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ዛሬ የምክር ቤቱን የአንድ ዓመት የስራ ቆይታ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በቀጣዩ ዓመት የሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲካሄድ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት መሰረት የአንድ የፓርላማ ዘመን ቆይታ አምስት ዓመት ነው። በዚህም መሰረት አምስተኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀጣዩ ዓመት የስራ ዘመኑን ያጠናቅቃል። በዚሁ ዓመት የሚካሄደው አገራዊ ምርጫም በህገ-መንንግስቱ መሰረት በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ምክር ቤቱ የተጣለበትን ሃላፊነት እንደሚወጣ አፈ-ጉባኤው ገልጸዋል። ምክር ቤቱ የምርጫ ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ የምርጫ ህጉን ማሻሻል አንዱ ነው።
Via #ENA

#ሀዋሳ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮምሽን የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የወጪና ገቢ እቃዎች ጉምሩክ አገልግሎት በሐዋሳ ከተማ መጀመሩን አስታወቀ። አገልግሎቱ ከሀምሌ 1 2011ዓ.ም ጀምሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል።
አገልግሎቱ በሀዋሳ መጀመሩ መርካቶ ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረውን የአስመጪነት ተግባር ያልተማከለ በማድረግ የክልል ነጋዴዎች ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያስቀር ነው፡፡ ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ሸቀጦችን እንዲያገኙ ለማድረግ እንደሚረዳም ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም የክልሉን ነጋዴዎች አቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ እና በመርካቶ የሚሰሩ ህገ ወጥ ስራዎችን ለማዳከም እና ለማጋለጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

የገዛ ባለቤቱ ላይ #አሲድ እንዲደፋባት ያደረገዉ ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ። 👉https://telegra.ph/DA-07-11
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ግምገማ ሂደቱን በተመለከተ የቀረበ አጭር ማብራሪያ፦
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 28/2011 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይት መድረኩም አገራዊ እና ክልላዊ፣ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን በዝርዝርና በጥልቀት እየገመገመ ይገኛል፡፡ በክልሉ ህዝቦች የተነሱ የአደረጃጀት እና የመልካም አስተዳደር ጥቄዎችን አስመልክቶ ማዕከላዊ ኮሚቴው ፍፁም በሆነ በሰከነና በኃላፊነት መንፈስ እየተወያየ ይገኛል፡፡
ውይይቱም እጅግ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ በሳል በሆነ መንገድ እየተካሄደ ያለ ሲሆን የህዝቡን የጋራና ዘላቂ ጥቅሞችን እንዲያረጋግጥና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችል ውይይት ማዕከላዊ ኮሚቴው እያካሄደ ይገኛል፡፡
ደኢህዴን በክልሉ ህዝቦች የተነሱ የአደረጃጀት ጥያቄዎችንም አስመልክቶ ዝርዝር እና ሳይንሳዊ በሆነ አግባብ ሲያስጠና በቆየው የጥናት ውጤት ላይ ማዕከላዊ ኮሚቴዉ እጅግ ኃላፊነት በተሞላበት አኳሃን እየተወያየ ይገኛል፡፡ በክልሉ ህዝቦች የተነሱ ጥያቄዎች በመሪ ድርጅቱ ደኢህዴን እና በህዝቡ ፍቃድና ይሁንታ ብቻ ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጠው ነው፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው ልዩ ስብሰባውን ሲያጠቃልል ለአባላቱና ለክልሉ ህዝቦች እንዲሁም ለደጋፊ ኃይሎች ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ የክልሉ ህዝብም በሚቀርቡ የመፍትሄ ሐሳቦች ላይ በየደረጃው በሚዘጋጁ የውይይት መድረኮች እንዲሳተፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጪ በተለያዩ ሃይሎች በሚሰራጨው ውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ሳይደነጋገር በትግስት እንዲጠብቅ ደኢህዴን ጥሪውን ያስተላልፋል።
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን #በመርሐቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማ አስገድዶ ከመድፈር ሙከራ ጋር ተያይዞ ህይወት አጥፍቷል የተባለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ጽኑ አስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AA-07-11-5
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AA-07-11-5
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ከአዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ፦ https://telegra.ph/ADP-07-12
#FakeNews የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አብዲ መሃመድ /አብዲ ኢሌ/ በማረሚያ ቤት ውስጥ ህይወቱ አለፈ እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የስዋዚላንድ መንግስት የድግምትና ጥንቆላ ውድድር በሃገሪቱ ማገዱን ኤ ኤፍ ፒን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከጥንቆላና ጥንታዊ ከሆኑ ልማዶች ጋር የተያያዘ ድርጊት የሚከውኑ ግለሰቦች ከተገኙ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሃገሪቱ የመንግሰት ቃል-አቀባይ ፐርሲ ሲመላኔ መናገራቸውን በዘገባው ተመልክቷል፡፡
በሳምንቱ መጨረሻም በሃገሪቱ የሚገኙ የድግምት ፈዋሾች የእርስ በርስ የጥንቆላና ድግምት ፉክክር ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው እንደነበር አጃንስ ፋራንስ ፕሬስ በዘገባው ጠቅሷል።
የአፍሪካ ጋማ የተሰኘው የጥንት አባቶች ባህላዊ የፈውስ ፉክክር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሊዘጋጅ እንደነበርም ታይምስ ኦፍ ስዋዚላንድን በዋቢነት በመጥቀስ ዘገባው አመልክቷል።
ባህላዊ ፈዋሽ የነበረው ሚስተር ጋማ እኤአ በ1982 ህልፈተ ህይወታቸው በተሰማው በዳግማዊ ሶቡዛ የንግስና ዘመን ተመሳሳይ በሆነ ውድድር ላይ ተሳትፎ ያደርጉ እንደነበርም ታይምስ ኦፍ ስዋዚላንድ አክሏል።
ንጉሱ ይህን #እርምጃ ለመውሰድ የወሰኑት አንዳንድ ሃሰተኛ ፈዋሾችን ለማጥፍት ፈልገው ይሆናል፤ ነገር ግን ይህን ትክክለኛ ውድድር ባልተደራጀ ሁኔታ መከልከል ተገቢ አይደለም ሲሉሚስተር ጋማ መናገራቸውን ዘገባው አስፍሯል፡፡
Via #BBC/#ENA

የዕለቱ መልዕክት፦
ሰላምን ባህል ማድረግ የሰላም ጥቅምን በመገንዘብ ለሰላም ምቹ የሆኑ ነገሮችን ለይቶ በትኩረት መንቀሳቀስ ሲቻል ነው፡፡
ሰላም ካለ፡-
•ለውጥና እድገት ማምጣት፤
•ከአድሏዊ አሰራር ነጻ መሆን፤
•ግጭትን በውይይት መፍታት፤
•ከማህበራዊ መፈረካከስ ወደ አንድነት መምጣት፤
•ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎን ማሳደግ፤
•ነፃ አስተሳሰብን ማዳበር፤
•የተፈጥሮ ደህንነትን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ሰላማችን ህልውናችን ነው!
ሰላም እደሩ!

አደገኛ እፅ ሲያዘዋውር የተገኘው #ኢትዮጲያዊ ወጣት በእስራት ተቀጣ፡፡ ተከሳሽ ታፈሰ ተስፋየ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 525 (1ለ) ስር የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት በመተላለፍ አደገኛ እፅችን በማዘዋወር ወንጀል ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡
ተከሳሽ ታህሳስ 5 ቀን 2010 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 5 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኢትዮጲያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ታይላንድ ባንኮክ ለመሄድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ከደረሰ በኋላ ለመብረር በዝግጅት ላይ እንዳለ በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ እፅ ክትትልና ቁጥጥር ዲቪዥን አባሎች በተደረገ ፍተሻ በያዘው የጀርባ ቦርሳ ውስጥ በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ክብደቱ 3 ኪ.ግ የሆነ የኮኬይን ዕፅ ይዞ መገኘቱን በክሱ ላይ ተመልክቷል፡፡
ተከሳሽ በኢትዮጲያ ደረጃ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወር እንዲሁም በጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከለ እፅ ይዞ በመገኘቱ በፈፀመው መርዛማ እፆችን ይዞ በመገኘትና በማዘዋወር ወንጀል መከሰሱን የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ያብራራል፡፡
ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽን ጥፋተኛ የሚያስብሉ የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ውጤቶችን፣ የሰውና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችን በግብዓትነት በመጠቀም ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ ተከራክሯል፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ተኛ የወንጀል ችሎት ሀምሌ 02 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

#NewsAlert የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ማክሸፉን አስታወቀ። ምክር ቤቱ በሀገሪቱ የመንግሥት ቴሌቪዥን ባቀረበው መግለጫ እንዳለው ከከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ጋር በተገናኘ 16 ወታደራዊ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ጀኔራል ጀማል ኦማር በመግለጫቸው መፈንቅል መንግስት የተሞከረው በተወሰኑ ወታደራዊ መኮንኖች፣ የደህንነት አባላት እና ከሃላፊነት የተሰናበቱ አካላት መሆኑን ተናግረዋል።
መፈንቅል መንግስቱ መቼ እንደተሞከረ ያልተናገሩት ጀኔራሉ፥ በመደበኛ ወታደራዊ ሃይሉ መክሸፉን ነው ያነሱት። ሴራውን በማቀነባበር የተሳተፉ ተጨማሪ ሃይሎችን ለመያዝም ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ጀኔራል ኦማር ገልጸዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት እና የተቃዋሚ ሃይሎች ሀገሪቱን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚመራ የሽግግር ምክር ቤት ለማቋቋም መስማማታቸው ይታወሳል።
ምንጭ፦አል ጄዚራ