TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-SPORT
ሞሮኳዊው የዳኛ ባምላክ ደብዳቢ ተቀጡ!

ኢትዮጵያዊውን ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማን የደበደቡት የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት፣ የካፍ ምክትል ፕሬዚዳንትና የሞሮኮው ቤርካን ክለብ የክብር ፕሬዚዳንት ፉዚ ሌክጃ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ ለአንድ አመት ከማንኛውም ስፖርታዊ አመራር ታግደዋል።

Via #PetrosAshenafi
@tikvahethsport
#update የአዲስ አበባ አዴፓ ኮሚቴ በአማራ ክልል መስዋእት ለሆኑ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለተጎጂ ቤተሰቦች የመስርያ ቦታ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የአዲስ አበባ አዴፓ ኮሚቴ ከከተማው ህብረተሰብ በአጭር ቀናት ውስጥ ያሰባሰበውን ከ5 ሚሊዮን በላይ ገንዘብ በአማራ ክልል ሰኔ 15 መስዋእት ለሆኑት አመራሮች ቤተሰቦች ለሶስቱም ቤተሰቦች በእኩል መጠን ትናንት በሸራተን አዲስ ሆቴል ለተጎጂዎቹ ማስታወሻ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ አበርክቷል፡፡

Via #EPA
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አማረ አምሳሉን ጨምሮ በ10 የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል።

ተከሳሾች፦

1ኛ ተከሳሽ አማረ አምሳሉ፣
2ኛ ተከሳሽ ወልደጊዮርጊስ ወልዱ፣
3ኛ ተከሳሽ ኢሳያስ ዳኘው፣
4ኛ ተከሳሽ አብዱል ሃፊዝ አህመድ፣
5ኛ ተከሳሽ ማስረሻ ጥላሁን፣
6ኛ ተከሳሽ ሰይፈ ኃይለስላሴ፣
7ኛ ተከሳሽ ፀጋየ መኮንን፣
8ኛ ተከሳሽ አይተንፍስ ወርቁ፣
9ኛ ተከሳሽ ጌታሁን ያሲን እንዲሁም
10ኛ ተከሳሽ ሳሙኤል ፈጠነ ሲሆኑ ስልጣንን #ያላግባብ በመገልገል እንዲሁም የመንግስትን ስራ በማያመች አኳኋን በመምራት ከባድ የሙስና ወንጀል ከ259 ሚሊየን ብር በላይ በኢትዮ ቴሌኮም፣ በህዝብና በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀል ተጠርጥረው ዐቃቤ ሕግ በትላንትናው ዕለት ክሱን መስርቷል፡፡

Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
ፎቶ: ፋይል
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሶስት የትእምት ኩባንያ ሼሮች ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ። የመሰቦ ሲሜንቶ ፋብሪካ፣ ሱር ኮንስትራክሽንና የትራንስ ኢትዮጵያ ሼሮች ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ዝግጅት መደረጉን የትግራይ ክልል አስታወቀ፡፡

በምክትል ርእሰ መስተዳድር መዓረግ የትግራይ ክልል የከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብርሃም ተኸስተ የትግራይ ክልል ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በኩባንያዎቹ በተዘጋጀው የሼር ሽያጭ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ ባለፈ የግል ኩባንያ በማቋቋም በክልሉ ባለው የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት የሚፈልጉ ባለሀብቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉም ነው የተነገረው።

Via #fbc
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች እና አካባቢዎች ያሉ ነባር ህንጻዎቹን በአዲስ ለመቀየር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ተናገሩ። ፕሬዘዳንቱ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ ዩኒቨርሲቲው በህንጻ ግንባታ በኩል በጣም ኋላ ቀርና ያረጁ በመሆናቸው ለመማር ማስተማር ምቹ አልነበሩም፤ በዩኒቨርሲቲው በቅርስነት ከሚቀሩት በስተቀር ሌሎቹ በአዳዲስ ግንባታዎች ይተካሉ ብለዋል።

Via EPA
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በየመንገዱ የሚሸጡ ፀረ ተባይ መድኃኒቶችን ባለመግዛት እና #በማጋለጥ ለሕግ ማቅረብ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/AMRS-07-10
#update የሊቢያ ባለስልጣናት ባሳለፍነው ሳምንት ትሪፖል አቅራብያ ባለችው ታጁራ ፊንዳታ ደርሶ ከነበረበት የስደተኞች ማቆያ ማዕከል ስደተኞችን በማስወጣት ላይ መሆናቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰባዓዊ እና የስደተኞች ጉዳይ መግለፁን ታወቀ።

የጄኔራል ካህሊፋ ሃፍታር ታማኝ ወታደሮች አድርሰውታል በተባለው ጥቃት 50 ስደተኞች የተገደሉ ሲሆን የጄኔራሉ ታማኝ ሃይሎች ግን ለጥቃቱ መንግስትን ተጠያቂ ያደርጋሉ።
በአብዛኛው በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡት በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር ከሳሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች እንደሆኑ ይታመናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

Via #BBC
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአቋም መግለጫ ደብዳቤ ልካያለሁ #በአፋጣኝ ውሳኔ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።

ክለቡ የላከው ልኬያለሁ የሚለው ደብዳቤ👇
https://telegra.ph/FasilKenema-07-10
"ክለቦች ለመገናኛ ብዙሃን የሚያደርሷቸው #የሀሰት ውንጀላዎች የኢትዮጵያን እግር ኳስ ዕድገትን ያቀጭጨዋል እንጂ አያሳድገውም!" የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ቻይና በኢትዮጵያ ረዥሙን ድልድይ ልትገነባ ነው። ኢትዮጵያ 49 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተያዘለት ረዥም ድልድይ ልትገነባ መሆኗን ፌስ ቱ ፌስ አፍሪካ በድረገፁ አስነበበ፡፡

ግንባታውም በቻይናው ሲሲሲሲ ኮንስትራክሽን ኩባንያ የሚከናወን ሲሆን ኩባንያው የድልድዩን ግንባታና ዲዛይን በሚመለከት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የስምምነት ፊርማ ማስቀመጣቸውን ዘገባው አስፍሯል፡፡

በባህርዳር አካባቢ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ድልድይ በ3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ዕቅድ ተይዞለታል፡፡

በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ድልድይ 21.5 ሜትር ስፋትና ሶስት መስመሮችን የሚይዝ ሲሆን ይህም የብስክሌት፣ የመኪና መስተላለፊያና የእግረኛ መንገድን የሚያካትት እንደሆነ በዘገባው ሰፍሯል፡፡ የፕሮጀክቱ ወጪ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ስለመሆኑም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

የባህርዳሩ አባይ ድልድይ ከተጠናቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ እረዥሙ ድልድይ እንደሚሆን የታወቀ ሲሆን ጥቅምት ወር 2006 ለትራፊክ ክፍት የሆነውን 319 ሜትር ርዝመት ያለውን የባሽሎ ወንዝ ድልድይ በርዝመት እንደሚበልጥ ዘገባው አመልክቷል፡፡

Via #ENA
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የጥላቻ_ንግግሮች: የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሆነው ትዊተር የጥላቻ ንግግር የሚነዙ ተጠቃሚዎችን ከገጹ እንደሚያግድ አስታወቀ። በተለይም ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ ሰብአዊነትን የሚያጎድፉ ይዘት ያላቸው መረጃዎችና እና ጽሁፎችን የሚለቁ አካላትን ሙሉ በሙሉ ከገጹ እንደሚያግድ ነው ያስታወቀው። ኩባንያው ይህንን ለማድረግ የሚረዳው አዲስ #ህግ ማውጣቱም ተነግሯል።

በአዲሱ የትዊተር ሀግ መሰረት ከዚህ በፊት በገጹ የተለቀቁ የጥላቻ ንግግሮችም ከገጹ እንዲነሱ እንደሚደረግ ታውቋል። ሆኖም ግን ግለሰቦቹ የጥላቻ ንግግሮቹን የለቀቁት ህጉ ከመውጣቱ በፊት በመሆኑ ከገጹ እንደማይታገዱ ተነግሯል።

ትዊተር ከዚህ ቀደምም የመተግበሪያውን ህግና ደንብ የሚተላለፉ የሃገር መሪዎችና ፖለቲከኞች የሚያሰራጩትን መልዕክት ሊደብቅ መሆኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ትዊተር ይህን ውሳኔ ያሳለፈው የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች የመተግበሪያውን ህግና ደንብ በመጣስ ተገቢ ያልሆኑ መረጃዎችን ለተከታዮቻቻው በማሰራጨታቸው እንደሆነም ነው በወቅቱ የተጠቀመው።

ከዚህ በተጨማሪም #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው ተከትሎ ችግሩን ከስሩ ለማድረቅ ትዊተር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሀሰተኛ አካውንቶችን ማገዱም ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.cnet.com---/#fbc/
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CPJ ሲፒጄ "ለውጥ እየተካሄደ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ ፕሬስን ለመቆጣጠር አሮጌውን ዘዴ እየተጠቀመች ነው" በሚል ባወጣው ሪፖርት የኢንትርኔት አገልግሎትን ማቋረጥና ጋዜጠኞችን ማሰርን እንደምክንያትነት ጠቅሷል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/CPJ-07-10
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከደቡብ ኮሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካንግ ዩንግ ኋ ጋር ተወያዩ። በውይይታቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል ባለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም የግብርና እና ጉምሩክ ስርዓቱን ማዘመን በሚቻልበት አግባብ ላይም ተወያይተዋል። በተጨማሪም በትምህርቱ ዘርፍ ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት እንዲያደርጉም ጋብዘዋቸዋል።

Via #fbc
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ዑማ የስልጣን ዘመናቸው ስላለቀ ሊነሱ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት አሳሰበ። የአዲስ አበባ ምክር ቤት የስልጣን ዘመን ባለፈው አመት ተጠናቆ ለተጨማሪ 1 ዓመት ተራዝሞ እንደነበር ያስታወሰው ምክር ቤቱ የተጨመረው አንድ አመትም ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም #የተጠናቀቀ ቢሆንም ታከለ ዑማ ከህግ ውጭ አሁንም ስልጣን ላይ ናቸው ብሏል።

🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ #ተቃውሞ ገጠመው!

ዛሬ በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአ/አ ባላደራ ምክርቤት መግለጫ ተቃውሞ ማስተናገዱ ተሰምቷል። መግለጫውን ሲቃወሙ የነበሩት ወጣቶች ይህን ሲሉም ተደምጧል፦

"ኢትዮጵያን በደማችን ነው ያቆምናት!!"

"ይሄው🇪🇹ባንዲራችን!"

"ጥያቄ አለን! እንጮሃለን~እኛ የሚያስፈልገን ሃገር መገንባት ነው እንጂ ሀገር ማፍረስ አይደለም!!"

"በደም የተገነባች ሀገር ናት"

"የሚያፈርሰንን አንፈልግም፤ በብሄር መከፋፈል አንፈልግም!"

"አትከፋፍላትም፤ አይሳካልህም፤አይሳካላችሁም"

"ዛሬም ነገም ኢትዮጵያ ትኖራለች!"

"ኢትዮጵያ አትፈርስም!"

"የራስን ቤት ማፍረስ አይቻልም!"

#TIKVAH_ETH
ቪድዮ: ኢትዮ ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ወጣቶቹ መግለጫው ከሚሰጥበት አዳራሽ ከውጡ በኃላ ለጋዜጠኞች የተናገሩት፦

"ባለስልጣናትን እየሰደበ፤ ክብራቸውን እያንቋሸሸ፤ ማንነታቸውን እየተቸ፤ እንዴት ነው መግለጫ የሚሰጠው? ካለፈው ወራት የተለየ መግለጫ እየሰጠ አይደለም፤ ሁሌም ስድብ ነው፣ ሁሌም ትችት ነው፣ ሁሌም የአንድን ብሄረሰብ ማንነት ማንቋሸሽ ነው። ኦሮሞን ያገለለ ኢትዮጵያ እንዴት ሙሉ ሊሆን ይችላል?"
.
.
"ፊንፊኔ/አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ከተማ ናት ከተባለ እንዴት ኦሮሚያን ሊያገል ይችላል?እንዴት የኦሮሞ ተማሪ ተምሮ ፊንፊኔ ውስጥ ስራ ሊያጣ መግለጫ ይወጣበታል? ኢንጂነር ታከለ አ/አ ቢያስተዳድሩ ምን ችግር አለው? ካፒታላችን እሷ ሆና ቆሻሻው የሚጣልብን በኛ ላይ ነው..."

ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ጥያቄ፦

ለምን በስርዓት ኢትዮጵያዊ ባህልን ጠብቃችሁ ጥያቄ አልጠየቃችሁም?

ከወጣቶቹ አንዱ፦

"ከዚህ በፊት መጥቼ ነበር፤ #ለጋዜጠኛ ብቻ ነው የሚሰጠው ለሲቪሉ አይሰጥም። ጋዜጠኛ ብቻ ነው የሚጠይቀው አሉ። አሁንም ልጠይቅ ብሞክር ለጋዜጠኞች ብቻ ነው #የምንሰጠው ሲቪል የመጣችሁ በግላችሁ አንሰጥም ነው ያሉን፤ ስለዚህ መጠየቅ አንችልም ያለን እድል...። እኛ ጥያቄ ይዘን መጥተናል፤ ወሳኝ ወሳኝ #ጥያቄ በግላችን ይዘናል ጥያቄዎችን ለመጠየቅ መብት ስለማይሰጥ ይሄ ሰውዬ ምንም ማድረግ አንችልም።...አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት #የሁላችንም ናት። እሱ ግን ኦሮሞን ባገለለ ...ታከለ መጤ! ማነው የዚህች ሀገር ተወላጅ? ማነው የአ/አ ተወላጅ?

"መጠየቅ ትችላላችሁ እየተባልን እየተገፈተርን ነበር። ከቦታው ተገፍትረን ወጥተን ነው እናተም ቪድዮ አላችሁ ስንገፈተር..."

#TIKVAH_ETH
ቪድዮ: ኢትዮ ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ማምረቻ እንዲሆን ታስቦ የተገነባው የባሕር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ‹ሆፕ ለን› ለተባለ ግዙፍ የቻይና ሆንግ ኮንግ ኩባንያ ተላልፏል፡፡

🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ከባድ መኪኖችን በቀን ለማሽከርከር አሳማኝ ምክንያት ላላቸው ፈቃድ እየተሰጠ ነው። #AddisAbeba

Via #ShegerFM
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርጉ ነው። ወታደራዊ ልምምዱ የአሜሪካ መከላከያ አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ጋር በጥምረት የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል። ልምምዱ #በሶማሊያ በተሰማራው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) አባላትን አቅም ማሳደግ ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ ወደ 1 ሺህ 100 የሚጠጉ ወታደራዊና የመንግስት ሃላፊዎች ይሳተፉበታል። ልምምዱ የመከላከያ አባላትን ዝግጁነትና አቅም በማሳደግ ሰላምን ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉና በቀጠናው ሰላምን ለማስፈን እንደሚያግዝም ታምኖበታል። የፊታችን ሰኞ የሚጀመረው የ2019 ወታደራዊ ልምምድ ለ17 ቀናት እንደሚቆይ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኤምባሲን ጠቅሶ ኤፍ ቢሲ ዘቧል።

በወታደራዊ ልምምዱ ላይ፦

•ከብራዚል
•ከብሩንዲ
•ከካናዳ
•ከጂቡቲ
•ከፈረንሳይ
•ከጀርመን
•ከጣሊያን
•ከኬንያ
•ከኔዘርላንድስ
•ከሩዋንዳ
•ከሶማሊያ
•ከኡጋንዳ እና ዩናይትድ ኪንግደም የተውጣጡ #ወታደሮች ይሳተፋሉ።

Via #EPA/fbc/
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ ምርት አይነቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳሰበ። ባለስልጣኑ ለfbc በላከው መግለጫ በምግቦቹ ጥራትና ደህንነት ላይ ባደረገው የገበያ ጥናት የምግብ ምርቶቹ መሰረታዊ የገላጭ የፅሁፍ ክፍተት ያለባቸው፣ የሚመረቱበት ቦታ የማይታወቅ፣ የንጥረ ነገር ይዘት የሌላቸው፣ አምራች ድርጅቶቹ የማይታወቁ፣ የምርት መለያ ቁጥር፣ የተመረቱበት ጊዜ እና የምርቱ ማብቂያ ጊዜ ገላጽ ፅሁፍ የሌላቸው ናቸው ብሏል። ከዚህር ተያይዞም ምርቶቹን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸውና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቹን በአፋጣኝ ከገበያ ላይ እንዲሰበስቡም ጥሪውን አቅርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ህብተረሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተከለከሉ የምግብ አይነት ዝርዝሮች፦

የከረሚላ ምርቶች

•ጆሊ ሎሊፖፕ
•አናናስ ከረሚላ
•ኮላስ ከረሚላ
•ኦሊ ፖፕ
•ቤስት ከረሚላ
•የስ ከረሚላ (ኮፊ ከረሚላ)
•ማሚ ሎሊ ፖፕ
•ሳራ ከረሚላ
•ጃር ሎሊ ፖፕ
•ጸሃይ ሎሊ ፖፕ
•ዩኒክ ሎሊ ፖፕ
•እንጆሪ ከረሚላ
•ብርቱካን ከረሚላ
•ይናቱ ሎሊ ፖፕ እና ሃላዋ ከረሚላ

የማር ምርቶች፦

•አፍያ የተፈጥሮ ማር
•ሪትም ማር እና በላይ ማር

የገበታ ጨው፦

•ዊዲ
•ሱላ
•ናይ
•ሃያት
•አቤት
•በእምነት
•እናት
•አባይ
•አባት፣ ሴፍ እና ጣዕም የገበታ ጨው

የለውዝ ቅቤ፦

•ደስታ
•አስነብ
•ኑኑ
•አቢሲኒያ
•ብስራት
•ፈሌ
•ሳባ፣ አዳ እና አደይ የለውዝ ቅቤ

የኑግ ዘይት፦

•አደይ አበባ እና ቀመር የኑግ ዘይት

አልሚ የህጻናት ምግቦች፦

•ምሳሌ የህጻናት ምግብ
•ኤልሞ የልጆች ምግብ
•ሂሩት የህጻናት አጃ
•ዘይነብ የህጻናት አጥሚት
•ተወዳጅ ገንቢ የህጻናት አጥሚት
•ተወዳጅ የህጻናት ሽሮ እና ፋሚሊ ሃይል ሰጭና ገንቢ የህጻናት ሽሮ

ቪንቶ፦

•ዴኮ
•እስፔሻል
•ዳና
•ቃና
•ላራ
•ዛጎል አቼቶ
•ናይስ አቼቶ
•አምቴሳ አቼቶ
•ማይ አቼቶ
•መስ አቼቶ እና ቫይኪንግ አቼቶ ምርቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው #ታግደዋል

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia