TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FakeNews ሌተናል ጄነራል #ሃሰን_ኢብራሂም ታሰሩ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጎንደር #Gondar

ጎንደር ከተማ #ሰላማዊ መሆንዋን ምክትል ከንቲባ በሪሁን ካሣዉ ገልፀዋል። ትላንት አነስተኛ ውዝግብ ከተማ ውስጥ መፈጠሩን ያነሱት ምክትል ከንቲባው የነበረውን አነስተኛ ዉዝግብ ተጠቅመዉ ረብሻ ለማስነሳት የሞከሩ እና አንዳንድ ያልተገባ ነገር ለመፈፀም የሞከሩ፤ ድርጊታቸዉን ሳይፈፅሙ በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል፤ #ከጀርባቸዉ ማን እንዳለም እያጣራን ነዉ ሲሉ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

Via #DW
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትላንትናው ዕለት በጎንደር ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር አንዳንድ የንግድ ተቋማት ላይ #ጉዳት መድረሱን፤ የደረሰውን የጉዳት መጠንም የማጣራት ስራ መጀመሩን #የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ኮማንደር ማረልኝ ወንድሙ ተናግረዋል። በጥፋቱ የተሳተፉ ግለሰቦችም በቀጣይ የማጣራት ስራ ከተከናወነ በኋላ በህግ #ተጠያቂ እንደሚደረጉም ገልፀዋል።

🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የባሕር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ ለባለሀብቶች ሊሰጥ ነው፡፡ ከሆንግ ኮንግ የመጡ የባለሀብቶች ቡድን አባላት የኢንዱስትሪ ፓርኩን #ነገ እንደሚረከቡ ታውቋል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአገር አቀፍ ደረጃ ተከስቶ የነበረው የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ #እየቀነሰ ቢሆንም ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል።

ተጨማሪ ያብቡ👇
https://telegra.ph/CH-07-09
#update አትሌት ደራርቱ ቱሉ በኢጣልያ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ሽልማት የህይወት ዘመን የስፖርታዊ ጨዋነት ዘርፍ ተሸላሚ ሆነች። ሽልማቱ ኢጣልያ በሚገኝ ”ፕሪሞ ኢንተርናሽናል ፌር ፕሌይ” በተሰኘ ድርጅት በስፖርቱ ታሪክ የሰሩ፣ በታማኝነት የተወዳደሩ እና ዘርፉን ያገለገሉና ስፖርትን በማስፋፋት ታሪክ ለሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና የሚሰጥበት ነው።

🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የአዲስ_አበባ_ሞተረኞች...

የሞተር ብስክሌት #እገዳው በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን–የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/Mot-07-09-2
የዕለቱ መልዕክት፦

"ሰዎች ንቃተ–ህሊና ቢኖራቸው ኖሮ በአለም ላይ በርካታ #ጦርነቶችን ማስወገድ ይችሉ ነበር!" #ጉጅረየፍ
___________________________________________

ህሊናዊ ንቃት ማለት #እውነታውንና #ገሀዳዊውን አለም በትክክል #መረዳት ማለት ነው፤ ይህ ብቻ ሳይሆን አንድ ሰው እርሱም ሆነ ሌሎች የሚያደርጉትን ነገር ውጤቱን ወይንም #መዘዙን የሚረዳ መሆን አለበት።

ራሳችንን እንፈትሽ!
ሰላም እደሩ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን ‹‹ፍትሕ ካልተሰጠኝ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው ማንኛውም ውድድር አልሳተፍም›› ብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/STG-07-10

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የፌደራሉ ጠቅላይ አቃቢ ህግ በቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አማረ አምሳሉን ጨምሮ 10 የሥራ ኃላፊና ሰራተኞች ላይ ክስ መሰረተ።

አቃቢ ህግ በክሱ እንዳመላከተው፤ ተከሳሾች በሶማሌ ክልል የሞባይል ማስፋፊያ የግንባታ የአገልግሎት ግዢ ውል በሚከናወንበት ወቅት ለራሳቸው ብሎም ለብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ የኢትዮ ቴሌኮምና የመንግስት የግዢ አፈፃፀም መመሪያን ወደጎን በመተው ያለ ውድድር ከ221 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ገንዘብ ላይ ጉዳት በማድሳቸው ነው።

እንዲሁም 51 የኢትዮቴሌኮም ፕሮጀክቶች ሳይጠናቀቁ ከደንብና መመሪያ ውጪ ርክክብ ሳይደረግ ገንዘብ መክፈላቸውም በክሱ ላይ ተመልክቷል።

Via #ENA
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በማዕድን ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ሥራቸውን በተለያየ ምክንያት አቋርጠው ወጥተዋል እየተባለ ያለው #ሀሰት መሆኑን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዓለም ዓቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች መታሰር እንዳሳሰበው ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AMN-07-10
Forwarded from TIKVAH-SPORT
ሞሮኳዊው የዳኛ ባምላክ ደብዳቢ ተቀጡ!

ኢትዮጵያዊውን ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማን የደበደቡት የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት፣ የካፍ ምክትል ፕሬዚዳንትና የሞሮኮው ቤርካን ክለብ የክብር ፕሬዚዳንት ፉዚ ሌክጃ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ ለአንድ አመት ከማንኛውም ስፖርታዊ አመራር ታግደዋል።

Via #PetrosAshenafi
@tikvahethsport
#update የአዲስ አበባ አዴፓ ኮሚቴ በአማራ ክልል መስዋእት ለሆኑ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለተጎጂ ቤተሰቦች የመስርያ ቦታ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የአዲስ አበባ አዴፓ ኮሚቴ ከከተማው ህብረተሰብ በአጭር ቀናት ውስጥ ያሰባሰበውን ከ5 ሚሊዮን በላይ ገንዘብ በአማራ ክልል ሰኔ 15 መስዋእት ለሆኑት አመራሮች ቤተሰቦች ለሶስቱም ቤተሰቦች በእኩል መጠን ትናንት በሸራተን አዲስ ሆቴል ለተጎጂዎቹ ማስታወሻ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ አበርክቷል፡፡

Via #EPA
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አማረ አምሳሉን ጨምሮ በ10 የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል።

ተከሳሾች፦

1ኛ ተከሳሽ አማረ አምሳሉ፣
2ኛ ተከሳሽ ወልደጊዮርጊስ ወልዱ፣
3ኛ ተከሳሽ ኢሳያስ ዳኘው፣
4ኛ ተከሳሽ አብዱል ሃፊዝ አህመድ፣
5ኛ ተከሳሽ ማስረሻ ጥላሁን፣
6ኛ ተከሳሽ ሰይፈ ኃይለስላሴ፣
7ኛ ተከሳሽ ፀጋየ መኮንን፣
8ኛ ተከሳሽ አይተንፍስ ወርቁ፣
9ኛ ተከሳሽ ጌታሁን ያሲን እንዲሁም
10ኛ ተከሳሽ ሳሙኤል ፈጠነ ሲሆኑ ስልጣንን #ያላግባብ በመገልገል እንዲሁም የመንግስትን ስራ በማያመች አኳኋን በመምራት ከባድ የሙስና ወንጀል ከ259 ሚሊየን ብር በላይ በኢትዮ ቴሌኮም፣ በህዝብና በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀል ተጠርጥረው ዐቃቤ ሕግ በትላንትናው ዕለት ክሱን መስርቷል፡፡

Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
ፎቶ: ፋይል
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሶስት የትእምት ኩባንያ ሼሮች ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ። የመሰቦ ሲሜንቶ ፋብሪካ፣ ሱር ኮንስትራክሽንና የትራንስ ኢትዮጵያ ሼሮች ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ዝግጅት መደረጉን የትግራይ ክልል አስታወቀ፡፡

በምክትል ርእሰ መስተዳድር መዓረግ የትግራይ ክልል የከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብርሃም ተኸስተ የትግራይ ክልል ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በኩባንያዎቹ በተዘጋጀው የሼር ሽያጭ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ ባለፈ የግል ኩባንያ በማቋቋም በክልሉ ባለው የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት የሚፈልጉ ባለሀብቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉም ነው የተነገረው።

Via #fbc
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች እና አካባቢዎች ያሉ ነባር ህንጻዎቹን በአዲስ ለመቀየር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ተናገሩ። ፕሬዘዳንቱ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ ዩኒቨርሲቲው በህንጻ ግንባታ በኩል በጣም ኋላ ቀርና ያረጁ በመሆናቸው ለመማር ማስተማር ምቹ አልነበሩም፤ በዩኒቨርሲቲው በቅርስነት ከሚቀሩት በስተቀር ሌሎቹ በአዳዲስ ግንባታዎች ይተካሉ ብለዋል።

Via EPA
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በየመንገዱ የሚሸጡ ፀረ ተባይ መድኃኒቶችን ባለመግዛት እና #በማጋለጥ ለሕግ ማቅረብ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/AMRS-07-10
#update የሊቢያ ባለስልጣናት ባሳለፍነው ሳምንት ትሪፖል አቅራብያ ባለችው ታጁራ ፊንዳታ ደርሶ ከነበረበት የስደተኞች ማቆያ ማዕከል ስደተኞችን በማስወጣት ላይ መሆናቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰባዓዊ እና የስደተኞች ጉዳይ መግለፁን ታወቀ።

የጄኔራል ካህሊፋ ሃፍታር ታማኝ ወታደሮች አድርሰውታል በተባለው ጥቃት 50 ስደተኞች የተገደሉ ሲሆን የጄኔራሉ ታማኝ ሃይሎች ግን ለጥቃቱ መንግስትን ተጠያቂ ያደርጋሉ።
በአብዛኛው በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡት በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር ከሳሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች እንደሆኑ ይታመናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

Via #BBC
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአቋም መግለጫ ደብዳቤ ልካያለሁ #በአፋጣኝ ውሳኔ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።

ክለቡ የላከው ልኬያለሁ የሚለው ደብዳቤ👇
https://telegra.ph/FasilKenema-07-10
"ክለቦች ለመገናኛ ብዙሃን የሚያደርሷቸው #የሀሰት ውንጀላዎች የኢትዮጵያን እግር ኳስ ዕድገትን ያቀጭጨዋል እንጂ አያሳድገውም!" የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia