TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሰሞኑን ከባሕር ዳሩ ግድያ ጋር በተያያዘ የተያዙ #እስረኞች ብቻቸውን #ጨለማ ክፍል ውስጥ እንደታሰሩና አያያዛቸውን ኢሰብዓዊ መሆኑን #ጠበቃቸው ገልጠዋል፡፡ ጠበቃ #ኄኖክ_አክሊሉ ደንበኞቻቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማቆያ ክፍል ትናንት ከጎበኙ በኋላ ክፍሉ በጣም ጠባብና ቀዝቃዛ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል፡፡ ከክፍሏ የሚወጡት በ24 ሰዓት አንዴ ብቻ ነው፡፡ ቤተሰብና ወዳጅ እንዳይጎበኛቸው ተከልክለዋል፡፡ ጠበቃው የወከሏቸው ታሳሪዎች በሪሁን አዳነ (አሥራት ሜዲያ)፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ መርከቡ ኃይሌ (ባላደራ ም/ቤት) እና ማስተዋል አረጋ (የቀድሞ የገቢዎች ሚንስቴር ባልደረባ) ናቸው፡፡

Via #wezema
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተነሳ #ግጭት የህይወት፣የአካልና የንብረት ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ።

በዩኒቨርሲቲው በጀነራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ ትላንት በተነሳው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ተማሪዎች ህይወት ሲያልፍ ሌሎች አምስት ተማሪዎች መቁሰላቸው ተመልክቷል።

በግቢው የተማሪዎች ዲን ዋቅጋሪ ጉልማ እንደገለጸው በህመም ላይ የነበረ አንድ ተማሪ ከትላንት በስቲያ ህይወቱ ካለፈ በኋላ በአንዳንድ ተማሪዎች ሌሊቱን ግጭት እንዲቀሰቀስ ተደርጓል።

በዚህ ግጭትም ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ተማሪዎች ህይወት ሲያልፍ በሌሎች አምስት ተማሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በተማሪዎች መኝታ አካባቢ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከክልል ከፌዴራልና ከዞኑ የተውጣጣ ግብር-ሃይል ተቋቁሞ ተማሪዎችን ለማቀራረብና ለማግባባት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት ሊቀመንበር ዩሴፍ ደቻሳ በበኩሉ ችግሩ በተፈጥሯዊ መንገድ የሞተን ተማሪ ተገፍትሮ ነው የሞተው በሚል አንዳንድ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ በነዙት ወሬ ምክንያት መፈጠሩን ተናግሯል።

በአሁኑ ወቅት በጀኔራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ የሚገኙ ተማሪዎች ተበታትነው ያሉ ቢሆንም የማግባባት፣ በችግሩ ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠርና ጉዳት ያደረሱ ተማሪዎችንም በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዳኞች በክረምት ወራት በእረፍት ሰአታቸው ከአመቱ የተጠራቀሙ መዝገቦችን እልባት ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንደጨረሱ ተነገረ፡፡ የተሻሻለው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳኞች ስነምግባርና የዲሲፕሊን ደንብም ተመርቋል፡፡

ዳኞች ለበርካታ አመታት መፍትሄ ያልሰጡባቸውን ውዝፍ የክስ መዝገቦች በእረፍት ሰአታቸው እልባት ለማሰጠት የመግባቢያ ሰነድ በተፈረመበት ወቅት የ“በጀስቲስ ፎር ኦል ፌሎው ሽፕ ኢትዮጲያ” ፕሬዝዳንት ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ እንዳሉት ዳኞች በመጪው የክረምት ወራት የተጠራቀሙ መዝገቦችን እልባት ለመስጠትና በተለያዩ ክልሎች ዳኞች ሲያጠፉ የሚቀጡበትን የስነስርአት ደንብ ለማሳተም እየሰሩ ነው፡፡ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ከ20 እስከ 30 ሺህ መዝገቦች ይቀንሳሉ ብለው እንደሚያስቡ የጠቀሱት ፓስተር ዳንኤል ባለፈው አመት 23 ሺህ መዝገብ በመሰራቱ 23 ሺህ ዜጎች ፍትህ አግኝተዋልም ብለዋል፡፡

እንደ ፓሰተር ዳንኤል ድርጅታቸው ከክልሎች ጋር በመስራት ላይ ሲሆን በአራቱ ክልሎች ማለትም የአማራ፣ የትግራይ፣የደቡብ እና የኦሮሚያ ክልሎች ጋር እየሰራ ነው፤ በዛሬው እለትም የተሻሻለው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳኞች ስነምግባርና የዲሲፕሊን ደንብም ተመርቋል፡፡ የመግባቢያ ሰነዱ የተፈረመው በ“በጀስቲስ ፎር ኦል ፌሎው ሽፕ ኢትዮጲያ” እና በፌዴራልና ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች መካከል ነው።

Via #EPA
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰጭውን መቅጣት...

በአዲስ አበባ የተንሰራፋዉን #ልመና በዘላቂነት ለመቀነስ ሰጭዉን መቅጣት የሚያስችል ረቂቅ ሕግ እየተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አባባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገልጿል፡፡

Via waltainfo
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በክልል ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ጀምሯል...

ከአንድ ሳምንት በላይ በሀገሪቱ ውስጥ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተመልሷል። ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ ኢንተርኔት መስራት መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን በክልል ከተሞችም ከሰዓታት በፊት የኢንተርኔት አገልግሎት መስራት መጀመሩን ማረጋገጥ ተችሏል።

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል...

በሐረር ከተማ ሸዋበር መብራት ኃይል በተባለ የገበያ ሥፍራ ትናንት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎና የንብረት ዝርፊያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ጣሰው ቻለው ለኢዜአ እንደገለጹት በገበያ ስፍራው የደረሰውን የእሳት አደጋ ለማጣራት ኮሚቴ ተዋቅሮ ከትላንት ጀምሮ እንቅስቃሴ ጀምሯል።

በዚህም በእሳት ቃጠሎውና በንብረት ዘረፋ የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አመልክተዋል።

ተጠርጥረው ከተያዙት ግለሰቦች መካከል 3ቱ ተከስቶ በነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ የተጠረጠሩ ሲሆን ቀሪዎች የተያዙት ንብረት ዘርፈዋል በሚል ነው።

እንደ ኮማንደር ጣሰው ገለጻ በአሁኑ ወቅት የገበያ ስፍራው የተረጋጋ ሲሆን ህብረተሰቡም የተበታተኑ እቃዎችን ከፖሊስ ጋር በመሆን የማሰባሰብ ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

Via #etv
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ሜሴንጀር እና ዋትስአፕ በአብዛኛው የዓለም ክፍል በአግባቡ #እየሰሩ_አይደለም። ተጠቃሚዎች ፎቶ እና ቪዲዮ መመልከት እና መጫን አይችሉም። የፌስቡክ ቃል አቀባይ ችግሩ መፈጠሩን አምነው #መፍትሔ_ፍለጋ እየሰራን ነው ብለዋል። ባለፈው መጋቢት ፌስቡክ በሶስቱ መተግበሪያዎች ላይ ተመሳሳይ እክል ገጥሞት ነበር።

Via #EshetBekele
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢንዶኔዥያና ኢትዮጵያ ለተከሰከሱት ሁለት የ737 ማክስ አውሮፕላን ተጎጂ ቤተሰቦች ቦይንግ መቶ ሚሊዮን ዶላር አቀረበ። ይህ ገንዘብ በሁለቱ አውሮፕላኖች አደጋ ለሞቱ በድምሩ ለ346 ተጎጂ ቤተሰቦች የሚሰጥ ነው። ገንዘቡ የሟች ቤተሰቦችን የትምህርትና የኑሮ ወጪን የሚሸፍነው ነው ብሏል ቦይንግ። ይህ ገንዘብ የሟች ቤተሰቦች በፍርድ ቤት ለከሰሱት ክስ የቀረበ ሳይሆን ድርጅቱ ከፍርድ ሂደቱ ውጭ ያደረገው ክፍያ ነው።

ቦይንግ ዛሬ ሰኔ 26፣ 2011 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "የሚሰጠው ገንዘብ ለትምህርት፣ ከችግር ለመውጣት እንዲሁም የችግሩ ገፈት ቀማሽ ለሆኑት ቤተሰቦች የዕለት ተዕለት ኑሮና ለኢኮኖሚ ልማት ይውላል።

"ቦይንግ ከአካባቢው አስተዳዳሪዎች እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ይተባበራል። ይሄ የመጀመሪያው ኢንቨስትመንትም በዓመታት ውስጥ የሚከፈል ይሆናል" ብሏል። የቦይንግ ሊቀ መንበርና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ሙይልንበርግ " ቦይንግ በሁለቱም አደጋዎች በተቀጠፈው ሕይወት በከፍተኛ ሁኔታ አዝኗል። የጠፋው ሕይወት በሚቀጥሉት ዓመታትም የሚረሳ አይሆንም" ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም "ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ላጡት ከልባችን ሀዘናችንን እየገለፅን ይሄ የመጀመሪያ ገንዘብ ምቾትን ይፈጥርላቸዋል ብለን እናስባለን" ብለዋል። በኢንዶኔዥያ ላየን ኤይርና በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ተጎጂ የሆኑት ቦይንግን የከሰሱት ሲሆን እስካሁንም ገና ውሳኔ ላይ አልተደረሰም።

ኩባንያው በኢንዶኔዥያ ላየር ኤይር አደጋ ለተጎዱት ጉዳዩን በስምምነት ለመጨረስና ብር ለመክፈል እየተነጋገረ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ተጠቂዎችንም በስምምነት ለመፍታት ሀሳብ ቢያቀርብም በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡት ለመስማማት ዝግጁ እንዳልሆኑ አሳውቀዋል።

Via #BBC
#ጥንቃቄ_ይደረግ

በኢትዮጵያ እስካሁን 17 ሰዎች በኮሌራ ሞተዋል፤ በኮሌራ ተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 871 ደርሷል። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አርከበ ሆስፒታል ናቸው...

"በሚንስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚንስትሩ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር #አርከበ_እቁባይ ታመው ቤልጅዬም በሚገኝ ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ።" ይህ መረጃ #PetrosAshenafi እና ethiopiaobserver.com ናቸው ያወጡት።

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ኣርከበ #በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ...

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ዶ/ር #ኣርከበ_እቁባይ በጠና ታመው ሆስፒታል ገብተዋል ተብሎ በፌስቡክ እና መሰል ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ስህተት እንደሆነ የዶክተር ኣርከበ የቅርብ ሰውና የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆኑ ሰው ከደቂቃዎች በፊት በላኩልኝ የፅሁፍ መልዕክት አሳውቀውኛል። ዶክተር ኣርከበ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለህዝቡ ንገርልኝ ብለዋል።

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ኒጀር አቅንተዋል፡፡ የጉዟቸው ዐለማ በኒያሚ በሚካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ኅብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመገኘት እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ከጉባዔው በፊት ነገ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ይካሄዳል፡፡ ለመሪዎቹ ጉባዔ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ይገኙ አይገኙ ዘገባው ያለው ነገር የለም፡፡ ጉባዔው ኢትዮጵያ ያጸደቀችውን የአፍሪካ አሕጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና በይፋ ያውጃል፡፡

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ይቅርታ ጠይቋል!

#ኢትዮ_ቴሌኮም በሃገሪቱ ተዘግቶ የሰነበተው የፊክስድ ብሮድባንድ እና የሞባይል ኢንተርኔት የተቋረጠው ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት ተወስኖ እንደሆነ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል። በተገልጋዮች በኩል ለተፈጠረው መጉላላት እና ለደረሰው የኢኮኖሚ ኪሳራም #ይቅርታ ጠይቋል። የፊክስድ ብሮድባንድ አገልግሎቱ ከሰኔ 18 ጀምሮ መለቀቁን የገለጸው ኩባንያው የስልክ ኢንተርኔት በአሁኑ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ ተለቋል ብሏል። ነገር ግን አሁንም የስልክ ኢንተርኔት የማይሠራባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል። ኩባንያው በበኩሉ እንዲህ ያለው ችግር እንዳይደጋገም ምን ይበጃል የሚለውን በመለየት የመፍትሄ እያፈላለገ መሆኑን ይናገራል።

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማስታወቂያዎችን በተመለከተ፦

TIKVAH-ETH ለሚሰራቸውና ለሚያደርጋቸው ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴዎች ከየትኛውም የመንግስት እና የግል አካላት እስካሁን ልዩ ድጋፍ አልተደረገለትም፤ አሁንም አይደረግለትም፤ ይደረግልህ ቢባልም አይቀበልም! ቻናሉ በራሱ የቤተሰቦቹ አቅም የሚንቀሳቀስ ነው። ከገንዘብ በፊት ሀገር እና ህዝብ እንዲሁም ስራን የሚያስቀድም ቻናል ነው።

TIKVAH-ETH ለማስታወቂያ ክፍት የሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ የቤተሰቡ አባላት በየቀኑ በሚከታተሉት ገፅ በሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ምናልባት ተገልጋዮች አገልግሎት አቅራቢዎች የሚጠቅሟቸው በርካታ ጥቅሞች ስላሉ ነው። ነገር ግን የማስታወቂያ ስራው ለሁሉም ክፍት ከመሆኑ አንፃር እጅግ በርካታ ማስታወቂያዎች በTIKVAH-ETH እንዲቀርቡ ይጠየቃል እስከዛሬም ሲቀርቡ ቆይቷል፤ ነገር ግን የማስታወቂያ ብዛት ተከታዩን እያማረረ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል። በርካታ አስተያየቶችምንም ተቀብለናል። በዚህም የማስታወቂያ ቁጥር እንዳይበዛ ለማድረግ አዲስ የማስታወቂያ ፓኬጅ አዘጋጅተናል። አዲስ በተዘጋጀው ፓኬጅ መጠቀም የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አነጋግሩን።

ማስታወቂያ አስነጋሪዎች፦

▪️ህጋዊነታችሁ የተረጋገጠ/ፍቃድ ያላችሁ/
▪️ለምታስተዋውቁት ማንኛውም ነገር ተጠያቂ እንዲሁም
▪️ማስታወቂያችሁ ተገልጋዩን የሚጠቅም ሊሆን ይገባል።

በሌላ በኩል...

√ከዚህ ቀደም ውል ያላችሁ በኔትዎርክ መጥፋት ብዙ ስራዎች ባለመሰራታቸው ከነገ ጀምሮ ሁሉም ማስታወቂያዎች ወደ መደበኛ ቦታቸው ይመለሳሉ።

እናመሰግናለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሙስ እና ቅዳሜ በነፃ!!

√አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች እና ወጣቶች እንዲሁም ሌሎች የTIVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለህዝብ የሚጠቅም #አዲስ የስራ ፈጠራ ውጤት ካላችሁ በተጨማሪም በአዲስ የስራ ዘርፍ የተሰማራችሁ ካላችሁ ሀሙስ እና ቅዳሜ በነፃ አገልግሎታችሁን ስራችሁን ማስተዋወቅ ትችላላችሁ።

TIKVAH-ETH የቤተሰቡ አባላት ነው!
ለህዝብ ሊጠቅሙ ይችላሉ የምንላቸውን ነገሮች በሙሉ ከማድረግ ወደኃላ አንልም!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ክንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በመዲናዋ አምስቱ መግቢያ በሮች የመሠረታዊ ፍጆታ የግብይት መጋዘኖች ሊገነቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የመጋዘኖቹ መገንባት አሁን ላይ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር እንደሚያስችልም ገልጸዋል፡፡

🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ መልካም ስራችን እንመለስ!

በኔትዎርክ መቋረጥ ምክንያት ለእህት እና ወንድሞቻችን እንዲሁም ለልጆቻችን ተገቢውን ነገር ሳናደርግ ቆይተናል፦

#1

√ስም፦ #ሳምራዊት_አረጋ
√እድሜ 22
√የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
√በደረሰባት ድንገተኛ የኩላሊት ህመም በአልጋ ላይ የወደቀች እህታችን...ልጃችን

#2

√ስም፦ #ምህረቱ_መንግስቴ
√ከ8ተኛ ክፍል ትምህርቱን አቋርጦ ለ11አመታት በየሆስፒታሉ ሲንከራተት የቆየ በሰው እቅፍ ካልሆነ መንቀሳቀስ የማይችል ሲመገብም ሆነ ለተፈጥሮ ግዳጅ መቀመጥ የማይችል
√በከፋተኛ የአጥንት ቁስለት እየተሰቃየ ከግራታፋው 5 የተለያዩ ቁስለቶች ፈሳሽ የሚፈሰው
√ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውጭ ሀገር እንዲታከም ሪፈር የፃፈለት 1.2ሚሊየን ብር የተጠየቀ ነገር ግን ወላጁን በሞት ያጣና ምንም ገቢ የሌለው አሳዛኝ የ21 አመት ታዳጊ

#3

√ስም፦ #ካሊድ_ኡመር
√የ16 አመት ታዳጊ
√በኩላሊት ህመም የሚሰቃይ ልጃችን..ወንድማችን

በTIKVAH-ETH አተባባሪነት 1የጋራ የባንክ አካውንት እንዲከፍቱ ተደርጓል።

1000278664612 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

💰400,000 ብር (ለማሰባሰብ የታቀደው ገንዘብ)

በትንሹ 40 ሺ አባላት ተሳታፊ እንድትሆኑ እንማፀናለን ፦ 10 ብር * 40,000 የtikvahethiopia አባላት=400,000 ብር

🏷እስካሁን የተገኘው 48,000 ብር

የሞባይል ባንኪንግ ተጠቅችሁ አሁኑኑ ድጋፋችሁን ታደርጉ ዘንድ እንማፀናለን! #TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡባት የአቢዬ ግዛት የዘመቱ 860 ገደማ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ 30 ወታደራዊ ሰራተኞችና የተባበሩት መንግሥታት ፖሊሶች የግዛቲቱን ሰላም እና ፀጥታ ለመስጠበቅ ለነበራቸው ሚና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሜዳይ ተሸለሙ። በአቢዬ የተባበሩት መንግሥታት ጊዜያዊ የጸጥታ ጥበቃ ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴየር ጄኔራል ሙሉ ገብረሕይወት በሽልማቱ ወቅት በአቢዬ የደፈሩ ወታደሮችን አመስግነዋል። የኢትዮጵያ ሴት ወታደሮች የአካባቢው ሴቶች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ለተጫወቱት ሚና ተመስግነዋል።

Via #EshetBekele
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና ተቃዋሚ ሃይሎች ተቋርጦ የነበረውን ውይይት በድጋሚ መጀመራቸው ተገልጿል።

🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጄኔራል ሰዓረ መኮንን የመጨረሻ ሰዓታት
-----------------------------------------------------
(በእንግሊዝኛ የካፒታል ጋዜጣ እንደተፃፈዉ)
-------------------------------------------------------
ከአንድ የጄኔራሉ ቤተሰብ እንደተገኘዉ መረጃ የዚያች ቀን የሆነዉ ይህ ነበር፦

ሰኔ 15 በዕለተ ቅዳሜ ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ ላይ የመከላከያ ሃይል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ቦሌ ደሳለኝ ሆቴል ጀርባ በሚገኝ ቤታቸዉ እየጠበቃቸዉ የነበረዉን ጓደኛቸዉን ለማግኘት እየተቻኮሉ ከቢሯቸዉ ወጥተዉ ወደ ቤታቸዉ አቀኑ፡፡ ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ቤታቸዉ እንደደረሱ ከሳምንት በፊት የተካሄደዉን የልጃቸዉን የመዓሾ ሰዓረን ከዩኒቨርስቲ መመረቅን በማስመልከት እንኳን ደስ ያለህ ለማለት ሲጠብቃቸዉ የነበረዉን ጓደኛቸዉን ቤት ሲያገኙት አቀፉት፤ ቀጥሎም ወደ ቤታቸዉ በረንዳ በማምራት በረንዳዉ ላይ በነበሩት ሁለት ትናንሽ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጡ፡፡

አብዛኛዉን ጊዜ ጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ብርጋዴር ጌጀነራል ገዛኢ አበራ ሲገናኙ ሁለቱም በጋራ ተሳትፈዉባቸዉ የነበሩትን ጦርነቶች በማነሳሳት አስቂኝ ትዉስታዎቻቸዉን በማዉሳት በመሳሳቅ ያሳልፉ ነበር፡፡

ገዛኢ “ስራ በጣም ስለበዛብኝ ነዉ በልጅህ ምርቃት ላይ ያልተገኘሁት በጣም ይቅርታ ጓደኛዬ” ሲለዉ ጄነራል ሰዓረም በምላሹ ፈገግ እያለ “ችግር የለዉም” አለዉ፡፡

ከዚያም የጄኔራል ሰዓረ-ባለቤት የሆኑት ኮለኔል ጥጌ ወይን መጠጥ ካመጣችላቸዉ በኋላ ምግብ ለማምጣት ወደ ኩሺና በምትመለስበት ወቅት የሁለቱ ጄኔራሎች ህይወት በድንገት ጠፋ፡፡ መስፍን ጥጋቡ የሚባል እድሜዉ ከ25-27 የሚገመተዉ ወጣቱ የጄኔራል ሰዓረ ጠባቂ ብቻዉን ወደ መኖርያ ቤቱ በረንዳ በመምጣት መሳርያዉን ደቅኖ ጥይት አዘነበባቸዉ፡፡ ከዚያም ከፍተኛ ጩሀት አካባቢዉን አደበላለቀዉ፡፡ ኮለኔል ፅጌ ከልጃቸዉ ጋር በመሆን ከተደበቁበት ክፍል ሳይወጡ ማልቀስና መጮህ ጀመሩ፡፡ የተኩስ እሩምታ በብዛት ቢሰማም አንድም ሰዉ ዝር አላለም፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከቤቱ ዉጪ የነበሩ ሌሎች ጠባቂዎች ሲመጡ ጄነራሎቹ መሬት ላይ ተዘርግተዉና ከፍተኛ ደም እየፈሰሳቸዉ አገኟቸዉ፡፡ በጄኔራሎቹ መሃከል ጠባቂዉ መሳፍንትም ተዘርግቶ ነበር፡፡ ቤተሰቦቹ ሁለቱንም ጄኔራሎች ይዘዉ ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ወደ ዋሺንግተን ሜዲካል ማዕከል ቢያቀኑም ሆስፒታሉ ሳይደርሱ ሁለቱ ጄኔራሎች አረፉ፡፡

አንድ የቤተሰቡ የቅርብ ሰዉም እንዲህ አለ “ጄኔራሎቹ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ ከጄኔራሎቹ መካከል ተዘርግቶ የነበረዉ ጠባቂ ሁሉም ሰዉ የሞተ መስሏቸዉ ነበር ግን ሰዉዬዉ አልሞተም ነበር፡፡ የሞተ ለማስመሰል ተዘርግቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ከዛን ተነስቶ ለመሮጥ ሞከረ፣ ሌሎቹ ጠባቂዎች ሲዩት ተኩሰዉ እግሩን መቱት፤ ከዚየም ወደ ትንሽ የጥበቃ ክፍል ሮጦ ገባ፤ ከዚያ በኋላ ሰዉዬዉ ራሱ ላይ እስኪተኩስ ድረስ ብዙ የተኩስ ልዉዉጦች ነበሩ፤ ከዚያም ጥበቃዎቹ ጎትተዉ አዉጥተዉት ወደ ሆስፒታል ወሰዱት”፡፡

ከዚህ ሁሉ ግድያ በፊት ጄኔራል ሰዓረን መኖርያ ቤት ለ4 ወራት ሲጠብቅ የነበረዉ ወታደር ከጄኔራሉ ቤት እንዲቀየር መዳቢዎችን (ሃላፊዎችን) ጠይቆ ነበር፡፡ ከዚያም ዉጪ የጄኔራሉ ባለቤት የሆኑት ኮለኔል ፅጌ የመሳፍንትን ሁኔታ ስላልወደዱት ባለቤታቸዉን (ጄኔራል ሰዓረ) ጠባቂዉን በሌላ ጠባቂ እንዲቀየር በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ጄነራሉ ሃሳባቸዉንና ጭቅጨቃቸዉን ባለመስማት ጠባቂያቸዉን በማመን ቀጠሉ ይላል ለካፒታል ጋዜጣ የተሰጠዉ ምላሽ፡፡

Via #ኤግል_ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia