TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ተዛውሯል...

በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቡድኖች በአዲስ አበባ ስታዲዬም ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በፀጥታ ስጋት ለሌላ ግዜ ተዛውሯል።

🗞ቀን 22/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌስቡክ አስተያየት ሰጪዎች እነማን ናቸው

#አብዛኞቹ በተለያዩ #የፌስቡክ_ፖስቶች ላይ/በዜና ማሰራጫዎች፣ በታዋቂ ግለሰቦች ገፅ፣ በአክቲቪስቶች እንዲሁም በሌሎች.../ የስድብ ናዳ የሚያወርዱት፤ ህዝብን የሚያሸብሩት፤ ሀገሪቱ ፍፁም እልቂት ውስጥ ልትገባ እንደሆነ የሚዝቱት፤ እርስ በእርስ ፍጅት እንዲነሳ የሚቀሰቅሱት፤ በተላለፉ መረጃዎች ላይ በሙሉ ስድብ እና ጥላቻን፣ አሉባልታን የሚፅፉት አብዛኞቹ #ሀሰተኛ ገፅ ናቸው። የሰዎቹ ማንነት የማይታወቅ፣ ምስላቸው የሌለ፣ ለግጭት እንዲሁም ህዝብን ለማወናበድ የተከፈቱ ናቸውና ተጠንቀቁ። በምታነቡት አስተያየትም ተስፋ አትቁረጡ።

በሌላ በኩል...

ትክክለኛ አመለካከታቸውን #በስድብ እና በኃይል ለመግለፅ የሚሞክሩም እንዳሉ ልታውቁ ይገባል። ማስረጃን አቅርቦ ከመከራከር ይልቅ ስድብ ባህል ያደረጉ ወገኖች አሉና ከቻልን ቀርበን እናስተካክላቸው።

ኢትዮጵያ ሰላም ትሁን፤
ዜጎቿም ሰላም ወጥተው ይግቡ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አላችሁ!

የተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን በዛሬው እለት #አስመርቀዋል። በዛሬው እለት ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ፣ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ መቱ ዩኒቨርሲቲ፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል።

TIKVAH-ETH ለተመራቂዎች እና ለቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ለዚህ አበቃችሁ ለማለት ይወዳል!!

ፎቶ #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የመንግሥትን የ2011 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያቀረቡ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች በመሳተፍ የተጠረጠሩ ግለሰቦች እና ቡድኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት 48 የሽብር ቡድን አባላት፣ 799 ብሔርን መሠረት ባደረገ ጥቃት የተጠረጠሩ መሪዎችና የፀጥታ አካላት፣ በኢኮኖሚያዊ ወንጀሎች የተጠረጠሩ 34፣ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር 64 ግለሰቦች፣ እና 51 ሰዎች በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝቅቅር በሕግ ጥላ ሥር ውለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን በሪፖርታቸው ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመጋቢት 2010 ዓ.ም ጀምሮ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች እንደተፈናቀሉም ተናግረዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 400 ሺህ የሚሆኑት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተፈጠረ ድርቅና የተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅለዋል፡፡

በሀገሪቱ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች በሚኖሩበት ክልል ውስጥ የተፈናቀሉ ሲሆን 800 ሺህ ዜጎች ደግሞ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል የተፈናቀሉ መሆናቸውን በሪፖርቱ አመላክተዋል፡፡

አሁን ላይ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን የሚበልጡት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱና ቀሪዎቹን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረዋል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የ2019 የዩኔስኮ ፌሊክስ ሁፉዌ ብዋኚ (Félix Houphouët-Boigny) የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በተለይ በኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት ላይ በነበራቸው ከፍተኛ ሚና ለሽልማቱ የታጩ መሆናቸውንም ዩኔስኮ አሳውቋል።

መቀመጫውን ፈረንሳይ ፓሪ ያደረገው የመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም ዩኔስኮ አስቀድሞ ሽልማቱን ለመስጠት የፊታችን ጁላይ 9 ቀን መርሐ ግብር ተይዞለት የነበረ ቢሆንም ተቋሙ የሽልማቱን መስጫ ቀን ላልተወሰነ ቀን ማራዘሙን አሳውቋል። https://en.unesco.org/news/ceremony-award-felix-houphouet-boigny-unesco-peace-prize-ethiopian-pm-abiy-ahmed-ali

Via #PetrosAshenafi
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሰሜን አሜሪካ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል በአትላንታ ተጀምሯል፡፡ ለ36ተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባላሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍፁም አረጋ ተገኝተው ፌስቲቫሉን በይፋ ከፍተዋል፡፡

🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአማራ ክልል ለሦስት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ተሰጥቷል፤ በዚህም መሠረት፡-

•አቶ አገኘሁ ተሻገር----የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ፣

•አቶ አረጋ ከበደ----የክልሉ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣

•ኮሎኔል ጌታቸው ብርሌ----የክልሉ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ሆነው ተሹመዋል።

🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና በምሥራቅ አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ስኬታማውና በኢትዮጵያ ገበያም ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳየው ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ቦብ ኮሊሞር ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ድርጅታቸው አስታደቀ። ሳፋሪኮም የዋና ሥራ አስፈጻሚውን ዜና እረፍት ይፋ ባደረገበት መግለጫው ላይ እንዳመለከተው፤ ቦብ ኮሊሞር በ61 ዓመት እድሜያቸው በካንሰር ምክንያት ዛሬ ጠዋት ቤታቸው ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

Via #BBC
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሰሜን ኮሪያ በማቅናት ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ተገናኝተዋል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሰሜን ኮሪያ ያቀኑ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ናቸው።

🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ኮሎኔል #ጌታቸው_ብርሌ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ፦ ኮሎኔሉ ከብርጋዴየር ጄነራል አሳምነው ጽጌ እና ከብርጋዴየር ጄነራል ተፈራ ማሞ ጋር 9 ዓመት በእስር አሳልፈዋል። #Ethiopia #Amhara

Via #TesfalemWoldeyes
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: አዲሱ የአማራ ክልል ሚሊሺያ ጽህፈት ኃላፊ አቶ #አረጋ_ከበደ። አቶ አረጋ የክልሉ የወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል። #Ethiopia #Amhara

Via #TesfalemWoldeyes
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: አቶ አገኘሁ ተሻገር----የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ! #ETHIOPIA #AMHARA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነአቶ በረከት ስምኦን የክስ መዝገብ ላይ ቀሪ አንድ የዐቃቢ ሕግ የምስክር ቃል ለመስማት ዛሬ የተሰየመው ችሎት ምስክሩ ባለመቅረባቸው ድጋሜ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

በክስ መዝገብ ተራ ቁጥር አንድ ላይ የቀሪ አንድ ምስክር ቃል ለመስማት ለዛሬ ቀጠሮ የተሰጠ ቢሆንም ምስክሩ በተለያዩ ችግሮች ምክያት ሊቀርቡ ስላልቻሉ ለሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

በዚሁ የክስ መዝገብ ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ከጤና ችግር ጋር በተያያዘ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡትን ጥያቄም ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ትዕግስታችን አልቋል" ዶ/ር አብይ

"በደቡብ ክልል የቀረበውን የክልል እንሁን ጥያቄ ተቀብለን እየተከታተልን ነው። ምላሹ ለመስጠት ጊዜ ይፈልጋል። ነገር ግን በጩኸት የሚሆን ነገር የለም። ሁሉም ከኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ጉዳይ ጋር ይያያዛል። ይህን የማይቀበል አካል ካለ ግን መንግስት ትእግስቱ ስላለቀ በህጋዊ መንገድ #እናስከብራለን።" ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ

#elu
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እግዚአብሄር በናንተ ላይ ይፍረድ"

ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ በአውሮፓና በአሜሪካ ሀገር እየኖሩ፣ #ኢትዮጵያውያንን ለማባላት የበሬ ወለደ መረጃ ያሰረጫሉ ያሏቸውን ግለሰቦች በፓርላማ ፊት እረግመዋል።

#elu
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከስራ አጥነት ጋር በተያያዘ እስከ ሚቀጥለው አመት መጨረሻ ድረስ ለ3 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ተይዟል። አዲስ አበባ ላይ በርካታ ፕሮጀክቶች ይተገበራሉ፤ ይህም የከተማዋን የስራ አጥ ቁጥር ለመቅረፍ ያግዛል። እስካሁን ያለው የቀጣሪነት ንጽጽር ከ100 አስር ነው። ከዚህ ውስጥ የመንግስት ድርሻ 40 በመቶ ሲሆን የግሉን ዘርፍ የመቅጠር ሚና ማሳደግ ይገባል።

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጀኔራል አብርሃ ወ/ ማርያም (ኳርተር) የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በመቀሌ ከተማ ይከናወናል። የጄኔራል አብርሃ አስክሬን ትናንት አዲስ አበባ የገባ ሲሆን፥ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቤተሰቦቻቸው፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ወታደራዊ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገዋል። ጀኔራል አብርሃ ወልደማርያም በጠና ታመው በታይላንድ ባንኮክ በሚገኝ አለም አቀፍ ሆስፒታል ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ሰኔ 21 ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡

🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የሚቃጡ አካላት ካሉ ብዕራችንን አስቀምጠን ጠብመንጃችንን እናነሳለን"

ጠ/ሚንስትር ዐብይ አህመድ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዛሬም በኢትዮዽያ አንድነት እንደማይደራደሩ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት በተደጋጋሚ ተናግረዋል። #elu

🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ክልል የመሆን ጥንያቄ ህገ መንግስታዊ መብት ነው። ማንም ህዝብ ክልል ልሁን ብሎ መጠየቅና በህግ አግባብ ጉዳዩን ማስፈፀም መብቱ ነውና አትችልም መጠየቅ አንለውም፤ ህገ መንግስትን መብቱ ነውን ይሄን ህገ መንግስታዊ መብት ህጋዊ የሆነውን ጥያቄ በህጋዊ መንገድ ብቻ ነው መልስ ማግኘት የሚችለው።

ህጋዊ ጥያቄን በግርግር ከፈለክ ዘላቂ መፍትሄ አታመጣም፤ ፍትህ እንኳን ብታመጣ ርትዕ አታመጣም። ፍትህም ርትዕም Equally exercise ለማድረግ ከፈለገ አንድ ማህበረሰብ በህግ የጠየቀውን በህግ እስኪመለስ መጠበቅ ያስፈልጋል። ምን ማለት ነው፤ አንድ ክልል እራሱን በራሱ ማስተዳደር ሲፈልግ ያንን ጉዳይ የሚያስፈፅመው የምርጫ ቦርድ ነው።...ይሄ ተቋም በሁለት እግሩ ሳይቆም ክልል የመፍጠር ጉዳይ ብንሞክር ግን ፍላጎት ብቻ ነው የሚሆነው።

...አሁን ደቡብ አካባቢ ያለውን ነገር መንግስት በክብር ተቀብሏል። ደኢህዴን የሚባለው ክልሉን የሚያስተዳድረው ድርጅትም ጥያቄውን ተቀብሎ በህግ እየመረመረ ይገኛል። ደኢህዴን የመጨረሻ ውጤቱን እስከሚያሳውቅ፤ምርጫ ቦርድ ዝግጅቱን እስከሚያሳውቅ በደቡብ ክልል ውስጥ ክልል ለመሆን የጠየቃችሁ ህዝቦች በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠብቁን በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ።

ከህጋዊ መንገድ ውጪ ምንም አይነት ሙከራ ማድረግ ሱማሌ እንደሆነው ደቡብም ይሆናል፤ በኢትዮጵያ አንድነት የሚደራደር መንግስት የለም። ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ተቀብለናል #በትዕግስት መጠበቅ! አልተቀበልንም ሲባል በህጋዊ መንገድ እናስተካክለዋለን። በዚህ መንገድ ቢታይ ጥሩ ነው በደቦ፣ በጩኸት የሚፈጠር ነገር ከእንግዲህ በኃላ ማስተናገድ ትዕግስታችን አልቋል። ሁሉም ስርዓትን ጠብቆ ይሄዳል፤ በስርዓት እንመልሳለን ያን የማይጠብቅ ከሆነ በተለመደው መንገድ እናስተካክለዋለን!" ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ~#ቲክቫህ
በለቅሶ የታጀበው የፓርላማ ውሎ...

ስሜታዊነት በተጫነው የዛሬው የፓርላማ ጥያቄ እና መልስ ጊዜ የምክር ቤት አባላት #ሲያለቅሱ ታይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለተገደሉ ባለስልጣናት ሲናገሩ ካለቀሱት መካከል የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል አንዷ ናቸው።

#TesfalemWaldyes
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መፈንቅለ መንግሥት

ሰሞኑን መንግሥት በብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ነው ማለቱን ተከትሎ በርካቶች እንዴት መፈንቅለ መንግሥት በክልል ደረጃ ይደረጋል፤ ይህን ተግባር መፈንቅለ መንግሥት ብሎ መጥራቱ ትክክል አይደለም ሲሉ የሞገቱት ጥቂት አይደሉም።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በዛሬው የፓርላማ ውሏቸው የተፈጸመው ጥቃት ''በኢፌዴሪ መንግሥት ላይ የተፈጸመ መፈንቅለ መንግሥት ነው'' ብለዋል።

"በየትኛውም የፌደራል ሥርዓቱ ላይ የሚቃጣ ጥቃት የኢፌዴሪ ጥቃት ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ''አመራር ገድሎ እና አግቶ ሲያበቃ፤ የመንግሥት ተቋማትን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ 'ለምን መፈንቅለ መንግሥት ትሉታላችሁ' መባሉ ትክክል አይደለም" ብለዋል።

የሰሞኑ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድራጊዎች ከባህር ዳርና ከአዲስ አበባ ውጪ በቤኒሻንጉል ጉሙዝም ኃይል አሰማርተው እንደነበረ እና ከኦሮሚያ የተመለመሉ ''ገዳዮችን'' ያካተት እንደነበረ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ ላይ ከወራት በፊት የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ አለን ብለው የመጡ የሠራዊቱ አባላት መኖራቸውንም ተናግረዋል። ''መከላከያ አስሮ ገምግሞ 'እነዚህ ወጣቶች ናቸው ይማራሉ' ብሎ የለቀቃቸው በርካታ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነውበታል'' ብለዋል።

''እንዴት ሰው አምባቸው መኮንን ይገድላል?'' በማለት የጠየቁት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ''አምባቸው እንኳን ልትገድለው፤ ልትቆጣው እንኳን የሚያሳሳ ሰው ነው'' ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

''ሰዓረ እንደ ሃበሻ ዳቦ ከላይ እና ከታች እሳት እየነደደበት፤ ጓዶቼን ቀብሬ የመጣሁባትን ኢትዮጵያን አላፈርስም ያለ ጀግናን እንዴት ሰው ይገድላል?" ሲሉ ጠይቀዋል።

Via #BBC
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia