#ጥንቃቄ #ባህር_ዳር
"ባህርዳር መንገዶች ተዘግተዋል። አሁንም የተኩስ ድምፅ ይሰማል። ሰላማዊ ሰዎች በዚህ የተኩስ ልውውጥ የጥቃቱ ሰለባ እንዳይሆኑ መደወል የምትችሉ ሰዎች ደውላችሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አድርጉ። ይህንን መልዕክት የደረሳችሁ ባህር ዳር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እላለሁ። ሰላም ለባህር ዳር!"
Via Seyum Argaw
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ላይ የተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት የሚፃረር፣ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ለረጅም ጊዜ የታገሉለትን ሰላምና መረጋጋት ለመንጠቅ የተደራጀ በመሆኑ የፌደራል መንግሥት ሙሉ በሙሉ እንደሚያወግዘው የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
የፌደራል መንግሥት የጸጥታ መዋቅር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር አውሎ በፈጸሙት አካላት ላይ ተገቢውን ርምጃ እንዲወስድ ትእዛዝ ተቀብሎ ተፈጻሚ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ጥቃት በመንግሥት መዋቅር ላይ ብቻ ሳይሆን በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣ መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ ሕዝብ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅና ተረጋግቶ ሁኔታዎችን እንዲመለከት ጥሪ ቀርቧል።
ይህን ሕገ ወጥ ሙከራ ክልሉ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ክልልና መላው ኢትዮጵያዊ ሊያወግዘው የሚገባ ሲሆን የፌደራል መንግሥት የታጠቁ ቡድኖችን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ የመቀልበስ፣ የመግታትና በቁጥጥር ሥር የማዋል ሙሉ ዐቅም ያለው መሆኑን ያረጋግጣል።
Via #PMOEthiopia

#ባህር_ዳር
"አሁን ላይ ባህር ዳር ተኩሱ ቆሟል። መረጋጋት እየተፈጠረ ነው። የአማራ ልዩ ኃይል ሁኔታውን እያረጋጋ እንደሆነ ታውቋል።" #በላይ_ማናዬ

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል መንግስት ላይ ተሰነዘረ ያሉትን "መፈንቅለ መንግስት" አወገዙ። አሜሪካን ሀገር የሚገኙት የአዴፓ ሊቀመንበር "የፌደራል መንግስት ጉዳዩን በመከታተል አስፈላጊው #እርምጃ ይወስዳል" ብለዋል። #elu

"የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው የአማራን ህዝብና ክልል የማይመጥን አሳፋሪና አሳዛኝ ክስተት ነው" :- አቶ ደመቀ መኮንን
----------------------------------------------------------------------
ዛሬ በአማራ ክልላዊ መንግስት የተቃጣው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እና ጥቃት የአማራን ህዝብና ታሪክ የማይመጥን አሳፋሪና አሳዛኝ ክስተት እንደሆነ የኢፌዲሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ። አቶ ደመቀ ከአሜሪካ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩን የፌደራልና የክልል አካላት በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን ተጠያቂ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ ይደረጋል ብለዋል። ህብረተሰቡም ውዥንብር ውስጥ ሳይገባ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ አቶ ደመቀ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
Via #etv
Pic #elias_meseret

#ሰበር_መረጃ
በነገው ዕለት #በአዲስ_አበባ ከተማ ሊካሄዱ የነበሩት የጠዋቱ የኦሎምፒክ ሳምንት የመክፈቻ ፕሮግራም እና የከሰዓቱ የስጦታ-ለአዲስአበባዬ ፕሮግራሞች ሙሉ በሙሉ #ተሰርዘዋል።
Via Mayor Office AA

የፌደራል የጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ በተደረገባት የባሕር ዳር ከተማ ተሰማሩ። የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት #መኮድ ተብሎ ከሚጠራው የጦር ሰፈር ወደ ከተማዋ የዘለቁ ወታደሮች የጸጥታ ቁጥጥር እያደረጉ ናቸው።
Via #DW

#ጥንቃቄ
በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ዜናዎች ከየቦታው እየወጡ ነው። አጣርተን፣ ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች ተቀብለን ትክክለኛውን ብቻ የምናቀርብ ይሆናል። ብዙ ዜናዎች እያጣራን ነው እውነት ሆኖ የተገኘውን ብቻ እናቀርባለን።

እንዴት ከረማችሁ??
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከባለፈው ቅዳሜ አመሻሹን አንስቶ ሃዘን ፀንቶባት ቆይታለች። የሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች መገደላቸውን ተከትሎ የሀዘን ቀናት ተውጆ ነበር። ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮም የኢንተርኔት አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ ተቋርጦ ቆይቷል። የWiFi እና #Broadband አገልግሎት ቢጀመርም የሞባይል ዳታ አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።

#update የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በቤተ ጊዎርጊስ የቀብር ቦታ ተፈጽሟል።
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለፈው ሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በአማራ ክልል መንግሥት ላይ በተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሕይወታቸው ያለፉ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች ሥርዓተ ቀብር ትላንት በባሕር ዳር ተፈፅሟል።
በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ የቀብር ሥነ-ስርዓት ትላንት በባሕር ዳር ከተማ ዓባይ ማዶ ገብርኤል ተከናውኗል፡፡
የቀብር ሥነ-ስርዓቱ ከመከናወኑ በፊት ደግሞ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲዮም የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ የቀብር ሥነ-ስርዓት ትላንት በባሕር ዳር ከተማ ዓባይ ማዶ ገብርኤል ተከናውኗል፡፡
የቀብር ሥነ-ስርዓቱ ከመከናወኑ በፊት ደግሞ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲዮም የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና የሜጄር ጄኔራል ገዛኢ አበራ የቀብር ስነ ስርዓት ትላንት ተፈፅሟል።
የቀብር ስነ ስርዓቱ በመቐለ ከተማ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ነው የተፈጸመው።
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጀኔራል ገዛኢ አበራ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ላይ በተፈጸመባቸው ጥቃት መሰዋታቸው ይታወሳል።
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀብር ስነ ስርዓቱ በመቐለ ከተማ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ነው የተፈጸመው።
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጀኔራል ገዛኢ አበራ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ላይ በተፈጸመባቸው ጥቃት መሰዋታቸው ይታወሳል።
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አካላዊ ጉዳት አልደረሰብኝም" አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)
በጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመካፈል ወደ መቀሌ ያቀኑት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር( ትዴት) መሪ አረጋዊ በርሀ (ዶ/ር) "የወጣቶች መንጋ" ባሏቸው ሰዎች ጥቃት እንደተሞከረባቸው ተናግረዋል፡፡ ቢሆንም ግን "አካላዊ ጉዳት አልደረሰብኝም" ብለዋል።
የቀብር ስነስርዓቱ ላይ ለመገኘት የሰማእታት ሃውልት ደጃፍ ላይ ሲደርሱ ከውስጥና ከውጭ የነበሩት ወጣቶች "መግባት የለበትም" ብለው በመቃወማቸውና ጥቃት ለማድረስ በመሞከራቸው የክልሉ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ሊታደጋቸው እንደቻለ ገልፀዋል።
ይህን ተከትሎ ግርግር በመፈጠሩ ወጣቶቹ በወረወሩት ድንጋይ የፖሊስ ኣባላት ላይ እንዲሁም መኪኖች ላይ ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡
ፖሊስ ግርግሩን ለመቆጣጠርም አስለቃሽ ጭስ ለመጠቀም ተገዶም ነበር ተብሏል። ከግርግሩ በኋላ አረጋዊ በርሀ (ዶ/ር) ወደ ዞኑ የፖሊስ ጽህፈት ቤት የተወሰዱ ሲሆን፤ ማምሻውን በእንግዳ ማረፍያ ማሳለፋቸውንም ተናግረዋል።
'ባዶ ስድስት' የሚባል እስር ቤት ውስጥ ታስረዋል የተባለው ስህተት እንደሆነና ዛሬ ጧት ወደ አዲስ አበባ እየተመለሱ እንደሆነም ገልጸዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት በዓይደር ሆስፒታል ህክምና እያገኙ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ

አሳዛኝ ዜና‼️
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የታጠቁ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ ከ30 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲል ሀሰን ለቢቢሲ ገለፁ።
ጥቃቱ የደረሰው እሁድ ለሰኞ አጥቢያ 11 ሰዓት ላይ መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በጥቃቱ ወደ 16 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልፀው ወደ 66 ቤቶች በቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት በአማራ ክልል የሚኖሩ የጉሙዝ ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መድረሱን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ያኔም ለቁጥር መግለፅ ከባድ ያሉት ሰው መሞቱን ተናግረዋል።
ጥቃት አድራሾቹ 'ከአማራ ክልል መምጣታቸውን' የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በቁጥጥር የዋለ መሳሪያና ሰው ቢኖርም ምን ያህል እንደሆነ ግን የተጠናከረ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል።
በስፍራው አሁንም ስጋት መኖሩን የተናገሩት አቶ አሻድሊ ሀሰን ጉዳዩን ለመፍታት ከመከላከያና ከፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ጋር እየሰሩ መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል።
በጉዳቱ የቆሰሉ ሰዎች በፓዊ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው ገልፀዋል።
Via #BBC

መንግስት #በባህርዳር ከተማ ተሞከረ ባለው መፈንቅለ መንግስት ክስተቶችን ያስተናገዱ ዋና ዋና ቦታዎችን በካርታዎቹ ላይ መመልከት ይቻላል። ካርታውን ያይን እማኞች ነን ያሉ ግለሰቦችና የመንግስት ባለስልጣናት የተናገሩትን መሰረት ያደረገ ነው።
Via #elu

ዶክተር አምባቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው የተገደሉበት የፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት በከተማ ማህል የሚገኝ ባለ 3 ፎቅ ህንጻ ሲሆን ዘወትር ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግለታል።

ብርጋዴር ጄነራል #አሳምነው የሚኖሩበትና ትዕዛዝ ሲሰጡበት ነበር የተባለው 'ገስት ሀውስ' በጣና ዳርቻ የሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት በጫካ የተከበበ ባለ 2 ፎቅ ህንጻ ነው። ይህ ህንጻ ከፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት 1 ፌርማታ ይርቃል።

የክልሉ ም/ደህንነት ሀላፊና የፕሬዝደንቱ ሹፌር ታገቱበት የተባለውና "መፈንቅለ መንግስት" አድራጊዎች እንደካምፕ የተጠቀሙበት የአማራ ስራ አመራር ተቋም ከገስት ሀውሱ በ3 ፌርማታ እርቀት ይገኛል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ና በአባይ ወንዝ ይዋሰናል።

ከግድያው ቀደም ብሎ የክልሉ የጸጥታና የደህንነት ሀላፊዎች ተሰበሰቡበት፣ ቀጥሎም እገታ ተፈጸመባቸው የተባለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስርያቤት ከፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት ቢያንስ በ3 ወይም በ4 ፌርማታ ይርቃል። በዚሁ ህንጻ በጸጥታ ሀይሎች መካከል ለሰዐታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። ሕንጻው የሚገኝበት አካባቢ የአማራ ቴሌቪዥንና ራዲዮን ጨምሮ አብዛኞቹ የክልሉ መንግስት ቢሮዎች ይገኛሉ።

በቅዳሜ ከፍተኛ ጥቃት ካስተናገዱ የከተማው አካባቢዎች፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚኖሩበት ቀበሌ ሶስት የሚገኝ በአጥር የተከለለ የመኖሪያ መንደር (gated community) አንዱ ነው። በፒካፕ መኪኖች የተጫኑ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ግቢውን ከሚጠብቁ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት ቢያንስ 6 ተገለዋል። በግቢው ከሚኖሩ ባለስልጣናት ጋርም የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው የተገደሉባት #ዘንዘልማ 'ከገስት ሀውሱ' በ6 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኝ 'ሳተላይት' ከተማ ናት። በከተማዋ የግብርና ኮሌጅ የሚገኝ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ በአብዛኛው ጫት በማምረት የሚተዳደሩ ናቸው። አካባቢውም በጫት ማሳ የተሸፈነ ነው። በከተማው ምዕራባዊ ዳርቻ የኢ.መ.ሠ ምዕራብ ዕዝ ዋና መስሪያቤትና የኢ.አ.ሀ ሰሜን ምድብ ዋና ጣቢያን ጨምሮ የወታደርና የፌ. ፖሊስ ካምፖች የሚገኙ ሲሆን፣ ቃል አቀባይ ንጉሱ ጥላሁን እንዳሉት በክልሉ ም/ፕሬዝደንት ግብዣ ወደ ከተማው እንዲገቡ ሆኗል። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም።