TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአዲስ አበባ ከተማ ያለ ደረሰኝ ግብይት ባከናወኑ፣ የዳቦ ግራም በቀነሱና የምርት ጥራት ጉድለት አስከትለዋል የተባሉ 40 የንግድ ቤቶች ታሸጉ፡፡

የማሸግ እርምጃው የተወሰደው በ27 ወፍጮ ቤቶች፣ 7 ዳቦ ቤቶች፣ 2 አትክልት ቤቶች እና በሌሎች የንግድ ቤቶች ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እርምጃውን የወሰደው የጉለሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት 60 ለሚሆኑ የንግድ ተቋማትም የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አስታውቋል፡፡

በከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ከተማ አቀፍ የቁጥጥርና የክትትል ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቴዎድሮስ ዓለሙ ተናግረዋል፡፡

በነጋዴዎች ላይ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች የተሰጠ መሆኑንም አቶ ቴዎድሮስ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የቁጥጥር ስራ ብቻውን በቂ እንዳልሆነና በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች መሰረታዊ የሚባሉ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋት ወደ ገበያ እንዲያስገቡ ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር ውይይት መደረጉም ተገልጿል፡፡

የፀረ-ኮንትሮባንድ ስራዎችንም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በአዲስ አበባ መውጫና መግቢያ ላይ ከፍተኛ የቁጥጥር ስራ እንደሚከናወን ሀላፊውን ጠቁመዋል፡፡

Via የክፍለከተማው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
🗞ቀን 13/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሙርሲ #ተገደሉ እንጂ የተፈጥሮ ሞት አልሞቱም" ፕሬዘዳንት #ረሲፕ_ጣይፕ_ኤርዶጋን
.
.
የቀድሞው የግብፅ ፕሬዘዳንት የነበሩትና እ.አ.አ በ 2013 #በመፈንቀለ መንግስት ከስልጣን የተወገዱትን #ማሃመድ_ሙርሲ አሟሟትን በተመለከተ የቱርኩ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን የሰጡት አስተያየት ሃላፊነት የጎደለው ስትል ግብፅ ኮነነች፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ኤርዶጋን የሙርሲን አሟሟት በተመለከተ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የግብፅ መንግስት የሙርሲን ህይወት ለመታደግ ምንም አይነት የወሰደው እርምጃ የለም የሚለው አስተያየት ተገቢነት የጎደለውና መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ኤርዶጋን ትላንት በተደረገው የምርጫ ዘመቻ ሰልፍ ላይ ሙርሲ “ተገደሉ እንጂ በተፈጥሮ ሞት አልሞቱም ”ብለው ሲናገሩ በቴሌቭዥን ተደምጠዋል፡፡

ኤርዶጋን አክለውም “ሙርሲ ለ20 ደቂቃ መሬት ላይ ወድቀው ሲያጣጥሩ ቢቆዩም ህይወታቸውን ለማዳን የሞከረ ግን አልነበረም”ማለታቸው ይታወሳል።

ምንጭ፡-ፕሬስ ቲቪ
🗞ቀን 13/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwdeode @tikvahethiopia
"የጦርነት እና የጥላቻ ንግግሮችን #እቃወማለሁ። "ሌላውን" ህዝብ በመሳደብ የሚገኝ "ጀግንነት" ይቅርብኝ። የሚያለማኝን ሰላም ትቼ የሚያጠፋኝን ግጭት አልመኝም። ሰው ሁሉ ወገኔ ነው። ለጥላቻ ሳይሆን ለህዝብ ፍቅር አሜን በሉ። አሜን!" #አብርሃ_ደስታ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ...

"I am an Instructor from #Mizan_Tepi university... (let my name be secret for time being)...all teachers who are teaching in tepi campus has stopped their job due to loss of guarantee in their stay in the city.. one of the reason which let us stop was the rape done on our statistics department colleague. There were so many robbery done on our staffs and the city dwellers, perhaps the rape was our last warning to stop our regular task and all staffs has signed petition to Ministry of education having copies will be sent to Prime minister office.... we need life guarantee to proceed!..Thank you #Tikvah"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጣሊያን መንግስት ከሚቀጥለው ሀገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዙ ስራዎችን ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በትላንትናው ዕለት ከጣልያን ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑኤል ሲ ዴል ሪ ጋር ተወያይተዋል።

🗞ቀን 14/10/2011
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንተርናሽናል ኮሚዩኒቲ ት/ቤት(ICS) ከፍተኛ ውጤት ላላቸውና በመንግስት ት/ቤት ለሚማሩ 10 የከተማችን ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠ። ኢ/ር ታከለ ከትምህርት ቤቱ ተማሪዎች እና መምህራን ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ኢ/ር ታከለ የICS ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት ላላቸዉ እና መክፈል ለማይችሉ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል እንዲሰጥ በጠየቁት ጥያቄ መሠረት ት/ቤቱ 10 ተማሪዎችን ተቀብሎ በነፃ ለማስተማር ቃል ገብቷል።

በመጨረሻም ኢ/ር ታከለ ኡማ ከተማሪዎች ጋር በመሆን በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል።

Via @mayorofficeAA
🗞ቀን 14/10/2011
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ!

#በአምቦ መስመር ልዩ ስሙ #አሸዋ_ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የመኪና አደጋ ደርሷል፤ ወደዛው መስመር እየተጓዛችሁ የምትገኙ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንድታደርጉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ከጎዴ ወደ ጅግጅጋ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ሕይወታቸው ካለፈው አምስት ሰዎች በተጨማሪ 23 ሰዎች ላይም ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የሶማሌ ክልል ፖሊስ አስታውቋል።ተሽከርካሪው 28 መንገደኞችን አሳፍሮ ይጓዝ እንደነበርም ነው ፖሊስ የገለጸው። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ክፍል የተሽከርካሪ አደጋ ምርመራ ቡድን መሪ ኢንስፔክተር አህመድ ኑር እንዳሉት አደጋው ትናንት ጠዋት በግምት 12፡30 ሰዓት አካባቢ የደረሰ ነው።

ተሽከርካሪው 28 ሰዎችን አሳፍሮ ከጎዴ ወደ ጅግጅጋ ከተማ ሲጓዝ ነበር የመገልበጥ አደጋ የደረሰበት።አደጋው ተሽከርካሪው ጠመዝማዛ መንገድ ላይ በፍጥነት በመጓዝ ላይ እያለ ድንገት ከመንገድ በመውጣቱ መድረሱንም ተናግረዋል።ተጎጅዎቹ በጅግጅጋና በጎዴ ሆስፒታሎች የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑንም ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Via #FBC
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የ2011 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ችግኞችን በመትከልና የደም ልገሳ በማድረግ ዛሬ በአዳማ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

Via #EPA
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-SPORT
የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ በግብፅ ካይሮ ይጀመራል!

ለመጀመሪያ ግዜ 24 ቡድኖችን ያሳተፈው ሰላሳ ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ በግብጽ ካይሮ ዛሬ ይጀመራል፡፡ በመክፈቻው ጨዋታ አዘጋጇ ግብፅ ዙንባቤውን ከምሽቱ አምስት ሰአት ላይ የምታስተናግድ ይሆናል፡፡

የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን በጸጥታና በዝግጅት ችግር ምክንያት አዘጋጅነቷ ተነጥቆ ለግብጽ የተሰጣት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ኪዘህ ቀደም በጥር ወር ላይ የሚካሄድ ሲሆን ዘንድሮ ግን በሰኔ ወር እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡

በግብጹ አፍሪካ ዋንጫ ካለው ሙቀት አንጻር በ32 ተኛውና በ75 ተኛው ደቂቃ የውሀ እረፍት የሚኖረው ይሆናል፡፡ ውድድሩ ከሰኔ 14 እስከ ሃምሌ 14 የሚካሄድ ሲሆን በስድስት ምድብ ተከፍሎ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ እኤአ በ19 57 በሱዳን አዘጋጅነት የተጀመረ ሲሆን ግብጽ አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ሳሙሄል ኤቶ አስራ ስምንት ጎል በማግባት የአፍሪካ ዋንጫ የምንግዜም ጎል አግቢ ነው፡፡

የ2019 አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ግብጽ ሰባት ግዜ በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫን ብዙ ግዜ በማንሳት ቀዳሚ ነች፡፡

ምንጭ:- ቢቢሲ
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tikvahethsport
#update በህንድ አውቶብስ ወደ ወንዝ ሸለቆ ገብቶ 44 ሰዎች ሞተዋል። አደጋው በሀገረ ሰሜናዊ የተራራማ ክፍል በሚገኘው የሂማቻል ፕራዴሽ ግዛት ኩሉ ወረዳ ነው።

የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳሉት 60 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ መንገድ ስቶ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሸለቆ ገብቶ ከሞቱት በተጨማሪ ብዙዎች ተጎድተዋል።

የተወሰኑ ሰዎችም በአውቶብሱ ጣሪያ ላይ ተንጠላጥለው ሲጓዙ እንደነበር ነው የተገለጸው። የዓይን እማኞች እንዳሉት አውቶብሱ በቀጭንና ኩርባ መንገድ ላይ ለመታጠፍ ሲሞክር ነው ወደ ሸለቆው የገባው።

የአካባቢው ፖሊስ ኮሚሽነር ሻሊኒ አግኒሆትሪ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለጹት፤ በአደጋው ከሞቱትና ከተጎዱት ውስጥ ከስራና ከትምህርት ቤት ሲመለሱ የነበሩ ሴቶችና ህጻናት ይገኙበታል።

ህንድ ውስጥ የተሽከርካሪ አደጋ በተደጋጋሚ ይከሰታል። በሂማቻል ፕራዴሽ ግዛት ብቻ ከፈረንጆቹ 2009-2018 ድረስ ከ30 ሺህ በላይ አደጋዎች ተመዝግበዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Via #BBC/#ENA
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
40/60...
/#ሼር/#share/

√የ40/60 ባለዕድለኞች የውል ፕሮግራም
√የውል ቦታ ቦሌ ክ/ከተማ አዳራሽ
√ውል የሚጀምርበት ቀን 14/10/2011

Via HAA
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልቃይት ስኳር ፋብሪካ...

የወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ ቢሆንም ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚያስፈልገውን ግድብ በውኃ ለመሙላት ከሦስት እስከ አራት ዓመታት ሊፈጅ ይችላል። ይኸንንም ጉድለት ለመሙላት ኔታፊም (Netafim) የተባለ የእስራኤል ኩባንያ ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚያገለግል የጠብታ መስኖ ግንባታ በማከናወን ላይ ይገኛል። ለስኳር ፋብሪካው የሚያስፈልገው የአገዳ ልማት በዚህ ዓመት ሊጀመር ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ቀድሞ ቢጠናቀቅም በሸንኮራ አገዳ እጦት ምክንያት በ2012 ዓ.ም. ምርት አይጀምርም ተብሏል።ግንባታውን የሚያከናውነው ካንስ የተባለ የቻይና ኩባንያ ነው።

Via Eshet Bekele
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች...

"የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር "የነገይቱን ኢትዮጵያ ዛሬ የተሻለ ትውልድ በመፍጠር በጋራ እንገንባ!" በሚል መሪ ቃል ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓም በቦሌ ቡልቡላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ፈንድ ተመስርቷል።"

Via #ERMIAS/TIKVAH-ETH/
🗞ቀን 14/10/2010 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ር ዶ/ር #አብይ_አህመድ የመንግስትን የ2011የሥራ አፈጻጸም ሪፓርት ሰኞ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 8ኛ ልዩ ስብሰባውን ሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2011ዓ.ም ጠዋት ያካሂዳል።

Via #EPA
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ክልል መንግስት ለ2 ሺህ 4 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ፡፡ የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ለሚገኙ 2 ሺህ 4 ታራሚዎች ይቅርታ ያደረገው 31ኛ ዓመት የሰማዓታት ቀን ምክንያት በማድረግ መሆኑን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል፡፡

Via #FBC
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በየዓመቱ ሰኔ 15 ቀን ታስቦ የሚውለው የትግራይ ታጋይ ሰማእታት ቀን የዘንድሮው 31ኛው ዓመት “የተጋይ ሰማእታት አደራ፣ የትግራይ ህዝብ ደህንነትና ህልውና በፅናት ማረጋገጥ ነው!!” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፓልም ዘይትን አስመልክቶ በአንዳንድ ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ኢንስቲትዩቱ ከገለጸው ውጪ በመሆኑ #ሊታረም እንደሚገባው የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሰጠው መግለጫ እንዳለው፤ ፓልም ኦይል እየተባለ የሚጠራውን ዘይት በየቀኑ መጠቀም ዘይቱ በውስጡ ካለው ሳቹሬቲድ ፋቲ አሲድ አንፃር በረዥም ጊዜ መጠቀም የኮልስትሮል መጠንን ከፍ ያደርጋል ተባለ እንጂ ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም አላልከኵም ብሏል።

በአንዳንድ ሚዲያዎች “ኢንስቲትዩቱ የሚረጋውን ዘይት ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም አስጠነቀቀ” ተብሎ የተላለፈው ዘገባ “ከእውነታው የራቀ” መሆኑን የኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛህኝ ተስፋዬ አስረድተዋል።

Via waltainfo
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ተቋርጦ የነበርው የኢትዮ-ጁቡቲ የምድር ባቡር የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የትራስፖርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የጀመረው የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ጉብኝት ካደረጉ በኃላ ነው ተብሏል። የባቡር ትራንስፖርቱ የሀገሪቱን የገቢና የወጪ እቃዎች በማሳለጥ ረገድ ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ፡- የትራንስፖርት ሚ/ር
🗞ቀን 14/10/2010 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#1 በአዲስ አበባ ከተማ #ከሰኔ 30 ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው የሞተር ብስክሌትና የጭነት ተሽከርካሪዎች መመሪያ:-
#2 በአዲስ አበባ ከተማ #ከሰኔ 30 ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው የሞተር ብስክሌትና የጭነት ተሽከርካሪዎች መመሪያ:-