ማሳሰቢያ! በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከሰኞ ጀምሮ የስራ ማቆም እና ከቤት ያለመውጣት አድማ አለ በማለት ህዝብን የማደናገር ስራ እየተሰራ መሆኑን ለመመልከት ተችሏል። ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከእንደዚህ አይነት ከእውነት የራቁ እና ህዝብን ወደተሳሳተ መንገድ ከሚወስዱ መረጃዎች እርቃችሁ መደበኛ የእለት ተእለት ስራችሁን በሰላም እንድታከናውኑ እንመክራለን።
ሀገር ወዳድ መስለው ህዝብን ወደተሳሳተ መንገድ ከሚወስዱ የማህበራዊ ሚዲያ ሰዎች ተጠንቀቁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

አሳዛኝ ዜና! ሞያሌ! ዛሬ በሞያሌ ከተማ በትንሹ የ9 ሰዎች ህይወት በፀጥታ አስከባሪዎች መጥፋቱ ተሰማ። ከ10 የሚበልጡ ሰዎችም ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ተነግሯል። የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ(OBN) እንደዘገበው። በሌላ በኩል የተለያዩ አክቲቪስቶች የሟቾችን ቁጥር 15 ያደርሳሉ። ለሰው ሞት እና ጉዳት ምክንያት የሆነው ነገር እስካሁን በውል አልታወቀም።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞያሌ! በሞያሌ ከተማ ከተጎዱት ሰዎች መካከል 4 የሚሆኑት ሀዋሳ እና ወላይታ ወደሚገኙ ሆስፒታሎች ሪፈር ተደርገዋል።
ምንጭ፦ RDH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ RDH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በሞያሌ ከተማ የፀጥታ ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ....
. የ13 ሰው ህይወት አልፏል።(እንደ ከተማው ነዋሪዎች ገለፃ)
. ኮማንድ ፖስቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 9 ብቻ ነው ብሏል።
. ከ12 የሚበልጡ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
. አብዛኞቹ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሞያሌ ከተማ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን...
. 4 የተጎዱ ሰዎች ደግሞ ወደ ሀዋሳ እና ወላይታ ሆስፒታሎች ሪፈር ተደርገዋል።
....
ከሟቾች መካከል አቶ ተማም ነጌሶ የተባለ የመደ ሚጎ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ይገኝበታል።
ምንጭ፦ OBN,RDH

መጋቢት 02! ቆሼ ተንዶ የበርካቶችን ሕይወት ከበላ አመት ሞላው። በትክክል ስንት ሰው እንደሞተ እንኳ በአግባቡ አልተመረመረም። ትኩስ ሞት፤ ትኩስ እስራት፤ ትኩስ ቀውስ፤ እያጣደፈ የተፈጠረው ሳይመረመር ጥፋተኛው ሳይጠየቅ ጊዜ ይነጉድ ያዘ። የኢትዮጵያ ውጥንቅጥ ፍጥነት አሰቃቂ እና አስደንጋጭ ኩነቶች እንደ ቀልድ እንዲዘነጉ ከሚያስገድድበት ደረጃ ደርሷል።
መጋቢት ሁለት ቀን 2009 ዓ.ም. ቆሼ ተናደ። እናቶች፣ ሕጻናት ወጣቶችን ጨምሮ ድሕነት የገፋቸው አዲስ አቤዎች ቆሻሻ ከተደረመሰባቸው አመት ሞላ። ሙሉ አንድ አመት! ቆሼን ረስተን ስንት ሞት ቆጠርን?
ምንጭ፦ እሸቴ በቀለ(ዶቼ ቨለ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መጋቢት ሁለት ቀን 2009 ዓ.ም. ቆሼ ተናደ። እናቶች፣ ሕጻናት ወጣቶችን ጨምሮ ድሕነት የገፋቸው አዲስ አቤዎች ቆሻሻ ከተደረመሰባቸው አመት ሞላ። ሙሉ አንድ አመት! ቆሼን ረስተን ስንት ሞት ቆጠርን?
ምንጭ፦ እሸቴ በቀለ(ዶቼ ቨለ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ አዲሱ አረጋ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ በዛሬው እለት በሞያሌ ከተማ በጠፋው የሰው ህይወት ማዘናቸውን ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ! በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረው የ2010 ዓ.ም የመጀመሪያው ሴሚስተር የማጠቃለያ ፈተና ተጠናቋል። ሁለተኛውን ሴሚስተር ለመጀመር ለተማሪዎች የ5 ቀን እረፍት ተሰጥቷል።
ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል በነበረው አድማ ሳቢያ ፈተናው ለቀናት ተቋርጦ እንደነበር አይዘነጋም።
ምንጭ፦ ጃክሰን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል በነበረው አድማ ሳቢያ ፈተናው ለቀናት ተቋርጦ እንደነበር አይዘነጋም።
ምንጭ፦ ጃክሰን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሞያሌ #Moyalle በሞያሌ ከተማ በጠፋው የወገኖቻችን ህይወት ልባዊ ሀዘን እንደተሰማኝ እየገለፅኩ ለሟች ቤተሰቦች፣ ለዘመድ አዝማዶች፣ ጓደኞች እና ወዳጆች እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በቻናሉ እና በራሴ ስም መፅናናትን እመኛለሁ። የተጎዱት ወገኖቻችንን ፈጣሪ ይማርልን።
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
የወገን ሞት ያማል!
በኢትዮጵያ ተስፋ አንቆርጥም!
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
የወገን ሞት ያማል!
በኢትዮጵያ ተስፋ አንቆርጥም!
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮማንድ ፖስቱ! በሞያሌ አከባቢ አምስት የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተሳሳተ መረጃ ይዘው ባደረጉት እንቅስቃሴ የዘጠኝ ሰዎች ህትወት ሲያልፍ በ12 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።
በአሁኑ ወቅት የሻለቃዋን አዛዥ ጨምሮ አምስቱ የሰራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን ፈተው በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራ እየተካሄደባቸው ነው።
በአገራችን የተከሰተውን ሁከትና ግርግር በማረጋጋት የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ ሲባል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ ተግባራዊ እየተደረገ ነው። አዋጁን ለማስተግበርም በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫ የጸጥታ ኃይሎች ተሰማርተው ግዳጃቸውን በመወጣት ላይ ናቸው።
ይህን በአገራችን የተፈጠረውን ሁከትና ግርግር እንደምቹ አጋጣሚ በመቁጠር ሁኔታውን ለማባባስና ለራሳቸው የጥፋት ሴራ ለማዋል በሞያሌ አከባቢ የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው
የገቡ የኦነግ ታጣቂዎችን ለመቆጣጠርና ለመደምሰስ አንድ የሻለቃ ጦር በስፍራው ላይ ለግዳጅ ተሰማርቶ ይገኛል።
ይሁን እንጂ የሻለቃዋ ጦር አዛዥ የሚገኝበት አምስት የሻለቃዋ የሰራዊት አባላት የተሳሳተ መረጃ ይዘው ባደረጉት እንቅስቃሴ በአከባቢው ሕብረተሰብ ላይ ጉዳት ደርሷል። በጉዳቱ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 12 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።

የማጣራት ስራውንም በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ዝርዝር ውጤቱ ለህዝቡ የሚገልጽ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታርያት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታርያት ጽሕፈት ቤት ለኢቢሲ በላከው መግለጫው በአጋጣሚው ለጠፋው የሰው ህይወትና ጉዳት ጥልቅ ሀዘኑን ይገልጻል ብሏል።
ምንጭ፦ EBC

ኢትዮጵያ! የመከላከያ ሰራዊት አባላት #በተሳሳተ መረጃ በሞያሌ ከተማ 9 ሰዎችን ሲገድሉ 12 ሰዎችን ደግሞ አቁስለዋል።
.
.
ምን አይነት ዜና ነው እየሰማን ያለነው?? ፈጣሪ ሆይ ይቅር በለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
.
.
ምን አይነት ዜና ነው እየሰማን ያለነው?? ፈጣሪ ሆይ ይቅር በለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ትላንት ተጀምሯል።
በፎቶው እንደምትመለከቱት 3 የደኢሕዴን፣ 3 የሕወሓት እና አንድ የኦሕዴድ ተወካዮች ፊት ለፊት ተቀምጠዋል።
ምንጭ፦ እሸቴ በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በፎቶው እንደምትመለከቱት 3 የደኢሕዴን፣ 3 የሕወሓት እና አንድ የኦሕዴድ ተወካዮች ፊት ለፊት ተቀምጠዋል።
ምንጭ፦ እሸቴ በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ርዋንዳ! ቅዳሜ እለት መብረቅ ርዋንዳ ውስጥ ያለን የሰባት ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን መትቶ 16 ሰው ገድሎ ከ140 የማያንሱ እንዳቆሰለ ተነገረ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
https://www.bbc.com/news/world-africa-43362508

BBC News
Rwanda Seventh-Day Adventist churchgoers killed by lightning
At least 16 people were killed and dozens more injured at a Seventh-Day Adventist church in the south.
ሞያሌ! ሌተናል ጄነራል ሐሰን ኢብራሒም በሞያሌ 9 ሰዎች የተገደሉበትና 12 በቆሰሉበት "ግጭት" የተወሰደው እርምጃ "የግዳጅ አፈፃፀም ደምብ ያልተከተለ" ነበር ብለዋል። "የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች የሚገኙበት ቡድን በሔሊኮፕተር ወደ ቦታው ሔዷል" ሲሉ አክለዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞያሌ! በሞያሌ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 10 ደረሰ፤ ሺህዎች ወደ ኬንያ ተሰደዋል።
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 10 መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣን እና የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ገልፀዋል፡፡
ትላንት እሁድ አንድ ሰው ሲገደል ሌላ አንድ ሰው መቁሰሉን ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የቅዳሜውን ግድያ ተከትሎ የደኅንነት ሥጋት የገባቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ኬንያ ተሰድደዋል ተብሏል፡፡
የሞያሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አስቻለው ዮሃንስ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ትላንት ከተገደሉት ውስጥ የአራቱ ቀብር ዛሬ ተፈጽሟል፡፡ የቆሰሉት ሰዎች ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሐዋሳ መላካቸውንም ከንቲባው ገልጸዋል፡፡
የከተማይቱ ነዋሪዎች ቅዳሜ እና እሁድ ወደ ኬንያ መሰደዳቸውን አቶ አስቻለው አረጋግጠው ብዛታቸው ምን ያህል እንደሆነ ግን እንደማያውቁ አስረድተዋል፡፡ “ቅዳሜ እለት በትክክል የሞቱት ዘጠኝ ናቸው፡፡ ከቆሰሉት ውስጥ አንድ ተጨምሮ አሁን የሟች ቁጥር አስር ደርሷል፡፡ ከዚያ ውጭ የቆሰለው አስራ አንድ ሰው ነው፡፡ እሁድ አራት ሰው እዚህ ተቀብሯል፡፡ ሌላ ሶስት ሰው ወደ ሀገር ቤት ሄዷል፡፡ አንዱ የጉራጌ ተወላጅ ነው፡፡ ሁለቱ የኦሮሞ አርሲ ተወላጆች ናቸው፡፡ እነዚያ ትላንት ወደ ቤተሰቦቻቸው ተልከዋል፡፡ ከዚያ ውጭ ሁለት ቤተሰቦቻቸው ያልታወቁ አሉ፡፡ እነርሱን እስከ ዛሬ(ሰኞ) ጠብቀን የሚደረገውን ነገር ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ተወያይተን ውሳኔ እንሰጣለን፡፡ ቅዳሜ ያው በተፈጠረው ሁኔታ ህዝቡ ስጋት ስለገባው ምንም የደህንነት ማስተማመኛ የለም በሚል ወደዚያ መሸጋገሩ ያለ ነገር ነው፡፡ ህዝቡ አሁን ወደ ኬንያ ማዶ ሴሺ ሞያሌ ታውን የሚባል አካባቢዎች ላይ ነው ሰፍሮ ያለው፡፡”
ስለትላንቱ ሁኔታ የተጠየቁት የሞያሌ ከንቲባ አንድ ሰው በሞተር ሳይክል ሲሄድ በጥይት ተመቶ መቁሰሉን መስማታቸው እና ተጨማሪ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
አንድ የሞያሌ ሆስፒታል ሰራተኛ ግን ትላንት በጥይት ከተመቱት ውስጥ አንደኛው ሞቶ ሌላኛው መቁሰሉን እማኝነታቸውን ለዶይቸ ቬለ ሰጥተዋል፡፡
ቅዳሜ የተመለከቱትንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ “ዛሬ(እሁድ) ራሱ ሰባት ተኩል ላይ ሰው ተመትቷል፡፡ ጫሜ የሚባል ቦታ፡፡ ከሆስፒታል በኩል ነው ራቅ ይላል፡፡ ሁለት ሰው ተመትቷል፡፡ አንዱ ሆስፒታል ነው ያለው፡፡ አንዱ ሞቷል ይባላል፡፡ መከላከያ፣ አጋዚ ነው፡፡ ከአጋዚ ውጭ ማንም አይደለም፡፡ እኔ በአይኔ ያየሁት የ10 ሰው ሞት ነው፡፡ ሬሳ ክፍል ውስጥ ነው፡፡ የሞተ፣ ህይወቱ የጠፋ፡፡ የቆሰለ አስራ ምናምን ሰው ነው፡፡ ከስልጤም፣ ከወላይታም፣ ከኦሮሞም ብሔር ብሔረሰብ ነው የተገደለው፡፡ ያለምንም ጥፋት ያለምንም ጥያቄ ነው የተገደሉት እነዚህ ሰዎች፡፡”
በሆስፒታል በመገኘት አስር የሞቱ ሰዎችን በአይናቸው መመልከታቸውን የተናገሩ አንድ የሸዋ በር ነዋሪ ደግሞ ወደ አስር ሰዓት ግድም እርሳቸውን ጨምሮ በርካታ የቀበሌያቸው ነዋሪዎች ድንበር አቋርጠው ወደ ኬንያ መግባታቸውን አስረድተዋል።
አሁን በትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ የተናገሩት ተፈናቃዩ መሬት ላይ ተኝተው ማደራቸውን ገልጸዋል፡፡ አሁን ስለተጠሉለበት ቦታ ደግሞ ተከታዮን ብለዋል።
“እኛ አካባቢ እዚህ የተጠልለነው ትንሽ ነን፡፡ አንድ ሁለት ሺህ አንበልጥም፡፡ እንደኬንያ አጠራር ሴሺ ነው የሚባለው፡፡ ሞያሌ አውራጃ ውስጥ ሆነ በማርሳቤት አስተዳደር ውስጥ ነው፡፡ የቅዳሜውን ጭፈጨፋ ህዝቡ ፈርቶ ነው፡፡ ያንን ፍራቻ እንደገና ይደገማል ብሎ ሀዝቡ ከሶስት ቀበሌ ወጥቷል፡፡ ከጫሙቅ፣ ሸዋበር እና አርበሌ ቀበሌዎች ኬንያ ተሰድደው ማለት ይቻላል፡፡ በተለይ ህጻናት እና ሴቶች አብዛኞቹ ሄደዋል፡፡ አንዳንድ ደግሞ ወንዶች እዚያ የቀሩ አሉ፡፡” ወደ አራት ሺህ የሚጠጉ የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች በሌላ ቦታ ተጠልለው መመልከታቸውን እኚሁ ተፈናቃይ ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡
ተፈናቃዩ እንዳሉት በኬንያ ግዛት የአካባቢው አስተዳደር እና የቀይ መስቀል ሰዎች ምግብ እና መጠጥ ለተፈናቃዮቹ ያደሉ ሲሆን ዛሬም ምዝገባ ሲያካሄዱ ውለዋል።
ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግን ማንም ሰው መጥቶ እንዳልጎበኛቸው አስረድተዋል፡፡
በሞያሌ ስለተፈጠረው ሁኔታ ለመንግስታዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ማብራሪያ የሰጡት የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ሴክሬተሪያት ተወካይ ሌተናል ጄነራል ሀሰን ኢብራሂም የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦችን ያካተተ ቡድን ትላንት በሄሌኮፕተር ወደ አካባቢው በፍጥነት መሄዱን ገልጸው ነበር፡፡
ሌተናል ጄነራል ሀሰን ቅዳሜ በሞያሌ የተፈጠረውን ሁኔታ “የተሳሳተ መረጃ በመያዝ የተፈጠረ ግጭት” ሲሉ የጠሩት ሲሆን ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በግጭቱ ተሳትፏል የተባለ የአንድ ሻለቃ ጦር ትጥቅ እንዲፈታ ተደርጎ አምስት አባላቱ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ

ሞያሌ! በትላንትናው ዕለት በሞያሌ ተጨማሪ 1 ሰው ሲገደል ሌላ 1 ሰው ቆስሎ ሐኪም ቤት ገብቷል። ቅዳሜ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 10 ደርሷል። 12 ሰዎች ቆስለዋል። ሥጋት የገባቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች መሰደድ ጀምረዋል።
ምንጭ፦ E.B
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ E.B
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስፖርት! ትላንት በሶዶ ከተማ በተደረገ አንድ ተስተካካይ የኢትዮጵያ ፕርሜርሊግ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ወልዲያን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ተጨማሪ....
ከባለፈው የዛማሌኩ ድል በኃላ በከተማው በነበረ የደስታ አገላለፅ አንድ ህፃን ኤሌክትሪክ ይዞት መሞቱ የሚታወስ ሲሆን የዚህን ህፃን ቤተሰቦች ለመደገፍ በደጋፊዎች ማህበር በኩል በስታዲየም ከተገኘው ህዝብ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ተሰርቷል። ህፃኑ አሳምቡሳ እየጠበሰ ቤተሰቦቹ ይረዳ እንደነበር የዲቻ ደጋፊዎች ማህበር ገልጿል።
.....
የወላይታ ድቻ የእግርኳስ ክለብ ከዛማሌክ ጋር ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ ሀሙስ ወደ ግብፅ ይበራል።
......
የቡድኑን ወደ ገብፅ ማቅናት አስመልክቶ የደጋፊዎች ማህበር ነገ ማክሰኞ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ከተማ የማስዋብ ስራ እንደሚሰራ ገልጿል። ለደጋፊዎችም ይህን ጥሪ አቅርቧል።

መቐለ! የመቐለ ዩኒቨርስቲ የዓይደር አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የህክምና የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸው 36ዐ ተማሪዎችን መጋቢት 02/2010 አስመርቋል፡፡
ከተመራቂዎች መካከል 157ቱ የህክምና ዶክተሮች ሲሆኑ 5ዐዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡
በሃገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በፎረንሲክ ህክምና ፣ በፊዚዮትራፒ፣ በቀዶ ህክምና እና ሌሎች የህክምና የሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ከተመራቂዎቹ መካከል ናቸው፡፡
የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ህይወት ተመራቂዎቹ በሰለጠኑበት ሙያ ሃገራቸውን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን የሀገሪቱ የጤና ስርዓት ለማዘመን በአገር አቀፍ ደረጃ በ24ዐ ወረዳዎች እና በ1855 ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ዘመናዊ የጤና የመረጃ ቋት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሠዋል፡፡
ተመራቂዎቹም ለምርምር ሥራዎች ትኩረት እንዲሠጡም አሳስበዋል፡፡
ተመራቂዎች በበኩላቸው ያገኙትን ዕውት በመጠቀም ማህበረሰባቸውን በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

ኢትዮጵያ! ዛሬ በአዲስ አበባ እና በአካባቢዋ ከተሞች ምንም አይነት የተለይ እንቅስቃሴ የለም። መንግዶችና የንግድ ተቋማት ክፍት ናቸው። ሰዎችም የእለት ተእለት ስራቸውን በሰላም እያከናወኑ ነው።
በሌላ በኩል በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው ያለው። የመንግድ መዘጋት እና የንግድ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጥ የታየበት ከተማ እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።
....
አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ መንግዶች እንደሚዘጉ እንዱሁም የንግድ ተቋማት አገልግሎት እንደማይሰጡ በመላው ሃገሪቱም አድማ እንዳለ በፌስቡክ በማሰራጨት ህዝብን የማደናገር ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ተደርሶበታል።
.
.
በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሚፈጠሩ አዳዲስ ክስተቶች ካሉ በተቻለኝ ፍጥነት ላሳውቃችሁ እሞክራለሁ።

አዳማ! አዳማ የሚገኘው ኩሪፍቱ ሪዞርት የእሳት አደጋ እንደደረሰበት አሁንም እሳቱ እንዳልቆመ መረጃዎች እየደረሱኝ ነው።
አዳማ የምትገኙ ተከታዮች እውነት መሆኑን እንድታረጋግጡልን በአክብሮት እንጠይቃለን።