TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦሮምኛ ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ገድሏል የተባለው የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት👇
ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ገድሏል የተባለው ተከሳሽ፣ ከተማ ረጋሳ፣ የእድሜ ልክ እስራት ተበየነበት።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 28 2011ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ከተማ ረጋሳ ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ለመግደል ሆነ ብሎና አቅዶ የካቲት 4 2011 ዓ.ም. ከምሽቱ 5፡30 ላይ በሊበን ጩቃላ ወረዳ በሽጉጥ ሁለት ግዜ ተኩሶ ደረቱን መትቶ መግደሉ ተረጋግጧል ብሏል።

ድምጻዊ ዳዲ ገላን በጥይት ተመትቶ የሞተ ዕለት አሟሟቱ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት እንጂ ሆነ ተብሎ የተደረገ አይደለም የሚል እምነት ነበር።

በወቅቱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የድምጻዊው ጓደኛ እና የሊበን ጩቃላ ወረዳ ፖሊስ ፅፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ግርማ ሚደቅሳ ድምጻዊው ለደስታ በተተኮስ ጥይት መገደሉን ገልጸው ነበር።

የአስክሬን የምረመራ ውጤት አርቲስቱ ሁለት ግዜ በሽጉጥ ጥይት ተመትቶ መገደሉን ያረጋገጠ ሲሆን አንድ ጥይት የሟች አስክሬን ውስጥ ተገኝቷል ተብሏል።

ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም ከሟች አስክሬን ውስጥ የወጣው ጥይት አይነት ተከሳሽ ከሚይዘው ሽጉጥ የተተኮሰ መሆኑ ተረጋግጧል ብሏል።ተከሳሹ ግድያውን አልፈጸምኩ ሲል ቢከራከርም የቀረበበትን ማስረጃ መከላከል ግን አልቻለም።

አቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የቅጣት ማክበጃ ሃሳብ የለኝም በማለት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ጠይቋል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው ደንበኛቸው ከዚህ በፊት ተከስሰው እንደማያውቁ፣ የተመሩ ሰው አለመሆናቸውን፣ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ላይ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን እንዲሁም የበርካታ ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን በመጥቀስ ቅጣቱ እንዲቀንስ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ተከሳሹም አቅመ ደካማ የሆኑ ሰዎችን ጨምሮ 9 የቤተሰብ አባላት አስተዳዳሪ መሆናቸውን በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን እንዲቀንስላቸው ተማጽነዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሸ ከተማ ረጋሳ ድምጻዊ ዳዲ ገላንን መግደሉ በመረጋገጡ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት በይኖበታል።

ድምጻዊ ዳዲ ገላን ፓለቲካዊ ይዘት ያላቸውን የኦሮምኛ ሙዚቃዎችን በመጫወት የሚታወቅ ሲሆን በዘፈኖቹ በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርጎ ነበር።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአቶ ኢሳያስ ዳኘው ጠበቆች የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በደንበኛቸው ላይ አሻሸሎ ያቀረበው ክስ ከፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ውጭ መሆኑን በመግለጽ አቤቱታ አቀረቡ።

የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም በእነ አቶ ወልደጊዮርጊስ ወልዱ የክስ መዝገብ ሁለተኛ ተከሳሽ በሆኑት በአቶ ኢሳያስ ዳኝው ላይ የተሻሻለ ክሱን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

የአቶ ኢሳያስ ዳኝው ጠበቆች ዛሬ ለፍርድ ቤቱ በጽሑፍ ያቀረቡት አቤቱታ አቃቤ ሕግ አሻሽሎ ባቀረበው በዚህ ክስ ላይ ቃላትና ቁጥር አውጥቶ ከፍርድ ቤቱ ፈቃድ ውጪ ሶስት ምስክሮችን አቅርቧል ይላል።

በመሆኑም አቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበውን ክስ አቀራረብ በተለይም የማስረጃዎችን ጉዳይ ለመረዳት አዳጋች ሆኖብናል በማለት አስታውቀዋል።

አቃቤ ሕግ ያሻሻለው የክስ አቀራረብ በተለይም የማስረጃ ጉዳዩን ለመረዳት አዳጋች አድርጎብናል በዚህም ምክንያት ጉዳዩን በምን መልኩ ማስኬድና ደንበኞቻችንን ማማከር እንዳለብን ለመወሰን ተቸግረናል ነው ያሉት።

እናም ፍርድ ቤቱ በቀረበው አቤቱታ ላይ የሚሰጠውን ትዕዛዝ ተመልክተን በተሻሻለው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እናቅርባለን ወይም ቀጥታ ምስክር ወደማሰማት ሂደት እንገባለን የሚለውን እንመለከታለን ብለዋል ጠበቆቹ።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ለአቤቱታው ምላሽ ለመስጠት ለግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ለአንድ ተማሪ ህልፈት ምክንያት የሆኑ #ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ መጀመሩን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገለጹ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳደዱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ ላይ በተማሪው ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

ህይወቱ ላለፈው ተማሪ ቤተሰቦችና ጓደኞች መፅናናትን የተመኙት ዶክተር ደብረጽዮን፥“ድርጊቱ አስነዋሪ ነው” ብለዋል።

“ትግራይ የብሄሮችና ብሄረሰቦች መኖሪያ መሆኗን አምኖ ለመጣ ተማሪ እንዲህ አይነት ተግባር መፈፀም ሰላም ወዳዱን የክልሉን ህዝብ ባህልና ታሪክ የማይገልፅ ነው” ብለዋል።

ድርጊቱን የፈፀሙ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር መጀመሩን አስረድተው፥ ተጠርጣሪዎቹ ጥፋታቸውን በማጣራት የክልሉ መንግስት ወደ ህግ የሚያቀርባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በመስዋእትነት የተረጋገጠው ሰላም በጥቂት ግለሰቦች አይደፈርስም ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ፥ “ህብረተሰቡ ሰላሙን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መነሳት ይኖርበታል” ነው ያሉት።

በክልሉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይም በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የጠየቁት ዶክተር ደብረጽዮን፥ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ኤዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADP

ግንቦት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአክሱም ዩኒቨርስቲ የ2ኛው አመት የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ በነበረው ዮሐንስ ማስረሻ ሰይፈ ላይ የተፈፀመውን ግድያ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አጥብቆ ያወግዛል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተማሪ ዮሐንስ ማስረሻ ሞት የተሰማውን መሪር ሃዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞቹና ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የሚገኙ የመስተዳድር እና የጸጥታ አካላት እንዲህ አይነት አስነዋሪ ድርጊቶች ወደፊት እንዳይደገሙ አስቀድሞ በመከላከል ረገድ እንዲሁም የተማሪዎችን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ይህንን አጸያፊ ድርጊት የፈጸሙ ወንጀለኞች በአስቸኳይ ተለይተው ለፍርድ እንዲቀርቡ ለማድረግ እና ወደፊትም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ይገልጻል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም.
ባህር ዳር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የግብረ ሰዶማዊያኑ ጉዞ ተወገዘ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ አንድ የግብረ ሰዶማዊያን ቡድን በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ማቀዱን አውግዟል፡፡ ጉብኝቱን ያዘጋጀው “ቶቶ” የተሰኘ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ አስጎብኝ ድርጅት ሲሆን ሲኖዶሱ ይህንኑ ድርጅትም መውቀሱን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡ ቡድኑ ጉብኝቱን ሊያደርግ ያሰበው በላሊበላ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዝግጅቱ ተጠናቋል...

ለሀገር አቀፍ የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተናዎች አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነአቶ በረከት እና ታደሰ ክስ ላይ የዐቃቢ ሕግ ምስክሮች ሲያዳምጡ ውለዋል፤ የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ዘገባ ደግሞ ማብራሪያ እንዲሰጥ በፍርድ ቤቱ ተጠይቋል፡፡

አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ በተከሰሱባቸው መዝገብ ቁጥር 2፣ 3 እና 4 ዛሬ ከሰዓት በፊት በተሰየመው ችሎት የዐቃቢ ሕግ ምስክሮችን ቃል መስማት የጀመረው ፍርድ ቤቱ ከሰዓት በኋላም የአንድ ምስክር ቃልን አድምጧል፡፡ የቀሪ ምስክሮችን ቃል ለመስማትም ለነገ ግንቦት 29 ቀን 2011ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከዚህ በፊት በተሰየመው ችሎት ያዳመጠውን የዐቃቢ ሕግ ምስክሮች ቃል ወደ ጽሑፍ ሳይቀየር እና ትክክለኛነቱን ፍርድ ቤቱ ሳያረጋግጥ የክልሉ ፀረ ሙስና ኮሚሽን መዘገቡን ተከትሎ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ነገ ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ...

ተማሪዎች በመማሪያ ክፍላቸው በመገኘት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠ። ትምህርታቸውን በማይከታተሉ ተማሪዎች ላይ ዩኒቨርሲቲው ደረጃ በደረጃ ማናቸውንም አገልግሎቶች የሚያቆምና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

አተያየታቸውን ለTIKVAH-ETH የሰጡ ተማሪዎች በበኩላቸው፦ ዩኒቨርሲቲው አሁንም ወደቀደመው ሰላሙ እንዳልተመለሰና የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ገልፀው የሚመለከተው አካል ችግሮችን #በዘላቂነት ሊፈታ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
/የአክሱም ዩኒቨረስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፀሐይ አስመላሽ/ የተናገሩት፦
.
.
"ከአክሱም ከተማ ነዋሪዎች፣ ከሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን ውይይት ተጀምሯል፤ የተደረገው ውይይት ተማሪዎችን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል"

"በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ ፖሊስ ምርመራ የጀመረ ሲሆን ህብረተሰቡም መረጃ በማቅረብ ትብብር እያደረግ ይገኛል"

"የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከመሰል ድርጊቶች ራሳቸውን በማራቅ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመጡበት ዓላማ ሊቆሙ ይገባል"

Via #ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
/የደብረማርቆስ ዩኒቨረስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ/ የተናገሩት፦
.
.
"ተማሪዎች ከየትኛውም የፖለቲካ እንቅሰቃሴዎች ራሳቸውን ነፃ በማድረግ ለያዙት #ዓላማ ተገዥ እና የመፍትሄ አካል ሊሆኑ ይገባል"

"የተለያዩ አካላት ድርጊቱን #ከማውገዝ ይልቅ #ለፖለቲካ ጥቅም ለመጠቀም ሞክረዋል ብለዋል"

"ከከተማው ነዋሪ ጋር በተከታታይ የተደረጉ ውይይቶች ተማሪዎች #ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ አስችሏል"

"መሰል ድርጊቶች እንዳያጋጥሙ አሁንም ከአካባቢው ማህበረስብ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል"

Via #ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ከፍትሕ አካል አባላት ጋር እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ ላይ ከ3 ሺህ በላይ ዳኞች፣ ዐቃብያነ ሕግ፣ ጠበቆችና የፍትሕ ዘርፍ አመራሮች መሳተፋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኝ መረጃ ያመላክታል።

በውይይት መድረኩ በፍትሕ ሥርዓቱ ለውጥና የማሻሻያ ሥራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ምክክር የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና ህልፈት | የነቀምት ከተማው ተጫዋች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ። በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ እየተወዳደረ የሚገኘው ነቀምት ከተማ ተጫዋች የሆነው ወንድወሰን ዮሐንስ በትላንትናው ዕለት በተነሳ ድንገተኛ ግርግር በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፏል።

ተጫዋቹ ከክለብ አጋሮቹ ጋር በመሆን እራት ተመግበው ከሆቴል በመውጣት ላይ ሳሉ በአካባቢው የተነሳውና መነሻው ያልታወቀ ድንገተኛ ሁከት እስከ ቦንብ ፍንዳታ የደረሰ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ተጫዋቹ ከግርግሩ ለመሸሽ ሲሞክር ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ ሊያልፍ እንደቻለ ታውቋል። (ተጫዋቹ በግርግሩ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ አልነበረውም)

ስለጉዳዩ የነቀምት ከተማው ዋና አሰልጣኝ ቾምቤ ገብርህይወት ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ” በጣም አሳዛኝ ነገር ነው ያጋጠመን። ቦንቡ የፈነዳው እኔ ካለሁበት ቦታ ቅርብ በመሆኑ ተጫዋቾቹ ተረፍክ ወይ ብለው ደውለውልኝ ነበር። እነሱ ካሉበት ሆቴል በፍተሻ ከወጡ በኋላ ከጓደኞቹ ጋር በሚሄድበት ጊዜ ነው ከመከላከያ ፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን ያጣው። ወንድወሰን ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የማውቀው። በጣም ጭምት ነው ቤተሰቡን የሚረዳ ነው። ሁለት መንታ ልጆች ይረዳል። እንጃ ለምን እንዲ እንደተደረገ፤ ወንድወሰን በቡድናችን ትልቅ ቦታ ነበረው። ለቡድኑ አባላት ለወላጆቹ እና ለወዳጆቹ በሙሉ መፅናናትን እመኛለሁ።” ብለዋል።

ወንድወሰን ዮሐንስ ትውልድ እና እድገቱ በሀዋሳ ኮረም ሰፈር አካባቢ ሲሆን በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ የእድሜ እርከኖች ከተጫወተ በኋላ በስልጤ ወራቤ እና ኢትዮጵያ ውሀ ስራ (ኢኮስኮ) ሲጫወት ቆይቶ አሁን ወደሚገኝበት ነቀምት ከተማ አምርቶ እየተጫወተ የሚገኝ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ነበር። የተጫዋቹ አስከሬን ወደ ሀዋሳ እያመራ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በነገው ዕለትም በትውልድ ከተማው ሥርዓተ ቀብሩ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

Via ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና...

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ እየተወዳደረ የሚገኘው ነቀምት ከተማ ተጫዋች የሆነው ወንድወሰን ዮሐንስ በትላንትናው ዕለት በተነሳ ድንገተኛ ግርግር በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፏል።

Via ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👉 ‘የግብረ ሰዶማውያኑን ጉብኝት አንቀበልም’ - ላሊበላ ገዳም

👉 ‘ይህን ተላልፈው ቢመጡ ለሚፈጠረው ሁከት እና ግጭት ቤተክርስቲያኒቱም ሆነች የአካባቢው ምዕመን ኃላፊነቱን አይወስዱም’

የግብረ ሶዶማውያን አስጎብኚ ማኅበር በኢትዮጵያ ሊያደርግ ያቀደውን የጉብኝት መርሀ-ግብር እንደማይቀበል የቅዱስ ላልይበላ ገዳም አስታወቀ፡፡

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ‹ቶቶ› የተባለ የግብረ ሶዶማውያን አስጎብኚ ድርጅት በቀጣዩ አመት ጥቅምት ወር ላይ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ መርሀ ግብር መንደፉ ይታወቃል፡፡

ጉብኝት ከሚያደርግባቸው ቦታዎች መካከል የቅዱስ ላልይበላ ገዳም አንዱ ሲሆን ድርጅቱ በማኅበራዊ ሚዲያ የፊት ገጹ ላይ የቤተ ጊዮርጊስን ፎቶ በመለጠፍ ‹‹ላልይበላ እንገናኝ›› የሚል መልዕክት አስፍሯል፡፡

የአካባቢው ማኅበረሰብ እና የገዳሙ አስተዳዳሪ አባ ጽጌ ሥላሴ መዝገቡ ዕቅዱን ከተመለከቱ በኋላ የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

አባ ጽጌ ሥላሴ እንደተናገሩት ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተወገዘ እና ከተፈጥሮ የወጣ ተግባር ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ወንድ ከወንድ ሴት ከሴት ጋር ግንኙነት ቢያደርግ የተረገመ ይሁን፤ ከሃይማኖቱ ማኅበርም ይለይ›› በማለት እንደሚያስቀምጥ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም ጉብኝቱ ተገቢ እንዳልሆነና እንደማይደግፉት አባ ጽጌ ሥላሴ መዝገቡ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያውያን ባሕል፣ እሴት እና ወግም ቢሆን ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው፡፡ የሀገሪቱ ሕግም ቢሆን ድርጊቱን በወንጀል አስቀምጦታል፡፡

በመሆኑም አስጎብኝ ድርጅቱ ቢቻል ወደ ሀገሪቱ እንዳይገባ የሚመለከተው አካል መከላከል እንዲችል፤ ካልሆነ ግን ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲገባ የማይፈቀድለት መሆኑን እንዲያውቅ አባ ጽጌ ሥላሴ አሳስበዋል፡፡

ይህንን ተላልፎ ቢመጣ ለሚፈጠረው ሁከት እና ግጭት ቤተክርስቲያኒቱም ሆነች የአካባቢው ምዕመን ኃላፊነቱን እንደማይወስዱ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ይህንን አስመልክቶ እኛ አቋማችንን በደብዳቤ አሳውቀናል›› ብለዋል፡፡

የቱሪስት ወደ ሀገሪቱ መምጣት ለአስጎብኝ ድርጅቶች፣ ለሆቴሎች፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ ለሀገሪቱ የሚሰጠው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከፍተኛ እንደሆነ እንደሚረዱ ያስወቁት የገዳሙ አስተዳዳሪ ‹‹ማንነታቸውን በግልጽ አሳውቀው በቡድን መምጣታቸው በማንኛውም መንገድ ተቀባይነት አይኖረውም›› ብለዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ መንግሥት አቋሙን በአጭር ጊዜ እንዲያሳዉቅ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የጎንደር ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት ኅብረት ጠይቋል፡፡

የግብረ ሰዶማውያን የኢትዮጵያ ጉብኝት መርሀ-ግብር ከሃይማኖት፣ ከሕግ፣ ከሞራል እና ከሀገሪቱ ባሕል ጋር የሚጻረር ስለሆነ መርሀ-ግብሩ እዉን የሚሆን ከሆነ ለሚፈጠረዉ ማንኛዉም ችግር መንግሥት ኃላፊነቱን እንደሚወስድም አስታውቋል፡፡

ኅብረቱ ለኢፌዴሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጻፈዉ ደብዳቤ ‹ቶቶ› የተባለዉ አስጎብኚ ድርጅት ሊጎበኛቸው ካሰባቸው ቦታዎች መካከል ታሪካዊቷ ጎንደር እና በዉስጧ የሚገኙ ጥንታዊ አድባራትም ተጠቅሰዋል፡፡

ቶቶ የተሰኘውን አስጎብኝ ድርጅት ምላሽ ለማካተት ሙከራ ብናደርግም ‹‹ከዚህ ቀደም ለመገናኛ ብዙኃን ከሰጠነው የተለዬ መረጃ የለንም›› በማለት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ድርጅቱ የኢትዮጵያ የጉብኝት ዕቅዱን ለመቀጠል ያስብ ወይም ይከልስ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

ምንጭ - አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወንደሰን አስክሬን ወደሀዋሳ እያመራ ነው...

ነቀምት ከተማ ተጫዋች የሆነው ወንድወሰን ዮሐንስ በትላንትናው ዕለት በነቀምቴ ከተማ በተነሳ ድንገተኛ #ግርግር በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፏል። ወንድወሰን ዮሐንስ ትውልድ እና እድገቱ #በሀዋሳ ኮረም ሰፈር አካባቢ ሲሆን በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ የእድሜ እርከኖች ከተጫወተ በኋላ በስልጤ ወራቤ እና ኢትዮጵያ ውሀ ስራ (ኢኮስኮ) ሲጫወት ቆይቶ አሁን ወደሚገኝበት ነቀምት ከተማ አምርቶ እየተጫወተ የሚገኝ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ነበር። የተጫዋቹ አስከሬን ወደ ሀዋሳ እያመራ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በነገው ዕለትም በትውልድ ከተማው ሥርዓተ ቀብሩ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

Via SoccerEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቃት ፈፃሚዎቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል...

የነቀምቴ ከተማው ተጫዋች ወንድወሰን ዮሐንስ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ህይወቱ አለፈ።

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ እየተወዳደረ የሚገኘው የነቀምቴ ከተማ ተጫዋች የሆነው ወንድወሰን ዮሐንስ በትላንትናው ዕለት በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት ህይዎቱ አልፏል።

በነቀምቴ ከተማ ፋክት በተሰኛ ሆቴል በተፈፀመው የቦንብ ጥቃት ከደረሰው የሞት አደጋ በተጨማሪ ሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማው ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ጥቃቱን የፈጸሙት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጿል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ሰዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከትላንት የቀጠለው ስብሰባ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፦
1. ዶ/ር ኪሮስ እና ዶ/ር ፀሃየ (ከጊቢው አስተዳደሮች)
2. ዶ/ር ስንታየው ወ/ሚካኤል (የዩንቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ)
3. ዶ/ር ስዩም መስፍን (የፌደራል ተጠሪ)
4. የአክሱም ከንቲባ
5. የሃይማኖት አባቶ ና የሀገር ሽማግሌዎች
6. ዶ/ር ፀሃዬ እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ አመራሮች ናቸው የስብሰባው መሪዎች ናቸው።

ተማሪዎች ግቢው እንዲለቃቸው መጠየቃቸው ይታወቃል። በዛሬው ዕለት ከውይይት በኃላ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዓለም ዓቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን(ፊፋ) ትላንት 69ኛውን ጉባዔውን በፈረንሳይ ፓሪስ አካሂዷል። ጉባዔው ቀጣዩ ማለትም 70ኛው ጉባዔውን የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ እንዲካሄድ ወስኗል። ጉባዔው በግንቦት ወር በ2020 እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከ3000 ሺህ ከሚልቁ የዐቃብያነ ሕግ፣ ጠበቆችና የፍትሕ ዘርፍ አመራሮች ጋር ዛሬ ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹የአማራና ትግራይ ሕዝብ ልዩነት ከብሔር ልዩነት በታች ነው፤ የቋንቋ ልዩነት እንጅ የባሕል፣ የሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የሥነ-ልቦና አንድነት ያለን ሕዝቦች ነን፡፡ በጥቂት ሰዎች የማይሆን ነገር እየተፈጠረ ቅርሶቻችንና ጀግኖቻችንን ተከፋፍለን የትም አንደርስም፡፡ ለግጭት የሚጋብዝና ‹ይለይልን› የሚል አስተሳሰብ አይጠቅምም›› --- ተባባሪ ፕሮፌሰር ገብረየሱስ ተክሉ ባሕታ(ዶክተር) በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ የሥነ-ጽሑፍና ግጭት አወጋገድ መምህር እና ተመራማሪ

@tsegabwolde @tikvahethiopia