ሴት - ጥንካሬ፣ ብልሀት፣ ማስተዋል፣ ብርታት እና ተስፋ ናት። ሴት ማለት ሀገር ናት ሀገር ማለትም ሴት ናት።
ሴትን ማክበር ፈጣሪን ማክበር ነው። ሴትን ማክበር ራስን ማክበር ነው። ለሴቶች እና ለሴቶች ቀን ክብር እንሰጣለን!
መልካም የሴቶች ቀን ይሁንላችሁ!
#MARCH8-TIKVAH-ETH
@tsegabwolde

ከሀገር ተባረረ! በኢትዮጵያ ለበርካታ አመታት በጋዜጠኝነት ሲሰራ የነበረው ዊልያም ዴቪሰን በኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን
ሀላፊዎች ከሀገር እንደተባረረ ገለፀ። ለብሉምበርግ እና ጋርዲያን በመፃፍ የሚታወቀው እንግሊዛዊው ዊልያም የተባረረበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንደማያውቅ ጠቅሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ቢሮ እጅ ግን ሳይኖርበት እንደማይቀር ጠቁሟል።
ምንጭ፦ ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ተራዘመ! ጨፌ ኦሮሚያ ሊያካሂድ የነበረውን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ወደ ሌላ ጊዜ ማዛወሩን ጽህፈት ቤቱ አስታወቀ።
ጉባኤው ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ም እንደሚካሄድ መነገሩ ይታወሳል።
የጽህፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽን እና የመረጃ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ደምሴ እንደተናገሩት በአካባቢው ያለው የሰላም ሁኔታ የተረጋጋ ባለመሆኑ የጨፌው መደበኛ ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።
ምንጭ፦ FanaBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉባኤው ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ም እንደሚካሄድ መነገሩ ይታወሳል።
የጽህፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽን እና የመረጃ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ደምሴ እንደተናገሩት በአካባቢው ያለው የሰላም ሁኔታ የተረጋጋ ባለመሆኑ የጨፌው መደበኛ ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።
ምንጭ፦ FanaBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቲለርሰን! የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ በአፍሪካ ህብረት ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ ሀገራት ከሰሜን ኮርያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቆሙ የጠየቁ ሲሆን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ግን አስተያየት ሳይሰጡ ቀርተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ-ከሴቶች ቀን በፊት ሴትነትን ያስከበሩ ሴቶች ምድር!
እንግዲህ ዓለም ዛሬን ለሴቶች ሰጥቶ ያለ ሴት ውሎ ያደረባት አንዲት ቀን ያለች ይመስል ሆ እያለ ነው፡፡ ሴቶችም በየዓለም ጥጉ እንደ ሀገራቸው ርዕዮት የካቲት መጨረሻ ያለችዋን ቀን ያከብሯታል፡፡
ማርች 8 በዓለም ቋንቋ የጋራ ሆናለች፡፡ የትም ያለች ሴት ቀበሌዋ ማርች 8 ከአፍ መፍቻዋ አስማምቶላታል፡፡ እንግዲህ ዛሬ ለሰለጠኑ ትናንት በጨለማ ለነበሩ ይሄ ቀን በእርግጥም ስለ ሴት አንድ ተጨማሪ ነገር ያወቁበት፤ ድንገት የተነሱ ብርቱ ሴቶች የዓለምን ታሪክ በድምጻቸው ቀየሩ የተባለበት ቀን ነው፡፡
ለእኛ ምናችን ሆኖ፤ እዚህ ዛሬም በአደባባይ በጩቤ የምትወጋ፣ አሲድ የሚደፋባት፣ ጥይት የሚርከፈከፍባት ቢሆንም ጠንካራ ሴት በማፍራት ግን ከሴቶች ቀን በፊት ተአምር የሰሩ ሴቶች የተፈጠሩባት ሀገር ናት፡፡
ኢትዮጵያውያን ከአፋችን መቼ ዮዲት የተባለችው ጦረኛ ስም ጠፍቶ ያውቅና? ልብን በልቧ አግዝፋ፣ ያገዘፈችውን ጥበብ ስትሻ ባህር የተሻገረችዋን ንግሥት ገናናነት ዓለም ተረትም ይበለው እውነት የእኛ ሴት ነበረች፡፡
የነብዩ መሐመድ ሰ.ዐ.ወ ምስጉና ሞግዚት ሀገሯ የት ሆኖ? እንደ ወለተ ጴጥሮስ ያልተሸነፈ ወኔ የነበራቸው ሴቶች ሲፈጠሩ ዓለም ማርች 8 ማለት አልጀመረም ነበር፡፡ የጎንደር ቤተ መንግሥት በጥበበኛዋ ንግሥት በእቴጌ ምንትዋብ ብቃት ሲሾር የእቴጌይቱን ወኔ የቀሰቀሰው ይሄ ዓለም አቀፋዊነት አይዞሽ ባይነት አልነበረም፡፡
የባቲ ድል ወንበሯ ወኔ ስንቱን ወንበር ሲገለብጥ ከጄኒቫ በተቀሰቀሰ ጥሪ የመጣ አይደለም፡፡ ይልቁንስ እዚህ ይሄንን ቀን ቀድመው ይሄ ቀን በአሳር የተመኘውን ከፍታ የተቆናጠጡ ጀግኖች ነበሩ፡፡ አይቻልምን ያሸነፉ ጀግኖች፡፡
ሴት በስልጡን ነን ባዮቹ ሸንጎ ሳይሰየም የጌዴኦ እናቶች በአኮማኖየ ወንዶችን እየመሩ፤ ከአረንጓዴ ደናቸው ውስጥ ወታደርም ንጉሥም ሆነው አልፈዋል፡፡ ከጎፋ እስከ ዳውሮ የካዎ ቀኝ እጆች ሴቶች ነበሩ፡፡
የንግሥት ፉራ ሲኖር አይደለም ሲተረክ እንዴት የሚያስብል ጀብድ ከማርች 8 ቀድሞ እዚህች ያልተነገረላት ሀገር የኖረ ያልተነገረ ታሪክ ነው፡፡ ከታሪካችን የማይለዩት ሴቶች ከዓለም መንቃት ቀድመው ይቻላልን ያሳዩ ናቸው፡፡
የጋራድ ልጅ እሌኒ የስሜንን እና የሀዲያ ሱልጣኔትን መጎሻሸም እልባት የሰጠች ቅመም ነበረች፡፡ ወርቂት እና መስታወት ያልተጻፈላቸው ድንቅ የጦር መሪዎች ነበሩ፡፡
የራስ አሊ እናት እቴጌይቱ መነን የዘመነ መሳፍንትን ታሪክ ታሪካቸው ሲያደርጉት፤ እቴጌ ጣይቱ አዲሲቷን ኢትዮጵያ በነጻነት ከደመቀ ታሪክ ጋር ሲያበጇት፤ እነ እሞሃይ ገላነሽ ወንድ ነኝ የሚለውን ባለቅኔ አፍ ሲያሲዙ፣ እነ ቃቂ ወርዶት ቤት ለቤት የቆመ ስርወ መንግስት ሲመሰርቱ ዓለም ማንዋል አዘጋጅቶች ሴቷ ንቂ አላለም ነበር፡፡ እናም እዚህ ከሴቶች ቀን በፊት ሴትነትን ያስከበሩ ሴቶች ነበሩ፡፡
ምንጭ፦ DIRETUBE(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም)

አምቦ! የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር፣ የአምደ-መረብ ጸሀፊ እና የፖለቲካ ተንታኝ ስዩም ተሾመ ዛሬ ጠዋት 3 ሰዓት ገደማ ወሊሶ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸውን የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ገለፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማርች 08! የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ቀን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 08) ምክንያት በማድረግ በሴቶች ብቻ የሚመራ የተሳካ በረራ አደረገ።
የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ፓይለት/፣ የበረራ አስተናጋጅ እና መላው የአውሮፕላን ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚደረግ በረራ ሲሆን፣ በረራው ከአዲስ አበባ ወደ አርጀንቲና መዲና ቦነስ አይሪስ ተደርጓል።
በአሸኛኘት ዝግጅቱ ላይ አትሌቴ ጥሩነሽ ዲባባ እና ገንዘቤ ዲባባ ተገኝተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ፓይለት/፣ የበረራ አስተናጋጅ እና መላው የአውሮፕላን ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚደረግ በረራ ሲሆን፣ በረራው ከአዲስ አበባ ወደ አርጀንቲና መዲና ቦነስ አይሪስ ተደርጓል።
በአሸኛኘት ዝግጅቱ ላይ አትሌቴ ጥሩነሽ ዲባባ እና ገንዘቤ ዲባባ ተገኝተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅናሽ ለሴቶች! ኢትዮ ቴሌኮም ለሴቶች ብቻ ቅናሽ የተደረገባቸው 3 መቶ ሺህ የሞባይል ቀፎዎችን ለሽያጭ አቀረበ ኢትዮ ቴሌኮም ከ2ዐ እስከ 4ዐ በመቶ ቅናሽ የተደረገባቸው ሴቶችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርጉ 3 መቶ ሺህ የሞባይል ቀፎዎችን ለሽያጭ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡
የሞባይል ቀፎዎቹ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ1ዐ7ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ42ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሴቶችን ቀን ማርች 8 ምክንያት በማድረግ ከየካቲት 3ዐ ጀምሮ በኢትዮ ቴሌኮም ሱቆች ለሽያጭ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ ተቋሙ በአሉን በብሄራዊ ቲያትር ያከበረ ሲሆን ሴቶችን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማደረግ እንደሚሰራም ገልጿል፡፡
በበአሉ የተጋበዙት ሴት የህግ ባለሙያዎች የፓናል ውይይት ያደረጉ ሲሆን በፍትህ ዙሪያ ሴቶች ተጠቃሚ ለማድረግ አንዳንድ የህግ ክፍተቶች መሻሻል እንዳለባቸው ተናግርዋል፡፡
ባለሙያዎቹም ሴቶች በቤተሰብ ጉዳይ በንብረት አስተዳደር በህግ ዕውቀትና በክርክር ሂደቶች የአቅም ማነስ ችግር ይታይባቸዋል፡፡ በዚህም የተለያዩ ተፅዕኖዎች እየደረሱባቸው ይገኛሉ፡፡ እንደ EBC ዘገባ ይህን ለማስተካከልም ሴቶችን ማብቃት፣ ማሰልጠን እና ማስተማር እንደሚገባ ተገግረዋል፡፡
ምንጭ፦ EBC

ኦሮሚያ! የተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እየተመለሱ እንደሆነ ተሰምቷል።
መንገዶች እየተከፈቱ እንደሆነ ለመስማትም ችያለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዶች እየተከፈቱ እንደሆነ ለመስማትም ችያለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍርድ! የታንዛኒያ ፍርድ ቤት በ84 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የ3 ዓመት እሥራት አስተላልፏል። ስደተኞቹ በኮንቴይነር ተጭነው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ከታንዛኒያ ወደ ማላዊ ሲሻገሩ ነው የተያዙት።
ምንጭ፦ Hahu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ Hahu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሴትነት! ሴትነት ሰው የመሆን ሁለንተናነት ነው። አንድ ሰው የሴትነትን ታላቅነት ካልተረዳ ገና ሰው የመሆንን ሚስጢር አልተገነዘበም ማለት ነው። ምክንያቱም ሴት እናት ነች። እናት ደግሞ የማያልቅ ዘላለማዊ ፍቅርን በስስት የምትለግሰን የፍቅርን ምንነት መገለጫ ናት። ታዲያ ከፍቅርና ፍቅርን ከማወቅ በላይ ምን ታላቅ የህይወት ሚስጢር ይኖራል? ምንም አይኖርም።
ሌላው ታላቅ ከሚያደርጓት ነገሮች ደግሞ በህይወት ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተጋፍጣ በብልሃት እና አሸናፊነት የምትወጣ ጠንካራ ፍጥረትነቷ ነው።
ሩህሩህነትን ከአፍቃሪነት ጋር ታድላ የተፈጠረች ለወንድ የህይወቱ ማገር እና ምሶሶ ናት። ወንድ ያለ ሴት ሙሉነት እና የህይወት ጣእም የሌለው ያላለቀ የእግዜር ጅምር ስራ ነው።
ሴት ልጅ ስቃይዋን እና ሃዘኗን መደበቅ ካስፈለጋት መከፋትዋን ሳታሳይ ደስተኛ በመምሰል ለምትወደው ሃሴትን መስጠት የምትችል ረቂቅ ፍጠረት ናት።
ሴትነትን ሆነው ካላዩት በእርግጥ ስለ ሴትነት ሙሉ በሙሉ መናገር የሚቻለው አይኖርም። ረቂቅ እና የህይወት ጣእም ሚስጢር አድርጎ ከፈጠራት ፈጣሪ በስተቀር።
ሴት ልጅ ከወንድ የጎን አጠንት ብትሰራም በህይወት ዘመኑ የጀርባ አጥንቱ ሆና ብርታትን እና ፀናትን የምትሰጠው “ሃይል” ናት። የታላላቅ ስኬቱ ጀንበር ሆና የምትፈነጥቅለት ነገር ግን ከእርሱ ልቃ የማትታይ የመድመቂያው ጮራ መፍለቂያ ናት።
ሴት ልጅ ከልብ የመነጨ ክብር ይገባታል። ሴትን የሚያከበር ራሱን የሚያከብር ነው። ሴትን የማያከብር ቢኖር የህይወትን ጣእም እና ፍቅርን ካለማወቁም በላይ ሰው የመሆን ብቃት የጎደለው ነው።
ምንጭ ፦ ደምቢካ(ከፌስቡክ)

ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኢነርጅ ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተወያይተዋል።
ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኬንያ! የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ እርቀ ሰላም ለማውረድ ተስማሙ።
ሁለቱ ወገኖች በሃገሪቱ ቴሌቪዥን በጋራ በሰጡት መግለጫ በቀጣይ ያሉ ልዩነቶችን በውውይት ለመፍታት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
በኬንያ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ውጤቱን አልቀበልም በሚል የተፈጠረው ውዝግብ ለ150 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።
ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁለቱ ወገኖች በሃገሪቱ ቴሌቪዥን በጋራ በሰጡት መግለጫ በቀጣይ ያሉ ልዩነቶችን በውውይት ለመፍታት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
በኬንያ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ውጤቱን አልቀበልም በሚል የተፈጠረው ውዝግብ ለ150 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።
ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሶሪያ! ዓለማቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የተመድ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ ወደ ምሥራቃዊቷ የሦርያ ከተማ ጉታ የሚሄደውን እርዳታ የጫኑ ካሜዎኖች ዛሬ ዐርብ መንቀሳቀሳቸው ተሰምቷል። ነገር ግን በአካባቢው የሚካሄደው የአየር ጥቃት በአስቸኳይ የተፈለገውን እርዳታ ማራገፍ እንዳላስቻለ ታውቋል።
ምንጭ፦ VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦሮሚያ! ከትላንት በስቲያ በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን በኦሞናዳ ወረዳ አሰንዳቦ በተባለች ቦታ በቄሮዎችና በታጠቁ የመከላከያ ሠራዊት አባላይ መካከል በተፈጠረ ግጭት ወጣቶች በጥይት ተመተው ሆስፒታል መግባታቸውን ከቄሮ፣ ከወጣቶችና ከሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። በሌሎች የክልሉ ከተሞችም ግጭትና ውጥረት መኖሩን ነዋሪዎች ለVOA ተናግረዋል።
ምንጭ፦ VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቲለርሰን! ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር መልሱ "የበለጠ ነፃነት እንጂ መገደብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር መልሱ "የበለጠ ነፃነት እንጂ መገደብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ ሃገራቸው ስትገልፅ የቆየችውን አቋም ያጠናከሩት ቲለርሰን መሰብሰብንና ሃሣብን የመግለፅ
ነፃነትን የመሳሰሉትን መብቶች እንደሚገድብ አመልክተው አዋጁ በተቻለ ፍጥነት እንዲነሣ ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያዊያን ዜጎችም ሃሣባቸውን በሰላማዊ መንገድ ብቻ የመግለፅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ቲለርሰን አሳስበዋል።

የዋልድባ መነኮሳት! በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት ለአንድ አመት ያህል በአንድ ልብስ ብቻ በጨለማ ቤት መቆየታቸውን ለፍርድ ቤት ገለጹ።
በተለይም በአባ ገብረስላሴና በአባ ገብረየሱስ ላይ የተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት አስከፊ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።
ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤቱን መልስ ከተቀበለ በኋላ ሁኔታውን መርምሮ መልስ እንደሚሰጥ ገልጿል።
እስረኞቹን ለመጠየቅ የመጡ ሰዎች ለመነኮሳቱ ልብስ እንዲሰጡም ፍርድቤቱ መፍቀዱ ታውቋል።
የዋልድባ መነኮሳት ክሳቸው እንደተቋረጠ በሪፖርትር ጋዜጣ መገለጹ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የመነኮሳቱ የክስ ሂደት ዛሬም በፍርድ ቤት መቀጠሉ ነው የተነገረው።
ትላንት የካቲት 30 በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ታዲያ የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤቱ የደረሰባቸውን እንግልትና ስቃይ ለዳኞች አስረድተዋል።
መነኮሳቱ ለአንድ አመት ያህል ልብስ እንዳይቀይሩ ከመደረጋቸውም ሌላ በጨለማ ቤት ውስጥ ተለያይተው እንዲቀመጡ መደረጉንም ነው ለችሎቱ የገለጹት።
በተለይም አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነማርያም ዞን አምስት ተብሎ በሚጠራው እስር ቤት በጨለማ ቤት ውስጥ የደረሰባቸውን ስቃይ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።
አባ ገብረስላሴ ለአንድ አመት ያህል ልብስ ሳይቀይሩ በጨለማ እስር ቤት መቆየታቸውም ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል። ፍርድቤቱም ይህ ለምን እንደሆነ ጠይቆ ከእስር ቤቱ በደብዳቤ ምላሽ በማግኘቱ ሁኔታውን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለመጋቢት 5/2010 ቀጠሮ ሰቷል።
ዳኞቹ ለመነኮሳቱ ለምን ልብስ እንዳይገባ ተደረገ ሲሉ በጠየቁ ጊዜ ችሎቱን ሲከታተሉ ከነበሩ ጠያቂዎች አንዱ ልብስ ይዞ በመገኘቱ ዳኞቹ እንዲሰጣቸው አድርገዋል ነው የተባለው። የእስር ቤቱ ሃላፊ ልብስ እንዳይሰጣቸው ቢከለክሉም ዳኞቹ ልብስ እንዲሰጥ ማድረጋቸውን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የዋልድባ መነኮሳቱ መደበኛ ክስ መጋቢት 18 እንደሚቀጥልና ምስክሮችን የመስማት ሒደት እንደሚኖርም ተገልጿል።
ምንጭ፦ አቶ ጌታቸው

የትነበርሽ! ለሴቶች መብት ለአካል ጉዳተኞች መብትና ዕኩልነት ተሟጋች ጠበቃዋ፣ የትነበርሽ በማርች 08 ዓለምቀፍ የሴቶች ቀን የከፍተኛ ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።
መሰረቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው ሔለን ኬለር ኢንተርናሽናል የዘንድሮ ‘Spirit of Award’ የሄለን ኬለር መንፈስ ሽልማት ሰጥቷታል።
የትነበርሽም በአሁኑ ጊዜ የምትሰራበት “ላይት ፎር ዘ ዎርልድ” የተሰኘው ድርጅት ለመጀመሪያ ታላላቅ ክንዋኔዎች ላስመዘገቡ አካል ጉዳተኛ ሴቶች የሚሰጠውን አዲስ ዓመታዊ ሽልማትም አስተዋውቃለች።
ምንጭ፦ ቆንጅት ታየ