TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"GALANNI KAN RABBI GUDDAATI. Asiin nu gahe. Waliigaltee taba haphee itti godhee nuuf haa maxxansu. Odeeffannoo guutuuf gabaasa miidiyaalee daaw’adhaa."

Via #Jawar_Mohammed
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በአዘርባጃኗ ዋና ከተማ ባኩ መካሄዱ ብዙ ቅሬታዎችን አስነስቷል።

የፊታችን ቅዳሜ የሚደረገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ለመታደም ብዙ እንግሊዛውያን ወደ ስፔኗ መዲና ማድሪድ እንደሚጎርፉ ይጠበቃል።

ነገር ግን ዛሬ የሚካሄደውን የአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ለማየት ወደ አዘርባጃን መዲና ባኩ መምጣት የሚችሉት የአርሰናልና የቼልሲ ደጋፊዎች ቁጥር ከ6000 እንደማይበልጥ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ የአርሰናሉ ሄነሪክ ሚኪታሪያን #በአርሜኒያዊ ዜግነቱ ምክንያት ደህንት አይሰማኝም በማለት ወደ አዘርባጃን እንደማይሄድ አስታውቋል። አርሜኒያ እና አዘርባጃን 'ናጎርኖ ካራባክ' የተባለው #ክልል የይገባኛል ፍጥጫ ውስጥ ያሉ ሲሆኑ የሚኪታሪያንም #የስጋት ምንጭ ይሄው ነው።

ብዙዎችም የፍጻሜ ጨዋታውን ለምን በአዘርባጃን ማካሄድ አስፈለገ? በማለት ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ግን ሃገሪቱ ለምስራቅ አውሮፓ ሩቅ በመሆኗ ምክንያት ውድድሩን ከማዘጋጀት ልትታገድ አይገባም ብሏል።

ባላት የነዳጅ ሃብት ምክንያት እጅግ የበለጸገችው አዘርባጃን ብዙ ሚሊዮን ዶላሮችን ፈሰስ በማድረግ በዓለማቀፍ ስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ ያላትን ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ እየሰራች ነው።

Via #ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በቶክዮ አንዲት ተማሪና አንድ ጎልማሳ መገደላቸው ተገለፀ። በሁለት እጆቹ #ቢላ የያዘ ሰው "ካዋሳኪ" በተባለች ከተማ ተማሪ ሴቶች፣ አውቶብስ ሲጠበቁ በነበሩበት ቦታ ላይ ደርሶ በቢላ ማጥቃት እንደጀመረ ተዘግቧል።

በሃምሳ ዓመታት ዕድሜ ክልል ውስጥ የነበረው አጥቂ፣ ራሱን በቢላ ወግቶ እንደገደለ የጃፓን ብሄራዊ ማሰራጫ ዘግቧል።

የተገደሉት ሰዎች የ12 ዓመት ዕድሜ ተማሪ ሴትና የ39 ዓመት ዕድሜ ወንድ ናቸው ተብሏል። ሦስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

Via #VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የገዛ ባሏን በመርዝ የገደለችው ተከሳሽ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ አቶ ዋቁማ ጡሪ እንዳስታወቁት በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ ውስጥ በምትኖረው ተከሳሽ ወይዘሮ እልፍነሽ በቀለ ጅራታ ላይውሳኔው የተላለፈው ባሏን አቶ አዳነ አሰፋውን በመርዝ መግደሏ በመረጋገጡ ነው።

ሟች ከኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ከተበደሩት 86ሺህ ብር ውስጥ 10ሺህ ብር እንዲሰጣት ጠይቃ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ቂም ይዛ መርዝና አይብ በማደባለቅ መጋቢት 01/2011ዓ.ም ከምሽቱ በግምት አራት ሰዓት አካባቢ እንዲመገብ አድርጋለች።

ወደ መኝታ ክፍል እንደገባም በሩን በውጭ በኩል ዘግታ መሞቱን ካረጋገጠች በኋላ ራሱን በራሱ የገደለ ለማስመሰል ’’ፀፀት’’ ተብሎ የተፃፈና ሁለት ገጽ ያለው ወረቀት በደረቱ ላይ አስቀምጣ መኖሪያ ቤቱን በመዝጋት ንብረት ስታሸሽ መያዟን አመልክተዋል።

የተከሳሿ ድርጊት በዞኑ ዓቃቤ ሕግየሕግ ምሥክሮች በመረጋገጡ፣ ራሷም የፈጸመችውን ድርጊት ማመኗንና የመከላከያ ማስረጃም የለኝም ማለቷን አቶ ዋቁማ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በግንቦት 21/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሿ ሆን ብላ የሰውን ሕይወት ለማጥፋት ተዘጋጅታ የፈጸመችው ድርጊት በመሆኑ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 2 ሚሊዮን 255 ሺ 880 ብር የሚያወጡ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ በሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር በሚገኙ በቡሌ ሆራና ያቤሎ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ግንቦት 19/2011 ዓ.ም ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የጉምሩክ ሰራተኞች ባደረጉት ፍተሻ እንደሆነ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጥተዋል...

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ቁጥራቸዉ በዉል ያልተገለፀ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ግቢ ለቀዉ መዉጣታቸዉ ተዘገበ።

Via #DW

https://p.dw.com/p/3JT7C?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ከሃዋሳ ...

"በፎቶው የምትለመከቷት የሲዳማ እናት ነገ እና ከነገ ወዲያ ለሚከበረዉ ፊቼ ጨምበላላ የሚቀርብ ግሩም የሆነዉን የሲዳማ ባህላዊ ምግብ "ቡሪሳሜ"ን ለማዘጋጀት የምትኳትን እናት ነች። ግሩሙን "ቡሪሳሜ" በ "ጌእንቶ"(እርጎ ወተት) ለመመገብ በበዓሉ ቀን ሀዋሳ ከች ማለት!! ኑና አብረን በዓለም የጋራ ቅርሳችን የሆነዉን ፊቼ ጨምባላላን በዓል አብረን በዉቢቱ ሀዋሳ-አዳሬ እናክብር!! Peoples are gathered in to #Hawassa-Adare from tomorrow on to celebrate The new year of Sidama people Fichee Chambalallal...Lets celebrate together!!"

Via #Job
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በዓል ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር ይጀምራል፡፡ የዋዜማ በዓሉ በዛሬው ዕለት በተለያዩ ስነ ስርዓች በጎዳና ላይ በሀዋሳ ከተማ ተከብሮ ውሏል፡፡ በሲዳማ ብሔር ባህላዊ ጭፈራ“ቄጣላ ” እና በሌሎች ስነ ሰርዓቶች ነው በሃዋሳ ከተማ ጎዳናዎች የፊቼ ጫምባላላ ሲከበር የዋለው፡፡ በርካታ ባህላዊና ማኅበራዊ ፋይዳዎች እንዳሉት የሚነገረው ፊቼ የሲዳማ ብሔር አንኳር የሆኑ ባህላዊ ገጽታዎች የሚንጸባረቁበት እንደሆነ ይነገራል፡፡ የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡ የሚታወቅ ነው፡፡ በዓሉ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር ይጀምራል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የባጃጅ አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተገደሉ‼️

በጋምቤላ ክልል ሁለት በባጃጅ ስራ የሚተዳደሩ ግለሰቦች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን የክልሉ የፀጥታና አስተዳደር የመረጃ ባለሞያ የሆኑት አቶ አልቢኖ ዶክ ሊዩ ገልፀዋል።

ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው ማቾቹ ከጋምቤላ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ አቦል ወረዳ ላለፉት አምስት አመታት በባጃጅ ስራ ሲተዳደደሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ግድያው የተፈጸመው ሟቾቹ እንደተለመደው ከስራ ወደ ከተማ ሲመለሱ መሆኑን ነዋሪው ገልፀዋል።

ግድያውን ተከትሎ በከተማዋ መጠነኛ ግርግር የተነሳ ሲሆን፤ የሟቾቹ አስከሬን በአካባቢው ወደ ሚገኘው ሆስፒታል ለምርመራ መወሰዱን ይኼው ግለሰብ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በባጃጅ ስራ የተሰማሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ግድያውን በመቃወም አድማ አስነስተው የነበሩ ሲሆን ነዋሪው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ማን እንደሆኑ እንዲጣራና ለህግ እንዲቀርቡ ጥያቄ ማቅረቡንም ገልፀዋል።

"ሥራ ላይ እያሉ ነው የተገደሉት። ማን ይግደላቸው ማን ግን የሚታወቅ ነገር የለም። የአንደኛው ሬሣ ወደ መቀሌ የአንደኛውን ሬሣ ደግሞ ወደ ሽሬ ሄዷል። የፀጥታ ሰዎች ማጣሪያ እናደርጋለን ብለውናል። እኔ እስከማውቀው ድረስ የተወሰኑ የባጃጅ ሾፌሮች ሁኔታውን ተቃውመው አድማ መተው ነበር፤ አካባቢው በጣም አስቸጋሪ ነው" በማለት ነዋሪው አክሏል።

በግድያው የተሳተፉ ሰዎች እስከአሁን በቁጥጥር አለመዋላቸውን የገለጹት አቶ አልቢኖ ግድያው የተፈጸመው በጥይት እንደሆነና አስከሬናቸው ዛሬ ጧት ወደ ትግራይ መላኩን አረጋገጠዋል።

በአካባቢው ብዙ ችግሮች እንደሚከሰቱ የገለፁት ባለሙያው መንስኤውን ለማጣራት ምርመራ ላይ እንደሆኑም ተናግረዋል።

"ግድያው ብሔር ተኮር ነው ብሎ ለመደምደም ያስቸግራል፤ በአካባቢው በብዙ ጉዳዮች ግጭቶች ይነሳሉም" ብለዋል።

Via #BBC
ፎቶ፦ ከጋምቤላ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ ወደ መኖሪያ ቀያቸው የተመለሱ ተፋናቃዮችን እየገበኙ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ የችግኝ ተከላ በማከናወን ህብረተሰቡ ይፋ በተደረገው በዘንድሮው ክረምት ችግኝ የመትከል ዘመቻ ላይ እንዲሳተፉ አበረታተዋል። ባለፈው እሁድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስጀመሩት ዘመቻ መሰረት በመላው ሀገሪቱ 4 ቢሊየን ችግኞችን በክረምቱ ለመትከል እቅድ ተይዟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በባንግላዴሽ ኑስራት ጃሃን የተባለች ተማሪ ርዕሰ መምህር ፆታዊ ትንኮሳ ሪፖርት ማድረጓን ተከትሎ በነጭ ጋዝ አርከፍከው አቃጥለው ገድለዋታል የተባሉ 16 ተጠርጣሪዎች ታስረዋል።

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር፣የአካባቢው ፖለቲከኞችና ተማሪዎች ይገኙበታል።

ርዕሰ መምህሩ ግድያውንም መናዘዙንም ፖሊስ አስታውቋል። ብዙዎቹም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሞት ፍርድ ተግባራዊ እንዲሆንም እየጠየቁ ነው።

በትንሽ መንደር የተወለደችው የአስራ ዘጠኝ አመቷ ኑስራት ማዳራሳ ወይም የእስልምና ትምህርትን ትከታተል ነበር።

የደረሰባትን ትንኮሳ በመናገሯ ድፍረቷን ብዙዎች ቢያደንቁትም ከቀናት በኋላ ግን ሰቅጣጭ የሆነው አገዳደሏ ብዙዎችን አስደንግጧል።

ከመሞቷ በፊት ኑስራት በሰጠችው መግለጫ አንዲት ሴት ተማሪ አንድ ጓደኛዋ እንደተጎዳ ነግራት ጣራው ላይ ወሰደቻት። ጣራው ላይ ስትደርስ ግን አምስት ተማሪዎች እንደከበቧትና በርዕሰ መምህሩ ላይ ያቀረበችውን ክስ እንድትተው ጫና ሊያደርጉባት ሞክረዋል። እምቢ ስትልም በእሳት እንደለኮሷት ተናግራለች።

የወንጀል መርማሪ ፖሊስ ኩማር ማጁምደር እንደገለፀው ገዳዮቿ ራሷን ያጠፋች ለማስመሰል ቢሞከሩም እቅዳቸው ሳይሳካም ለጥቂት ቀናትም ቢሆን በህይወት ተርፋ መግለጫ መስጠት ችላለች።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንድ ብር ለወገኔ የበጎ አድራጎት ማህበር ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርና ከብሄራዊ አደጋ ስጋት መከላከል ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከፊታችን ግንቦት 23_25 ድረስ የሚቆይ የደም ልገሳ ፕሮግራም እንዲሁም ቅዳሜ ግንቦት 24 በአይነቱ ለየት ያለ ፕሮግራም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ተዘጋጅቶ እርሶን እየጠበቆት ነወ።
በዕለቱ ታላላቅ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል
1⃣ የአነቃቂ ንግግር (motivational speech) አቅራቢ የሆኑት #ዶክተር_በድሉ_ዋቅጅራ
2⃣ የተለያዩ ገጣሚያን እና ደራሲያን እንዲሁም የተለያዩ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚገኙ ክለባት ስራቸውን ያቀርባሉ።
ሰለሆነም #ተማሪዎች _ለሰብአዊነት በሚል መሪ ቃል በሚዘጋጀው በዚህ ልዩ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
የፕሮግራሙ መቅረቢያ ቦታ #በአፍሪካ_ህብረት
የመግቢያ ዋጋ 2.00 birr
VIP 5.00 birr
@OBFMC
@OBFMC
@OBFMC
ለበለጠ መረጃ +251904451280
+251965818419
+251973156161
#update በምዕራብ ኦሮሚያ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የጦር መሪ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ፤ በምዕራቡ ክፍል የሚገኘው የኦነግ ጦር የትጥቅ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል ተናገረ።

መንግሥትን እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ለማስታረቅ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚቴ ትናንት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት መድረክ ላይ የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከአሁን በኋላ ኦነግ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ የጦር ኃይል አይኖረውም ማለታቸውን ተከትሎ ነው የጦሩ መሪ ይህን የተናገረው።በምዕራብ ኦሮሚያ የጦር መሪ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ፤ ''የተለወጠ ነገር የለም'' በማለት ከኦነግ ሊቀ መንበር በተለየ መልኩ የኦነግ ጦር የትጥቅ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል ለቢቢሲ ተናግሯል።

መሮ መከላከያው፣ ፖሊስ እና የደህንነት አካሉ ሙሉ በሙሉ የፓርቲ ወገንተኝነቱን አቁሞ የሕዝብ ወገንተኝነቱን እስካላረጋገጠ ድረስ የመንግሥትን ጥሪ አንቀበልም ብሏል። ''እኛ ለፓርቲ ወግኖ ህዝብን የሚጎዳ የመከላከያ አካል መሆን አንሻም'' ሲል ከዚህ በፊት ከመንግሥት ጋር በተደረሰው ስምምነት የግንባሩ ታጣቂዎች ከመንግሥት የጸጥታና የመከላከያ ኃይል ጋር ለማካተት የቀረበውን ሃሳብ መሮ ውድቅ አድርጎታል።

ጨምሮም ''ለጊዜያዊ ጥቅም ተብሎ በንግግር ተሸፋፍኖ የሚያልፍ ነገር አያዛልቅም። ነገ እሳት መነሳቱ አይቀርም። ዘላቂ መፍትሄ በሚሰጡ ምክክሮች ላይ ለመወያየት ግን ዝግጁ ነን'' በማለት ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ጠቁሟል።መንግሥትን እና ኦነግን ለማስታረቅ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚቴም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት መሳሪያ አንገበው ጫካ ገብተው የነበሩ የኦነግ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ወይም ወደሚዘጋጅላቸው ስፍራ ለስልጠና እንዲገቡ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስታውሷል።

ኮሚቴው የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በተገኙበት ነው ሪፖርቱን ያቀረበው። ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኦነግ ከአሁን በኋላ ጦር አንግቦ የሚንቀሳቀስ ሠራዊት አይኖረውም፤ መንግሥት ሕግ ለማስከበር የሚወስደውን እርምጃም እንደግፋለን ብለዋል።

የአስታራቂ ኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረቡት አቶ #በቀለ_ገርባ ሲሆኑ ባቀረቡት ሪፖርት ውስጥ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል። ኦነግ ከአሁን በኋላ #ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ጦር ስለማይኖረው ኮሚቴው የተቋቋመበትን ዓላማ ማሳካቱን ጠቅሰው፤ ኮሚቴው በኦነግ እና በመንግሥት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ታስረው የነበሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል። በተጨማሪውም ኮሚቴው ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካዊ ትግሉን ለመቀጠል በሚያደርገው እንቅስቃሴ የመንግሥት ድጋፍ እንዳይለይ እና የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ የገቡ የኦነግ ጦር አባላት ቃል የተገባላቸው ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ኮሚቴው ጠይቋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የድንች ችፕስ #እየሸጠች ልጇንና ወንድሟን ስታስተዳደር የነበረችው ወጣት የመደበኛ ሎተሪ 1ኛ ዕጣ #ዕድለኛ ሆነች፡፡

==============================

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ክ/ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሪት ፀጋነሽ አየሁ በ1621ኛ መደበኛ ሎተሪ በ1ኛ ዕጣ 600,000 ብር ዕድለኛ ሆነች፡፡ ዕድለኛዋ ሎተሪዎችን የቆረጠችው ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ክ/ሃገር ደርሳ ስትመለስ ለምሳ በወረደችበት ጊዜ በደ/ማርቆስ ከተማ ነበር፡፡ ወ/ሪት ፀጋነሽ የድንች ችፕስ እየሸጠች የዘጠኝ አመት ልጇንና ወንድሟን እያስተማረች ያለች ሲሆን በደረሳት ገንዘብም በመጀመሪያ እናቷን ማገዝና የአትክልትና ፍራፍሬ ጭማቂ (ጁስ ቤት) #ለመክፈት እንደሰበች ተናግራለች፡፡

Via ብሄራዊ ሎተሪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ማርክ ዙከርበርግ የፌስቡክ ሊቀመንበርነቱን ሊያጣ ይችላል ተባለ። ዛሬ በሚካሄደው የፌስቡክ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ማርክ ዙከርበርግ ከፌስቡክ ሊቀመንበርነቱ እንዲነሳ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ማርክ ዙከርበርግ የፌስቡክ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ነው። ዙከርበርግ ከሀላፊነቱ እንዲለቅ የሚፈልጉ አካላት የኩባንያውን ስራ በማስኬድ ላይ ብቻ እንዲያተኩር እንደሚፈልጉ ተገልጿል፡፡

ዙከርበርግ በድርጅቱ 60 በመቶ ድርሻ ስላለው በምርጫው ሊሸነፍ የሚችልበት እድል ጠባብ ነው የተባለ ሲሆን ሌሎች የድርጅቱ ባለድርሻዎች በአመራር ብቃቱ ላይ ምን ያህል እምነት እንዳላቸው የሚታይበት ምርጫ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

በያዝነው ወር ዙከርበርግ ከፌስቡክ ኃላፊነት እንዲነሳ የቀድሞው የፌስቡክ ደህንነት ክፍል ኃላፊ አሌክስ ስታሞስ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው።

ከዚህ ቀደም ማርክ የአስተዳደር ቦታው ላይ መቀመጡ ተገቢ እንደሆነ ሲገልጽ "እንደፌስቡክ ያለ ዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ነገር ሲጀመር ስህተቶች ሊፈጠሩ ይቸላሉ። ከስህተታችን እየተማርን መሆኑን ሰዎች እንዲገነዘቡ እፈልጋለሁ" ብሎ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia