TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወሎ ዩኒቨርሲቲ👆

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የረመዳንን ጾም ምክንያት በማድረግ ልዩ የፈጢር ፕሮግራም ለተማሪዎች ተዘጋጅቶ ነበር። በዚህም የፈጢር ፕሮግራም የዩንቨርሲቲው አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የደሴ ከተማ ከንቲባ በቦታው በመገኘት ተማሪዎችን አስፈጥረዋል።

Via Wollo University PR
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋልጉኝ!!

ህፃን ሱመያ አብዱልሰመድ እድሜዋ 10 ዓመት ሲሆን በ09/09/2011 ዓ/ም ከጥዋቱ 3:00 ለአዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት አካባቢ ለትምህርት እንደወጣች አልተመለሰችም። ህፃን ሱመያ በሰዓቱ ቀይ ቀሚስ ቢጫ ሹራብ ልብስ ነበር በመሆኑም ይህችን ህፃን ያየ የሰማ በፈጣሪ ስም እንድትነግሩን እንጠይቃለን

ፈላጊ አብዱልሰመድ ክብር
0914155599
0913506982
0913583704

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኬንያ ዜጎች ቁጣ...

ኬንያ ከአለም ባንክ 750 ሚሊዮን ዶላር ልትበደር የመጠየቋ ዜና ዜጎቿን አስቆጥቷል። ብድሩን የምትጠይቀው በዚህ አመት የገጠማትን የገንዘብ ቀዳዳ ለመሙላት ነው ተብሏል።

ኃገሪቷ ከአስር አመት በኋላ ነው ከአለም ባንክ ለመበደር ድርድሩን የጀመረችው። ምንምእ እንኳን አንዳንድ የኃገሪቷ የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች የኬንያን ውሳኔ ቢደግፉም ብዙ አስተያየት ሰጭዎች ግን ሃገሪቱ ከቻይና የእዳ ዝፈቃ ሳትወጣ፤ ሌላ እዳ መጨመሯ ሊዋጥላቸው አልቻለም።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ስጦታዬ - ለአዲስ አበባዬ"👆

የከተማ አስተዳደሩ አንድ ሚሊየን ነዋሪዎችን የሚያሳትፍ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩን ይፋ አድርጓል፡፡

የከንቲባ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክረተሪያት ከባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን ዝርዝር ዕቅዱ ላይ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

1. "ይሄው ስጦታዬ" ዝግጅት በሚሊኒየም አዳራሽ

- ህብረተሰቡ ለተቸገሩ ወገኖች አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ የሚሰጥበት እና ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፊ የሚሰበሰብበት ይሆናል፡፡

- 'የከንቲባው ልዩ ሽልማት' (Mayor's Award) በሚል መጠሪያ በትምህርታቸው ላቅ ያለ ውጤት ላስመዘገቡየ12ኛ ክፍል 10 ተማሪዎች ከንቲባው የነፃ የውጪ ትምህርት ዕድል ሽልማት ያበረክታሉ፡፡

2. "አዲስ ካርኒቫል"

በአርአያነቱ የባህል ኢንዱስትሪውን የማበልፀግ ፣ ምርቶችን የማስተዋወቅ እና የገበያ ትስስርን ከመፍጠር በተጨማሪ የጋራ ባህላዊ እና ሰስነ ጥበባዊ ዕሴቶቻችንን ፣ ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ፣ አብሮነታችንን ፣ አልባሳቶቻችንን እና የፈጠራ ውጤቶቻችን በጎዳና እና በክፍት መኪኖች ለህብረተሰቡ የሚታዩበት መርሃ ግብር ነው፡፡

3. "አንድ ቀን ለሃገሬ!" የበጎ አድራጎት እና መልካም ፈቃድ መርሃ ግብር

- በቁጥር 1000 ለሚሆኑ አካል ጉዳተኞች ፣ አረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ማደስ

- ከከፍተኛ የት/ት ተቋማት ለእረፍት የሚመለሱ ተማሪዎች 5000 ለሚሆኑ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሰጡ ማድረግ

- በጥናት በተለዩ ቦታዎች የ1ሚሊየን አገር በቀል ችግኝ ተከላ ማካሄድ

- የደም ልገሳ ማከናወን

4. "ቆይታ ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ጋር!"

- የአዲስ አበባ እህትማማች ከሆኑ ከተሞች ጋር የባህል እና የልምድ ልውውጥ ማድረግ

- የከተማችንን የመሠረተ ልማት ስራዎችን እና የቱሪዝም ፀጋዎችን ማስጎብኘት

- በኢ/ር ታከለ ኡማ ሰብሳቢነት የምስራቅ አፍሪካ የከንቲባዎች ፎረምን ማሰናዳት

5. የኪነ-ጥበብ ምሽት

የአዲስ አበባ ከተማ ነወሪዎች የሚሳተፉበት የ"አዲስ አበባ ቤቴ" የስነ ፅሁፍ ፣ የግጥም ፣ የሙዚቃ እና የዲስኩር መሠናዶ ዝግጅት፡፡

በዚህ 'ስጦታዬ - ለአዲስ አበባዬ!' የክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር ላይ ከአንድ ሚሊየን በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ እነዚህን ሁሉ ተግባራት ከነዋሪው ለነዋሪው የሚሠጠው የአዲስ ዓመት ስጦታ እንደሆነም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ወ/ት ፌቨን ተሾመ ተናግረዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ በአቶ በረከት ስምዖንና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ ያቀረባቸውን የቃል ምስክሮች በዛሬው ዕለት ማዳመጥ ጀምሯል።

ፍርድ ቤቱ ግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዓቃቤ ህግ በአቶ በረከት ስምዖንና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ አሉኝ ያላቸውን የቃል ምስክሮች ከግንቦት 21 ጀምሮ እንዲያሠማ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህ መሰረትም በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸው የቃል ምስክሮች በሁለቱ ተከሳሾች ላይ መስክረዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በብቸና ከተማ በፀጥታ መደፍረስ የተጠረጠሩ 17 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ‼️
.
.
ከሰሞኑ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ ‹‹በሃይማኖታዊ አገልግሎት መስጫ ቦታ ይገባኛል›› ሰበብ በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡ ግጭቱ ሃይማኖታዊ ይዘት እንዳልነበረውና ይልቁንም ሆን ተብሎ ሃይማኖታዊ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ የተሞከረ እንደሆነና በፅኑ እንደሚያወግዘው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ጉዳዩን ሲያጣራ ቆይቶ 8 የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን፣ 2 የቀድሞ የሥራ ኃላፊዎችንና 7 በግጭት እንደተሳተፉ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

የመምሪያው የወንጀል የሥራ ሂደት ባለቤት ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ ተስፋዬ እንደተናገሩት ግጭቱ እንዲፈጠር እና በግጭቱ በመሳተፍ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ የተጠረጠሩ አካላትን በሚመለከት ሁለት መዝገቦች ተደራጅተው ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ ሕብረተሰቡ የችግሩ ባለቤት አመራሩ መሆኑን አስመልክቶ ያቀረበውን ጥቆማ በአንድ መዝገብ እና ጉዳዩን በሕግ መፍታት ሲገባ ወደ ግጭት የገቡ ግለሰቦችን በተመለከተ በሌላ መዝገብ ነው የምርመራ ሥራ የተጀመረው፡፡

ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ እንደተናገሩት የግጭቱ አንደኛው መሠረታዊ መነሻ ተብሎ በሕብረተሰቡ የተነገረው ባሕረ ጥምቀት ሆኖ ለረዥም ጊዜ ያገለገለውንና በመሪ ፕላን የተመላከተውን ቦታ ‹‹የከንቲባ አመራሩ ልንሰጣችሁ አይገባም፤ አረንጓዴ ልማት ነው›› ማለቱ ቅሬታ ማስነሳቱ ነው፡፡ ጉዳዩ የመብት ጥያቄ ሆኖ ለረዥም ጊዜ ሲነሳ መቆየቱንም ነው የተናገሩት፡፡

ሁለተኛ የግጭት መነሻ ሰበብ ተደርጎ የተወሰደው ደግሞ ከብቸና ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ (200 ሜትር ሬዲየስ) ያለውን ቦታ ወደ መስጅድ ለማሳደግ መታቀዱና በአዲሱ ፕላን አለመካተቱ ነበር፡፡

ፖሊስ በእነዚህ ጭብጦች ተመሥርቶ ማስረጃ አሰባስቦ ስምንት በኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉና ሁለት የቀድሞ የሥራ ኃላፊዎችን እንዲሁም ሰባት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የወንጀል የሥራ ሂደት ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

የብቸና ከተማ ከንቲባ በጉዳዩ ተጠርጥረው እየተፈለጉ ሲሆን እስካሁን በቁጥጥር ሥር አለመዋላቸውም ታውቋል፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉትም ምክትል ከንቲባው፣ የንግድ፣ የገቢዎች፣ የሲቪል ሰርቪስ፣ የቅሬታ ሰሚ፣ የማዘጋጃ ቤትና የገንዘብና ኢኮኖሚ ጽሕፈት ኃላፊዎችና አፈ-ጉባኤ ናቸው፡፡

ከቀድሞ የሥራ ኃላፊዎች ደግሞ የማዘጋጃ ቤት ኃላፊና ቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

ሌሎቹ ሰባት ግለሰቦች ደግሞ በግጭቱ ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፤ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ቃል የመቀበል ሥራ መጀመሩም ታውቋል ሲል የአብመድ ዘገባ ያመለክታል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከንቲባው እየተፈለጉ ነው...

የብቸና ከተማ ከንቲባ #ከሰሞኑን ከተፈጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ #ተጠርጥረው እየተፈለጉ ሲሆን እስካሁን በቁጥጥር ሥር አልዋሉም። እስካሁን ምክትል ከንቲባው፣ የንግድ፣ የገቢዎች፣ የሲቪል ሰርቪስ፣ የቅሬታ ሰሚ፣ የማዘጋጃ ቤትና የገንዘብና ኢኮኖሚ ጽሕፈት ኃላፊዎችና አፈ-ጉባኤ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአልኮል መጠጦችን በቴሌቪዥን፤ በሬዲዮ እና በግዙፍ የአደባባይ ሠሌዳዎች ማስተዋወቅን የሚከለክለው «የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ» ከዛሬ ግንቦት 21 ቀን፤ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚኾን የጤና ጥበቃ ሚንሥትር ዐስታውቋል።

ከዚህ ቀደም በግዙፍ ሠሌዳዎች ላይ በአደባባይ የተሰቀሉ የአልኮል ማስታወቂያዎች እንዲነሱ ማሳሰቢያ ተላልፏል። ክልከላውን በማናቸውም መንገድ የሚተላለፉ አካላት ካሉ ኅብረተሰቡ በ«8482» ላይ ደውሎ እንዲጠቊም ሚንሥትር መሥሪያ ቤቱ ጥሪ አስተላልፏል። የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ፌስቡክ ገጽ ላይም ጥቆማ ማድረግ እንደሚቻል የጤና ጥበቃ ሚንሥትር ዶክተር አሚር አማን በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

አንዳንድ የግል መገናኛ አውታሮች ከማስታወቂያ የሚያገኙት ገቢ እጅግ የሚቀንስ በመኾኑ የሠራተኛ ቅነሳ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ገልጠዋል።

Via #DW
ፎቶ፦ የጤና ጥበቃ ሚንሥቴር ዶ/ር አሚር አማን ትዊተር ገጽ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰኞ አመሻሽ ላይ በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ዞን በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ተወረወረ በተባለ የእጅ ቦንብ ቢያንስ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡

የቄለም ዞን፣ የዞን ጽሕፈት ቤት ፐብሊሲቲ ኃላፊ አቶ ሐምዛ አብዱልቃድር አደጋው የደረሰው በዞናቸው አንጪሌ ወረዳ ሙጊ 02 ቀበሌ የሚባል ቦታ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰኞ አስር ሰዓት አካባቢ የኦነግ ሸኔ አባላት በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚናገሩት #ኃላፊው የወረወሩት ቦንቡ ፈንድቶ በአካባቢው የሚገኙ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን አስረድተዋል።

የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ ከጋምቤላ ወደ ሙጊ ቀበሌ #በእግርና #በመኪና እየተጓዙ የነበሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ኃላፊው በቦንቡ ጉዳት የደረሰባቸው ግን የደፈጣ ጥቃቱን ሊፈጽሙ በነበሩት የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ለቢቢሲ እንደገለፁት ሰኞ እለት ቦንብ መወርወሩን እንደሚያውቁ ነገር ግን የቦንብ ፍንዳታውን ተከትሎ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ #ሰባት ንፁሀን ተገለዋል ብለዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ👆

"በአሁን ሰዓት መላው የዩንቨርሲትው ማህበረሰብ ፊቼ ጫምባላላን በደማቅ ሁኔታ እያከበርን ነው። በዝግጅቱ ላይ ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ ተማሪዎች እና የጊቢው ሰራተኞች በጋራ እያከበሩ ይገኛሉ። በአከባበሩ ላይ ላይ የተለያዩ በአሉን የሚያንፀባርቁ ዝግጅቶች እየቀረቡ ይገኛሉ።"

Via #KIYA ~~ /TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia