TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
JiT👆

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የዓመቱ የማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥብት ቀን #ይራዘምልን በማለት ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። ተማሪዎቹ ፦ "ፊርማ አሰባስበን የፈተናው ቀን እንዲራዘም ብንጠይቅም ተቋሙ ጥያቄያችንን ወደኃላ በማለት በአቋሙ ፀንቷል፤ ብዙ portion ያልጨረስን በመሆኑ ተማሪውን ከግቢ #ለማባረር የተጠነሰሰ ሴራ ነው" ብለን እናምናለን ሲሉ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ከJiT አመራሮች የሚሰጥ #ምላሽ ካለ ተከታትዬ የማቀርብላችሁ ይሆናል። #JiT
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌደራልና የክልል ፓሊስ ኮሚሽነሮች ከቤተመንግስት ጉብኝታቸው ተከትሎ ከጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ጋር የችግኝ ተከላ አካሄዱ:: ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በቤተመንግስትና በከተማዋ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ራዕይና የደረሱበትን ደረጃ አስረድተው ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች በሌሎችም ከተሞች እንዲተገበር አላማ እንዳለ ገልፀዋል።

#PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ አድርሱ~~8482👆

ህብረተሰቡ የተሰቀሉ የአልኮል ማስታወቂያ ቢልቦርዶች ሲመለከት #በ8482 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠየቀ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣው አዋጅ ቁጥር 1112/2011 የአልኮል ምርት በማንኛውም በብሮድካስትና ቢል ቦርድ ማስተዋወቅ የተከለከሉ ድንጋጌዎች መውጣቱን ተከትሎ አብዛኛው የአልኮል ምርት አምራቾች ህጉን ተከትሎ በአ/አ ስታዲየም ዙሪያና በተለያዩ ቦታዎች የተሰቀሉ ቢልቦርዶችን #በማንሳት ላይ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል። ሆኖም በአንዳንድ ቦታዎች እስካሁን ድረስ የቢልቦርድ ማስታወቂያ ያልተነሱ መሆኑንና የአልኮል አምራች ድርጅትና የማስታወቂያ ሰሪ ድርጅቶች በየቦታው የተሰቀለውን ቢልቦርድ እንዲያነሱ አሳስቦ ህብረተሰቡም በየቦታው የተሰቀሉ ቢልቦርዶች ሲመለከት በ8482 በመደወል #ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቋል።

√√በህዝብ ተወካዬች ም/ቤት በቅርቡ በፀደቀውን የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ 1112 መሰረት ከዛሬ ግንቦት 21 ጀምሮ የአልኮል ማስታወቂያዎችን በብሮድካስት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ህግ ተግባራዊ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወሳል ።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#8482

የተሰቀሉ የአልኮል ማስታወቂያ ቢልቦርዶች ስትመለከቱ #በ8482 በመደወል ጥቆማ እንድትሰጡ ተጠይቃችኃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድንጋጌው ተፈፃሚ መሆን ጀምሯል...

የአልኮል መጠጥን በብሮድካስት አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው #ድንጋጌ ከዛሬ ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል፤ ከዛሬ ጅምሮ ማንኛውም የብሮድካስት ሚድያ #የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ ማስተላለፈፍ እንደማይችል ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወሎ ዩኒቨርሲቲ👆

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የረመዳንን ጾም ምክንያት በማድረግ ልዩ የፈጢር ፕሮግራም ለተማሪዎች ተዘጋጅቶ ነበር። በዚህም የፈጢር ፕሮግራም የዩንቨርሲቲው አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የደሴ ከተማ ከንቲባ በቦታው በመገኘት ተማሪዎችን አስፈጥረዋል።

Via Wollo University PR
@tsegabwolde @tikvahethiopia