#update የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ቤተ መንግሥቱን ጎበኙ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በቤተ መንግሥት ግቢ ዉስጥ የሚሰሠሩ ሥራዎችን ጎብኝተዋል:: ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም በከተማዋ የሚተገበሩትን 'ሸገርን የማስዋብ' ፕሮጀክቶችና ለዜጎች የሚኖራቸዉን ሁለንተናዊ ፋይዳ አብራርተዉላቸዋል፡፡
ምንጭ፡- የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡- የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ዉስጥ የማዕድናት ቁፋሮ ለሚያከናውኑ ባለሀብቶች የሐገሪቱ የማዕድን ሚንስቴር ፍቃድ ሰጠ። የምርት እና የምርምር ፍቃድ ከተሰጣቸው በተጨማሪ ሌሎች ኩባንያዎች ደግሞ ፍቃዳቸው ተራዝሞላቸዋል። ፈቃድ የተሰጣቸዉ ኩባንያዎች በኢትዮጵያዉያን ባለቤትነት የተመዘገቡ ወይም ኢትዮጵያዉያን በሽርክና የሚያስተዳድሯቸዉ ናቸዉ። በፈቃድ አሰጣጡ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተነገረዉ ለኩባንዮቹ የሥራ ፈቃድ ለመስጠት ብዙ ዉጣ ዉረድ ነበረዉ። ሚኒስትሩ ዶክተር ሳሙኤል «ችግሩ እንዲቀረፍ በተለይ ደግሞ ኢንቨስትመንት ቀላል እንዲሆን ሀገሪቱ እየሰራች ነው» ብለዋል። አሁን ወደ ምርት የገቡት ባለሀብቶች ቢያንስ 10 ዓመት ያህል በፍለጋ እና በምርመራ ላይ የቆዩ ናቸው ተብሏል።
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ -- ዝግጅቱ ተጠናቋል!!
#StopHateSpeech
#Jimmaa #ጅማ
Barattoonni mooraa Guddichaa,Beeko,Kittoo fi mooraa qonnaa hundinuu affeeramtanii jirtu____Iddo istaadiyoomii xiqqaa mooraa guddichaa.
ዋናው ግቢ፣ ቤኮ፣ አግሪ፣ ቴክኖ ተማሪዎች በሙሉ #ተጋብዛችዋል፤ በሚኒ ስታዲየም ዋናው ግቢ!
#TIKVAH_ETH #ሰላም_ፎረም #ተማሪ_ህብረት

#update የኢትዮጵያ ዜግነት ማህበራዊ ፍትህ (አዜማ) የመሠረቱት ፓርቲዎች ራሳቸውን ስለማክሰማቸው እንደማያውቅ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተናግሯል፡፡ አዜማም ለቦርዱ ቀርቦ ሕጋዊ ፓርቲ ሆኖ አልተመዘገበም- ብለዋል የቦርዱ የኮምኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ለአዲስ ዘመን ሲናገሩ፡፡ የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው ምርጫ ቦርድ ሊያዘን አይችልም፤ ፓርቲዎቹ በመተዳደሪያ ደንባቸው በጉባዔ ወስነው አዲሱን ፓርቲ መስርተዋል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በቅርቡ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲና የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ ተዋህደን አዜማን መስረተናል ማለታቸው ይታወሳል።
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የ2018/19 ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከነገ በስቲያ ፍፃሜውን ሲያገኝ በግብፁ ዛማሌክ እና የሞሮኮው በርካኔ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ በዓምላክ ተሰማ እንዲመራው በካፍ ተመድቧል። ከ5 ቀናት በፊት በሞሮኮ በተደረገው የመጀመርያ ጨዋታ ባለሜዳው አር ኤስ በርካኔ በመጨረሻ ደቂቃ ኮጆ ላባ ባስቆጠረው ጎል ማሸነፍ የቻለ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ በአሌክሳንድሪያው ቦርግ አል አረብ ስታድየም እሁድ ምሽት ይካሄዳል። ይህን ጨዋታም ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ በመሐል ዳኝነት ይመራዋል። ደቡብ አፍሪካዊው ዛኪይ ሲዎሊ እና የሴኔጋሉ አልሀጂ ማሊክ በረዳትነት ሲመሩ ቱኒዚያዊው ሳዶክ ሴልሚ በአራተኛ ዳኝነት ተመድቧል። በሞሮኮ የተካሄደውን የመጀመርያው ጨዋታ የመራው ጃኒ ሲክዌዜ ደግሞ ከሱዳናዊው ዋሊድ አህመድ እና ሴኔጋላዊው ጋብሬል ካማራ ጋር በመሆን የVAR ዳኝነቱን ይመራል።
ምንጭ:- ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ:- ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምርጫ ቦርድ በመጭው ሰኞ ለጋዜጠኞች መግለጫ እሰጣለሁ ብሏል፡፡ መገናኛ ብዙሃንም ተገኝተው እንዲዘግቡ ጥሪ አድርጓል፡፡ መግለጫው በቦርዱ አዲስ አወቃቀር፣ በአዳዲስ ቦርድ አባላት አሰያየም፣ በምርጫ በጀት፣ በሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ጥያቄና የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘምና ተፈናቃዮች በምርጫው ላይ ስለሚፈጥሩት ተጽዕኖ በሚሉት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል- ይላል የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ፡፡
Via #አዲስ_ስታንዳርድ/wazema/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #አዲስ_ስታንዳርድ/wazema/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኤርትራ ነጻነቷን ከኢትዮጵያ ያገኘችበትን 28ኛ የነጻነት በዐል ትላንት ስታከብር ውላለች፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ትናነት የ“እንኳን አደረሳችሁ” መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡ የትግራይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልም በትግራይ ቴሌቪዥን ዛሬ ባሰተላለፉት መልዕክት የትግራይ ሕዝብና ሕወሓት የኤርትራን ነጻነት ቀናዒ መሆኑን መግለጻቸውን DW ዘግቧል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ባለፈው ዐመት ሰላም ስምምነት ከደረሱ ወዲህ ኤርትራ የነጻነት በዐሏን ስታከብር ያሁኑ የመጀመሪያዋ ነው፡፡ በቅርቡ ከኤርትራ በኩል መልሶ የተዘጋው ሁለቱ ሀገሮች ድንበር እስከዛሬው ዕለት አልተከፈተም፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ላይ የሳይበር ትንኮሳ እየተቃጣ ነው"--- INSA
በሃገሪቱ በ2011 ዓ.ም የተሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች ካለፉት ሁለት ሩብ አመቶች በ3ኛው ሩብ ዓመት የሳይበር ጥቃት መጠን በሶስት እጥፍ አድጓል፡፡
በሃገሪቱ ያሉ ወሳኝ መሰረተ-ልማቶችን ያነጣጠረው የሳይበር ጥቃቱ የአጥፊ ሶፍትዌሮች(malware) ማሰራጨት ፣ድረ-ገጾች ማጥቃት ፣የሳይበር ትንኮሳዎች መፈጸም ፣መሰረተ-ልማቶችን ለማጥቃት ቅኝቶችን ማድረግ ወንጀለኞቹ ያነጣጠሩባቸው መስኮች ነበሩ፡፡
እነዚህ የተሰነዘሩ እና ሊሰነዘሩ የነበሩ የሳይበር ጥቃቶች በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አማካኝነት ከሽፈዋል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በሃገሪቱ 488 አደገኛ የሚባሉ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች የተፈጠሩ ሲሆን በድረ-ገጾች ላይ የተቃጣው ከፍተኛውን ድርሻ በመውስድ ከአጠቃላዩ (39.9) በመቶ ይዟል፡፡
በወሳኝ መሰረ-ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የተደረጉ ቅኝቶች 17.6 በመቶ እንዲሁም ወዳልተፈቀደ የኮምፒውተር ስርዓቶች ሰርጎ የመግባት ተግባር 14.95 በመቶ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል፡፡
አብዛኛዎቹ የሳይበር ጥቃት እንቅስቃሴዎች ጥቃት ከመፈጸማቸው በፊት በቅኝት ላይ ሳሉ እንቅስቃሴያቸው ተገቷል፡፡
ለሳይበር ጥቃት የተጋለጡ ሲስተሞች ፣ የኮምፒውተር ስርዓቶች እና መጠቀሚያ መሳሪያዎችን ክፍተት በመለየትም ክፍተቱን የመሙላት ስራ ተከናውኗል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው ተሞክሮም በየወቅቱ የሳይበር ጥቃት መጠን እያደገ ሲሆን በሃገራችን ባለፉት 3 ወራት የተቃጣው የሳይበር ጥቃትም ከ3 እጥፍ በላይ ጨምራል፡፡
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ስርአቶች እንዲሁም ወሳኝ የሚባሉ መሰረት ልማቶች ከኮምፒውተር ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
Via Information Network Security Agency (INSA)