TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ቤተ መንግሥቱን ጎበኙ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በቤተ መንግሥት ግቢ ዉስጥ የሚሰሠሩ ሥራዎችን ጎብኝተዋል:: ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም በከተማዋ የሚተገበሩትን 'ሸገርን የማስዋብ' ፕሮጀክቶችና ለዜጎች የሚኖራቸዉን ሁለንተናዊ ፋይዳ አብራርተዉላቸዋል፡፡

ምንጭ፡- የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ👆በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች መምህራን #ሰላማዊ_ሰልፍ ሲያካሂዱ ውለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ዉስጥ የማዕድናት ቁፋሮ ለሚያከናውኑ ባለሀብቶች የሐገሪቱ የማዕድን ሚንስቴር ፍቃድ ሰጠ። የምርት እና የምርምር ፍቃድ ከተሰጣቸው በተጨማሪ ሌሎች ኩባንያዎች ደግሞ ፍቃዳቸው ተራዝሞላቸዋል። ፈቃድ የተሰጣቸዉ ኩባንያዎች በኢትዮጵያዉያን ባለቤትነት የተመዘገቡ ወይም ኢትዮጵያዉያን በሽርክና የሚያስተዳድሯቸዉ ናቸዉ። በፈቃድ አሰጣጡ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተነገረዉ ለኩባንዮቹ የሥራ ፈቃድ ለመስጠት ብዙ ዉጣ ዉረድ ነበረዉ። ሚኒስትሩ ዶክተር ሳሙኤል «ችግሩ እንዲቀረፍ በተለይ ደግሞ ኢንቨስትመንት ቀላል እንዲሆን ሀገሪቱ እየሰራች ነው» ብለዋል። አሁን ወደ ምርት የገቡት ባለሀብቶች ቢያንስ 10 ዓመት ያህል በፍለጋ እና በምርመራ ላይ የቆዩ ናቸው ተብሏል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ -- ዝግጅቱ ተጠናቋል!!
#StopHateSpeech

#Jimmaa #ጅማ

Barattoonni mooraa Guddichaa,Beeko,Kittoo fi mooraa qonnaa hundinuu affeeramtanii jirtu____Iddo istaadiyoomii xiqqaa mooraa guddichaa.

ዋናው ግቢ፣ ቤኮ፣ አግሪ፣ ቴክኖ ተማሪዎች በሙሉ #ተጋብዛችዋል፤ በሚኒ ስታዲየም ዋናው ግቢ!

#TIKVAH_ETH #ሰላም_ፎረም #ተማሪ_ህብረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ዜግነት ማህበራዊ ፍትህ (አዜማ) የመሠረቱት ፓርቲዎች ራሳቸውን ስለማክሰማቸው እንደማያውቅ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተናግሯል፡፡ አዜማም ለቦርዱ ቀርቦ ሕጋዊ ፓርቲ ሆኖ አልተመዘገበም- ብለዋል የቦርዱ የኮምኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ለአዲስ ዘመን ሲናገሩ፡፡ የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው ምርጫ ቦርድ ሊያዘን አይችልም፤ ፓርቲዎቹ በመተዳደሪያ ደንባቸው በጉባዔ ወስነው አዲሱን ፓርቲ መስርተዋል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በቅርቡ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲና የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ ተዋህደን አዜማን መስረተናል ማለታቸው ይታወሳል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የ2018/19 ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከነገ በስቲያ ፍፃሜውን ሲያገኝ በግብፁ ዛማሌክ እና የሞሮኮው በርካኔ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ በዓምላክ ተሰማ እንዲመራው በካፍ ተመድቧል። ከ5 ቀናት በፊት በሞሮኮ በተደረገው የመጀመርያ ጨዋታ ባለሜዳው አር ኤስ በርካኔ በመጨረሻ ደቂቃ ኮጆ ላባ ባስቆጠረው ጎል ማሸነፍ የቻለ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ በአሌክሳንድሪያው ቦርግ አል አረብ ስታድየም እሁድ ምሽት ይካሄዳል። ይህን ጨዋታም ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ በመሐል ዳኝነት ይመራዋል። ደቡብ አፍሪካዊው ዛኪይ ሲዎሊ እና የሴኔጋሉ አልሀጂ ማሊክ በረዳትነት ሲመሩ ቱኒዚያዊው ሳዶክ ሴልሚ በአራተኛ ዳኝነት ተመድቧል። በሞሮኮ የተካሄደውን የመጀመርያው ጨዋታ የመራው ጃኒ ሲክዌዜ ደግሞ ከሱዳናዊው ዋሊድ አህመድ እና ሴኔጋላዊው ጋብሬል ካማራ ጋር በመሆን የVAR ዳኝነቱን ይመራል።

ምንጭ:- ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia