TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማህበር ሕውነት ደቂስብ ማእከል👆
/መቐለ/

የTIKVAH-ETH አባላት ድግማይ ትንሳኤን በማህበር ሕውነት ደቂስብ ማእከል /ለወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ/ ከኢንፎርመሽን ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎቻን አክብረናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሌላኛው በጉዟችን...

የTIKVAH-ETH ቤተሰብ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለእስልምና እምነት ተከታይ የቤተሰቡ አባላት "እንኳን ለረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ፤ የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ ፆም እዲሆንላችሁ ምኞታችን ነው ፈጣሪ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈፅማችሁ" በሚል ቤተሰባዊ ምኞታቸውን ገልፀውላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር ክንደያ👆

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላትን የመቐለ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ስራዎች በትዊተር ገፃቸው በየሰዓቱ ለህዝብ ሲገልፁ ስለነበር እንዲሁም በግቢው ቆይታችን መስተንግዶው የተመቻቸ እንዲሆን ስላደረጉ #እናመሰግናለን!!

@tsegbwolde @tikvahethiopi
•ለአብሮነታችሁ ምስጋና ከTIKAVH-ETH•

#StopHateSpeech እንቅስቃሴው ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ እስካሁን አብራችሁን #በፅናት ለቆማችሁ ኢትዩጵያዊያን ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን!!

እያንዳዷን እንቅስቃሴ እንደተቋም እና እንደግል ከባልደረቦቻችሁ ጋር በመደግፍ - ለቤተሰባችን አባላት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲመቻች እና የምግብ ወጪያቸው እንዲሸፈንና #ለሰላም እና #ለፍቅር የሚያደርጉትን ጉዞ የተሳካ እንዲሆን ግንባር ቀደም በመሆን ስለደገፋችሁ አሁንም #እየደገፋችሁ ስላለ ከልብ እናመሰግናለን!! ወደፊት ታሪክ ያስታውሳችኃል!!

የኢትዮጵያ ህዝብ ውለታችሁን ይክፍል!!
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት በፀዳ መልኩ አንድነትን የሚያመጣ ስራ እንድንሰራ ስላገዛችሁን እናመሰግናለን።

√ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

▪️ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ/የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት/

▪️ወ/ሮ ገነት ወልዴ/የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ልማት ኮፖሬት ም/ፕሬዝዳንት/

▪️ዶ/ር ሲሳይ ሸዋአማረ/የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት/

▪️ዶ/ር ሀብቴ ዱላ/የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አከዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት/

▪️አቶ ብሩ ሚጎራ/የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ልምት መልካም አስተዳደር ም/ፕሬዝዳንት/

▪️ብሩክ እሸቱ/የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን/

▪️የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተተማሪዎች ህብረት
/ወጣት ይድነቃቸው አየለ/

▪️የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ፎረም
/ግዛት ብርሃኑ/

√መቐለ ዩኒቨርሲቲ

▪️ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት /የዩኒቨረሲቲው ፕሬዘዳንት/

▪️ዶ/ር ከሳቴ ለገሰ/የተማሪዎች አገግሎት/ምስጋና

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት/ወጣት ግደይ ነዑል/

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

▪️ዶክተር #ታከለ_ታደሰ/የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት/

▪️ኤፍሬም ጉልፎ/ረዳት ፕሮፌሰር/የተማሪዎች አገ/ት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

▪️አቶ ፍሬይወት ናና/የተማሪዎች አገልግሎት/

▪️ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
/ወጣት ዘገየ ገ/መድን/

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

▪️Dr. ዳምጠው ዳርዛ/የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት/

▪️Dr. የቻለ ከበደ/Academic vice President/

▪️የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
/ቃልኪዳን አባይነህ/

▪️አቶ አየልኝ ጎታ/የተማሪዎች አገልግሎት/

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

▪️ዶክተር አያኖ በራሶ/የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት/

▪️ዶክተር መሳይ ሀይሉ/Vice President Administration & Student Service/

▪️ወ/ሮ አርማዬ አሰፋ/የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር/

▪️አቶ አመሎ የተማሪዎች አገልግሎት

▪️የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
/ወጣት ቀኔሳ እና ወጣት ምትኩ/

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ

▪️Dr. ሀይለማርያም ብርቄ/የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት/

▪️ኘሮፌሰር አለባቸው ጎስማ/የተማሪ አገልግሎት/

▪️ፍፁም ተክሌ/የሠላም ፎረም/

▪️የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት/አበበ በላይ/

ወሎ ዩኒቨርስቲ

▪️Dr. አባተ ጌታሁን/የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት/

▪️አቶ ጌትነት ካሴ/የተማሪዎች አገልግሎት/

▪️የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት /ወንድማገኝ ሠርጌታ/

▪️የሠላም ፎረም/ሀይሉ ጣፈጠ/

√ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

▪️Dr. ደሳለኝ ሞላ/የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት/

▪️የተማሪዎች ህብረት ኘሬዝዳንት/መላክ ያይኔአበባ/

የሠላም ፎረም/ብስራት ሠይፉ/

▪️የተማሪ አገልግሎት ዳይሬክተር/መኮንን ዘለለ/ /ተስፋው ወርቁ

ልዩ ምስጋና!

√ለአክሱም ዩንቨርስቲ
√ለአዲግራት ዩኒቨርሲቲ
√ለራያ ዩኒቨርሲቲ
√ሰመራ ዬኒቨርሳቲ

ልዩ ምስጋና

ሚያዚያ 23 አዲስ አበባ መግባታችንን ተከትሎ ስማቸውን የማልገልፀው ቤተሰባችን አባላት የታሸገ ውሃ በማምጣት ታልቅ ክብር አሳይታቹናል እናመሰግናለን!!

ልዩ ምስጋና

ሁሉንም የTIKVAH-ETH የሙዚቃ ባንድ አባላት። እናመሰግናለን!!

ልዩ ምስጋና

ለመኪና አሽከርካሪዎቻችን ረጅሙን መንገድ ተቸግራችሁ በሰላም አድርሳችሁ ስለመለሳችሁን እናመሰግናለን!! ፈጣሪ ረጅም እድሜ ይስጣችሁ!

ልዩ ምስጋና

በየከተማው አቅፋችሁ የተቀበላችሁን፣ ያበላችሁን፣ ያጠጣችሁን ፤ አይዟቹ በርቱ ያላችሁንን ፤ ፍቅር ያሸንፋል እኛም እናግዛለን ያላችሁን ወገኖቻችን በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እናመሰግናለን!!

በኢትዮጵያ ተስፋ አንቆርጥም!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የባሕር ዳር እና መቐለ ነጋዴዎች የሰላም ጥሪ!

ከባሕር ዳር እና ሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች የተውጣጡ ነጋዴዎች ወደ ትግራይ ክልል መቐለ በመጓዝ ከከተሟዋ ነጋዴዎች ጋር በሰላም ጉዳይ መከሩ፡፡ የሁለቱ ክልል ነጋዴዎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከርም የበኩላቸው እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡

በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች የንግድ እንቅስቃሴው እንደጎዳው የሁለቱ ክልሎች የንግድ ማኅበረሰብ ተናግረዋል። ነጋዴዎቹ ለሚፈጠሩ ችግሮች መንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ በመስጠት የሚያጋጥማቸውን እንግልት መቀነስ ይገባዋል ብለዋል። 

በባሕር ዳር ከተማ እንዲሁም ሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች የሚገኙ ነጋዴዎች ያቀፈው የባሕር ዳር ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት አመራሮችና አባላት ከአቻቸው የመቐለ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት ባደረጉት ውይይት በንግድ ሥራ በተጨማሪ በህዝብ ለህዝብ መቀራረብ ዙርያ መነጋገራቸው የመቐለ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ቦርድ አባል አቶ በሪሁ ሀፍቱ ገልፀዎል። 

የባሕር ዳር ከተማ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤትፕሬዝዳንት አቶ መንገሻ በላይ በበኩላቸው ከዚህ በፊትም የንግድ ማሕበረሰቡ ለሰላም የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱ ተናግረዋል። በትግራይና አማራ ንግድ እንቅስቃሴ ላይ የሚያጋጥሙ መሰናክሎች መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሊፈታው ይገባል ያሉት ነጋዴዎቹ የእነርሱን አርአያነት የፖለቲካ አመራሮች እንዲከተሉ አሳስበዋል። ለችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት የፖለቲካ አመራሮቹ መወያየት አለባቸው ብለዋል። 

በአማራና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥረው በነበሩ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተፅእኖ ሲፈጥር መቆየቱ ይታወሳል። በተለይም ትግራይ ከተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል የሚያገናኙ መንገዶች በተደጋጋሚ መዘጋታቸው የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው። በዚህም ነጋዴዎች ሥራቸው ለመከወን እየተቸሩ መቆየታቸው በተደጋጋሚ ይጠቅሳሉ። 

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝና የድፍድፍ ዘይት ነገር ከምን ደረሰ? የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት የተያዘው እቅድ በጊዜ ሰሌዳው አልተከናወነም - ለምን ይሆን?

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። ሰልፉ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እየተካሄደ ነው። እየተነሱ ያሉ ጥይቃቄዎችን በፎቶ አስደግፌ የማቀርብላችሁ ይሆናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ👆

በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የዞኑ አመራሮች፤ አባቶች እናቶች፤ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም በርካታ ወጣቶች እየተሳተፉበት ይገኛል።

በሰልፉ ላይ እየተነሱ የሚገኙ ጥያቄዎችን እና በሰልፉ ላይ እየተሰሙ ስላሉት መፈክሮች -- አዘጋጅቼ እንደጨረስኩ ወደእናተ አሰርሳለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተደረገ በሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ የተሰሙ መፈክሮች፦

√ከአጎራባች ህዝቦች ጋር ያለን #አብሮነታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!

√የክልልነት ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመለስ!

√የወላይታ ህዝብ በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ አንድነትን #ይደግፋል!

√ሀገራዊ ለውጡ #ተጠናክሮ እንዲቀጥል የህግ የበላይነት ሊከበር ይገባል!!

√መንግስት በወላይታ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት #ሊያስቆም ይገባል።

√የደቡብ ክልል ምክር ቤት የህዝባችንን የክልል ጥያቄ አዳፍኖ መያዙን አጥብቀን #እንቃወማለን!

√በ1950ቹ የነበረው የወላይታ አውሮፕላን ማረፊያ #ይመልስልን!

√አሁን ያለው ሀገራዊ ለውጥ በምንም አይነት ሁኔታ #ሊደናቀፍ አይገባም!!

√እኛ የለውጥ #ደጋፊዎች ብቻ ሳንሆን የለውጥ #ባለቤቶች ነን!!

√ሀገር ለነበረው ወላይታ #ክልል መሆን አይከለከልም!!

√ስራ ወዳድነት #ክብር እንጂ ውርደት አይደለም!

√ወላይታ በሞግዚቶች መመራት በቃው! ጋሞ፣ ጎፋ፣ ሲዳማ፣ ዳውሮ የወላይታ ወንድም ሕዝቦች ናቸው!

√ኢትዮጵያዊነት ፀጋ እንጂ ኩነኔ ሊሆን አይገባም!

√የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለወላይታ!


በአሁን ሰዓት በወላይታ ሶዶ ስታዲየም ብዙ ሺ ሰዎች በተገኙበት የማጠቃለያ ፕሮግራም እየተካሄደ እንደሆነ ለመስማት ችለናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia