TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ በቂርቆስ ክ/ከተማ የማምረቻ ሼድ ተሰጥቷቸው በስራ ላይ የሚገኙ የወጣት ማህበራትን ጎበኙ፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ በጫማ ማምረት ፣ በወረቀት ስራ ፣ በሽመና ስራ እና በልብስ ስፌት ስራ ላይ የተሰማሩ ለበርካታ የአከባቢው ወጣቶች የስራ ዕድል የፈጠሩ ማህበራትን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ የየስራ ማህበራቱ ተወካዮች የማምረቻ ማዕከል ጥበት እና የገበያ ትስስር ችግር እንዳለባቸው ለኢ/ር ታከለ ኡማ ገልፀዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ለስራ ማህበራቱ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር እንደሚሰራ እና ልዩ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ 2 ቢሊዮን ብር መድቦ ለወጣቱ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከግንቦት 5 እስከ 7 ድረስ ልዩ የደም ልገሳ መርሃግርብ ተዘጋጅቶ ነበር። በዚህ የደም ልገሳ መርሃግብር ላይ በርካቶች ተሳታፊ ሆነውበት አልፏል።

"ደም ለጋሽ ከሆኑ ይህንን የህይወት ስጦታ ለተቀበለው ሰው ከእርሶ በላይ ጀግና የለውም!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የማዕድን ግብይት አዋጅ ክልሎች ፈቃድ እንዲሰጡ እና እንዲያስተዳድሩ ስልጣን የሚሰጥ ሆኖ ተሻሽሎ ፀደቀ፡፡

ከዚህ ቀደም ማዕድናትን በተመለከተ ፈቃድ ለመስጠት አንዳንድ ስልጣንና ሀላፊነት የፌደራል መንግስቱ ሆኖ ቆይቷል፡፡

የፌደራል መንግስት ለክልልና ለከተማ አስተዳደሮች በአካባቢያቸው የሚወጣን ማዕድን እንዲያስተዳድሩ ውክልና ይሰጣቸውም ነበር፡፡
በተሻሻለው አዋጅ ግን ማዕድኑ የሚወጣበት ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ያለ ውክልና በራሱ ፈቃድ የመስጠትና የማስተዳደር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

የማዕድን ግብይትን በተመለከተ አዋጁ ለዜጎች የተሻለ የስራ እድል እንዲፈጠር ያግዛል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

ቀድሞ በነበረው አዋጅ የከበሩ ማዕድናት የላኪነት የፈቃድ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የወሰደ ሰው ያለ ገደብ ሁሉንም ዓይነት የከበሩ ማዕድናትን ወደ ውጪ እንዲልክ የሚፈቅድ ሆኖ በመቆየቱ ስራው በተወሰኑ ሰዎች ብቻ እንዲያዝ አድርጎት ቆይቷል ተብሏል፡፡

በመሆኑም በተሻሻለው አዋጅ የሚሰጠው ፈቃድና የብቃት ምስክር ወረቀት በማዕድን ዓይነቱ ተለይቶ የሚሰጥ ሆኗል፡፡ ይህም ለሌሎችም ዜጎች ሰፊ እድል እንዲፈጠር ያደርጋል ተብሏል፡፡

የተሻሻለው የማዕድን የግብይት አዋጅ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን እንደ ገና ለማቋቋም የቀረበለትን እና ሌሎችንም ረቂቅ አዋጆችን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ለዝርዝር እይታ መርቷል፡፡

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በእስራኤል የኢ. ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ረታ ዓለሙ ነጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን ዛሬ በኢየሩሳሌም ለአገሪቱ ፕሬዚደንት ረውቪን ሪቭሊን አቅርበዋል።

ምንጭ፡- የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር በነበረው #ቦይንግ_737_ማክስ አውሮፕን የደረሰው አደጋ ከመከሰቱ በፊት የአሜሪካ አውሮፕላን አብራሪዎች ቡድን በዚህ መሰል አውሮፕላኖች የደህንነት ስጋት እንዳለ ለኩባንያው አሳውቀው አንደነበር ተገለፀ፡፡ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በኢንዶኔዥያ ከደረሰው አደጋ በኋላ ሙከስ ተብሎ በሚጠራው መቆጣጠሪያ ስርዓት ላይ ችግር እንደነበረበትና በአፋጣኝ እንዲፈታ አሳስበው እንደነበር ተገልጿል፡፡ የአሜሪካው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ፣ ቦይንግ ግን አብራሪዎች ያነሱትን ጥያቄ ወደጎን በመተው ወደ ፊት የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሩን ለማስተካከል ቃል መግባቱን ዘገባው አክሏል፡፡ ኩባንያው ባለሙያዎቹ ያቀረቡትን ስጋት ባለመቀበሉ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡ ከችግሩ ጋር በተያያዘም በዓለም ላይ የነበሩ ሁሉም የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች እንዳይበሩ መታገዳቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድህረ ምረቃ ተማሪዎች (Residents) የተላለፈ መልእክት፦

እኛ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሬዚደንት ሀኪሞች ያሉብንን ችግሮች በተለያዩ ጊዜያት ለሆስፒታሉ እና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተለያዩ መድረኮች ያቀረብን ቢሆንም ለእነዚህ ጥያቄዎቻችን ተገቢውን ምላሽ ማግኘት ባለመቻላችን በጋራ ባደረግነው ውይይት መሰረት ሰላማዊ እና ህጋዊ አሰራርን በተከተለ፤ ታካሚዎችን በከፍተኛ ደረጃ ሊጎዳ በማይችል መልኩ ማለትም የጽኑ ህሙማን ክፍል( ICU)፣ የማዋለጃ ክፍል( Labor ward)፣ ድንገተኛ ክፍል( EOPD) እና ድንገተኛ ቀዶ ህክምና( Emergency surgery)ን በduty መርሀ ግብር ለመሸፈን ተስማምተን ስራ ማቆማችን ይታወቃል።

ሆኖም ግን በሆስፒታሉ የአስተዳደር ሰራተኞች በኩል እየተፈጸመ ያለው ዛቻ እና ከእውነታው የራቀ የሚዲያ ዘመቻ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው እና ከእውነታው የራቀ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ማስረጃዎች
1. በቀን 06/09/2011ዓ.ም ስራ የምናቆም መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አስቀድመን ካስገባነው የጥያቄዎች ሰነድ ጋር አባሪ አድርገን ለሁሉም የትምህርት ክፍል አስተባባሪዎች፣ ለሆስፒታሉ አስተዳደሮች እና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ያስገባንና የሆስፒታሉ አስተዳደር ( CED) እና አካዳሚክ ዳይሬክተር ግን የተላከላቸውን ደብዳቤ አንቀበልም ብለው የመለሱ ቢሆንም በቀን 07/09/2011ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ግን ስለሁኔታው ምንም እንደማያውቁ ገልጸዋል።

2. ሆስፒታሉ ውስጥ አሁንም እየሰራ የሚገኘው ሀኪም ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በduty መርሀ ግብር ብቻ እየተሸፈነ ባለበት ሁኔታ የሆስፒታሉ አስተዳድሮች ግን ምንም አይነት የስራ ክፍተት ያልተፈጠረ አስመስለው ማቅረባቸው ጉዳዩ ተገቢው ትኩረት እንዳይሰጠው ከማድረጕም በላይ በታካሚወች ላይ የተቃጣ ሀላፊነት የጎደለው ንግግር ሆኖ አግኝታነዋል።

3. በመግለጫው ላይ የቀረቡ ማስፋራሪያዎች እና የሀሰት መረጃዎች፤ ያቀረብናቸውን ጥያቄዎች በህግ አግባብ ከመመለስ ይልቅ ዛሬም እንደትላንቱ በሃይል እና በማስፋራራት ለማፈን እየተሞከረ ለመሆኑ ማሳያወች ናቸው።

በመሆኑም የሆስፒታሉ አስተዳደር ከእንደዚሕ አይነት ስራ እንዲቆጠቡ እያሳሰብን፤ ሌሎችም የሆስፒታላችን ነባር ሀኪሞች፤ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጥያቄዎቻችን ተራ የጥቅም ጥያቄዎች ሳይሆኑ በጤናው ዘርፍ የሚታየውን ብልሹ አሰራር እና ደረጃውን ያልጠበቀ የህክምና አሰጣጥ ስርዓት ለማስተካከል የሚደረግ ሁሉን አቀፍ ትግል መሆኑን ተረድታችሁ ከጎናችን በመቆም ታሪካዊ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

የአዲስ አበባ ሬዚደንት ሀኪሞች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ የFace Book page ይምረጡ። የጤና መረጃ÷ዜና እና ጠቃሚ ማስታወቂያዎች ይደርስዎታል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑት ። ሙሉውን ገጽ ያገኛሉ።

እንዲሁም ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናል ይከተሉ፦ t.iss.one/spmmc
https://www.facebook.com/sphmmc/
#update ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና ከአዋሳኝ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው በመመለሳቸው 45 የመጠለያ ካምፖች የተዘጉ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ አራት የሴራሚክስ፣ ግራናይትና ባኞ ቤት አከፋፋዮች ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈፀሙ እጅ ከፈንጅ መያዛቸውን የከተማው ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ።

ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ ከሰዐት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የባለስልጣኑ የታክስ ህግ ማስከበር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ንጉሴ አከፋፋዮቹ የተያዙት አንድ ወር በተደረገ የክትትልና የኦፕሬሽን ስራ ትናንት ነው።
ኡራኤልና ሲግናል አካባቢ የሚገኙት አራቱ አከፋፋዮችም፦
- የአብስራ ሴራሚክስ- በአቶ ቢኒያም እሸቱ ስም የተመዘገበ
- ልዩ አጨራረስ- በአቶ አመርጋ ወ/ፃዲቅ ስም የተመዘገበ
- ሳባ ግራናይትና ሴራሚክስ- በወ/ሮ ሳባ ጥላሁን ስም የተመዘገበ እና
- ፎዚያ ሴራሚክስ- በአቶ እስማኤል ነስሩ ስም የተመዘገበ ናቸው።
ግብይቱን ሲፈፅሙ የነበሩ ሁለት ባለቤቶችና ስምንት የሽያጭ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለፁት አቶ ታምራት ጉዳዩ በህግ መያዙን ተናግረዋል።

በአከፋፋዮቹ ላይ በተደረጋ ፍተሻ ባለፉት ሁለት አመታት ከ3-7 ሚሊዮን አመታዊ የሽያጭ መጠን እንዳላቸው ተረጋግጧልም ተብሏል በመግለጫው።

ባለስልጣኑ የታክስ ህግ ማስከበር ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ታምራት የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የመስክ ቁጥጥር፣ የኦዲት ስራ እና የኢንተለጀንስና ኦፕሬሽን ስራዎች ተጠናክረው እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ያለደረሰኝ ግብይት መፈፀም በታክስ አስተዳድር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 109 መሠረት በአስተዳድራዊ ቅጣት ለፈእያንዳንዱ ደረሰኝ ላልተሰጠበት ግብይት 50ሺህ ብር የሚያስቀጣ ሲሆን ጉዳዩ በፍ/ቤት ወንጀል ሆኖ ሲረጋገጥ ከ25-50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮና ከ3-5 አመት የእስራት ቅጣት ያስቀጣል።

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ይሁኑ፦

@tikvahethiopia - በቴሌግራም

https://meda.im/join/tikvahethiopia1 - በሜዳ ቻት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #ጌታቸው_አሰፋን ጨምሮ በሌሉበት ጉዳያቸው እየታየ ያሉ አራት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገለግሎት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መጥሪያ ደርሷቸው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጠ። የፌዴራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በድጋሚ ትዕዛዝ የሰጠው ሚያዚያ 30 በተሰጠው ትዕዛዝ መጥርያው ከፍርድ ቤት ወጪ ባለመሆኑ ነው። አሁን ግን ፍርድ ቤቱ የፌደራል ፖሊስ መጥሪያውን ባሉበት እንዲያደርስ ጠቅላይ አቃቢ ህግም ጉዳዩን እንዲከታተል ትዕዛዝ ሰጥቷል። የዚህን ውጤት ለመጠባበቅና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ፍርድቤቱ ለግንቦት 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መስራች ጉባኤውን እያደረገ ነው፡፡ ከመስራች ጉባኤው አባል፣ ከአቶ ግርማ በቀለ እንደተሰማው ፓርቲው በዛሬው እለት ሙሉ በሙሉ ፕሮግራሙን አፅድቆ አመራሮቹን ይመረጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከቀናት በፊት ፓርቲዎቻቸውን በይፋ አፍርሰው በዛሬው እለት ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ፓርቲን እንመስርት ያሉት የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት፣ ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ፣ ቱሣ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የኦማ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረትና ደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ቅንጅት መሆናቸውንም አስቀድሞ ሲነገር ተሰምቷል።

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 41ኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባዔ አስፈጻሚው አካል የህዝቡን ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ያከናወናቸው ተግባራትን ይገመግማል። በተለይም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረው የህግ የበላይነት በማረጋገጥ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት ትኩረት እንደሚሰጣቸው ይጠበቃል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው #የዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጣሰው ገብሬ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆነው በዛሬው ዕለት ተመርጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሱዳን ሰልፈኞች የዘጓቸውን መንገዶች በ72 ሰዓታት ውስጥ ካልከፈቱ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማያደርግ የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ገለጸ፡፡ የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ኣዛዥ የሆኑት ጄኔራል አብዱልፈታ አልቡረሃን በሀገሪቱ ቴሌቭዥን በቀጥታ ስርጭት ባስተላለፉት መልዕክት የሰልፈኞች ቁጥር እየተበረከተ መምጣቱን ተከትሎ የሲቪል አገዛዝ ስርዓትን እየተጣሰ ነው ብለዋል፡፡ በተደረገዉ ሰልፍ እስካሁን 8 ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia