TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
13 ታጣቂዎች ተገደሉ...

አሜሪካ በሶማሊያ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 13 የአይ ኤስ ታጣቂዎች መግደሏን አስታወቀች። ታጣቂዎቹ ረቡዕ ምሽት በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸውን በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ (አፍሪኮም) አስታውቋል። ጥቃቱ የቡድኑ ታጣቂዎች በመሸጉበት የጎሊስ ተራራዎች አካባቢ የተፈጸመ መሆኑም ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ የንግድ ሥራ ዕድሎችን ለማስተዋወቅ ያለመ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። ውይይቱ በመጪው ግንቦት 7 እና 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ይካሔዳል። ውይይቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካን መዋዕለ-ንዋይ ፍሰትን ለማፋጠን እና ለኢትዮጵያ የምጣኔ-ሐብት እና የንግድ ለውጥ አስተዋፅዖ ለማበርከት ያለመ መሆኑን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በድረ-ገፁ ይፋ ያደረገው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የንግድ ሥራ መሪዎች፣ ባለወረቶች፣ ዋና ዋና የአሜሪካ ኩባንያዎች፣ በጎ አድራጊዎች እና የሁለቱን አገሮች የንግድ እና የመዋዕለንዋይ ግንኙነት የማጠናከር ውጥን ያላቸው ሰዎች ለሁለት ቀናት በሚካሔደው ውይይት ላይ ይገኛሉ።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ ዩኒቨርስቲ👆

"የመቱ ዩንቨርስቲ መምህራን በዩኒቨርሲቲው የተንሰራፋውን #የመልካም_አስተዳደር እጦት ይታወቅልን በማለት #ሰልፍ ወጥተዋል።"

√Save Mettu University
√ያለ ፕሬዘዳንት እስከ መቼ?
√የመቱ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ያነጋግሩን
√ፋይናስ አስተዳደር ለስራችን እንቅፋት መሆን አይገባም
√ለመምህራን ማህበር የሚገባው እውቅና ይሰጠው
√የትምህርት ቁሣቁሦች ይሟሉልን
√ወጥ የሆን የክፍያ አሰራር ይኑር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በማዕከላዊ ጎንድር ዞን በፀጥታው ዘርፍ የታዬውን የዘጠኝ ወር አፈጻጸም እና የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት የሚያስችል ግምገማ በጎንድር ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ነው። በሁሉም የፀጥታ አካለት የነበሩ የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ከቀረበ በኋላ የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል። በግምገማው ከወረዳ እስከ ዞን የሚገኙ የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሁለተኛው የአዲስ ወግ የባለሞያዎች የውይይት መድረክ እየቀረበ ነው። የሕግ የበላይነት በዴሞክራሲ የሽግግር ሂደት ወቅት በሚል ርዕስ በወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ በወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል፣ በዶ/ር ዳኛቸው አሰፋና በዶ/ር ጌታቸው አሰፋ አቅራቢነት እየተካሄደ ነው።

ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጥረት ኮርፖሬት የሀብት ምዝበራና ብክነት ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የቀድሞ አመራሮች አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ በቀጠሯቸው መሠረት ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ አቶ በረከት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲሰጡ አቶ ታደሰ ካሳ ግን ቃላቸውን ዛሬ ለመስጠት ባለመፈለጋቸው ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ ተከሳሾቹ ከዚህ ቀደም ክሱ ውድቅ እንዲደረግላቸው ያቀረቡት አቤቱታም ዛሬ ብይን ተሰጥቶታል፤ በብይኑም የክስ መቃዋሚያዎቹን ችሎቱ ውድቅ አድርጓቸዋል፡፡

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ በረከት ስምኦን በቀረቡባቸው ሁሉም ክሶች ጥፋተኛ አለመሆናቸውን እና ወንጀል አለመፈጸማቸውን ለፍርድ ቤት ተናግረዋል። በቀረቡባቸው ክሶች እና ተከሳሾቹ ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት የተሰየመው ችሎት ተከሳሾቹ ያቀረቧቸውን የክስ መቃወሚያዎች በሙሉ ውድቅ አድርጓል። ተከሳሾቹ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ፍርድ ቤቱ በጠየቀው መሰረት አቶ በረከት ስምዓን በሁሉም ወንጀሎች ጥፋተኛ አይደለሁም ብለዋል። ሁለተኛው ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ዝግጁ አለመሆናቸውን ገልጸው ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ የባህር ዳር እና አከባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አቶ ታደሰ ካሳ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠኝ ባሉት መሰረት ለግንቦት 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጤና ባለሙያዎች የቀረበው የደረጃ እድገት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የጤና ባለሙያዎች የደረጃ እድገትን በተመለከተ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲያነሱ መቆየታቸውን ሚኒስቴሩ በገጹ አስታውሷል፡፡ በዚህም ከ2009 ዓ.ም ደመወዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በፌደራል ሆስፒታሎች ወደ ጎን የነበረውን የደረጃ እድገት ከግንቦት 2011 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ላይ እንዲያድግ ተወስኗል፡፡ በተመሳሳይ በክልሎችም የደረጃ እድገቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንዲደረግ ለካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ከስምምነት መደረሱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia