TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተጠርጣሪዎች እየተያዙ ነው...

ፖሊስ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በቅርቡ የተከሰተውን ግጭት በማነሳሳትና ማባባስ የተጠረጠሩ 16 ሰዎችን ይዣለሁ ማለቱን ሸገር ዘግቧል፡፡ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እያካሄደ ነው፤ ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም ለመያዝ ጥረቱን ቀጥሏል፡፡ የቤንሻንጉል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በግጭቱ 21 ሰዎች እንደሞቱ ገልጧል፡፡ 54 ሰዎች ደሞ የተለያዩ ጉዳቶች ደርሶባቸዋል፡፡

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርሲ ነጌሌ👆

"ሰላም ፀግሽ #በአርሲ_ነጌሌ ከተማ ታላቅ እሩጫ እሁድ እለት የአርሲ ነጌሌ ልጆች ለአንድነት እንሩጥ በሚል መሪ ቃል በስኬት ተከናውኗል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን እና በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑ የቤጉህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ረጋሳ ገለጹ። በመተከል ዞን በተከሠተው ግጭት 51 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ በጃዊ ወረዳ ከደረሰው ጉዳት ጋር በተያያዘ ደግሞ 12 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
JiT👆

"ጅማ ዩንቨርሲቲ(JIT) ሙስሊም ተማሪዎች ረመዳን ጾም ስለሆነ ሌሊት ምግብ ልዘጋጅልን ይገባል በምል ሰልፍ ላይ ናቸው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ ክስ መመስረቱን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል በፌደራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪዎች ላይ፤ በማረሚያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች ላይ እንዲሁም በብሔራው መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ሲካሔድ የነበረው የወንጀል ምርመራ ሲካሔድ መቆየቱ ያስታወሰው ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፤ በዚሁ መሰረት ዓቃቤ ሕግ በወንጀል መርማሪዎች ላይ፤ በማረሚያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ላይ እንዲሁም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ክስ ተመስርቷ ብሏል፡፡

በመርማሪዎች ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከፈተው እና በማረሚያ ቤት ኃላፊዎች በነበሩት ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከፈቱት መዛግብት የከስ ሂደቱ ቀጥሎ ምስክር ለመስማት ተቀጥረዋል፡፡

በሶስተኛውና በዚህኛው የመጨረሻ መዝገብ ላይ 26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በጠቅላላው 46 ክሶች ተመስርቶባቸዋል፡፡

በክሶቹ ውስጥ 22ቱ ተከሳሾች በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በሌላ በኩል የቀድሞ የአገልግሎቱን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ አቶ አጽብሃ ግደይ፣ አቶ አሠፋ በላይ እና አቶ ሽሻይ ልዑል በተባሉ የቀድሞ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎች ላይ በሌሉበት ክስ ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2011 ዓ.ም በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልዴታ ምድብ ችሎት ይመሰረትባችዋል፡፡

በአቶ ጌታቸው ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ (ሀ) (ለ) እና 407/1/ (ለ) (ሐ) እና 407/3/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል መፈጸም እንዲሁም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 /1/ (ለ) እና (ሐ) እና 9/3/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

በሌሎቹ ሁሉም ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ (ሀ) (ለ) እና 407/1/ (ለ) (ሐ) እና 407/2/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል መፈጸም እንዲሁም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 /1/ (ለ) እና (ሐ) እና 9/2/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ሥልጣንን ያለአግባብ መገልገል ክስ ሊቀርብባቸው የቻለው ተከሳሾች በግልጽ ከተሰጣቸው ሥልጣን ወይም ኃላፊነት አሳልፈው በመስራት እንዲሁም ሥልጣናቸው ወይም ኃላፊነታቸው የማይፈቅድላቸውን በተለይም ሥልጣን ወይም ኃላፊነት ሳይኖራቸው በሌላ ሰው መብት ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማሰብ በተበዳዮች ላይ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈጸማቸው ነው፡፡

በአቶ ጌታቸው ላይ በንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ክስ ሊቀርብባቸው የቻለው፦

1ኛ) በሚኒስትር ማዕረግ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩ በመሆናቸው የኃላፊነት ወይም የሥልጣን ደረጃቸው ከፍተኛ በመሆኑ፤
2ኛ) ኃላፊነታቸውን የጣሱበት ዓላማ ከባድ በመሆኑ እንዲሁም

3ኛ) በሕዝቦች ወይም በተጎጂዎች ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድ በመሆኑ የተፈጸመውን ወንጀል ከባድ ሊያደርገው በመቻሉ ነው፡፡

ቀሪዎቹ ተከሳሾች በሙሉ በንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ክስ ሊቀርብባቸው የቻለው ከላይ ለአቶ ጌታቸው ወንጀል ከባድነት ከተጠቀሱት ምክንያቶች ውስጥ ቢያንስ አንዱ ተሟልቶ በመገኘቱ ነው፡፡

አቶ ጌታቸውን ጨምሮ በአራቱ ተከሳሾች ላይ በሌሉበት ክስ ሊመሰረት የቻለው ደግሞ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 42/1/ለ እና 161/2/ሀ መሰረት ተከሳሾች የቀረቡባቸው ክሶች ከባድ በመሆናቸው በህጉ መሰረት በሌሉበት ክስ ሊቀርብባቸው የሚገባ በመሆኑ ነው ተብሏል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በ67ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ለመሳተፍ ዛሬ (ሚያዝያ 29 ቀን 2011 ዓም)ጧት ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ተጉዘዋል። ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው 67ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ሰብሰባ በደቡብ ሱዳን ተደራዳሪ ወገኖች የተደረሰው ስምምነት አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዲላ...

"ጤና ይስጥለኝ ፀግሽ ሁሉ ሰላም ነዋ ኤርምያስ እባላለው ከዲላ ነው ማወራህ ዲላ ላይ የመብራት ችግር ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት መቷል የፋሲካን በዓል እንኳን ያለ መብራት ነው ያሳለፍነው ለተከታታይ 6 ቀናት መብራት አይኖርም ምክኒያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይደጋገማል በተለያየ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ የቀን ገቢ ያላቸው ሰዎች ስራቸውን መስራት አልቻሉም ዲላ ላይ የውሃ ችግርን አውርተን ሳንጨርስ መብራትንም ጨመሩብን ግራ ተጋብተናል ለስኳር መሰለፍ የለመደ እግር ጄነሬተር ያለበት ስልክ እኳን ቻርጅ ለማድረግ እየተሰለፈ ነው። መላ በሉን መብራት ሀይሎች!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዜግነት ፖለቲካና ማህበራዊ ፍትህን መሰረት አድርጎ በቅርብ የሚመሰረተው አዲስ ፓርቲ በባለፉት ስምንት ወራት ሲያደርገው የነበረውን ዝግጅት አጠናቀቀ፡፡ የሚመሰረተው አዲስ ፓርቲም ቀደም ሲል የነበሩ ሰባት ፓርቲዎችን በማዋሀድ የሚፈጠር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ የአዲስ ፓርቲ ዝግጅቱም ከዚህ በፊት የነበረውን የፓርቲዎችን መዋቅር ለማክሰም እንዲሁም በተለያዮ ጉዳዮች መግባባት እንዲደረስበት ለማድረግ የተካሄደ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ፓርቲው በባለፉት ስምንት ወራት ሲያደርግ የነበረውን የውህደት ስራ አጠናቆ በመጪው ሐሙስና አርብ የፓርቲ መስራች ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚያካሄድ አስታውቋል፡፡ በጉባዔውም 1 ሺህ 700 ከየወረዳው የተወጣጡ ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ ፓርቲው የዜግነት ፖለቲካ በአሁኑ ሰዓት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia