TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደባርቅ👆

በአምባሳደር በላይነሽ ዛባድያ የሚመራው የቤተ-እስራኤላውያን የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ልዑክ ደባርቅ ከተማ ገብቷል፤ የከተማዋ ነዋሪዎችና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ለልዑኩ ከፍተኛ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ መውሪል ቦውዘር ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተገናኝተው ተወያዩ። በውይይታቸውም ሁለቱ ዋና ከተሞች እህትማማችነታቸውን አጠናክረው በጋራ ስለሚሰሩበት ሁኔታ መግባባት ላይ ደርሰዋል። ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ከንቲባ መውሪል ቦውዘር የአዲስ አበባ ከተማን እንዲጎበኙ የጋበዙዋቸው ሲሆን: ከንቲባዋም ግብዣውን የተቀበሉት መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

Via Fitsum Arega
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አስክሬን እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደሀገር ቤት እንደሚገባ ተሰምቷል። የቀብር ስነ ስርዓታቸው መቼ እንደሚፈፀም የታወቀ ነገር የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም ደርሰዋል!

#ከሀዋሳ_ከተማ የተነሱት #የሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት አዲስ አበባ ከተማ/መስቀል አደባባይ/ በሰላም ደርሰዋል።

ኑ ፍቅርን እንዝራ!
ኑ ፍቅርን እንስበክ!
ኑ ፍቅርን እናቀንቅን!
#StopHateSpeech

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም ደርሰዋል!

#ከወልቂጤ የተነሱት #የወልቂጤ_ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት አዲስ አበባ ከተማ/መስቀል አደባባይ/ በሰላም ደርሰዋል።

ኑ ፍቅርን እንዝራ!
ኑ ፍቅርን እንስበክ!
ኑ ፍቅርን እናቀንቅን!
#StopHateSpeech

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም ደርሰዋል!

#ከአርባምንጭ እና ከሶዶ የተነሱት #የአርባምንጭ_ዩኒቨርሲቲ እና የወላይታ_ሶዶ_ዩንቨርስቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት አዲስ አበባ ከተማ/መስቀል አደባባይ/ በሰላም ደርሰዋል።

ኑ ፍቅርን እንዝራ!
ኑ ፍቅርን እንስበክ!
ኑ ፍቅርን እናቀንቅን!
#StopHateSpeech

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ ቴሌኮም ሃብቱን በውጭ ኩባንያ እያስመረመረ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ መርማሪው የእንግሊዙ ፕራይስ ወተር ሃውስ ኩፐር የተባለው ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ካሁን በፊት የኢትዮ ቴሌኮምን የፋይናንስ አስተዳደርና የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት አደራጅቷል፡፡ ጥናቱ እስከ 6 ወራት ሊፈጅ ይችላል፡፡ የሃብት ግምቱ ሲጠናቀቅ ዲሊዮት የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያና ኧርነስት ኤንድ ያንግ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ደሞ ኢትዮ ቴሌኮም በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ባለሃብቶች ሲዘዋወር የአክሲዮን አወቃቀርና ሽያጭን በተመለከተ እንዲያማክሩ ተቀጥረዋል፡፡ የአማካሪ ኩባንዎችን ወጭ ዐለም ባንክና ለጋሽ ሀገራት ይሸፍናሉ፡፡ አጠቃላይ ሂደቱ የሚመራበት ረቂቅ ሕግ ገና በፓርላማ አልጸደቀም፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia