TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዳማ👆

የኦሮሚያ እና የሱማሌ ክልል ህዝቦች #በሰላምና #በፍቅር አብረው ለመኖርና ለመስራት ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚመክር የህዝብ ለህዝብ መድረክ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመተከል...

"ፀግሽ እባክህን አሁንም #የመተከል ነገር በጣም አሳሳቢ ነው #ማንቡክ ከተማ ያሉት በጭንቀት ነው የሚመለከተው አካል ይመልከተው እባክህ በአሁኑ ሰአት ሰው ፈርቶ ነው ያለው!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው...

በዳንጉር ወረዳ እንዲሁም ጃዊ አካባቢዎች አሁንም የፀጥታ መደፈረስ እንዳለ በአካባቢው የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። በአካባቢዎቹ የሚስተዋለው የፀጥታ መደፍረስ #ልዩ_ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባና ጉዳት ከደረሰ በኃላ ለማረጋጋት ከመሯሯጥ ቅድሚያ የመከላከል ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ወንጀለኞችም በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር #ዐብይ_አህመድ (ዶ/ር) ጋር በሸራተን አዲስ እየተወያየ ነው፡፡

#etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንሰማለን ወይ

የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በመላው ሀገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች በሚባል ደረጃ ይገኛሉ። የቤተሰቡ አባላትም ከሁሉም ብሄር እና ሀይማኖት የተውጣጡ ናቸው። ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያን ለመገንባትም ትልቅ መስዕዋትነት እየከፈሉ ያሉ ሀገር ወዳድ ወጣቶችንም በውስጡ ያቀፈ ነው። TIKVAH-ETH በሚሰራው ስራ ሁሉ ማንም አካልና ድጋፍ አያደርግለትም፤ ከትኛውም መንግስት አካል ድጋፍ የለውም እንዲሁም አይታገዝም። ሁሉም ስራ የሚሰራው በቤተሰቡ ጠንካራ ድጋፍ ነው።

ጥያቄያችን...

በዚህ ቻናል ውስጥ በርካታ ሰዎች አለን፤ በመንግስት ተቋማት ህዝብ የምናገለግል ሰዎች አለን፤ በስልጣን ላይ የምንገኝም አንጠፋም ለምን የህዝብ ጥቆማ አይሰማም??

ከዚህ በፊት፦ ቡራዩ እና አከባቢው ችግር ሲፈጠር የቤተሰባችን አባላት ስጋታቸውን ሲገልፁ ነበር። "Alert" እያልን ስንጮህ ነበር። የፖሊስ ስልኮችም ስንለጥፍ ነበር። ነገር ግን ሼር ያደረገው እና ለጉዳዩ ምላሽ የሰጠውም አልነበረም። ከ2 ቀን በኃላ ግን ፌስቡክን በሙሉ ጥቁር አለበስነው።

በተመሳሳይ፦ ከቀናት በፊት በቤንሻንጉል #መተከል ችግር እንዳለ ዜጎቻችን ህይወታቸው አደጋ ላይ እንዳለ ሲነግሩን እኛም #በAlert አሳውቀን ነበር። ነገር ግን ከ1 ቀን በኃላ ሆኖ የሰማነው የሰዎችን ህልፈት ነው። የሰላም መደፍረስን ነው።
.
.
ሁሉንም ባይሆን ለሚሰጡት ጥቆማዎች ፈጣን ምላሽ የምትሰጡ አካላትን በዚህ አጋጣሚ ሳናመሰግን አናልፍም።

አሁንም የቤተሰባችን አባላት ስቃያችሁን፣ ስጋታችሁን የሚደርስባችሁን ሁሉ እርስ በእርስ እንጋራዋለን!!

በኢትዮጵያ ተስፋ እንቆርጥም!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን የቀብር ስነ ስርዓት የሚያስፈፅም ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል። የብሄራዊ ኮሚቴው ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከመከላከያ ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከቤተሰቦቻቸው በመውጣጣት የተዋቀረ መሆኑም ተነግሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያና በሱማሌ ክልል የህዝብ ለህዝብ መድረክ ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• የኦሮሞና የሱማሌ ህዝብ ከአንድ ግንድ የተገኘና በአንድነት የኖረ ህዝብ ነው፡፡

• ሁለቱን ህዝቦች ከሚለያዩአቸው ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጓቸው ይበዛሉ፡፡

• የኦሮሞና የሱማሌ ህዝብ ተመሳሳይ ባህል፣ ቋንቋና ማንነትን የሚጋሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

• ሁለቱ ህዝቦች ለነፃነት እና ለእኩልነት ታግለዋል፣ ለዚህም ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡

• የኦሮሞና የሱማሌ አንድነት መጠናከር ወሳኝ ነው፡፡ የሁለቱ ህዝቦች ወንድማማችነት መጠናከር ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ አንድነትም ወሳኝ ነው፡፡

• አፈናቃዮች፣ ገዳዮች፣ ኮንትሮባንድስቶችና ሌቦች የሁለቱን ህዝቦች አንድነት ሊንዱት አይችሉም፡፡

• መድረኩን ሲያዩ የሚደሰቱ በርካቶች እንዳሉ ሁሉ ሌሎች ደግሞ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው የቀረውን ነገር ለመሞከር ይታትራሉ፡፡

• ክልሎች ጎረቤት አገራት አይደሉም፣ ክልሎች የኢትዮጵያ አካል ናቸውና በክልሎች መካከል አንድነት እንዲጠናከርና አብረው እንዲሻገሩ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

• ኦሮሞነት ሁሉን እንደ ራስ ማየት ነው፣ ለሌላው ከራስ በላይ ክብር መስጠት ነው፣ ሌለውን ማቀፍ ነው፡፡

• የኢትዮጵያ ቱባ ባህሎች በአፈናቃዮች ሴራ ሊደበዝዙ አይገባም፡፡

• አገራችን ለሁላችንም በቂ ስለሆነች የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከር ሌት ቀን ተግተን መስራት ይጠበቅብናል፡፡

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሱማሌ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ ኡመር በኦሮሚያና በሱማሌ ክልል የህዝብ ለህዝብ መድረክ ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• አንድነት ኃይል ነው

• የኦሮሚያና የሱማሌ ህዝቦች ከአንድ ግንድ የፈለሱ ናቸው፤ ለረዥም ዘመናት አብረው ሲደጋገፉ የነበሩ ህዝቦች ናቸው

• ሁለቱ ህዝቦች የትግል ትስስር ፈጥረው ይደርስባቸው የነበረውን ጭቆና በጋራ ተጋፍጠዋል፤ ቋንቋቸውንና ባህላቸውን ለማሳደግ በጋራ ታግለዋል

• ኦሮሚያ የሱማሌው መኖሪያ ነች

• ሁለቱ ህዝቦች ከአሁን በኋላም የሚያጋጫቸዉን የጥፋት ኃይል በጋራ ይታገላሉ

• የአሁኑ ትዉልድም ይህን ዕድል ተጠቅሞ የኢኮኖሚ ብልጽግና ለማምጣትና አገሪቱን ለማሸጋገር መስራት ይጠበቅበታል

• በሁለቱ ህዝቦች መካከል የነበረዉን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የጋራ ወሰናቸውን ክፍት በማድረግ የንግድ ስራዉ እንዲቀጥል ማድረግ ይጠበቅብናል

• የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት የሚያጠናክሩ የጋራ ፕሮጀክቶችን ቀርጸን መስራት አለብን

• በየዓመቱ ህዝቦች የሚገናኙበትንና አንድነታቸዉን የሚያጠናክሩበትን የባህል ልዉዉጥ መድረክ መፍጠር አለብን፤ ለዚህም ዛሬ የመሰረት ድንጋይ እንጥላለን

• ከዚህ በፊት የተፈጠረዉን ግጭት የሁለቱ ህዝቦች ግጭት አድርጎ ማቅረብ ስህተት ነዉ፤ የነበረዉ ግጭት ሁለቱንም ህዝቦች የሚወክል አይደለም

• ለተፈጠረዉ ጦርነትና ግጭት የሱማሌ ልዩ ኃይል ተጠያቂ ነዉ

• በሂደቱ የተፈናቀሉ የኦሮሞ ህዝቦችን በሱማሌ ህዝብ ስም ይቅርታ እንጠይቃለን፤ በኦሮሚያ ክልል የነበረዉ የሱማሌ ህዝብም መፈናቀል አልነበረበትም

• የተፈናቀሉ የኦሮሞ ወንድሞች ተመልሰዉ ኑሯቸውንና ስራቸዉን እንዲጀምሩ እንሰራለን፣ እንደግፋለን

• የፖለቲካ አሻጥር ከሌለ ሁለቱን ህዝቦች ለግጭት የሚጋብዝ ነገር አይኖርም

#etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) በቅርቡ በሱማሊኛ ቋንቋ ስርጭት የሚጀምር መሆኑ ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀው በኣዳማ እየተካሄደ ባለው የኦሮሚያና የሱማሌ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ላይ ነው፡፡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት የሁለቱን ክልሎች ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) በቅርቡ በሱማሊኛ ቋንቋ ስርጭት ይጀምራል ብለዋል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia