TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በትልቅነቱ በታሪክ ሁለተኛ የሆነ ያልተቆራረጠ ዳይመንድ በቦትስዋና መገኘቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ የተገኘው ዳይመንድ ባለ1758 ካራት መሆኑና መጠኑም የቴኒስ ኳስ እንደሚያህል ተነግሯል፡፡ እኤአ በ1905 በደቡብ አፍሪካ የተገኘው ባለ3106 ካራት ዳይመድ በትልቅነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ እስካሁን ዘልቋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግጭቱ እየተረጋጋ ይገኛል...

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አይሲካ ቀበሌ እና ማንቡክ ከተማ የተከሰተው ግጭት እየተረጋጋ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመቐለ...🔝

"የዋልታ ፖሊስ ትግራይ ተጫዋች የ27 አመቱ #አማኒኤል_ብርሃነ ስርዓተ-ቀብር በመቐለ ማርያም ቤተ-ክርስትያን(እንዳ ማርያም) እየተፈፀመ ይገኛል።"

Via Eyo (በመቀለ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስመጪዎች እና ማናጀሮች

በተለያዩ ከተሞች የሚስተዋለው የውጭ ሀገራት ገንዘብ ህገወጥ ምንዛሬ በትላልቅ አስመጪዎች እና በባንክ ማናጀሮች ዋነኛ ተዋናይነት የሚመራ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገለጸ።

በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናንስ ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በህገወጥ የውጭ አገራት ገንዘብ ምንዛሬ ዋነኛ ተዋናዮች አስመጪዎች፣ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች በተለይም የባንክ ማናጀሮች ናቸው።

በየአካባቢው የሚገኙት ዶላር መንዛሬዎች ግን ሶስተኛ ወይንም አራተኛ አካላት ናቸው። እንደ ኮማንደር ታደሰ ገለጻ፣ በየአካባቢው የሚገኙት ዶላር መንዛሬዎች ዋነኛ የህገወጥ ተግባሩ ተዋናዮችን በውል የማያውቁ እና ለእነርሱ የሚሰሩ ናቸው።

ህገወጥ ተግባሩ በተዋረድ (በኔትወርክ) የሚከናወን እና በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያላቸው አስመጪዎች የሚያንቀሳቅሱት ነው። በተጨማሪ የባንክ #ማናጀሮች ዶላር ፈልጎ የመጣን ባለሀብት ቢሮክራሲ በማብዛት ዶላር እንደሌለ አስመስለው ያባርራሉ። በጎን ደግሞ ደላሎችን ልከው ወደ ህገወጥ መንገድ እንዲሄዱ በማመቻቸት ገንዘብ ተቀብለው ይሰጧቸዋል።

ኮማንደር ታደሰ እንደተናገሩት፤ በአንድ የአሜሪካን #ዶላር ከ10 ብር እስከ አስራ አራት ብር ትርፍ በመውሰድም #ከደላሎች እና በየደረጃው ካሉ ህገወጦች ጋር ይከፋፈላሉ። በተለይ በሶማሌ ክልል #ቶጎ_ውጫሌ የሚገሹ 16ቱም ባንኮች በህገወጥ የዶላር ምንዛሬ ውስጥ እንደሚሳተፉ መረጃ አለ። በሶማሌ ላንድ ጠረፍ ከተማዋ የሚገኙ እና በተለያዩ ከተሞች የሚሰሩ የባንክ ማናጀሮች በዚህ ህገወጥ ተግባር እንደሚሳተፉ የፌዴራል ፖሊስ መረጃው አለው። በሌላ በኩል በህገወጥ መንገድ ከአገር የዘረፉትን ገንዘብ በህጋዊ መንገድ ለማንቀሳቀስ የሚፈልጉ ሰዎች ሀብታቸውን ወደ ዶላር መንዝረው ከአገር ለማስወጣት ይጠቀሙበታል።

በዚህ ዓመት በመርካቶ እንደተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ አሁንም በቀጣይ እንደሚደረግ የገለጹት ኮማንደር ታደሰ፤ ይሁንና ዋነኞቹ የምንዛሬው ተዋናዮችን ለመያዝ መረጃ ሳይሆን ማስረጃ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ ለዚህ ደግሞ ህብረተሰቡ ተሳታፊ መሆን አለበት። ህብረተሰቡ ደግሞ መረጃ ቢያቀብልም መስካሪ ሆኖ የችግሩን አመንጪዎች ለመከላከል ፍላጎት አያሳይም። ፖሊስ ግን ገንዘብ የያዘን ሁሉ አስሮ መቅጣት ስለማይችል የህብረተሰቡ የማጋለጥ እና የመመስከር ልምድ መጠናከር አለበት። ፌዴራል ፖሊስም ማስረጃ ባጠናቀረ ወቅት ህገወጦችን ለመቅጣት የሚያስችል ስራ ማከናወኑ አይቀርም ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በጀርመን ሀገር ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተነግሯል።

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ርእስ ብሄር በመሆን በ1987 የተሾሙ ሲሆን፥ ለ7 ዓመታትም አገልግለዋል።

በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ላይ በደንቢ ዶሎ የግል ተወዳዳሪ በመሆን ፓርላማ መግባታቸውም ይታወሳል።

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከወጣትናቸው እድሜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲዘረጋ ሲደረግ በነበረው ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ነበራቸው።

ለዚህም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመሰለፍም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል።

በታሪክ ትምህረት ሶስተኛ ወይም ዶክትሬት ዲግሪያቸውን የያዙት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፥ እንደ ምሁርነታቸው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራትም የተለያዩ ግልጋሎቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል።

በተማሩት ትምህርትም የኦሮሞን ባህል፣ ታሪክ እና እሴት የሚያንፀባርቁ እና የኢትዮጵያን አንድነት የሚያጠናክሩ የተለያዩ ጥናቶችን አካሂደዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና እረፍት🔝

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ነጋሶ_ጊዳዳ በ75 አመታቸው ከዚህ አለም #በሞት ተለዩ። ዶ/ር ነጋሶ ለ7 አመታት ያህል ኢትዮጵያን በፕሬዚደንትነት አገልግለዋል። ነብስ ይማር!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ገልፀዋል። የቀብር ሥነ ሥርዓትን በተመለከተ ብሔራዊ ኮሚቴ የሚቋቋም ሲሆን፥ ዝርዝር ጉዳዮችን በየጊዜዉ የሚገለጽ ይሆናል መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በጀርመን ሀገር ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥዋት 4 ሠዓት ነው ያረፉት...

የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጀርመን ፍራንክፉርት ከተማ ውስጥ ከሐሙስ ጀምሮ ሲታከሙ ቆይተው ዛሬ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ጠዋት 4 ሰአት ላይ ዛክሰን ሐውስ ሆስፒታል ውስጥ አርፈዋል። ፍራንክፉርት ኡኒቨርሲቴት ክሊንኒክ ውስጥ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ሲታከሙ የቆዩት ዶ/ርነጋሶ ጊዳዳ ያረፉት በ76 ዓመታቸው ነው።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር #አሚር_አማን...

"ከሁሉም የጤና ባለሙያዎች፥ ከሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፥ ከክልል መንግስታትና ከሙያ ማህበራትና ጋር በመሆን በኢንተርን ሃኪሞች በተነሱ ጥያቄዎችና ከጤና ባለሙያዎች የሚነሱ ጥያቄዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የመወያያ መድረኮች ተዘጋጅተዋል። ይህ በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ በቅርብ በየደረጃው ላሉ የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ክፍት ይሆናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት...‼️

በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው ግድያ፣ አፈና እና የንብረት ጉዳት የማይቆም ከሆነ ስራ #ለማቆም እንደሚገደዱ የኢትዮዽያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር አስታወቀ።በኢትዮ-ጅቡቲ መስመር እና በሀረርና ድሬደዋ አካባቢዎች ባሽከርካሪዎች ላይ የሚደርስ እንግልት በተለይ የከፋ መሆኑ ተገልጿል።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአሽከርካሪዎች...

"ደንገጎ ላይ 5 መኪና መደዳ ነው የተሰበሩት፤ ዋልታ ቲቪ ዘገባ ሰርቶበታል ሰኞ ዕለት ነው እነሡ ዘገባ ሰርተው #በንጋታው አንድ ሹፌር #እጁን ሌላኛው #አፍንጫው ተሰብሮ ሆስፒታል የገበቱት።"

#ትኩረት_ለአሽከርካሪዎች!

Via ዳ(TIKVAH-ETHIOPIA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia