TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Breaking ባለቤትነቱ የትራንስፖርት ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በመብረር ላይ ሳለ ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ #መከስከሱ ታውቋል።

Via #reporter
ፎቶ-የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚድሮክ ሄሊኮፕተር ተከሰከሰ‼️

ባለቤትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በመብረር ላይ ሳለ ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ መከስከሱ ታወቀ፡፡ በበረራው ላይ የነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳልደረሰም ከምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ በሚድሮክ ቴክኖሌጂ ግሩፕ ሥር የሚተዳደር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የግል አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት የዚሁ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር በቦሌ አካባቢ መከስከሱ ይታወሳል፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ተከፍሏል"የደም ልገሳ

ኑ ደማችንን በመለገስ ሕይወት እናትርፍ‼️
ቀን: ዛሬ
ሰዓት: ከጠዋቱ 3:00 - 10:30
ቦታ: ስታዲየም ከሴቶችና ህፀናት ጉዳዮች ሚኒስቴር ቢሮ ፊት ለፊት ባለው አንበሳ ባስ ማቆሚያ ቦታ::

እናመሰግናለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሂሊኮፕተር አደጋው...

√ሄሊኮፕተሩ አምስት መንገዶኞችን እና ሁለት አብራሪዎችን ይዞ ነበር።

√በአደጋው በመንገደኞችም ሆነ በአብራሪዎች ላይ #የከፋ ጉዳት እልደረሰም።

√የአደጋው ምክንያት እና አጠቃላይ በአደጋው የደረሰው ጉዳት እየተጠራ ይገኛል።


Via #fbc/የኢትዮጵያ ሲቭል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ለስቅለት እና ለትንሳኤ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡፡

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ እንኳን ለስቅለት እና ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ !!

የስቅለት እና የፋሲካ በዓል የመስዋዕትነት፣የይቅርታ ፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ በአጠቃላይ ውብ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን ይበልጥ ከሚያጎሉና ከሚያደምቁ በዓላት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ስለሆነም በሕዝብ አገልግሎት ላይ የተሰማራን እኛ አገልጋዮች በተለይ የስቅለትን እና ትንሳኤን ትርጉም ጥቂቱን እንኳን ብንከውን ለህዝባችን ችግር ከመድረስ ባለፈ ለሀገራችን አይደለም ለአለምም እንተርፋለን።

ንፁህ ሆነን እንደተፈጠርነው ሁሉ በንፅህናና በቅንነት መኖር እና ህዝባችንን ከልብ ማገልገል ይጠበቅብናል።

የበዓላቱን ጥልቅ ተምሳሌትነቶች በእለት ተለት ህይወታችን ተግባራዊ በማድረግም በአምላክ አርአያ የተፈጠሩትን ወገኖቻችንን በማገልገልና ለችግሮቻቸው በመድረስ መንፈሳዊም ሆነ ሀገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ አደራ እላችኃለሁ፡፡

እናም ሁላችንም የህዝብ አገልጋዮች በተሰማራንበት መስክ ሃላፊነታችንን በትክክል በመወጣት መጨውን ጊዜያችንን ብሩህ እንድናደርግ ወንድማዊ የአክብሮት ጥሪዬን እያቀረብኩ መልካም የስቅለት እና የትንሳኤ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ።

አምላክ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

መልካም አውዳ ዓመት !!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ዋልታ ፖሊስ ትግራይ የእግር ኳስ ክለብ ዛሬ ጠዋት ባልታወቁ #ታጣቂዎች ጥቃት እንደደረሰበት ለማወቅ ተችሏል። በአንደኛ ሊግ ተሳታፊ የሆነው ዋልታ ፖሊስ ትግራይ ከሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ጋር ጨዋታ አድርጎ ወደ #መቐለ ሲመለስ በጉዞ ላይ እያለ ነበር በአፋር ክልል #ገዋኔ አካባቢ ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት የደረሰባቸው። እስካሁን ባለሁ ሁኔታም በአንድ የቡድኑ አባል ላይ #የሞት አደጋ መድረሱ ሲረጋገጥ በስምንት የቡድኑ አባላት ላይም ከበድ ያለ ጉዳት መድረሱን የቡድኑ መሪ ለትግራይ ቴሌቪዥን ገልፀዋል። በኮንስታብል ዮሃንስ ሲሳይ የሚመራው ዋልታ ፖሊስ በ1960ዎቹ የተመሰረተ አንጋፋ ክለብ ሲሆን በጥቃቱ ዙርያ እስካሁን የተሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።

Via ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ በተፈፀመው ጥቃት ሀዘኑን በመግለፅ ድርጊቱን አወግዟል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ👆ዛሬ ጥዋት የተከሰከሰው ሂሊኮፕተር የወደቀው በመኖሪያ ቤት ላይ ሲሆን፤ የተከሰከሰበት ምክንያትም የሞተር መጥፋት እንደሆነ ነው የታወቀው።

#reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia