TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#StopHateSpeech-----አባያ ካምፓስ👆

#በአባያ_ካምፓስ----አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከTIKVAH-EHT ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 2ኛው #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ #ዝግጅት በዛሬው ዕለት በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

እናመሰግናለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እርምጃ ተወሰደባቸው...🔝

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት አጀንሲ የትምህርት ጥራት ችግር ያለባቸውን ከፍተኛ የግል የትምህርት ተቋማት ላይ #እርምጃ ወሰደ፡፡

አጄንሲው በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ድንገተኛ ጉብኝት በማድረግ የህግ ጥሰት ፈፅመዋል ባላቸው ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሱዱን አስታውቋል፡፡

አጄንሲው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት አጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 650/2011 እና በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 261/2004 ያለዉን ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት በማድረግ ከላይ በተገለፁት የግል ከፍተኛ ተቋማማት ላይ ከእገዳ እስከ ፅሁፍ ቅጣት ማስተላለፉን ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከወር በፊት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር #ለተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ተጓዥ ለነበሩ እና ሕይወታቸው ላለፉ ሰዎች የ40 ቀን ማስታወሻ በጋራ ተከናወነ። የዝክር ስነ-ሥርዓቱ፦የሟቾች ቤተሰቦች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት፣ የቢሾፍቱ ወጣቶች እና የቱሉ ፈርዳ ወረዳ የሃማ ቁንጡሽሌ ቀበሌ ነዋሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የእምነት አባቶች በተገኙበት ጧፍ በማብራት እና በጸሎት ተከናውኗል። አደጋው በደረሰበት የሃማ ቁንጥሽሌ አከባቢ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መታሠቢያ እንዲሠራ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል። በዕለቱም 2500 የሚሆኑ #የቢሾፍቱ ወጣቶች በአደጋው ስፍራ #ደም ለግሰዋል።

Via DW
ፎቶ፦ TIKVAH-ETHIOPIA(DakStar)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቢሾፍቱ🔝

"ሰላም ፀግሽ....የቢሾፍቱ ከተማ ወጣቶች ማህበር ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው boing 737 max8 አውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች 40ኛ ቀን መታሰቢያ በሚያስደንቅ መልኩ በተለያዩ ስነስርዓቶች አክብረው ውለዋል። ወጣቶቹ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር የሚያስመሰግን ስራ ሰርተዋልና #ሊመሰገኑ ይገባል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ...🔝

"ፀግሽ በአሁኑ ሰዓት በጎፋ ዛን ከመኖርያ ስፍራዎች ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ድጋፍ ለማድረግ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች እና አባቶች በጋራ በመሆን ወደጰስፍራው እያቀናን እንገኛለን። በዚህ አጋጣሚ የአርባምንጭ ከተማን ነዋሪ አመስግንልን!!" #ፋሪስ ነኝ!

#ኢትዮጵያዊነትን ከመናገር በዘለለ #በተግባር ያገረጋገቹ የአርባምንጭ ከተማ እና አካባቢዋ ማህበረሰብ ላደረጋቹት መልካም ተግባር በፈጣሪ ስም እናመሰግናለን!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia