TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በትላንትናው እለት በአርሲ ዩኒቨርስቲ የመጨረሻ አመት የህክምና ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ጤና ሚንስቴር በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ተናገሩ፡፡ በዛሬው እለትም ከከፍተኛ ትምህርትና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ሃኪሞች ማህበር የተውጣጣ ቡድን ስለጉዳዩ ለማጣራትና ለመወያያት ወደ ስፍራው በማምራት ላይ ይገኛል ተብሏል።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጋምቤላ ክልል ሲዘዋወር የነበረ በድምሩ 50 ክላሽንኮቭ መሳርያ መያዙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በጋምቤላ ክልል በመኩሽ ወረዳና በሌሎችም አካባቢዎች ሲዘዋወር የነበረ በድምሩ 50 ክላሽንኮቭ መያዙን የክልሉ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ቱት ኮር ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ በህዝቡ ጥቆማ መሰረት ሌሊት 8 ሰዓት በተደረገው ክትትል 35 ጦር መሳሪያ የተያዘ ሲሆን የተቀረው 15 የጦር መሳሪያም ቀን በባጃጅ ሲዘዋወር መያዙ ነው የተገለጸው፡፡ እንደ ኢቢሲ ዘገባ የጦር መሳሪያውን ቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው ሂደት በአንድ የፖሊስ አባል ላይ የመቁሰል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትናንት ምሽት 2፡00 #አዋሽ_ኬላ 3910 የክላሽ ጥይት በጉምሩክ የፍተሻ ሰራተኞች ተያዘ። መነሻውን ከሀረር መስመር ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-47593 ኦሮ የሆነ ሚኒባስ ተሸካርካሪ የአዋሽ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሰራተኞች ባደረጉት ፍተሻ የክላሽ ጥይቱ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡ ጥይቶቹ የተያዙት በተሽከርካሪው ላይ በተሰራለት ድብቅ ቦታ ሲሆን የጉምሩክ ተቆጣጣሪዎቹ ያላቸውን ልምድ እና ብቃት በመጠቀም በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት ከሚሌ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በወቅቱ ማሜ ሻሚ አህመድ የተባለ አሽከርካሪ እጁ ሊኖርበት ይችላል በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ሚያዝያ 8/2011 ዓ.ም በተመሳሳይ መስመር አልበርከቴ ኬላ ላይ ብዛቱ 5947 የሆነ የክላሽ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉ የሚታወስ ነው፡፡

Via የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትላንት በአርሲ ዩንቨርስቲ በተማሪዎች እና በፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጥሮ ተማሪዎች ተጎድተዋል። የዩኒቨርሲቲው #ፕሬዘዳንት ስለተፈጠረው ሁኔታ ለሸገር ራድዮ ተናግረዋል። ከላይ ያዳምጡ👆
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት በአርባምንጭ ዩንቨርስቲ አባያ ካምፓስ ለሚካሄደው ዝግጅት የTIKVAH-ETH አባላት በተማሪዎች ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ውይይት አካሂደዋል። #StopHateSpeech

Via @tikvahethamu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Hana Hailu
የጥላቻም ንግግር ይቁም!
ራሳችንን ከጥላቻ ንግግር በመቆጠብ ሀገራችንን እንታደግ!
የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ቲክቫህ ኢትዮጲያ ሁላችሁንም በክብር ይጋብዛል!
@hanahailu
#update ጨፌ ኦሮሚያ አስቸኳይ ስብሰባውን በዛሬው እለት በማካሄድ ላይ ይገኛል። ጨፌው በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው አራተኛ አስቸኳይ ስብሰባው አዲስ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።

#fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ማን ይሆንከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ይታወቃል። #ጨፌ_ኦሮሚያ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሁነው ተሾሙ፡፡ ጨፌ ኦሮሚያ ዘሬ ከሰአት ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው አቶ ሽመልስ አብዲሳን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አድርጎ የሾመው፡፡ አቶ ሽመልስ በጨፌው ፊት ቆመው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል፡፡ በምክትል ርእሰ መስተዳድርነት የተሾሙት አቶ ሽመልስ የርእሰ መስተዳድርነት ስራውን ጨምረው እንደሚሰሩ ተነግሯል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking አቶ አዲሱ አረጋ የኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሁነው ተሾሙ። አቶ አዲሱ የኦዲፒ ፅህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩትን ዶክተር አለሙ ስሜን ተክተው ነው የተሾሙት፡፡ አቶ አዲሱ አረጋ ከዚህ ቀደም የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነበሩ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia