TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው እሳት ሙሉ ለሙሉ #መጥፋቱን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ያስታወቀ ሲሆን፣ በፓርኩ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ እስካሁን 700 ሄክታር የሚሆነው መሬት ላይ #ጉዳት ማድረሱን ገልጿል።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #የአድዋ ድልን የሚዘክር ማዕከል ሊገነባ ነው፡፡ #Adwa

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አድዋ ድል ነው።
አድዋ ታሪክ ነው።
አድዋ ፍልስፍና ነው።
አድዋ ትናንት ነው።
አድዋ ዛሬ ነው።
አድዋ ነገ ነው።
አድዋ ስለቅድመ አያቶቻችን ነው።
አድዋ ስለእኛ ነው።
አድዋ ስለልጆቻችን ነው።

ከአድዋ በላይ #ኢትዮጵያዊያንን አንድ የሚያደርግ ክስተት የለም፡፡ በመሆኑም የአድዋን ዙሪያ ገብ ሃሳብ ለመጨበጥ፣ ለማስተማር፣ ለማስፋት፣ በፅኑ ዘላቂ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ቋሚ መዘክር ያስፈልገናል።

ይህ መዘክር በአገራችን እምብርት፣ የርቀትም የስልጣኔም መነሻ ፣ የሁሉም የሃገራችን ከተሞች ርቀት መጀመሪያ (ዜሮ ኪሎሜትር) በሆነው አራዳ ላይ መወጠኑ ተምሳሌትነቱን ላቅ ያለ ያደርገዋል።" ኢ/ር ታከለ ኡማ-የአድዋ ማዕከልን ለማቋቋም በተደረገ ምክረ-ሃሳብ ላይ የተናገሩት፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሽኝት ተደረገላቸው...

በሰሜን ተራሮች ፓርክ ተከስቶ የነበረውን እሳት #ለማጥፋት ለመጡት #የእስራኤል የእሳት አደጋ መከላከል ቡድን እና #ለኬንያዊው አብራሪ ሽኝት ተደረገ። ሽኝቱን የሰሜን ጎንደር ከአካባቢው ባለሀብቶች ጋር በመሆን ሲሆን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ለእሳት መከላከል ቡድኑ ለአብራሪው እንዲሁም እሳቱን ለማጥፋት ለተረባረበው ህብረተሰብ #ምስጋና አቅርበዋል።

Via Debark wereda communication
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ ሀዘናችን ጥልቅ መሆኑን እንገልፃለን!

በሀገራችን #ወጣቶች ህልፈት የተሰማን #ሀዘን ጥልቅ ነው። ልባችን ደምቷል!! ለቤተሰቦቻቸው፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የሀገራችን ህዝብ መፅናናትን እንመኛል።

ነብስ ይማር!!
#ቀይ_ባህር ወንድም እህቶቻችንን በላብን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia