TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ልጅ እና አማካሪ ኢቫንካ ትራምፕ ጋር ተወያይተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ከተፈጸሙ የሙስና ወንጀሎች ጋር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ነው የቀረቡት። 20 ተጠርጣሪዎችም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የሱዳን ሪፐብሊክ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት አባል በሆኑት በጄነራል ጋላሌዲን አል ሼኽ ከተመራው የልኡካን ቡድን ጋር ዛሬ ሚያዝያ 7 2011 ተወያዩ። ጄነራል ጋላሌዲን ለጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በሱዳን ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ ያስረዱ ሲሆን ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት ስልታዊ እንደሆነ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ለሱዳን የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው መንግሥታቸው ለሱዳን ሕዝቦች የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ገልጸው ይህም ሉዓላዊነትን ባከበረና ጣልቃ ገብነትን ባስወገደ መልኩ ይሆና ብለዋል፡፡ በመልእክታቸውም ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ሽግግሩን ሰላማዊ ለማድረግ ቅሬታን ፈችና የሕዝቡን ጥያቄ መላሽ በሆነ መልኩ እንዲንቀሳቀስ አበረታትተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የቤተሰባችን አባላት-ከዚህ በታች የሚቀርቡት መረጃዎች በሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የነበረውን የStopHateSpeech ዘመቻ የሚያስቃኝ ነው። #WKU
#WKU ዝናብ ያልበገረው--ለፍቅር፤ለአንድነት እና ለሰላም ኑልኝ!! #የወልቂጤ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች #ለTikvah_Ethiopia ቤተሰብ አባላት ያደረጉት #አስገራሚ አቀባባል!!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት #wku
Photo: @Dura_pic

ፈጣሪ #ያክብርልን!!
#ኢትዮጵያ አለንልሽ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia