TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዲላላ...

"ወደ ወሊሶ በሚወስደው መንገድ ደላላ (delila) ሚባል አከባቢ የአከባቢ መንገድ ተዘግቷዋል፣ 1 ሰዓት አልፎናል። የሚመለከተው አካል ቢያውቀው"

በአካባቢው ምን እንደተፈጠረ እንዲሁም ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን አዘጋጅቼ ወደእናተ አደርሳለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ🔝

"ሰላም ዛሬ በሀዋሳ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ዉስጥ ከባድ የትራፊክ አደጋ ተከስቷል በዚህም አንድ የሰው ህይወት ጠፍቷል አደጋው የተከሰተው አንድ ሞተር ሳይክል ከ ከተማ ባስ ጋር በመጋጨቱ ነዉ፡፡ ናትናኤል ነኝ ከሀዋሳ አዲስ መረጃ ካለ ወዲያው አሳውቃለሁ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሳቱ በቁጥጥር ስር አልዋለም...

ስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቃጠሎ ሁኔታ አሁንም በቁጥጥር ሥር አልዋለም፡፡ የአማራ ክልል አካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በላይነህ አየለ ለአብመድ እንደተናገሩት ከትናንት ጀምሮ በሄሊኮፕተር ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ሄሊኮፕተሯን በአካባቢው አንቀሳቅሶ እሳቱን ለማጥፋት መልክአ ምድሩ ተጽእኖ እንዳላሳደረባት ከአብራሪው ማረጋገጣቸውንም ተናግረዋል፡፡

ሄሊኮፕተሯ እስከ 1ሺህ 300 ሊትር ውኃ ከደባርቅ አካባቢ አሰራ ወንዝ በመቅዳትና በእሳቱ ላይ በመርጨት ለማጥፋት እየሠራች እንደሆነ ዶክተር በላይነህ አስታውቀዋል፡፡ ነገር ግን ሄሊኮፕተሯ አንድ ጊዜ በሞላችው ነዳጅ ለ3፡00 ብቻ ስለምትሠራ ነዳጅ ለመሙላት ወደ ጎንደር በመሄድ ጊዜና ነዳጅ ታባክናለች ነው ያሉት፡፡ ‹‹የአውሮፕላን ነዳጅ የተለየና ከማንኛውም ማደያ የሚቀዳ ባለመሆኑ በቦቴ ተጭኖ ደባርቅ ድረስ እንዲቀርብልን ጠይቀን ምላሽ እየጠበቅን ነው›› ያሉት ዶክተር በላይነህ ምላሹ እስኪመጣ ወደ ጎንደር እየተመላለሰች መቅዳቷ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ትናንት ማምሻውን ከስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በስልክ ካነጋገርናቸው መካከል በአስጎብኝነት የሚሠራው አስረሳኸኝ ሞላ ‹‹ሄሊኮፕተሯ ውኃ እየረጨች ለማጥፋት እየሞከረች ነው፡፡ ነገር ግን ውኃ ከርቀት ስለትቀዳ እስክትመለስ ባለው ጊዜ ውስጥ እሳቱ የማገገሚያ ጊዜ እያገኘ ነው፡፡ የሄሊኮፕተሮቹ ቁጥር መጨመር አለበት›› ብሏል፡፡

አስረሳኸኝ ለአብመድ እንደተናገረው ቃጠሎው በገደላማው የፓርኩ ክፍል እንዳለ ነው፡፡ በሙጭላ መውረጃ በኩል ያለው ደግሞ ከፍተኛ መሆኑን ነው ያስረዳው፡፡

በፓርኩ ሁኔታውን እየተከታተሉ የሚገኙት ዶክተር በላይነህ አየለ አንድ ሄሊኮፕተር በቂ አለመሆኑን ገለጸው የእስራኤል የእሳት ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ቡድን በፍጥነት የሁኔታ ግምገማ አድርገው ተጨማሪ የእሳት ማጥፊያ አውሮፕላን እንዲሰማራ ያደርጋሉ ብለው ተስፋ እንዳደረጉ አስታውቀዋል፡፡ እስራኤላውያኑን ባለሙያዎች ከፊሉን በሄሊኮፕተር እና ከፊሉን በእግር የእሳቱንና የአካባቢውን ሁኔታ እያዩ መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከመጋቢት 30 ቀን 2011ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ከግጭ አካባቢ በተነሳ እሳት እየተቃጠለ ነው፡፡ እሳቱ ወደ ገደላማው የፓርኩ ክፍል ወርዶ ከቁጥጥር ውጭ ከሆነና በሰው ማጥፋት ከማይቻልበት ደረጃ ከደረሰ ሰንብቷል፡፡ ከሚያዝያ 6 ቀን 2011ዓ.ም ረፋድ አንስቶ አንድ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተርና 10 አባላት ያሉት የእስራኤል የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪ የባለሙያዎች ቡድን በስፍራው ተሠማርቷል፡፡ የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ደግሞ መንግሥት ፓርኩን እንዲታደገው በሰልፍ ትናንት ጠይቀዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወሊሶ🔝

"ፀግሽ ወሊሶ ከተማና ዲለላ ላይ ከጠዋት ጀምሮ ሰልፍ አለ መንገድ ዝግ ነው፡፡ የሰልፉ ምክንያት ጦላይ በሚገኘዉ ማሰልጠኛ የነበሩት 280 የቀድሞ የኦነግ ሰራዊት ላይ በደረሰዉ የምግብ መመረዝ ምክንያት ነዉ፡፡ ከሰራዊቱ አባላት የተወሰኑት አሁን በወሊሶ ቅዱስ ሉቃስ ሆስፒታል ይገኛሉ፡፡ የሞተ ሰዉ ይኑር አይኑር አላወኩም፡፡"

ፎቶ: OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከኖኖ ወረዳ እንዲሁም የድሬ ጎዶ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ወገኖች 300 ኩንታል በቆሎ እና የቤት መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ። የድጋፉ አስተባባሪዎች በአካባቢያቸው ብቻ ተወስነው ዕርዳታውን ቢያሰባስቡም ያገኙት ምላሽ ቀላል እንዳልሆነ ገልጸዋል። ሁኔታው ባይከሰት መልካም ነበር ያሉት የነዋሪዎቹ ተወካዮች "አሁንም ተፈናቃዮች በፍጥነት መቋቋምና ወደ ቀደመ ሕይወታቸው መመለስ አለባቸው" ብለዋል። ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራምና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አማረ ክንዴ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ድረስ ተጉዘው ድጋፍ ያደረጉትን ነዋሪዎች አመስግነዋል። ድጋፉ በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች ለሚገኙ አስቸኳይ ዕርዳታ ፈላጊዎች ፍትሐዊ በሆነ መልኩ የሚዳረስ መሆኑንም ለነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያን እየጎበኝ የሚገኙት #ኢቫንካ ትራምፕ #በቦይንግ አውሮፕላን አደጋ #ህይዎታቸውን ላጡ ዜጎች #የአበባ_ጉንጉን አስቀምጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia