“ብሶታችንን መርሳትና በአንድነት መንፈስ መሰባሰብ አለብን”፡- ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ 25ኛ ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ባደረጉት ንግግር ሌሎችን እንደ ራሳችን በማየት ያለፈ ብሶታችንን መርሳትና በአንድነት መንፈስ መሰባሰብ እንዳለብን አሳስበዋል።
ይህን መሰል ቀውስ ውስጥ ማለፍ አልነበረብንም ያሉት ጠ/ሚሩ የሩዋንዳ ሕዝብና መንግሥት አንድነትን: ይቅር ባይነትንና ዕርቅን ለሚደነቀው ዕድገታቸው መሠረት አድርገው መነሣታቸውን አድንቀዋል።
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከ250 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ሰለባዎች ባረፋበት የኪጋሊ የዘር ጭፍጨፋ መታሰቢያ ስፍራ የአበባ ጉንጉኑን አኑረዋል፡፡
የዘር ጭፍጨፋው 25ኛ ዓመት መታሰቢያ ለዓለም ሕዝብ ተግባብቶና በልዩነት መሐል ተቻችሎ የመኖርን አስፈላጊነት ለማሳሰብ ነው ተብሏል፡፡
ግልጽ ውይይትን በማበልጸግና የጋራ መግባባትን በማሳደግ ሰላማዊ ማህበረሰብን መመሥረት እንደሚቻል መገለፁን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡
800 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በተገደሉበት በዚህ የዘር ጭፍጨፋ በርካቶቹ ቱትሲዎች ሲሆኑ በወቅቱ ተደብድበዋል፣ ተጠልፈዋል እንዲሁም ተገድለዋል፡፡
ይህ በሀገሪቱ ታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈው ጭፍጨፋ በየአመቱ መጋቢት 29 የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮ ለ25ኛ ጊዜ የሚታሰብ ይሆናል፡፡
ሩዋንዳ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ በአፍሪካም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት መሳብ ብትችልም ይህ ጭፍጨፋ በሀገሪቱ ታሪክ ላይ ጥላውን አጥልቶ አልፏል፡፡
ይህ ቀን የዘር ጭፍጨፋ የተካሄደባቸውን ቀናት እና ብሄራዊ የሀዘን ቀናቱን ለማስታወስ የሚከበር ነው፡፡
ጠቅላይ ሚንስቴር ፅህፈት ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ለመላው የአርባ ምንጮ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በዋናው ግቢ ከዚህ ሠዓት ጀምሮ በፕሮግራሙ ላይ መታደም ትችላላችሁ!!
በሰላም ገብተዋል!
ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ #ለSTOP_HATE_SPEECH ሀገራዊ ንቅናቄ የተጓዙት #የኢትዮጵያ_ልጆች በሰላም ወደተቋማቸው ተመልሠዋል።
በቀጣይ-የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ #የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተያይዘው ለሰላም እና ለፍቅር ጉዞ ያደርጋሉ!!
ተዘጋጁ-
•አምቦ ዩኒቨርሲቲ
•ጅማ ዩኒቨርሲቲ
•ሀረማያ ዩንቨርስቲ
•ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ
#STOP_HATE_SPEECH

ጅማ፣ ሀዋሣ፣ አምቦ፣ መቀለ፣ ሀረማያ፣ ወልቂጤ፣ ድሬዳዋ፣ባህርዳር፣ ወልዲያ፣ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንመጣለን ተዘጋጁ!!
#ሰውነት ያስተሳሰረን የኢትዮጵያ ልጆች ነን!! በፍፁም ሀገራችን #እንድትፈርስ አንፈቅድም!!

የሩዳንዳ የዘር ጭፍጨፋ መታሠቢያ🔝
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው ለሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ 25ኛ ዓመት መታሰቢያ በተዘጋጀዉ የእግር ጉዞ ላይ ተሳትፈዋል። የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ 25ኛ ዓመት መታሰቢያ ላይ ለመገኘት ወደ ሩዋንዳ የቀኑት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በእግር ጉዞው የተሳተፉት ከፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜና ከሌሎችም የአለም መሪዎች ጋር በመሆን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሩዋንዳ ቆይታቸውን አጠናቀው ትላንት ማምሻዉን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ምንጭ:-ጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ቤት

አብን‼️
መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አብን ይጠይቃል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የፌዴራልና ክልል መንግሥታት የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት በአግባቡ ማስጠበቅ ባለመቻላቸው ከሰሞኑ ራሳቸውን የኦነግ አባላት መሆናቸውን የሚናገሩና የኦነግን ዓርማ የያዙ የቡድን ጦር መሣሪያዎችን የታጠቁ የጥፋት ኃይሎች በምድረገኝ/ከሚሴና አጣዬ አካባቢዎች በፈፀሙት ወረራ በወገኖቻችን ላይ ግድያን ጨምሮ በርካታ ማኅበረስነልቦናዊ ጫና ፈጥረዋል። የተደራጄ ወራሪ ቡድኑ ቤተእምነት ሳይቀር አቃጥሏል።
ሰላማዊ የሕዝባችን የዕለት ተዕለት ኑሮም በተፈፀመው ድንገቴ ወረራና የተደራጄ ዘረፋ ተናግቷል። የሆነው ሁሉ ታስቦበትና ታቅዶበት የተደረገ ወረራ ስለመሆኑ አብን ከፍተኛ ጥርጣሬ አለው። እስካሁን የተገኙ መረጃዎችም ይኸንኑ ጥርጣሬያችንን የሚያጠናክሩ ሆነው አግኝተናቸዋል። የክልሉ መንግሥት በወገኖቻችን ላይ በጥፋት ኃይሎች እየተፈፀመ ያለውን ግድያ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ በአስቸኳይ ሊያስቆመው ይገባል። የፌዴራል መንግሥትም ከወገንተኝነት ወጥቶ ወራሪዎችን ሊቆጣጠር ይገባዋል።
ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንዲሉ አማራ ጠል ወራሪ ኃይሎች በሕዝባችን ላይ ያደረሱት በደል አንሶ የአብንን ስም ለአደባባይ ቅሌታቸው መሸፈኛ ለማድረግ ሲሯሯጡ አስተውለናል። በከሚሴ ዞን የገጠር ቀበሌዎች አብን በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ጭፍጨፋ ሊያካሂድ ነው የሚል የአሉባልታ መርዛቸውን በመርጨትም ነዋሪዎችን እየቀሰቀሱ መሆናቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶናል። አብን ላይ መሰል የስም ማጠልሸት ተግባራት የሚያከናውኑ አካላት ለፈፀሙት የጭፍጨፋ ወንጀል የጎሳና ኃይማኖት መደበቂያ ዋሻ እየማሱ መሆኑን ብንረዳም ቅሉ፤ በእነዚህ ግለሰቦች የተሳሳተ መረጃ መነሻነት አካባቢው ተራዘመ የብጥብጥ ማዕከልነት እንዳይቀየር፤ መንግሥት አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ እርምጃ እንዲወስድ ከወዲሁ እናሳስባለን። አብን ሕዝባችንን በቋንቋና ኃይማኖት የሚከፋፍሉ አካላትን እያወገዘ ለወገናችን እንድነት በጽናት መቆሙንም ያረጋግጣል።
ንቅነቄያችን በምድረገኝ/ከሚሴና አጣዬ አካባቢዎች በደረሰው የወገኖቻችን ሕይወት መጥፋት የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን እየገለፀ፤ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ጥፋቶችን በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርቡ በአጽንዖት ይጠይቃል።
እጣፈንታችንን በራሳችን እጆች እንጽፋለን!
መጋቢት 30/2011 ዓ·ም
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ

የፌደራል እና የአማራ ክልል የጸጥታ አስከባሪ ተቋማት #እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዙ‼️
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ለማረጋጋት የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዙ። የጸጥታ ኃይሎቹ “አስፈላጊውን ህጋዊ እና #ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ” ትዕዛዝ መተላለፉን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ነው።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል “ከሚሴ እና በአጎራባች አካባቢዎች የተከሰተው የሰው ሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት በምንም አግባብ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው” ብሏል። የምክር ቤቱ መግለጫ በአካባቢዎቹ በተፈጸመው ጥቃት ስለሞቱ ሰዎች ብዛት ከመጥቀስ ተቆጥቧል።
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አጣዬ፣ ማጀቴ እና ካራቆሬ በተባሉ ከተሞች በተፈጸመ ጥቃት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ወረዳ መንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት “የኦነግ ታጣቂዎች” ሲል የጠራቸው ጥቃት ፈጻሚዎች በከፈቱት ተኩስ አራት ሰዎች መሞታቸውን በትላትናው ዕለት አስታውቆ ነበር። ህይወታቸው ካለፈው መካከል ሶስቱ “የከተማይቱን ሰላም ለማስጠበቅ የተሰማሩ የፀጥታ አባላት” መሆናቸውን የገለጸው የወረዳው የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አንደኛው በተባራሪ ጥይት ተመትቶ መሞቱን ገልጿል።
በአካባቢዎቹ የተከሰተውን ጥቃት “ብጥብጥ” ሲል የጠራው የብሔራዊ ጸጥታ ምክር ቤት “ችግሮች የሚከሰቱት የራሳቸው አጀንዳ ባላቸው ውስን የጥፋት ሃይሎች ነው” ብሏል። ምክር ቤቱ “በአካባቢዎቹ በተከሰተው ብጥብጥ ላይ “እጁ ያለበት ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ” ገልጿል። ብጥብጡን ያቀናበሩት፣ ያነሳሱትና የፈጸሙ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እንዲቻል ጥናት የሚያደርግ፣ ከአማራ ክልል እና ከፌደራል ተቋማት የተውጣጣ ቡድን ወደ አካባቢዎቹ መሰማራቱንም አስታውቋል።
መንግስት ህግን ለማስከበርና የዜጎችን ሰላም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ እንደሆነ የገለጸው የብሔራዊ ጸጥታ ምክር ቤት “በሕገወጥ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ መንግስት ሕግን ከማስከበር ወደ ኋላ እንደማይል በድጋሚ ያረጋግጣል” ሲል አስጠንቅቋል።
ምንጭ-የጀርመን ራድዮ

"የማረጋጋት ስራ እየሰራሁ ነው" - መከላከያ
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግጭት ተከስቶ በነበረባቸው በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች መካከል በመግባት የማረጋጋት ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚንስቴር የማረጋጋት ስራውን በመስራት ላይ የሚገኝው የአማራ ክልል መንግስት ባቀረበለት ጥሪ መሰረት እንደሆነ ገልጿል፡፡
አሁን ላይ አካባቢዎቹ #እየተረጋጉ ቢመጡም አልፎ አልፎ በመንገድ ዳርቻዎች ላይ #የተኩስ ልውውጦች አሉ ነው የተባለው፡፡ የተኩስ ልውውጡ የሚሰማው በገጠራማ አካባቢዎች መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
አካባቢዎቹ ሰፊ እንደመሆናቸው በብቃት ለመቆጣጠር #ተጨማሪ ሀይል ወደ ስፍራዎቹ #እየገባ መሆኑን ሚንስቴሩ ይፋ አድርጓል፡፡
ተዘግተው ያሉ የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ሲናና እና ደብረ በርሃን መንገዶችን የማስከፈት ስራ #እንደሚከናወንም ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ-#ፋና

አንፃራዊ ሰላም እየታየ ነው•••
በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ፣ካራቆሬ፣ ማጀቴ እና ሌሎችም ጥቃት የተፈፀመባቸው አካባቢዎች ከትናንቱ የተሻለ አንፃራዊ ሰላም እየታዬ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ለአብመድ አስተያዬታቸውን የሰጡ #የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ በተፈፀመው ጥቃት በሰው ህይዎት እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ከትናንቱ መጠነኛ የጸጥታ መሻሻል መኖሩንም ነው የተናገሩት፡፡
ይሁን እንጅ በተለምዶ ‹‹ድልድይ፣ውኃ ልማት እና መዘጋጃ›› ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ዛሬ ማለዳ የጥይት ተኩስ ይሰማ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡
ከማጀቴ አስተያዬት የሰጡን ነዋሪዎች ግን አሁን ያለው ሁኔታ የተረጋጋ ቢመስልም በቂ የፀጥታ አካላት በአካባቢው ባለመኖራቸው ስጋት እንደፈጠረባቸው ነው የተናገሩት፡፡
የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የጸጥታ አካላት አስተማማኝ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል፡፡ የክልሉ የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ በአካባቢዎቹ መከላከያ መግባቱን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
ምንጭ-አብመድ